Friday, May 18, 2012

በማኅበረ ቅዱሳን ተጽዕኖ ህልውናውን የካደ ኮሌጅ

                                  የጽሁፉ ምንጭ፤ ዐውደ ምሕረት ብሎግ
                     To read in PDF ( Click Here )
 አንድ የቤተክርስቲያንን ልጅ ለማባረር ሲል እራሱን ሕጋዊ ሰውነት የሌለው አድርጎ የሚያሳይ የክስ ወረቀት ለሰበር ሰሚ ችሎት አቀረበ
    ኮሌጁበሰበር ሰሚ ችሎት ከረታ ለተማሪዎቹ ከፍተኛ አደጋ አለው
                                                             
የኢዮቤልዩ በዓሉን ለማክበር ጥቂት ዓመታት የቀሩትና ከተመሰረተ 69 ዓመት የሆነው የቅድስት ስላሴ ኮሌጅ ከመምህር አሰግድ ሣህሉ ጋር ባለው የሕግ ክርክር በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የገጠመውን ሽንፈት ሽሮ በድል እንድወጣ ያስችለኛል ያለውን የይግባኝ አቤቱታ ለሰበር ሰሚ ሲያቀርብ ሕጋዊ ሰውነት የሌለኝና ከአንድ ግለሰብ እንኳ ያነስኩ ነኝ ሲል ህልውናውን ካደ።
የኮሌጁ ጠበቃ እያለች የሕግ ክርክሩን በራሴ በኩል ልምራው የሚለው ማኅበረ ቅዱሳን አመራር በሆነው ደስታ በርሔ በተባለ ጠበቃ በኩል የሕግ ክርክሩን ቢቀጥልም በስር ፍርድ ቤት የገጠመውን ሽንፈት ይሽርልኛል ብሎ ላለፉት አምስት ወራት ሲያስብ ቆይቶ ባቀረበው አቤቱታ በተራ ቁጥር 2 ላይ ያለው የአቤቱታው ዝርዝር በሚለው አንቀጽ በግልጽ ህጋዊ ሰውነት የሌለው ኮሌጅ ነው ሲል የኮሌጁን ህልውና ክዷል።
እኔ ያልኩት ብቻ ትክክል ነው የጠላሁትም መናፍቅ ነው የሚል መመሪያ ያለው ማቅ ፍላጎቱ እንዲሳካ የማያደርገው ነገር እንደሌለው የሚያስረዳው አቤቱታ 69 አመቱን አንጋፋ ኮሌጅ እዚህ ግባ የሚባል ካሪኩለም የሌለው እናደረጃውም የትምህርት ሚኒስቴርን ተቀባይነት የማይመጥን በማለት የኮሌጁ ተማሪ የሆነው መምህር አሰግድ ይባረርልኝ የሚለው አቤቱታ ይህን ይመስላል።
የአቤቱታው ዝርዝር
በመሠረቱ አመልካች ኮሌጅ በራሱ ሕጋዊ ሰውነት የለውም፡፡ እንደ ሌሎች የትምህርት ተቋማት በትምህርት ሚኒስቴር ተመዝግቦና የንግድ ፈቃድ አውጥቶ የሚያስተምር ተቋም አይደለም፡፡ ቀደም ሲል በነበረው መንግስት ተዘግቶ ከቆየ በኋላ በቀጥታ በመንግስት ፈቃድ ቤተክርስቲያኗ ከፍታ የሐይማኖቷን ተከታዮች ለማነጽ መምህራንን የምታፈራበት ነው፡፡ የሚሰጠው የትምህርት ዓይነትም ሆነ ብዛት በትምህርት ሚኒስቴር ቁጥጥር የሚደረግበት አይደለም፡፡ በመሆኑም በስሙ ሊከሰሰም ሆነ ሊፈረድበት አይችልም፡፡ በሕግ ‹‹ሰው›› የሚለውን መስፈረትም አያሟላምና፡፡ ስለዚህ የስር /ቤቶች ጉዳዩን ተቀብለው ማስተናገድም ሆነ አስገዳጅ ውሳኔ መስጠታቸው መሠረታዊ የህግ ስህተት ነው፡፡
ይህ አቤቱታ ቀላል የማይባሉ ስህተቶች ያሉትና እራሱ ኮሌጁ ባለፉት አመታት ባስተማርኩዋቸው ተማሪዎቼ ደረስኩበት የሚለውን ስኬት የሚንድና ተማሪዎቹ ወደ ሌላ የትምህርት ተቋማት ሄደው ለመማር ያላቸውን ፍላጎት ከንቱ የሚያደርግ ነው። አንድ የቤተክርስቲያን ልጅን ካላባረርኩ በሚል ህልውና እስከመካድ ድረስ የደረሰ አቤቱታ ማቅረብ እጅግ በጣም አሳፋሪ የሆነ ተግባር ነው።

