Thursday, March 29, 2012

«ክብሩን እንመልስ፤ እጃችንንም እንታጠብ!»

«ክብሬን ለሌላ አልሰጥም»
(by dejebirhan)        to read in PDF   (Click here)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ድርሻ አላት። በቀደሙት ዘመናት ውስጥ ሃይማኖታዊ መንግሥት የሀገሪቱ አስተዳደር ሥርዓት ስለነበረ ቦታዋና ወሳኝነቷ አሌ ሊባል የማይችል እውነት ነው። ቤተክርስቲያኒቱ ያልፈቀደችው ሰው ዙፋን ላይ ሊወጣ አይታሰብም ነበር። በጉልበትም ይሁን በዘዴ አንዱ አንዱን አጥፍቶ ሥልጣን ላይ ቢወጣ እንኳን የቤተክርስቲያኒቱን እውቅና ለመጠየቅ መገደዱ አይቀርም። የንጉሠ ነገሥትነቱ ክብር እሷ ካላጸደቀችው የጸና ስለማይሆን ይህንኑ ለመስጠትና ለመፍቀድ ድርሻዋ ትልቅ ነው። በእርግጥም «እምነ መንግሥት የዐቢ ክህነት» እንደሚለው ቃሉ ቢያንሳት እንጂ ይህ ድርሻዋ የሚበዛባት አይደለም። ከተወሰነኑ ወቅቶች ማለትም ከወለተ ጌዴዎን ዮዲት 40 ዘመንና ከኢብን ኢብራሂም አልጋዚ (ግራኝ) 15 ዓመታት ወረራ ጊዜያት በስተቀር የቤተክርስቲያኒቱ ሥፍራ ላለፉት 1600 ዓመታት ከቤተመንግሥቱ የራቀ አልነበረም። በዚህም የተነሳ ቤተክህነቱ ከቤተመንግሥቱ አልራቀም ወይም ቤተመንግሥቱ ከቤተክህነቱ አልወጣም ማለት ይቻላል።
በነዚህ ዘመናት ሀገርን በማስከበር፣ በተለይም ዛሬ ኢትዮጵያ የምንላትን ሀገር ከመገንባትና ከመጠበቅ አንጻር፣ ፊደላትንና ስነ ጽሁፋትን በማስፋት፣ ቅርስን እንዲሁም ትውልዱን ከታሪክ፣ ታሪኩን ከሀገር ጋር በማስተሳሰር ረገድም ሚናዋ የጎላ ነው። ብዙ ብዙ ሊባልላት እንደሚቻል የሚታወቅ እውነታ ነው።
ከዚሁ ጋር በተነጻጻሪ ነገሥታቱ በዘመናቸው በሰሯቸው መልካምም ይሁን መጥፎ ስራቸው ድርሻዋ አብሮ የሚታይ መሆኑንም መካድ አይገባንም። ለምሳሌ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ደቂቀ እስጢፋኖስ የተባሉ ክፍሎችን አንድ በአንድ እየለቀሙ ጆሮ እየቆረጡና አፍንጫ እየፎነኑ ሲያሰቃይዋቸው መናፍቃንንና ጸረ ማርያሞችን ማስወገድ ነው በማለት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ትብብሯን አሳይታለች። እነዚህን መናፍቃን አሰቃይቶ መግደል ተገቢ እንደነበር በማመንና በማሳመን በየተአምራት መጻሕፍቱና በየታሪክ ድርሳናቱ ጽፋ አቆይታለች። ዛሬም በነዚሁ ታሪክ የጸሎት ቡራኬ ይደርስባቸዋል።
ጉዳዩን አስቸጋሪ የሚያደርገው መናፍቃንንና ጸረ ማርያም የተባሉትን (ለዚያውም ሆነው ከተገኙ) እየለቀማችሁ አጥፏቸው የሚል አስተምህሮ አለ ወይ ብለን ብንጠይቅ የእውነቱን ጽዋ ለመጠጣት ካላስቸገረን በስተቀር በወንጌል አለሁ የሚል ማንም ቢኖር ይህንን በፍጹም ሊቀበል የሚችለው አይደለም።
«እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና» ማቴ 544
ብላ የምታስተምር ቤተክርስቲያን የነገሥታቱን የግድያ ተግባር ደግፋ ብቻ ሳይሆን አሞካሽታ ስታበቃ ግድያቸውን የጽድቅ ተግባር አድርጋ መጻፏ ወንጌል አልተሰበከም ወይም ሃይማኖቱ የቆመው ሠይፍ በታጠቀው ንጉሠ ነገሥት ብርታት ነው ለማለት እንደፍራለን።
መቼም እንደዚህ ዓይነት ጠጠር ያለ ግን እውነተኛ ጽሁፍ በአክራሪዎች የሚታየው ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት እንደሚነገር እንጂ በሰራነው መልካም ነገር መሞገስን እንደምንሻው ሁሉ ባጠፋው ነገር ደግሞ ልናዝን እንደሚገባን ለማሰብ በማይችሉ ሰዎች ዘንድ ይሆናል። «በሽታችንን ደብቀን መድኃኒት እናገኛለን ማለት ዘበት ነው»
ምንም ይሁን ምንም ነገሥታቱ በፈጸሙት ግድያና ትውልድን ለቅሞ የማጥፋት ዘመቻ አብራ በተሰለፈችው ቤተክርስቲያናችን ላይ አመልከዋለሁ የምትለው ኢየሱስ ክርስቶስ «እሰይ አበጀሽ፣ ለእኔ ስትይ ልቅምቅም አድርገሽ ስለፈጀሻቸው ደስ ብሎኛል» የሚል የምስራች ይነገራታል የሚል ቢኖር እሱ ክርስቶስን የማያውቅ ሰው መሆን አለበት ብለን እውነቱን አስረግጠን እንናገራለን።
ምክንያቱም ለሰቀሉት ይቅርታ የጠየቀ፣ ለሚገድሉ ክብርንና ጸጋን ይሰጣል ተብሎ አይጠበቅምና ነው።
«ኢየሱስም፦ አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ። ልብሱንም ተካፍለው ዕጣ ተጣጣሉበት» ሉቃ 2334
ስለዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በመልካምነትዋና በጥሩ ስራዋ በሀገራችን ታሪክ ከፍ አድርገን እንደምናያት ሁሉ በመጥፎ ነገሯና ይህንን መጥፎ ነገሯንም እንደጀብድ የምትቆርበትን የሚያሳዝን ተአምራዊ ድርሰቷን አንብበን ልናፍርብ ይገባል። ወደድንም ጠላንም የእነዚያን የእግዚአብሔር ፍጡራን ደም ከሰማይ ይጮሃል! እግዚአብሔርም ደማቸውን ከእጃችን ይፈልጋል።
እስኪ ከእነ አባ እስጢፋኖስ ፍጅት በኋላ የሆንነው እንይ!

