Monday, May 28, 2012

እውን “ማኅበረ ቅዱሳን” (ሰለፊያ) እየተዘጋ አይደለምን???

 የጽሁፉ ምንጭ፦ ዓውደ ምሕረት ብሎግ
To read in PDF ( Click Here )
አንዳንድ የዚህ ክፉ ነብሰ በላ የሆነ ድርጅት አመራሮችና አባለት “አባሠረቀንና አቡነ ጳውሎስን ብንገድል መንግስተ ሰማያት መግባታችን አይቀርም እንጸድቃለንም። በዚህ አንጠየቅም” እያሉ ሲያወሩ ስንሰማ ግራ እየገባን ይህ ከምን የመጣ አመለካከት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ የማይደግፈውን አስተሳሰብ እንዲህ በድፍረት የሚናገሩት ለምንድን ነው እያልን ለአመታት የቆየን ቢሆንም በስተመጨረሻ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ የሚሉት ለምን እንደሆነ በግልጽ ነግረውናል። እኛም ነገሩ ገብቶን ሰው በመግደል ገነት እንደሚወርሱ የሚያምኑ ሰለፊዎች መሆናቸውን አረጋግጠን ከየትኛው መጽሐፍ ይህን ትምህርት እንዳገኙት አውቀናል። ከማቅ ሰዎች ጋር በሀሳብና በአመለካከት ብቻ የተለያየን መሰሎን የነበረ ቢሆንም በምንመራበት መጽሐፍም ቢሆን ልዩነት እንዳለን አውቀናል።
ከዚህ እውነት በመነሳት “ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር” እንዲሉ በግንቦት ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የታዩ ክስተቶችን የተመለከተ ትንታኔ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቶአል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እራሱን በቅዱሳን ስም “ማኅበረ ቅዱሳን” በሚል የሰየመው የፖለቲካ ድርጅት ለአለፉት ሁለት አሥርት አመታት በቅድስት ቤተክርስቲያናችንም ሆነ በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ እያደረሰው ያለውን አሉታዊ ተጽእኖ ሁሉም የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የሚያውቁት ሐቅ ነው፡፡
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንዳስነበብናችሁ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የታቀፈውና በዲያቢሎስ መንፈስ የሚመራው ማቅን ለመሆኑ ማን መሠረተው? እነማንስ ስም ሰጡት የሚለውን እውነታ ስንመለከት ‹‹ማቅ›› የተሀድሶ ኮሚቴ ይባሉ በነበሩ የደርግ ደጋፊ አባላት የተመሠረተ ሲሆን ይኽ የጥፋት መልዕክተኛ ዘር ግንዱ እነኮሎኔል አጥናፉ አባተ ካቋቋሙት ”ጊዜያዊ የተሐድሶ ጉባኤ” ይነሳል። ጊዜያዊ የተሐድሶ ጉባኤ የማኅበረ ቅዱሳን አባቱ መሆኑ ነው። ይኽ አባቱ የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ለማፍረስ እና በውስጥዋም ሥርዐት አልበኝነት በማንገስ ቤተ ክርስቲያን ደካማ እንድትሆን ለደርግ ያገለገለ ነው። የእኛ ጊዜዋ ማቅ አገልግሎት ሁለት መልክ አለው - የሞተውን ሥርዐት ለመመለስ እና የየግል ጥቅማቸውን ማሳደግ እንዲሁም በሃይማኖት ሽፋን ስውር አላማን ማስፈጸም ነው፡፡

”ከሞኝ ደጅ ሞፈር ይቆረጣል” እንደሚባለው ይኽ ጊዜጣዊ የተሀድሶ ጉባኤ የመንደረተኝነቱን ቂም ለማርካት ሲል ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን ፓትርያርክዋን በገመድ አሳንቆ ያስገደለ የሠይጣን መልእክተኛ ነው። እንኩዋን የቤተ ክርስቲያኒቱን አደረጃጀት ሊያድስ ቀርቶ የዕሪያ መፈንጫ አድርጓት አረፈው። የያኔው የጊዜያዊ ተሀድሶ ጉባኤ አባላት ግማሹም በሹመት ግማሹም በሞት ሲበታተኑ ያደረገው ቀለማቸውን ለውጠው ”ማኅበረ ቅዱሳን” በሚል ሥያሜ የደርግ ወታደሮችን ሰብስቦ(አዲሱ ማቅ የተመሰረተው በደርግ ወታደሮች አማካኝነት እንደሆነ ማኅበርዋ አትክድም)ወራሹን ማደራጀት ነበር። ቤተ ክርስቲያኒቱን ተጠልሎ የወደቀ ሥርዐት ለማስመለስ ስለነበረ አባቱ የቤተ ክርስቲያኒቱን ጉልላት እየናደ ሲደልቅ ቆይቶ ልጁ ማኅበረ ቅዱሳን ደግሞ እንደሌሊት ሌባ መሠረትዋን እንዲሰረስር ክህነት ሰጥቶ ባረከና አደራጀው።

