Sunday, May 13, 2012
Saturday, May 12, 2012
የሲኖዶስን ውሳኔ የሚያወራ ግን እሱ ሊፈጽመው የማይፈልግ፣ በሌሎች ላይ ለመጫን የሚሮጥ አፄ በጉልበቱ ማኅበር ብቻ ነው!
ቅዱስ
ሲኖዶስ ባሳለፈው የ2002 ውሳኔ እንደተመለከተው መጻሕፍት፤ መጽሔት፤ የመዝሙር ካሴት፤ ሲዲ፤ ቪሲዲ፤ በአጠቃላይ የድምጽና የህትመት ውጤቶችን
ሁሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም አሳትሞ ለማውጣት በቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ጉባዔ በኩል አስመርምሮና የቤተክርስቲያኒቱን
ሥርዓት ጠብቆ ለመሆኑ ሲፈቀድለት ብቻ እንዲሆን አስረግጦ ይወስናል። ይህንኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የማኅበሩ አፈ ጉባዔ የሆነው
ደጀ ሰላም ብሎግ «እሰይ ቅዱስ ተግባር» በማለት ድጋፉን በድረ ገጹ ላይ በግንቦት 10/2010 ዓ/ም ጽሁፉ ያወጣል። ይህንኑ በማኅበሩ
አፈ ጉባዔ «ደጀ ሰላም» አድናቆት የተቸረውን ውሳኔ ተከትሎም አባ
ሠረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል የማደራጃ መምሪያ ኃላፊው የማቅ የ20 ዓመት ልሳኖቹና ሌሎች ህትመቶቹን ሁሉ በሊቃውንት ጉባዔው በኩል እየተመረመረ እንዲወጣ ትእዛዝ ይሰጣሉ። አፄ በጉልበቱ ማኅበርም ጆሮ ዳባ ልበስ ይልና በነበረው መልኩ ኅትመቶቹን
በጓሮው እያሳተመ ይቸበችባል። አባ ሠረቀም የሲኖዶስ ውሳኔ ተከብሮ ለሕትመት ማለፍ በሚገባው መንገድ ለመሄድ
ባለመቻሉ የአፄ በጉልበቱ ማኅበር ደንበኛ ለሆነው «ሜጋ ማተሚያ ድርጅት»
ምክንያቱን ጠቅሰው የአፄው መጽሔቶች መታተም እንደሌለባቸው ማገጃ ይጽፋሉ።
አፄ
በጉልበቱ፤ «አሁን በዓይኔ መጣህ!» ይልና ሀገር ይያዝልኝ በማለት ቀውጢ በማድረግ አቧራ ያስነሳል። የአፄ በጉልበቱ ጉዳይ ፈጻሚ የማደራጃ መምሪያው
ሊቀጳጳስ በግላቸው ቲተር፤ ማመልከቻቸውን ለሥራ አስኪያጁ በማስገባት እግዱ እንዲነሳና ህትመቱ እንዲቀጥል አቤቱታቸውን ያቀርባሉ።
እንግዲህ ይታያችሁ!! ሲኖዶሱ በሊቃውንት ጉባዔ በኩል ማንኛውም ህትመት ተመርምሮ እንዲያልፍ መወሰኑን ልብ በሉ!! በውሳኔው ላይ
የነበሩት ሊቀጳጳስ ግን ለአፄው ሲሆን እንዲሻር በደብዳቤ ጭምር የሚጠይቁበት ቤተክህነት መሆኑንም አስተውሉ!! እነ በጋሻው፤ ትዝታውና ምርትነሽ ላይ ሲሆን የሲኖዶሱን ውሳኔ ጥሰዋል እያለ
የሚጮኸው አፄ በጉልበቱ ህግ ማስከበሩ በእሱ ላይ ሲመጣ ግን ተላላኪ ጳጳሶቹን ሳይቀር ተጠቅሞ ህግ መሻር እንደሚችል ስንመለከት
ከመግረም አልፎ ያሳዝናል።
አፄው
በማደራጃ መምሪያው ሊቀጳጳስ በኩል ያቀረበው ማመልከቻ፤ የአባ ሠረቀ ብርሃን
የማገጃ ደብዳቤ እንዲነሳ ከመደረጉ በፊት ህትመቱ በጓሮ ማተሚያ ቤት ታትሞ ገበያ ላይ ይውላል። እንግዲህ የሲኖዶስ ውሳኔ ውሃ
በላው ማለት ነው። ሊቃውንት ጉባዔም የአፄውን ኅትመቶች ለመመርመር እንደተመኘ
አፉን ከፍቶ ቀረ። ከሁሉም የሚያሳዝነው ቤተክህነቱ ለእውነት የቆመ መስሏቸው አባ ሠረቀ ብርሃን ሕግ ይከበር በሚል አቋማቸው ሲዳክሩ
አፄ በጉልበቱ ይህንን ሰውዬ ከዚህ ቦታ ካላሽቀነጠርኩት ይልና «የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶና የሙስና ምሕዋር» የሚል ታርጋ ይለጥፍና
ዘመቻውን አጧጥፎ አባ ሠረቀን ያስነሳል። አፄውም በትግሉ ውጤት «እፎይ» ብሎ በመተንፈስ «ድሮስ ከእኔ ጋር መወዳደር ለመላላጥ!»