Wednesday, March 28, 2012

ፍጹም ከቅጣቱ!


ማን ይገኝ ነበረ?


(By dejebirhan)     to read in PDF (click here)
በከንቱ አትጥራኝ፤ ስሜን ባንተ ይክበር
ኢታምልክን ጠብቅ፣ ምልክት አታስቀር
ባልንጀራን ውደድ፤በሀሰት አትመስክር
እድሜህ እንዲረዝም፤ ወላጅህን አክብር
ገላህንም ቀድስ፣ክልክል ነው ማመንዘር
አድርግና ጠብቅ፣ የቆመውን አጥር
ያልሰማ ማን አለ? ኦሪት ስትናገር?
በከንቱ የጠራው በደለኛ ይሆናል፤ (ዘጸ ፳፣፯)
ከአምላኩ መጽሐፍ፤ ከርስቱ ይፋቃል፤ (ዘጸ ፴፪፣፴፫)
ቢሰግድና ቢወድቅ ለቀረጸው ምስል
ቢያሸው፤ ቢዳብሰው ሥሩ ቢንከባለል
የአምላኩ መልክ ሆኖ ከፊቱ ቢተከል፣
ኢታምልክን ሽሯል ትለዋለች ኦሪት
ሕጓን ትጠቅስና፣ ታወርዳለች ቅጣት
...................ከቶ ያየኝ የለም፤
አይቶኝም የሚቆም፣ (ዘጸ ፴፫፣፳)
ምስሌ ምንድነው፣ ከማን ጋር ልተያይ? (ኢሳ ፵፮፣፭)
ከቶ ማን አይቶኛል? ከደመናት በላይ፣ (ዘዳ ፴፫፣፳፮)
በምድር የተካኝ ፣እኔነቴን ወካይ፣
ከወዴት ተገኘ፣ሴትና ወንድ መሳይ? (ዘዳ ፬፣፲፮)