Sunday, May 27, 2012

ወርቁ እንዴት ደበሰ!(ሰቆ.ኤር. 4÷1)

           የጽሁፉ ምንጭ፤ቤተ ጳውሎስ/.www.betepawlos.com/
  /  ከደጀ ብርሃን፦ ቅዱሱን መጽሐፍ መሠረት አድርጎ ከወዲያም ይሁን ከወዲህ ያሉትንና ራሳቸውን የጽድቅ ሰራተኞች አድርገው የሚቆጥሩ ነገር ግን በዚያ ሥፍራ ተቀምጠው ያልተገኙትን ሁሉ የተመለከተበትን ይህንን ድንቅ ጽሑፍ እንድታነቡት አቅርበናል። /                  
ገና ሻዩን አዝዤ ወደ አፌ ላስጠጋው ስል ከወዲያ ማዶ ለመቆም የምትጣጣረውን መኪና እያየሁ ዓይኔ ተተክሎ ቀረ፡፡ መኪናዋን አላወቅኋትም፡፡ ዓይኔ ግን በእርሷ ላይ ቀረ፡፡ የሾፌሩ በር ተከፍቶ የወጣው ሰው ግን የማውቀው ወንድም ነበረ፡፡ ወዲያው ግን ማወቄ ወደ አለማወቅ ተለወጠ፡፡ እንኳን የእርሱን ህልውና የራሴን ህልውና ያጣሁት መሰለኝ፡፡ እውኑ ሕልም መሰለኝ፡፡ የጨበጥኩት የጉም ስፍር ሆነብኝ፡፡ ሻዩን ሳልቀምሰው አፌ እሬት ሆነብኝ፡፡ አጠገቤ ያሉትን ሰዎች ሁሉ ሕልውናቸውን መቀበል ከበደኝ፡፡ ዓለም ለቅጽበት ውሸት፣ የአሳብ ቤት ሆነችብኝ፡፡ ዓይኔ እዚያች መኪና ላይ የተተከለው የቀጠርኩት ሰው መጣ ብሎ አይደለም፡፡ ራሴን ቀጥሬ ራሴን እየጋበዝኩ ነበር፡፡ ያም ሰው እንደሚያገኘኝ ፍጹም አላሰበም፤ ነገር ግን ቀጠሮው ሞላ፡፡ እንደዚህ ባንገናኝ እመርጥ ነበር፡፡ በዓለም ግን የሆነው እንጂ የመረጡት አይታይም፡፡ ወዳጅ የሆነ ሰው ሊያየውም ላያየውም የሚገባ ሁኔታ ነበር፡፡ ማየቱ ለማጽናናት፣ አለማየቱ ላለመሰበር ነው። የመጣው ትንሽ ኬክ ቢጤ ገዝቶ ሊበላ ነው፡፡
ወደ እኔ መጓዝ ጀመረ፣ ይበልጥ ልቤ ፈራ፡፡ ያላየኝን ሰው ቀድሜ ዓይቼ የአሳብ ፍልሚያ ውስጥ ገባሁ፡፡ ያየ ታጋይ ነው፣ ያላየ ምን አለበት! ይህ ወንድሜ ቁመናው ያማረ፣ አንገቱ የንጉሥ ሕለተ ወርቅ የመሰለ፣ መልኩ የብር እንኮይ፣ አለባበሱ የጥቅምት አበባ፣ ቆፍጣናነቱ የድሮ ወታደር፣ አነጋገሩ በሥልጣን የተሞላ፣ ለሚረግጠው የሚጠነቀቅ፣ ለሚለብሰው የሚጨነቅ፣ በአጠገብ ሲያፍ ሽቶው የሚያውድ ነበር፡፡ መኪናውን የያዘ እንደሆነ እንደ መኪና ሳይሆን ያለ አቅሟ እንደ ጀት ሁኚ እያለ ያስጨንቃታል። እንደ ንጉሥ ሞተረኛ ለራሱ ድምጽ እያሰማ በመኪናው ጥሩምባ አድባሩን እያወከ ይነጉዳል። ብዙም አልናገረውም ነበር፡፡ ምክንያቱም ወደ መሬት ገና አልወረደም ነበርና ስለማንደማመጥ ነው፡፡ ከመፈለጉ የተነሣ ኩሩ፣ ከመወደዱ የተነሣ ውድ ነበር፡፡ ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርብ ብዙ ዘመን ነገርኩት፡፡ እኔን ላለማስቀየም ብቻ በትዕግሥት ይሰማኛል፡፡ ነገር ግን እሺታው የውሃ ሽታ ሆኖ ይቀራል፡፡ የአሁኗ ዓለም እንደ እርሱ ያታላለችው ሰው አልነበረም፡፡ እኔም ሰው ነኝና ደክሞኝ ተውኩት። ዛሬ ያየሁት ከብዙ ወራቶች በኋላ ነው፡፡ ያቺ የቡልጋ አልቃሽ ያለችው በጆሮዬ አቃጨለ፡-
      ‹‹ምን ቆንጆ ቢሆኑ ቢረዝሙ እንዳክርማ
               መጠቅለል አይቀርም በነጠላ ሸማ››