በማለት በአባ ሠረቀ ድካም ላይ እንደተሳለቀ እኛም ግምታችንን አኑረናል። አባ ሠረቀ
ብርሃን ለጻፉት ደብዳቤና በአፄው ላይ ህግን ለማሳየት በመጣራቸው የተሰጣቸው ስም ይህንን ይመስላል።
አፄው
በሀሰት ስብከቱ ያሰከረው ምድረ ደጋፊ ሁሉ በአባ ሠረቀ መነሳት «እልል!» በማለት ድጋፉንና ደስታውን ለመግለጽ ጊዜ አልፈጀበትም። አባ ሠረቀ ግን የአፄው ዱላና እንግልት ያረፈባቸው ሲኖዶስ የወሰነውንና ራሱ
«ደጀሰላም» ብሎግ የዘገበውን መመሪያ ለመተግበር እንጂ በግል ከልባቸው አንቅተው አፄውን ለማጥቃት ያመነጩት አካሄድ አልነበረም።
ይሁን እንጂ አፄው የቀኝ እጁ ጳጳሳት የራሳቸውን ውሳኔ እንኳን እስከመሻር የት ድረስ እንደሚሄዱለት በማሳየት አንድ እውነት ያረጋገጠ ነበር።
የማይዘልቅ ማኅበር በጠጅ ይጀመራል የማያድግም ልጅ ዓይነምድሩ ይበዛል!
የጽሁፉ ምንጭ፤ አባ ሰላማ Wednesday, May 18, 2011
ፖስት
አንድ
ማኅበር ለመጀመሪያ ጊዜ በጠጅ ከተጀመረ የሰካራሞች መሰብሰቢያ ይሆንና በመጨረሻ በብጥብጥ ይበተናል፤ ምክንያቱም ማህበሩን የጀመረው ግለሰብ በጠጅ ከጀመረው የሚቀጥለው ተረኛም ከማን አንሼ በሚል ስሜት ለአባላቱ ጠጅ ስለሚያቀርብ፤ ቀጥሎ ማህበር የሚደግሰውም እንዲሁ እንደጓደኞቹ ስለሚወዳደር ማህበሩ በጠጅ ተጀምሮ በጠጅ ይበተናል ማለት ነው ሰካራሞች የሚናገሩትን እና የሚሠሩትን ስለማያውቁ ሁልጊዜ መስከራቸው ሕይወታቸውንም ሆነ ኢኮኖሚያቸውን ያቃውሳልና።
የማያድግ
ልጅም ከሚበላው ፍሬ ነገር ይልቅ ወደ ውጭ የሚያወጣው ዓይነ ምድር ከበዛ ሰውነቱ ንጥረ ምግቦችን መቀበል ስለማይችል ሆዱ ተነፍቶ መሞቱ ወይም ቀጭጮ አቅመ ቢስ ሆኖ መቅረቱ አይቀርም፤ የማያድግ ልጅ እንትኑ ይበዛል የተባለው ለዚህ ነው።
ማኅበረ
ቅዱሳንም ገና ሲጀመር ዓይነምድሩ የበዛ በነገር የተጀመረና በጠንቋዮች ምክር ስለሚመራ ባጭሩ መቀጨቱ የማይቀር ነው። ማህበረ ቅዱሳን በነ አቡነ ማቴዎስ፤በነ ቀሲስ ዳኛቸው፤ በነ ኃይለ ጊዮርጊስ በነ አቶ ታየ [የሽዋ ንጉሥ ሊሆን የነበረ] ወዘተ በደገሱት የተንኮል ድግስ ወጣቱን በነገር እያሰከረ ሲያወላግድ ከዚህ ደርሷል። ዛሬም መካኒሳ አካባቢ በአንድ ግለሰብ ቤት ውስጥ በሚደረግ ምሥጢራዊ ስብሰባ ነገር እየተቀበለ ወደ ቤተ ክህነት ብቅ ይልና በግማት የተሞላውን ዓይነምድሩን ጥሎ ይሄዳል።
Subscribe to:
Posts (Atom)