Monday, March 26, 2012

«ማኅበረ ቅዱሳን» ከፍተኛ የፖለቲካ ኪሳራ ደረሰበት

 ይህ ድንቅ ጽሁፍ በደጀብርሃን ሲገለጽ ለበጎች ነጻነት የተቆጣው እንስሳን  ያስታውሰናል ።
(የጽሁፍ ምንጭ፤http://dejeselaam-dejeselaam.blogspot.com)
እውን "ማኅበረ ቅዱሳን" ከመንበረ ፓትርያርክ፣ ከቅዱስ ሲኖዶስና ከጠቅላይ ቤተክህነት በላይ የሃይማኖት ጠባቂ እና ተቆርቋሪ ነውን?
ግርግር ለሌባ ይመቻል፤ "ማኅበረ ቅዱሳን" የዝቋላን እሳት ለማጥፋት ለአንድ ጀሪካን ውኃ 40 ብር ለሁለቱ ደግሞ 80 ብር ያስፈልገኛል ብሏል
በዋልድባ፣ በአሰቦትና በዝቋላ ገዳማት ጉዳይ የ"ማኅበረ ቅዱሳን" ዌብሳይቶችና ብሎጎች ለምን ተንጫጩ? ሌሎቹ ለምን እርጋታ ታየባቸው?
መንግሥት፣ ሃይማኖትና ቀጣዩ ልማታችን
"ማኅበረ ቅዱሳን" በቅርቡ ከገዳማት ሕይወት ጋር ተያይዞ በተነሳው ውዝግብ ከምንጊዜውም በላይ የፖለቲካ ኪሣራ የደረሰበት መሆኑን ልዩ ልዩ ምንጮች አረጋገጡ፡፡ ምንም እንኳን ሃይማኖታዊ ተፈጥሮ ባይኖረውም "ማኅበረ ቅዱሳን" የሃይማኖት ተቋም መስሎ በመንቀሳቀስ ብዙዎችን ቢያሳስትም፣ ዛሬ በፈጠረው የፖለቲካ ግጭት ከመንግሥትና ከሕግ ጋር ተፋጦ በመገኘቱ እውነተኛ ማንነቱ መጋለጡን የወቅቱ ሁኔታው ያስረዳል፡፡
ከአፈጣጠሩ ጀምሮ ከፖለቲካ አካሄድ ተላቆ የማያውቀው "ማቅ" ውስጥ ውስጡን ሲያተራምስ ከርሞ ዛሬ ሙሉ በሙሉ ራሱን በመግለጥ ፀረ ቤተክርስቲያንና ፀረ መንግሥት መሆኑን አሳይቷል፡፡ ይህ የሃይማኖት "ማኅበር" ነኝ ባይ ተቃዋሚ ድርጅት ቤተክርስቲያንን በእርስ በርስ ሁከት ሲያተራምስ ቆይቶ በአሁኑ ወቅት ቀይ መስመሩን አልፎ ከሕዝብና ከመንግሥት ጋር የሚያጋጨውን ድርጊት በመፈጸም ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡
"ማኅበሩ" ከ40 ሺህ እስከ 80 ሺህ የሚሆኑ አባላት አሉኝ የሚል ሲሆን በመንግሥትም ሆነ በቤተክርስቲያን የአባላቱ ዝርዝር አይታወቅም፡፡ ይህ ኅቡዕ አደረጃጀቱም እጅግ አደገኛ፣ ለውንብድናም ለምለም ሁኔታን እንደሚፈጥር ልብ ይሏል፡፡ ስውር ኃይል እንደሚመራውም የማኅበሩ አመራር የሆነው ዳንኤል ክብረት እንዳጋለጠም የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሚደረጉት የገንዘብ ዝውውሮቹ ቁጥጥር አይደረግባቸውም፡፡ ከዚህ የተነሳም አደገኛነቱን ማስተዋል ይቻላል፡፡
ቤተክርስቲያን ላወጣችው መመሪያ አይገዛም፡፡ በዚህም ምክንያት ተከታታይ መመሪያዎች ሲወጡበት ይታያል፡፡ በቤተክርስቲያን ስም የንግድ ፈቃድ ይወስዳል፡፡ ነገር ግን ለቤተክርስቲያንም ሆነ ለመንግሥት ተገቢውን ገቢ አያስገባም፡፡ ገቢዎቹንና ወጪዎቹን ቤተክርስቲያን በምታሳትማቸው ደረሰኞች እንዲመዘግብ ቢነገረውም ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ሀብትና ንብረቱን በነፃና ገለልተኛ ኦዲተር እንዲያስመረምር ቢታዘዝም በእምቢተኝነቱ ጸንቷል፡፡ በአጠቃላይ ሲገመገም፣ የ"ማኅበሩ" አደገኛነት ሊለካ የማይችል እጅግ አስጊ ነው፡፡ ጉዳዩ ፈር እንዲይዝ ከተለያዩ አካላት ለመንግሥትና ለጠቅላይ ቤተክህነት ጥቆማ ቢቀርብም በተለያዩ ምክንያቶች ችግሩ ከመባባስ በስተቀር መፍትሔ አልተበጀለትም፡፡ "ማኅበሩ"ም ባላሰለሰ ጥፋት ውስጥ ቀጠለበት እንጂ የመታረም ዕድል አላገኘበትም፡፡
ምንም እንኳን "ማቅ" መቶ በመቶ ለጥፋቱ ተጠያቂ ነው ባንልም፣ ዛሬ ቤተክርስቲያናችን ለገባችበት ቀውስና አስተዳደራዊ መዋቅሯ ወደ ሁለትና ስምንት ቦታ መከፋፈሏ የ"ማኅበሩ" የሃያ ዓመታት እንቅስቃሴ ውጤት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ መሆኑ አሌ አይባልም፡፡ "ማኅበሩ" ካህናትንና ምዕመናንን በተሃድሶነትና በመናፍቅነት በመክሰስ እና በራሱ ሥልጣን ዱላ ሁሉ በማንሳት ብዙዎችን ከየአጥቢያው በማባረር የግፉአንንና የስደተኞችን ቁጥር አበራክቷል፡፡