ሰባ ስምንት ነፍስ የገደለው ሰው [በላኤ ሰብእ]በጥርኝ ውሃና በማርያም ጥላ ዳነ

ምንጭ፤ አባ ሰላማ ብሎግ፤ Friday, February 24, 2012
እኔ መንገድ እውነት ሕይወትም ነኝ በኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም [መጽሐፍ ቅዱስ ዮሐ 146]
ታምረ ማርያም የተባለው ጉደኛ መጽሐፍ ድንግል ማርያምን ያከበረ የሚመስል ነገር ግን ስድብ እና ክህደት የሞላበት መጽሐፍ መሆኑን ደጋግመን ለማሳየት ሞክረናል። መጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈ 1400 ዓመት በኋላ በኢትዮጵያ ንጉሥ በዘርዓ ያዕቆብ የተደረሰ ሲሆን በወቅቱ የነበሩ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት እና ምእመናን ይህ ልዩ ወንጌል ከሐዋርያት ትምህርት የወጣ ስለሆነ አንቀበለውም በማለታቸው፣ እስከ አንገታቸው በጉድጓድ ተቀብረው በጭንቅላታቸው ላይ የፈረስና የከብት መንጋ እንደተነዳባቸው ምላሳቸውንና አፍንጫቸውን እንደተቆረጡ እራሱ ታምረ ማርያም ይመሰክራል። [ታምር 24 እና 25 ገጽ 112- 121]

ታምረ ማርያምን ቁጭ ብለን በማስተዋል ብንመረምረው መጽሐፍ ቅዱስን ለመቃወም የክርስትናን ትምህርት ለመበረዝ በጠላት ሆን ተብሎ የተቀመመ ይመስላል። አጼ ዘርዓ ያዕቆብ እስራኤላዊ ነኝ ስለሚል ምን አልባት አይሁዶች መሲሐዊ እምነታችንን ለማጠፋት የፈጸሙት ሴራ ይሆን? ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል። ዘራ ያዕቆብ አይሁዳዊ ነኝ እያለ ይመካ ነበር፤ ከዚያም አልፎ የይሁዳ ነገድ ነኝ ይል ነበር። አባ እስጢፋኖስ ግን ኢትዮጵያዊ ነህ አትዋሽ ከአይሁዳዊነት ይልቅ ክርስቲያን መሆን ይበልጣልና በዚህ አትመካ በማለት እንደተከራከረው ገድለ እስጢፋኖስ ይናገራል [በሕግ አምላክ በፕሮፌሰር ጌታቸው]


መጽሐፉን ዛሬ መመርመር ለምን አስፈለገ? የሚል ጠያቂ ሊኖር ይችላል፣ መልሳችን አብዛኛው የዋሕ ምእመን እምነቱን የመሠረተው በታምረ ማርያም ላይ ነው የሚል ሥጋት ስላለን ነው። ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄድ ታምሯን ሰምቼ ልምጣ እንጂ ወንጌል ሰምቼ ልምጣ ብሎ አያስብም፣ እሑድ እሑድ ታምር የሚያነብ እንጂ ወንጌል ለማስተማር የሚያስብ ቄስም የለንም። 400 000 ካህናት እንዳላት የሚነገርላት ቤተ ክርስቲያናችን ታምረ ማርያም አንብቦ ከማሳለም ያላፈ አገልግሎት የሚሰጥ አይደለም። በተለይም ታምሯን ሰምቶ የሄደ ሥጋውና ደሙን እንደተቀበለ ይቆጠርለታል የሚለው ባዕድ ወንጌል ብዙ ሕዝብ ወደ ስጋውና ደሙ እንዳይደርስ ስላደረገው ይህም የስሕተት ትምህርቶች ውጤት ሆኖ ስላገኘነው፣ ሲኖዶሱ ከተኛበት እስኪነቃ ድረስ ጩኸታችንን አናቆምም። ወደ ተነሳንበት እርስ እንመለስ፥

መጽሐፉቅምርበሚባል አገር አንድ ሰው ነበር በማለት ታሪኩን ይጀምራል

ወኢየበልዕ እክለ ወኢ ሥጋ ላሕም ወኢ ካልአ እንሥሣ አላ ይበልዕ ሥጋ ሰብእ

ትርጉም እህል፥ የላም፥ ሥጋ የሌሎችንም እንሥሳ ሥጋ አይበላም ነበር የሰው ሥጋ ይበላ ነበር እንጂ 68