በመምህር ፈንታ
የማኅበረ ቅዱሳን አፈቀላጤ የሆነው ደጀ ሰላም
በወርሃ መጋቢት መጨረሻ ላይ የሚከበረውን የመድኃኔዓለም ዓመታዊ በዓል አስታኰ በዛሬማ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለውን የመንግሥት
የስኳር ልማት ለማጥናት ሳይሆን ለሽብር ፍጆታ የሚሆን መረጃ ለመሰብሰብ የማኅበሩን አባላት በተሳላሚ ሽፋን ወደ ገዳሙ ከላካቸው
አባላቶቹ የተገኘውን ዘገባ ደጀ ሰላም በገጹ አውጥቶ ነበር።
የስኳር ልማቱን ለማስቆም ሕዝቡ ለጦርነት ተመመ፤
መንግሥት አካባቢውን ለቆ ወጣ፤ ፖሊሶች አለቁ፤ ሬሳ ቆጠራው ቀጥሏል …..ወዘተ የብስጭት ማስተንፈሻ ስሜቶቻቸውን ከልካይ በሌለበት
ድረ ገጽ ውሸቱን በቆርጦ ቀጥል ጥበባቸው እንቶ ፈንቶአቸውን አስነብበውናል።
አሁን ደግሞ ጉዳዩ በወሬ የማይቆም መሆኑን ሲያረጋግጡ
ለጫወታ ወግ ፍለጋ ጥቂት ጊዜ እረፍት የወሰዱ መስለዋል። አንድ ነገር ፈጥረው የሽብር ዜና እስኪያሰሙን ድረስ የሚያስተምሩት የወንጌል
ቃል ስለሌላቸው ጥሩ የእረፍት ጊዜ ይሁንላችሁ ብለናቸዋል።
ይህንን ያህል ለመግቢያ ካልን የጽሁፋችን ርእስ
ወደ ሆነው ጉዳይ እናምራ። ከሁከት ውጪ ነገረ መለኰትን የማያውቁ ሽፍቶች» በሚለው ጉዳይ ተንተርሰን ወደ ርእሳችን ስንገባ ደጀ ሰላም በተሳላሚ ሽፋን በማቅ አባላቶቿ ያስጠናችው የጥናት አንዱ ክፍል በዋልድባ ገዳም «የዘጠኝ መለኰት አማኞች» መኖራቸው መዘገብ
ነበር። ስለዋልድባ መነኰሳት መናፍቅነትና ክሃዲነት ያገኘሁት ውጤት
ነው በማለት በስኳር ጥናቱ ለውሶና ስኳር አድርጎ በማቅረብ ስለዘጠኝ
መለኮት አማኞች ሊያስነብበን ፈልጎ ይህንኑ በኢንተርኔት ላይ ሰቅሎት አግኝተናል።
ከጽሁፏ የተወሰደው ዘገባዋ ይህንን ይመስላል።
ይሁን እንጂ እነ በጋሻውን፤ እነ አባ ሠረቀ ብርሃንንና
ሌሎችንም ሁሉ በአንድ ሙቀጫ አስገብታ በተሐድሶ ስም የምትወቅጠው ይህች ብሎግና ማኅበር ድሮውን በፈጠራና ስም በማጥፋት ላይ ተመስርታ
እንጂ የሃይማኖት እውቀት ስላላት በዚያ ላይ ተመስርታ ወይም የመናፍቃን ጉዳይ የሚያሳስባት ሆኖ አይደለም።