አቤቱታው ኮሌጁ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ    “…/ቤቱ ወደ ኮሌጅ ደረጃ ከፍ እንዲል የታቀደበት ዋናው ዓላማ የቤተክርስቲያኒቱን ከፍተኛ ትምህርት የተማሩ ሊቃውንት ዘመናዊውንም ትምህርት በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀስሙ የማድረጉን ጥረት ሊሟሉ የሚችሉ የሃይማኖትና የግብረ ገብነት መምህራንና የወንጌል ልዑካንን መልሰው እንዲያፈሩ፣ ለማድረግ ከኮሌጁ በዘመናዊውና በጥንታዊው ትምህርት በከፍተና ደረጃ ሰልጥነው የሚወጡት መምህራንም ለተከታዩ ትውልድ የኢትዮጵን መንፈሳዊ ቅርስ ለማስተላለፍ እንዲችሉ ታቅዶ ነበር፡፡…”የሚለውን የኮሌጁን ራዕይና እንዲሁም ይህ ኮሌጅ በመከፈቱ ደረስኩበት የሚለውን ስኬት ማለትም“…ተቋሙ 48 ዓመታት ዕድሜው በርካታ ኢትዮጵያውያንን በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በዲፕሎማ እና በሰርቲፊኬት ያስመረቀ ሲሆን ከእነዚህም መካከል በመንፈሳዊ አገልግሎት እስከ ፓትርያርክነት፣ በዩኒቨርስቲ መምህርነት እስከ ፕሮፌሰርነት፣ በመንግሥት መሥሪያ ቤት አገልግሎት እስከ ሚኒስትርነት፣ ደረጃ የደረሱ ይገኙበታል፡፡የሚለውን ዋጋ የሚያሳጣ ነው።
የክስ ሂደቱ ዝርዝር ምንድን ነው?
ኮሌጁ የቀድሞ የዲፕሎማ ተማሪዎቹ የዲግሪ ፕሮግራም ለመቀጠል እንደሚችሉ በፈቀደው መሰረት መምህር አሰግድ ሣህሉ ከዚህ ቀደም የኮሌጁ ዲፕሎማ ያለው በመሆኑ እድሉን ለመጠቀም ለመማር ይመዘገባል። ወዲያውኑ ያለበቂ ምክንያት የእግዚአብሔርን ሀሳብ ለምን ታገለግላለህ? በማለት በማኅበረ ቅዱሳን አድሮ ገና በልጅነቱ ሲዋጋው የነበረው ሰይጣን መንፈሱ ታወከበትና መምህሩን ከትምህርት ከበታው ለማባረር ግድግዳ መቧጠጥ ጀመረ።
