(ዘርዓ ያዕቆብ ፈላስፋ) ክፍል ሁለት
የሰው ፍጥረት ታካችና ደካማ መሰለኝ፡፡ ሰው ግን ፍቅርን ቢወዳትና በጣም ቢያፈቅራት የተሸሸገውንም ፍጥረትን ቢያውቅ ይወዳል፡፡ ይህም ነገር እጅግ ጥልቅ ነውና በትልቅ ድካምና ትዕግስት ካልሆነ በስተቀር አይገኝም፡፡ ጠቢቡ ሰለሞን፡ “ከፀሐይ በታች ስለተደረገው ሁሉ ጥበብን ለመፈለግና ለመመርመር ልቤን ሰጠሁ፡፡ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች እንዲደክሙበት የሰጣቸውን ክፉ ስራ አየሁ”ይላል፡፡
ስለዚህ ሰዎች ሊመረምሩት አይፈልጉም፡፡ ሳይመረምሩ ከአባቶቻቸው የሰሙትን ማመን ይመርጣሉ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ሰውን የምግባሩ ጌታ ክፉ ወይም መልካም የፈለገውን እንዲሆን ፈጠረው፡፡ ሰውም ክፉና ዋሾ መሆንን ቢመርጥ ለክፋቱ የሚገባውን ቅጣት እስኪያገኝ ድረስ ይችላል፡፡ ነገር ግን ሰው ሥጋዊ ነውና ለሥጋው የሚመቸውን ይወዳል፡፡ ክፉ ይሁን መልካም ለስጋው ፍላጎት የሚያገኝበትን መንገድ ሁሉ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር ሰው የፈለገውን እንዲሆን ለመምረጥ መብት ሰጠው እንጂ ለክፋት አልፈጠረውም፡፡ ስለዚህ መምረጥ ክፉ ቢሆን ለቅጣት መልካም ቢሆን ደግሞ የመልካምነት ዋጋ ለመቀበል የተዘጋጀ እንዲሆን እድል ሰጠው፡፡
በሕዝብ ዘንድ ክብርና ገንዘብ ለማግኝት የሚፈልግ ዋሾ ሰው ነው፡፡ ዋሾ ሰው ይህን በሐሰተኛ መንገድ ሲያገኝ እዉነት አስመስሎ ሀሰት ይናገራል፡፡ ሊመረምሩ የማይፈልጉ ሰዎች እውነት ይመስላቸውና በእርሱ በጽኑ ሃይማኖት ያምናሉ፡፡ እስኪ ሕዝባችን በስንት ውሸት ያምናል? በጽኑ ሃይማኖት ያምናል፡፡ በሃሳበ ከዋክብትና በሌላም አስማት፣ አጋንንት በመሳብና በመርጨት፣ አስማት በማድረግ፣ በጥንቆላ ሁሉ ያምናሉ፡፡ ይህንን ሁሉ መርምረው እውነቱን አግኝተው አያምኑም፡፡ ነገር ግን ከአባቶቻቸው ሰምተው ያምናሉ፡፡ እነዚያስ የፊተኞቹ ገንዘብና ክብር ለማግኝት ካልሆነ በቀር ስለምን ዋሹ? እንዲሁ ህዝብን ሊገዙ የሚፈልጉ ሁሉ እውነት እንነግራቸኋለን እግዚአብሔር ወደናንተ ላከን ይሏቸዋል፡፡ ሕዝቡም ያምናሉ፡፡
ከነርሱም በኋላ የመጡት እነርሱ ሳይመረምሩ የተቀበሏትን የአባቶቻቸውን እምነት አልመረመሩም፡፡ ከዚያ ይልቅ ለእውነትና ለሃይማኖታቸው ማስረጃ ታሪክን፣ ምልክቶችን ፣ ተዓምራትን እየጨመሩ እውነት አስመስለው አጸኑት፡፡ በነገሩ ሁሉ እግዚአብሔርን ስም ጨመሩ። እግዚአብሔርንም የሐሰኞች ተካፋይና የሐሰት ምስክር አደረጉት፡፡
ጥልቅ ምርመራ ስለ ሙሴና መሐመድ ሕግጋት
