ጉባዔ አርድእት የተሰኘ የአገልግሎት ጉባዔ በቤተክርስቲያኒቱ
እውቅና ምሁር ሠራተኞች እንደተመሰረተ ይሰማል። እንደ ደጀ ብርሃን ብሎግ እምነት በቤተክርስቲያኒቱ
ውስጥ ከጥንታዊው የጽዋ ማኅበራት ውጪ ምንም ዓይነት የተደራጀ ማኅበርም
ይሁን ጉባዔ እንዲኖር የማንፈልግ ቢሆንም እኛን የገረመንና የደነቀን
ነገር ማኅበረ ቅዱሳን እሱ ራሱ እንደማኅበር በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ እየነገደና እያጭበረበረ የቆየ ሆኖ ሳለ ጉባዔ አርድእት የሚባል
ስብስብ ሊደራጅ መሆኑን ከሰማበት ጊዜ ጀምሮ እንዲህ ጨርቁን አስጥሎ እንዲበር ያደረገው ነገር አስገራሚ ሆኖብናል።
የጉባዔ አርድእት ህልውና እውን መሆን ማኅበረ
ቅዱሳን ያሰጋኛል ከሚል የፍርሃት፤ የጭንቀትና የቅንዓት ዓላማ ተነስቶ ጉባዔውን ቶሎ ማዳፈንና ግብዓተ ሞቱን ማፋጠን በሚል እብደት
ውስጥ መግባቱን የሚያሳየው እንቅስቃሴ ማኅበሩ በራሱ ምን ዓይነት ማኅበር መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነው። በአጭር ቃል ማኅበረ
ቅዱሳን እያለ ያለው በማኅበር ደረጃ ከእኔ በስተቀር በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ፈጽሞ አይታሰብም፤ የኔ የመተዳደሪያ ሕገ መንግሥት
ተፎካካሪ የሚያገኘው በመቃብሬ ላይ ነው የሚል አንጀኛ መሆኑን በግልጽ አሳይቷል።
ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ ተደራጅቻለሁ፤
የቤተክርስቲያኒቱን እምነትና ትውፊት አስከብራለሁ፤ ሕግና ስርዓቷን አከብራለሁ፤ ከዚህም በላይ በእግዚአብሔር እተማመናለሁ የሚል
ከሆነ የሌላ ማኅበር ወይም ጉባዔ መቋቋም ስጋት የሚሆንበት ለምንድነው?
አዎ! ድሮውንም ቢሆን ማኅበሩ አጭበርባሪ፤ አስመሳይ፤ ነጋዴና ከሳሽ ፖለቲካዊ ድርጅት በመሆኑ አቻ የሚሆነውን ወይም ከሱ የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ የሚችል ምንም ዓይነት ተቋም እንዲመሰረት ስለማይፈልግ ነው። ይህንንም ባላቋረጠ የማጥፋት እንቅስቃሴው በተግባር ያረጋገጠ ሆኗል።
አዎ! ድሮውንም ቢሆን ማኅበሩ አጭበርባሪ፤ አስመሳይ፤ ነጋዴና ከሳሽ ፖለቲካዊ ድርጅት በመሆኑ አቻ የሚሆነውን ወይም ከሱ የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ የሚችል ምንም ዓይነት ተቋም እንዲመሰረት ስለማይፈልግ ነው። ይህንንም ባላቋረጠ የማጥፋት እንቅስቃሴው በተግባር ያረጋገጠ ሆኗል።
የውስጥ አዋቂዎችን መረጃ በመጠቀም ዓውደ ምሕረት
ብሎግ ማኅበሩ እያደረገ ያለውን የጥፋት ዘመቻና ለዘመቻው ግብ መምታት እየተጓዘ ያለበትንም ርቀት ሁሉ በመዘገብ ለመረጃ መረብ አቅርባ ይህንኑ መረጃ እኛም ማሰራጨታችን ይታወሳል። ከወጣው መረጃ ላይ ከርእሳችን ጋር የሄደውን ቃል ከታች ለማሳያነት በጥቂቱ እናቅርብ።
ከዚህ በፊት ሁሉንም የቤተክርስቲያኒቱ አካላት በተለያየ መንገድ እየከፋፈለ ቤተክርስቲያኒቱን ለውድቀት እያፋጠነ
የቆየውና ያለው ማሕበረ ቅዱሳን በተለይ በአሁኑ ሰዓት ከአክራሪዎችና ከፖለቲከኞች ጋር ግንባር በመፍጠር እያካሄደ ያለውን እኩይ
ተግባር እየተጋለጠበት በመምጣቱና በአገር ውስጥና በውጭ አገርም ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበት በመምጣቱ ከዚህ ያድኑኛል ያላቸውን አቶ
እስክንድር ገብረክርስቶስንና አቶ ተስፋዬ ውብሸትን(የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ሥራ አስኪያጅ) በመደበው በጅት በመደለል በዋና ሥራ አስኪያጁ በአቡነ ፊልጶስ እና በቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ አቡነ
ሕዝቅኤል አማካኝነት “ጉባኤ አርድእትን “ አናውቀውም ይታገድልን የሚል ደብዳቤ እንደሚያጽፉ የውስጥ ምንጮቻችን ገልጸዋል።