የደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል የሰንበቴ ማኅበራት ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተወከለውን ኦዲተር የኦዲት መርኃ ግብር በመቃወም ህገወጥ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

በአዲስ አበባ የደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል የሰንበቴ ማኅበራት ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተወከለውን ኦዲተር የኦዲት መርኃ ግብር በመቃወም ህገወጥ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ፡፡ በተለያየ መጥፎ ሥነ ምግባርና ድርጊት ከካቴድራሉ ሰንበት ትምህርት ቤት የተባረሩ ሁለት አባላትን ይዘው በካቴድራሉ ሁለተኛ ሰንበት ትምህርት ቤት ለማቋቋም ከጉርድ ሾላ እና አካባቢ የሰበሰቧቸው ወጣቶች ስለ ሰንበት ትምህርት ቤት አመሰራረት ግንዛቤ የሌላቸው በመሆናቸው የአዲሱ ሰንበት ትምህርት ቤት ምስረታ አልተሳካም፡፡  ቀደም ሲል የሰንበቴ ማኅበራቱ ከሀገረ ስብከቱም ሆነ ከካቴድራሉ አስተዳደር እውቅና ውጪ የሚሸጡትንና በወር እስከ 300.000.00 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) ገቢ የሚያገኙበት የቀብር ፉካ ሽያጭ እና የአዳራሽ ኪራይ ንግድ ወይ ለቤተክህነቱ ፈሰስ እንዲያደርጉ አልያም ንግድ ፈቃድ አውጥተው ለመንግሥት ግብር እንዲከፍሉ በሀገረ ስብከቱ የቀረበውን ሐሳብ አልተቀበሉትም፡፡ እናም በመስከረም ወር 2006 ዓ.ም ከጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ፤ የቅዱ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በተገኙበት ተመርጦ ሥራ የጀመረውን ሰበካ ጉባዔ አይመራንም፤ እነርሱ ባቀረቡት ጥቆማ መነሻነት ከመንግሥት እና ከገለልተኛ አካላት የተዋቀረው የኦዲት  ኮሚቴ እኛን (የሰንበቴ ማኅበራቱን እና እንደ አቶ ወልዴ የሺጥላ አይነት በሕንጻ አሰሪ ኮሚቴ ገንዘብ ጉድለት የተገኘባቸውንና በቤተክርስቲያኑ ግቢ በቤተልሔሙ ጎን 26 ፉካ በመስራት መናፍቅ ልጆቻቸውን ወራሽ በማድረግ ሕገ ወጥ ሰነድ ያዘጋጁትን) ኦዲት ሊያደርጉ አይገባም በሚል ነጻና ገለልተኛ ቤተክርስቲያን እንመሰርታለን የሚል ፖስተር በመያዝ  እሑድ የካቲት 2 ቀን ጠዋት በቅዳሴ ሰዓት የቅዳሴ ሥነ ሥርዓቱን ለማስተጓጎል ሞክረዋል፡፡
በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የሴት ሰባኪ የሆነችውና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሕጋዊ ባሏን ጥላ   ወልዴ የሺጥላ የተባለውን የቀድሞ የህንጻ ኮሚቴ ሊቀ መንበር የወሸመችው እራሷን የዘመኑ የወንጌል አብሳሪ በመንፈስ ቅዱስ የተቀባሁ ጳውሎሳዊት ነኝ በማለት ጸሎተ ፍትሐት አያስፈልግም እኔ በፍትሀቱ ፋንታ ጸሎት አድጋለሁ አስተምራለሁ በማለት ምንፍቅና የምታስፋፋው  ቅድስት አሳልፍ ወደ ቤተክርስቲያኑ ድንጋይ እንዲወረውሩ ተሰብሳቢዎቹን ስታግባባ ነበር፡፡
ከካቴድራሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ሴት አባላትን በመተናኮልና ወሲባዊ ጥቃት በማድረስ በሕግ ተከሶ የተቀጣውና ከሰንበት ትምህርት ቤት በዚህ ቅሌት የተባረረው ሰለሞን አጥሌ የተባለው የታክሲ ሾፌርና የሰንበት ትምህርት ቤቱን ገንዘብ በተለያየ ወቅት በመውሰድ በሌብነት ወንጀል ተከሶ ከሰንበት ትምህርት ቤት የተባረረውና ዲቃላ ልጁን ደብቆ ሁለተኛ ሚስት በተክሊል ያገባው የሰለሞን አጥሌ ወያላ የሆነው ሲሳይ አፈወርቅ የተባሉት ሁለት ግለሰቦች መናፍቃንን በማሰባሰብ ሁለተኛ ሰንበት ትምህርት ቤት ለማቋቋም ያደረጉት እንቅስቃሴ አልተሳካላቸውም፡፡
ከዚህ ቀደም በዋነኛነት የሰንበቴ ማኅበራቱንና በመንግሥት ላይ ያኮረፉትን እንደነ ታዋቂውና ጨካኙ የደርግ የምስራቅ  ጎጃም ክፍለ ሀገር አስተዳዳሪና የደርጉ አባል አንሙት ክንዴን አይነት ሰዎችን በማሰባሰብ የደርግ ሥርዓተ ማኅበርን በቤተክርስቲያን ለመመስረት የሚታገለው የደርግ የስለላ ሹም የመቶ አለቃ አባቡ ታከለው በአጣዳፊ ህመም ከሰልፉ ላይ ወጥቶ ወደ ሆስፒታል የተወሰደ ሲሆን ህመሙ ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ እለቱን ኦፕራሲዎን መደረጉንና እስካሁን ከሰመመን እንዳልነቃ ታውቋል፡፡
የካቴድራሉ አስተዳደር በሰንበቴ ማኅበር ስም ተደራጅተው የሚነግዱትን አንዳንድ የደርግ ጡረተኞችና የሰንበቴ አላማ ጠላ ማንቃረርና ቆሎ ማሸርደም የሚመስላቸው ሥራ ፈት አባወራዎችንና የሚገስጻቸው ያጡ ባሎቻቸው የዘነጓዋቸውን እንደነ ቅድስት አይነት መናፍቃንን በቅጡ በመቃወሙና በፍርድ ቤት በተወሰነ ቤተክርስቲያኒቱ  ባወጣችው ሕግ ሕገወጥ ንግድ እና የቦታ ወረራ በመቃወሙ በመረጃ ባልተረጋገጠ ሙስና እና ስም ማጥፋት ሆ ብለን በመጮህ  ከሰን እናስወግዳለን ከሚመጣውም ጋር በመደራደር የፉካ ንግዳችንን እንቀጥላለን በማለት  ለሀገረ ስብከቱ ቅሬታቸውን በሕጋዊ ሽፋን ቢያቀርቡም ሀገረ ስብከቱ በቦታው ያለውን ችግር በዘላቂ ሁኔታ ለመፍታት ከመንግሥትና ከገለልተኛ አካላት  የተመደበው አጣሪ ግን በተጨባጭ በደረሰው መረጃ  እና በተለያዩ ጊዜያት በሰንበቴ ማኅበራቱ በቤተክርስቲኗ የድንጋይ  መአድን ሽያጭ  ባገኙት ገንዘብ በገዟቸው የቢራ አክስዮኖች ባለቤትነት ጉዳይ እንዲሁም እነ ወልዴ የሺጥላ የህንጻ ኮሚቴ ሊቀመንበር መሆናቸውን ሽፋን በማድረግ በሌሎች አብበያተክርስቲያናት ባልተለመደ መልኩ በቤተክርስቲያኗ ግቢ መኖሪያ ቤት በመገንባት እና ለግላቸው 26 ፉካ በመገንባት ለፈጸሙት ምዝበራ ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ ኦዲት ለማድረግ በማሰብ ያዘጋጀውን የጊዜ አጠቃቀም መመሪያ በመቃወም ሰልፉን አደራጅተዋል፡፡
 ቁጥራቸው 60 የሚደርሱት እነዚሁ ሰልፈኞች ከያዟቸው መፈክሮች መካከል መንግሥትን የሚተቹ እና አመጹን በማስፋፋት ልክ በእስልምና እምነት በመስኪዶች አካባቢ እንዳለው አይነት ውጥረት ለመፍጠር ቢያስቡም ፖሊስ ደርሶ ሰልፉ እንዲበተን አድርጓል፡፡ በቅርቡ ከአሜሪካ የመጣውና የደህንነት አባል ነኝ በማለት አመጹን የሚያስተባብረው አለማየሁ ከልል  ክሰ ቢመጣ አዘጋላችኋለሁ በማለት ቃል እንደገባላቸው የሰንበቴ ማኅበራቱ አመራሮች አስታውቀዋል፡፡ በዚህ ድርጊት ውስጥ የተሳተፉት ዋናዎቹ ግለሰቦች የተለያየ ችግር ያለባቸው ሲሆኑ አንዳንዶቹ በአጫሽነት ፤ ሰካራምነት ፤ በቃሚነት የሚታወቁ እና በአካባቢ ማኅበረሰብ የእንጨት ሽበት ተብለው የተናቁ ሽማግሌዎች ናቸው፡፡ ይህን አጋጣሚ እንደ መልካም የቆጠሩት አንዳድ ፖለቲካ ኃይሎች ሰልፉን ለማጠናከርና ወደ ውጪ በመውጣት ህዝብን ቀልብ ለመሳብ ቢያስቡም ፖሊስ ግን ይህንን ሊፈቅድ አልቻለም፡፡ ከትግራይ የተመረጠ ፓትርያርክ ቤተክርስቲያኗን ሊመራ አይችልም መንግሥት እጁን ከቤተክርስቲያናችን ላይ ያንሳ ትግሬ ተወላጅ ሰራተኞች ይውጡ በማለት በዋናነት መፈክር ሲያሰሙ የዋሉት አንሙት ክንዴ፤ አስማረ ዋሴ ፤ ባዬ ባዘዘው፤ወልሴ የሺጥላ፤ አበበ ደስታ ፤ መልአከ ኃይሌ ፤ ታደሰ  ፤ ቅድስት አሳልፍ፤ ደሳለኝ ፋንታቢል፤ ወልደኢየሱስ በሻህ ፤ሙሉ በለጠ ሲሆኑ ከወጣቶቹ ደግሞ ሴሰኛው ታክሲ ሾፌር  ሰለሞን አጥሌ እና ሌባው ሲሳይ አፈወርቅ ሲሆኑ እነዚህ የግል ጥቅም ያሳወራቸውና እምነትና ፖለቲካ የተቀላቀለባቸው ግለሰቦች በፖሊስ ክስ እንደተመሰረተባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