ለሚመረምር ግን እውነት ቶሎ ይገለፃል፡፡ ፈጣሪ በሰው ልብ ያስገባውን ንጹህ ልቦና የፍጥረት ሕግጋትና ስርዓትን ተመልክቶ የሚመረምር እርሱ እውነትን ያገኛል፡፡ ሙሴ ፈቃዱንና ሕጉን ልነግራችሁ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኬ መጣሁ ይላል፡፡ ከሆነ ታዲያ «ሴት በወር አበባ ወቅት የረከሰች ናት» ለምን ይላል? የሙሴ መጽሐፍ ከፍጥረት ሕግ ሥርዓትና ከፈጣሪ ጥበብ ጋር አይስማማም፡፡ ከውስጡ የተሳሳተ ጥበብ ይገኛል፡፡ ለሚመረምር ግን እውነት አይመስለውም፡፡ በፈጣሪ ፈቃድና በፍጥረት ህግ የሰው ልጅ እንዳይጠፋ ልጆችን ለመውለድ ወንድና ሴት በፍትወተ ሥጋ እንዲገናኙ ታዟል፡፡ ይህም ግንኙነት እግዚአብሔር ለሰው በሕገ ተፈጥሮ የሰጠው ነው፡፡ እግዚአብሔርም የእጁን ሥራ አያረክስም፡፡ እግዚአብሔር ዘንድ እርኩሰት ሊገኝ አይችልም፡፡ ፈጣሪ የፈጠረውን መልሶ አያረክሰውም እላለሁ።
እንደገናም የክርስቲያን ሕግ ለማስረጃዋ ተአምራቶች ተገኝተዋልና ከእግዚአብሔር ናት ይላሉ፡፡ ነገር ግን የወሲብ ሥርዓት የተፈጥሮ ሥርዓት እንደሆነ ምንኩስና ግን ልጆች ከመውለድ ከልክሎ የሰውን ፍጥረት አጥፍቶ የፈጣሪን ጥበብ የሚያጠፋ እነደሆነ ልቦናችን ይነግረናልና ያስረዳናል፡፡ የክርስቲያን ሕግ ምንኩስና ከወሲብ ይበልጣል ብትል ሐሰት ትናገራለችና ከእግዚአብሔር አይደለችም፡፡ የፈጣሪን ሕግ የሚያፈርስ እንዴት ከጥበብ በለጠ ? ወይስ የእግዚአብሔርን ስራ የሰው ምስክር ሊያስተካክለው ይቻለዋልን ? ሰዎች ግን ሳይመረምሩ ምንኩስና ከጋብቻ ትበልጣለች ይላሉ። ዘርን የሰጠ ፈጣሪ ዘር አያስፈልግም አይልም። ቀጣፊዎች በእግዚአብሔር ስም እውነት አስመሰሉት እንጂ።
እንዲሁም መሐመድ የማዛችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበልኩትን ነው ይላል፡፡ መሐመድን መቀበል የሚያስረዱ የተዓምራት ፀሐፊዎች አልጠፉምና ከሱም አመኑ፡፡ እኛ ግን የመሐመድ ትምህርት ከእግዚአብሔር ሊሆን እንደማይችል እናውቃለን፡፡ የሚወለዱ ሰዎች ወንድና ሴት ቁጥራቸው ትክክል ነው፡፡ በአንድ ሰፊ ቦታ የሚኖሩ ወንድ ሴት ብንቆጥር ለእያንዳንዱ ወንድ አንዲት ሴት ትገኛለች እንጂ ለአንድ ወንድ ስምንት ወይም ዐሥር ሴቶች አይገኙም፡፡ የተፈጥሮ ህግም አንዱ ከአንዲት ጋር እንዲጋቡ አዟል፡፡ አንድ ወንድ ዐሥር ሴት ቢያገባ ግን ዘጠኝ ወንዶች ሴት የሌላቸው ይቀራሉ፡፡ ይህም የፈጣሪን ስርዓትና ሕገ ተፈጥሮን የጋብቻንም ጥቅም ያጠፋል፡፡ አንድ ወንድ ብዙ ሴቶች ሊያገባ ይገባዋል ብሎ በእግዚአብሔር ስም ያስተማረ መሐመድ ግን ትክክል ነው