መጀመሪያ የተጠቀመው ሁሌም የሚያደርገውን የፕሮፓጋንዳ ጦርነት አስቀድሞ ማወጅ ነበረ። ለዚህም ማቅ በሚያስተዳድረውና በፈረንጆቹ 2009 `Owned by mahebere kiduasan` የሚል ቃልን ለጥቂት ቀናት ከለጠፈበት በኃላ ያወረደው ደጀ ሰለም የተባለው የመአት፣ የክስ እና የነቀፋ ብሎጉ  ላይ ኮሌጁ የትምህርትህን አቁም ጥያቄ ከማቅረቡ ከወር በፊት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪውን አባረረ በማለት መምህሩ ጨርሶ የማያውቃቸውን የፈጠራ ታሪኮች በመደርደርሰፊ ሪፖርታዥ ሰራ። በዚህ ጊዜ መምህሩ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ አድሮ ማኅበሩን እንቅልፍ አሳጥጦ እያንቀሳቀሰ ያለው የክስና የአሳዳጅነት መንፈስ አሁንም እንደተከተለው አወቀና የሚገለጥበትን ጊዜ በጸሎት መጠበቅ ጀመረ።
ማኅበረ ቅዱሳን ደጀ ሰላም ላይ ተባረረ በማለት ካስነገረ ከአንድ ወር በኃላም ይኼን ለማስፈጸም ወደ ኮሌጁ ሄዱ በሰራው ሴራ መምህር አሰግድ ወደ ኮሌጁ ቅጥር ጊቢ እንዳይገባ የሚል ትዕዛዝ በኮሌጁ ዲን በኩል ለጥበቃዎች ተላለፈ። መምህሩም በሕጋዊ መስመር የገባሁ ተማሪ ስለሆንኩ በሕጋዊ መንገድ ካልሆነ በቀር እንዳትገባ በሚል የቃል ትዕዛዝ ትምህርቴን አላቆምም በማለቱ ከአንድ ሣምንት በኃላ በወረቀት ታግደሃል ተባለ። እሱም ደብዳቤውን ተቀብሎ ሲመለከተው የሕግ ክፍተት እንዳለበት ስለተረዳ ኮሌጁን ከሰሰ። የክስ ወረቀት ለኮሌጁ እንደደረሰ ያወቀው ማኅበረ ቅዱሳን አላማዬ ግብ ሳይመታ ሊቀር ነው በማለት የኮሌጁን ዲን ጉዳዩን ለኔ ጣሉት ብሎ ደስታ በርሔ የተባለ የአመራር አባሉን የኮሌጁ ጠበቃ አድርጎ በማቆም ከዚህ በፊት በፈጠራ ወሬ እንዲታገድ ያደረገው ተማሪ ትምህርቱን እንዳይቀጥል ለማድረግ የሀሰት ማስረጃዎችን በማደራጀት መከራከር ጀመረ። ፍርድ ቤቱ ክሱ እንዲንቀሳቀስ ሲያዝ ወዲያውኑም መምህር አሰግድ ሣህሉ ወደ ትምህርት ገበታው እንዲመለስ በማዘዙ መሞህሩ ትምህርቱን ቀጥሎ እንዲከራከር ተደረገ። የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ተመልክቶ በሐምሌ 7 ቀን 2003 .. ለመምህር አሰግድ በመፍረድ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላለፈ።

ቅዱስ ሲኖዶስ የግለሰቦችን ነጻነት በመጋፋት፤ስም በማጥፋትና ከማውገዝ የወንጀል ድርጊት ሊቆጠብ ይገባል!

አሁን ባለው ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ ማንኛውም ሰው የመሰለውን እምነት የመከተል መብቱ የተጠበቀ ነው። ከፕሮቴስታንቱ ጎራ ለመቀላቀል ወይም ካቶሊክ  ለመሆን አለያም  እስላም የማንም ክልከላ አይደርስበትም። የሌላውን መብት እስካልነካ ድረስ በመሰለው ቦታ እምነቱን የማስተማር፤ የመስበክ መብቱን እየተገበረ እንደሚገኝ ይታወቃል። ያንንም ስንል ሁሉ ነገር እንከን አልባ ነው እያልን እንዳልሆነም ሳይዘነጋ ነው። እያልን ያለነው ሁሉም እምነቶች ዋና መሠረታዊ ነጥብ በእያንዳንዳቸው በኩል የሚመለከው  አምላክ ከሌላው የተሻለ፤ ዋስትናን የሚሰጥ፤ ዘላለማዊነትን የሚያጎናጽፍ፤ የሚያጸድቅና የሚኰንን መሆኑን በማስረዳት  ለሌላው በማስተማር ተከታዮችና አባላትን ማፍራት መቻላቸው የማይካድ መሆኑን  ነው። በአብዛኛው  ችግሮች የሚመጡት በእምነት ተቋማት በራሳቸው በኩል ሲሆን ሌላውን አዲስና መጤ፤ የሰይጣን ትራፊ እንደሆነ አድርጎ ጥላሸት በመቀባት በትምህርት ሳይሆን በማስፈራራት አባሎቹን ጠብቆ ለማቆየት ሲሞክርና ማብጠልጠል ላይ ብቻ የመንጠልጠል ችግር እየተስተዋለ  ሲገኝ ነው። እንዲያውም አንዳንዶች የእምነት ተቋሙን ስም እየጠሩና የሰይጣን ቁራጭ አድርጎ በመሳል በጽሁፍ፤ በምስልና በቃል የተደገፈ አስተምህሮ የሚያስተላልፉና የሚያሰራጩ በየትኛውም ወገን ባሉ የእምነት ተቋማት በኩል ልቅ በሚባል ደረጃ ሲፈጽም ይስተዋላል።
 ስለስህተት አስተምህሮ ለመስበክ ከእምነቱ መሰረታዊ አቋም ተነስቶ ከሚሰጥ አንጻራዊ ስብከትና ትምህርት ውጪ የሌለ ነገር በመፍጠር ወይም በውሸት ላይ ተመስርቶ  በቀጥታ የእምነቱን ተቋም ስም በመጥራት ለማጥቃትና ለማንቋሸሽ የሚውል ከሆነ አሁን ባለው የኢትዮጵያ ወንጀል ሕግም ይሁን በአማኙ ወይም በእምነት ተቋሙ ላይ ለሚደርስ የሞራል ጉዳት በፍትሐ ብሔር ህግ የሚያስጠይቅ ጉዳይ ነው።

የማቅ ሁለት ባላ!

ማኅበረ ቅዱሳን ከደጀ ሰላም፤አንድ አድርገንና ከሌሎቹ ውርንጭላ ብሎጎቹ ውጪ የዘመቻ አድማሱን በማስፋትበሀገሪቱ  ፖለቲካዊ ለውጥ እንዲመጣ ከሚታገሉ ሚዲያዎች ጋር ኅብረቱን በማሳየት ወደግልጽ እርምጃ ቀይሮታል። ማንም በፈለገው የፖለቲካ አቋም የመሄድና የመሰለፍ መብት እንዳለው ብናምንም ማኅበረ ቅዱሳን ግን ሃይማኖታዊ አቋሙን ከየትኛውም ፖለቲካ ገለልተኛ ሆኖ ለመስራት የተስማማበትን መተዳደሪያ ደንቡን ጥሶ በማኅበሩ አመራር አባል በኩልም ጭምር መግለጫ በመስጠት ለፖለቲካዊ ለውጥ ትግል መድረኮች የጽሁፍና የቃል አቤቱታውን በመስጠት መቀላቀሉን አሳይቷል። ድሮም «ማቅ» ፖለቲካውንና ሃይማኖቱን እያቀላቀለ የሚሄድ እንጂ ስለኦርቶዶክስ የሚገደው አይደለምና ይህንኑ አሳይቷል። ማቅ ሁለት ባላ መትከሉን አቁም!