ዘሪሁን ሙላቱ እና ፋንቱ ወልዴ እንደተጋበዙ ውስጥ ዐዋቂ ምንጮቻችን ገልፀዋል።
በ"ማኅበረ ቅዱሳን" የሀዋሳ ንዑስ ማዕከል አስተባባሪነት በሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ስብከተ ወንጌል ክፍል ስም ከሚያዘያ 19 እስከ 21/ 2004 ዓ.ም እና ከግንቦት 3 እስከ 5/2004 ዓ.ም የሚቆዩ ሁለት ጉባዔያት በመዘጋጀት ላይ መሆናቸው ተሰማ፡፡
የአቡነ ገብርኤል ሀገረ ስብከት ከየካቲት 25 እስከ የካቲት 27/2004 በሕገ ወጥነት ያካሄደው ጉባዔ እንዳይካሄድ የካቲት 22 ቀን 2004 ዓ.ም በቁጥር 221/54/2004 በወጣ ደብዳቤ የዕግድ ደብዳቤ ቢታዘዝም፣ ትዕዛዙን ባለመቀበል፣ የኢትዮጵያ ሲኖዶስን ህልውና የማይቀበለውን መምህር ዘበነ ለማን፣ ዳንኤል ክብረትንና ምሕረተአብ አሰፋን በመጋበዝ ፍጹም ለማኅበረ ቅዱሳን የወገነ ድራማን ተጫውቷል፡፡
አሁንም፣ መምህር ዘበነ ለማን በድጋሚ በመጥራት፣ ፋንቱ ወልዴን ከአሜሪካ፣ ጎረምሳውን ዘሪሁን ሙላቱንና ዘማሪ ይልማ ኃይሉን በመጋበዝ ፍጹም የሆነውን ማኅበረ ቅዱሳናዊ ግዛት ለማስፋፋት ደፋ ቀና በመባል ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