አልልም፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ አልተላከም፡፡ ጥቂት ስለጋብቻ ሕግ መረመርኩ ፡፡ ከመጀመሪያም ለአዳም አንድ ሴት ከመፍጠር ይልቅ ዐሥር ሴት ያልፈጠረለት ለምንድነው? ይህን የፈጣሪ ሕግ ሳይመረምሩ የመሐመድን ሕግ መቀበል ስህተት ነው። ከእግዚአብሔር እንደተገኘ ብመረምርም በህገ ኦሪትና በክርስትናና በእስልምና ሕግ ፈጣሪ በልቦናችን ከሚገልጽልን እውነት እና እምነት ጋር የማይስማማ ብዙ ነገር አለ አልኩ።
ፈጣሪ ለሰው ልጅ ክፉና መልካም የሚለይበት ልቦና ሰጥቶታል፡፡ «በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን» እንደተባለውም የሚገባውን የማይገባውን ሊያውቅ፣ እውነትን ከሐሰት እንዲለይ ነው፡፡ ስለዚህ የልቦናችን ብርሃን እንደሚገባ በእርሱ ብናይበት ሊታይልን አይችልም፡፡ ፈጣሪያችን ይሄን ብርሃን የሰጠን በርሱ እንድንድን ነው እንጂ እንድንጠፋ አይደለም። የልቦናችን ብርሃን የሚያሳየን ሁሉም ከእውነት ምንጭ ነው፡፡ ሰዎች ከሐሰት ምንጭ ነው ቢሉን ግን ሁሉን የሰራ ፈጣሪ ቅን እንደሆነ ልቦናችን ያስረዳናል፡፡ ፈጣሪ በመልካም ጥበቡ ከሴት ልጅ ማህጸን በየወሩ ደም እንዲፈስ አዟል፡፡ ሙሴና ክርስቲያኖች ግን ይህን የፈጣሪ ጥበብ እርኩስ አደረጉት፡፡
እንደገና ሙሴ እንዲህ ያለችው ሴት ከተቀመጠችበት የተቀመጠውንም፤ የተገናኛትንም ያረክሳል፡፡ ይህም የሙሴ ህግ የሴትን ኑሮ በሙሉና ጋብቻዋን ከባድ አድርጎታል፡፡ የመራባትንም ህግ አጥፍቷል፡፡ ልጆችንም ከማሳደግ ከልክሎ ፍቅርንም ያፈርሳል፡፡ ስለዚህ ይህ የሙሴ ሕግ ሴትን ከፈጠረ ሊሆን አይችልም እላለሁ፡፡ «ሞተውን ሰው በድን የነካ ሁለመናውን ባያጠራ የእግዚአብሔርን ማደሪያ ያረክሳል ያ ሰው ከእስራኤል ዘንድ ተለይቶ ይጠፋል » የምትለው የሙሴ ሕግ ሞትን ከፈጠረ ከእግዚአብሔር አይደለችም። እንደገናም የሞቱትን ወንድሞቻችንን ልንቀብራቸው ተገቢ መሆኑን ልቦናችን ይነግረናል፡፡ በድኖቻቸውም በሙሴ ጥበብ ካልሆነ በስተቀር ከመሬት የተፈጠርንበት ወደ መሬትም ልንገባበት በፈጣሪያችን ጥበብ እርኩሳን አይደሉም፡፡ ነገር ግን ለፍጥረት ሁሉ እንደሚገባ በትልቅ ጥበብ የሰራ እግዚአብሔር ሥርዓቱን አያረክሳውም፡፡ ሰው ግን የሐሰትን ቃል እንዲያከብር ብሎ ሊያረክሰው ይፈልጋል፡፡
እንደዚሁም እግዚአብሔር የከንቱ ነገር አያዝም፡፡ «ጥረህ ግረህ በላብህ ወዝ ብላ» ያለው አምላክ ይህን ብላ፣ ይህን አትብላ፣ ዛሬ ብላ፣ ነገ አትብላ አይልም፡፡ ለክርስቲያኖች እንደሚመስላቸውና የጾም ሕግጋት እንደሚጠብቁ ሥጋን ዛሬ ብላ፤ ነገ አትብላ አይልም፡፡ ለክርስቲያኖች እንደሚመስላቸውና የጾም ሕግጋት እንደሚጠብቁ ሥጋን ዛሬ ብላ ነገ ግን አትብላ አይልም፡፡ እስላሞችንም እግዚአብሔር ለሊት ብሉ ቀን አትብሉ ብሎ ይሄንና የመሳሰሉትን አይላቸውም፡፡ የፍጥረታችንን ጤና የማያውክ ነገር ሁሉ ልንበላ እንደሰለጠንን ልቦናችን ያስተምረናል። አንድ የመብል ቀን፤ አንድ የጾም ቀን ግን ጤናን ያውካል፡፡ የጾም ህግ መብላትን ለሰው ሕይወት ከፈጠረና ልንበላቸው ከፈቀደ ፈጣሪ የወጣ አይደለም፡፡ በልተን ልናመሰግነው እንጂ በረከቱን ልናርም አይገባንም፡፡ ሕገ ፆም የሥጋን ፍትወት ለመግደል የተሰራ ነው የሚሉም ቢኖሩ ፍትወተ ሥጋ ወንድ ወደ ሴት ሊሳብ ሴትም ወደ ወንድ ልትሳብ የፈጣሪ ጥበብ ነውና እርሱ ፈጣሪ በሰራው በታወቀ ማጥፋት አይገባም እላለሁ፡፡ ፈጣሪያችን ይህን ፍትወት ለሰው፤ ለእንስሳት ሁሉ በከንቱ አልሰጠም፡፡ ነገር ግን ለዚህ ዓለም ሕይወትና ለፍጥረት የተሰራለት መንገድ ሁሉ መሠረቱ ሆኖ እንዲቆይ ይህ ፍትወት ለሰው ልጅ ተሰጠ፡፡ አስፈላጊያችንን ልንበላ ይገባናል፡፡ በእሁድ ቀንና በበዓል ቀናት በአስፈላጊው ልክ የበላ እንዳልበደለ እንዲሁ በአርብ ቀንና ከፋሲካ በፊት ባሉት ቀናት ለክቶ የሚበላ አልበደለም፡፡ እግዚአብሔር ሰውን በሁሉ ቀንና በሁሉ ወራት ካስፈላጊ ምግብ ጋር አስተካክሎ ፈጥሮታል፡፡ አይሁድ፣ ክርስቲያንና እስላም ግን የፆምን ሕግ ባወጡ ጊዜ ይህን የእግዚአብሔር ሥራ ልብ አላሉም፡፡ እግዚአብሔር ፆምን ሰራልን፤ እንዳንበላም ከለከለን እያሉ ይዋሻሉ፡፡ እግዚአብሔር ፈጣሪያችን ነው፡፡ ግን የምንበላውን ምግባችንን እንድንመገበው ሰጠን እንጂ እርሱን ልናርም አይደለም፡፡ በሚያስተውል ልቡናችን ለክተን መኖር የኛ ፈንታ ነው።
ስለ ሃይማኖቶች መለያየት
ሌላ ትልቅ ምርመራ አለ፡፡ ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ትክክል ናቸው፡፡ እርሱም አንድ ሕዝብ ለሕይወት፤ አንድ ሕዝብ ለሞት፤ አንድም ለምህረት፤ አንድም ለኩነኔ አልፈጠረም፡፡ ይህም አድሎ በስራው ሁሉ ጻድቅ በሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ እንደማይገኝ ልቦናችን ያስተምረናል፡፡ ሙሴ ግን አይሁድን ለብቻቸው እንዲያስተምራቸው ተላከ፡፡ ለሌሎች ሕዝቦች ፍርዱ አልተነገረም፡፡ እግዚአብሔር ስለምን ለአንድ ሕዝብ ፍርድ ሲነግር ለሌላው አልነገረም፡፡ በዚህም ጊዜ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ትምህርት ከኛ ጋር ካልሆነ በስተቀር አይገኝም ይላሉ፡፡ አይሁድና እስላም የህንድ ሰዎችም ሌሎችም ሁሉ እንደነሱ ይላሉ፡፡ እንዲሁ ደግሞ ክርስቲያኖች እርስ በርሳቸው አይስማሙም፡፡ ካቶሊኮች እግዚአብሔር ከኛ ጋር ነው ያለው እንጂ ከናንተ ጋር አይደለም ይሉናል፡፡ እኛም እንዲሁ እንላቸዋለን፡፡ ሰዎች እንደምንሰማቸው ግን የእግዚአብሔር ትምህርት እጅግ ጥቂቶች ወደ ሆኑት እንጂ ለብዙዎቹ አልደረሰም፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ደግሞ ወደ ማን እንደደረሰ አናውቅም፡፡ እግዚአብሔር ከፈቀደ ቃሉን በሰው ዘንድ ማጽናት ተስኖት ነውን? ሆኖም ግን የእግዚአብሔር ጥበብ በመልካም ምክር ይህ ነገር እውነት እንዳይመስላቸው ሰዎች በሐሰት ሊስማሙ አልተወም፡፡ ሰዎች ሁሉ በአንድ ነገር በተስማሙ ጊዜ ይህ ነገር እውነት ይመስላል፡፡ ሰዎች ሁሉ በሃይማኖታቸው ምንም እንደማይስማሙ በሃሳብም ሊስማሙ አይችሉም፡፡
እስኪ እናስብ ሰዎች ሁሉ ሁሉን የፈጠረ እግዚአብሔር አለ በማለታቸው ስለምን ይስማማሉ? ፍጡር ያለ ፈጣሪ ሊገኝ እንደማይችል፤ ስለዚህም ፈጣሪ እንዳለ እውነት ነውና ነው፡፡ ይህ የምናየው ሁሉ ፍጡር እንደሆነ የሰው ሁሉ ልቦና ያውቃል ፡፡ ሰዎች ሁሉ በዚህ ይስማማሉ፡፡ ነገር ግን ሰዎች ያስተማሩትን ሃይማኖት በመረመርን ጊዜ በውስጡ ሐሰት ከእውነት ጋር ተቀላቅሎበታል፡፡ ስለዚህ እርስ በርሱ አይስማማም፡፡ ሰዎች እርስ በርሳቸው አንዱ ይህ እውነት ነው ሲል፤ ሁለተኛው አይደለም፤ ሐሰት ነው ሲል ይጣላሉ፡፡ ሁሉም የእግዚአብሔርን ቃል የሰው ቃል እያደረጉ ይዋሻሉ፡፡ እንደገናም የሰው ሃይማኖት ከእግዚአብሔር ብትሆን ክፉዎችን ክፉ እንዲያደርጉ እያስፈራራች መልካም እንዳያደርጉ ትፈቅድላቸው ነበር፡፡ ደጎችንም በትዕግስታቸው ታጸናቸው ነበር፡፡
ለኔም እንዲህ ያለው ሃይማኖት ባሏ ሳያውቅ በምንዝርና የወለደች ሴትን ትመስለኛለች፡፡ ባሏ ግን ስለመሰለው በሕፃኑ ይደሰታል፡፡ እናቲቱንም ይወዳታል፡፡ በዝሙት እንደወለደችው ባወቀ ጊዜ ግን ያዝናል፡፡ ሚስቱንም ልጅዋንም ያባርራል፡፡ እንዲሁም እኔም ሀይማኖቴን አመንዝራና ዋሾ መሆኑዋን ካወኩ በኋላ ስለርሷ በዝሙት ስለተወለዱ ልጆቿ አዘንኩ ፡፡ እነሱ በጠብ፣ በማሳደድ፣ በመማታት፣ በማሰር፣ በመግደል ወደዚህ ዋሻ ያባረሩኝ ናቸው፡፡ ከውሸታቸው ጋር ስላልተባበርኩ ጠሉኝ። ነገር ግን የክርስቲያን ሃይማኖት ሀሰት ናት እንዳልል በዘመነ ወንጌል እንደተሰራ ክፉ አልሆነችም፡፡ የምህረትን ሥራ በሙሉ እርስ በርስ መፋቀርን ታዛለች፡፡ እነሱ ግን ፍቅርን ፈጽሞ አያውቋትም። በዚህ ዘመን ግን የሀገራችን ሰዎች የወንጌልን ፍቅር ወደ ጠብና ኃይል ወደ ምድራዊ መርዝ ለወጡት፡፡ ሃይማኖታቸውን ከመሰረቱ ዐመጻ እየሰሩ ከንቱ ያስተምራሉ፡፡ በሐሰትም ክርስቲያኖች ይባላሉ፡፡