በሰአሊተ ምህረት ያለው የሰንበቴ አካሄድ ገና ከጅምሩ በ34ኛው አጠቃላይ መንፈሳዊ ሰበበካ ጉባዔ ታላቅ ተቃውሞ የገጠምውና ሲኖዶሱ እልባት እንዲሰጠው በተሰብሳቢዎቹ አቋም የተያዘበትቤተክርስቲያን የምትመዘበርበት መንገድ ነው፡፡ የሰንበቴ ማኅበራቱ ወደ እድርነትና እክስዮን ማኅበርነት በመለወጣቸው እና ከቀብር ፉካና ከአዳራሽ ኪራይ ያገኙትን ገቢ የቢራ አክስዮኖችን በመግዛት ከመንፈሳዊ ተግባት ውጪ የሚያውሉት ሲሆን ለረፈደበት የፖለቲካ ዓላማ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚያንቀሳቅሱ ማወቅ ተችሏል፡፡ የዚህ ድርጊት ዋነኛ መሪ ወልዴ የሺጥላ በኢትዮ ቴሌኮም ሲሰራ በጽዳት ሰራተኞች ላይ በፈጸመው የወሲብ ትንኮሳ በአስተዳደር ተከሶ ከቅርንጫፍሥ አስኪጅነት ወደ ሽያጭ ሰራተኛነት የወረደ ግለሰብ መሆኑ ስለርሱ የሚያውቁት ሁሉ ይመሰክራሉ፡፡
በካቴድራሉ ጉብኝት ያደረጉት ቅዱስ ፓትርያርኩ እና ብፁአን ሊቃነጳጳሳት በሰንበቴ ማኅበራ የተወረረውንና ለብዝኃኑ ጥቅም መስጠት ያለበትን ቦታ እና ግንባታ ተመልክተው ማዘናቸው ታውቋል፡፡ የደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል ሰፊ የልማት ቦታና በሰንበቴ የተወረረ የቀብር ስፍራ እንዲሁም በሰንበቴ ማኅበራ ቁጥጥር ሥር የሆነ በብዙ ሚሊዮን ብር የሚገመት የድንጋይ ማእድን ሐብት እና ከ100.000 በላይ አማንያን ያሉበት ሲሆን በሰንበቴ የጥቅም ሰንሰለት የተደራጁ ከ60 የማይበልጡ ግለሰቦች ምክንያት ሰላሙን አጥቶ የቆየ ደብር ነው፡፡
Share this article :

+ የተሰጡ አስተያየቶች + 7 የተሰጡ አስተያየቶች

Anonymous
March 17, 2014 at 7:34 PM

እውነታው ይሄ ነው
ይህን ከላይ የተዘረዘሩትን አሉባልታዎች በሙሉ የጻፉት ግለሰቦች በተለይም (አቤል አሰፋ) የተባሉት ግለሰብ
1 ድፍረት ፡-ደቡብ ጎንደር በነበሩበት ወቅት ድቁና ሳይኖራቸው የቆሎ ተማሪዎችን የድቁና ማስረጃ በመስረቅ ዲያቆን ነኝ በማለት ከላይ በተጠቀሰው ቤ/ክ መቅደስ መግባት
2 አጭበርባሪ ፡
- በትምህርታቸው በወደቁ ጊዜ ደብረ ታቦር በመሄድ ፎርጅድ የ12 ክፍል በማውጣት ዩኒቨርሱቲ ገብተዋል
- የመንግስት ደህንነት ነኝ በማለት ፎርጅድ መታወቂያ በማሰራት የደብሩን ካህናት ማስፈራራት
- የደብሩ ተወካይ ነኝ በማለት ከዲሜትሪ ሆቴል ለጥምቀት በዐል ዝግጅት አዋጡ ተብላቹሀል ብሎ 50.000(ሀምሳ ሺ) ብር በመቀበል ለግል ጥቅሙ አውሎዋል
- በሚኖርበት አካባቢ ያሉ አንድ ግለሰብን ንግድ እንዲሳካሎት በማለት አብሮት ከሚውለውና ከሚያድረው የአፍሪካ ህብረት አለቃ ጋር በመሆን ከፍተኛ ብር በመቀበል ያጭበረበረ ሲሆን ግለሰብዋ ለፖሊስ እንዳያስይዙት በሌሊት ቤታቸው ድረስ በመሄድ በሽጉጥ እያስፈራራ ይገኛል
- ሽጉጥ አጎቴ ከጎንደር አመጣልኝ በማለት በደብሩ ያሉትን የሱ ደጋፊ የሆኑ 6 የቆሎ ተማሪዎችን በረጅም ጊዜ ብድር በሚል ሸጦላቸዋል
-
3 ሌባ ፡- የደብሩ ሰበካ ጉባዔ አባል በነበረበት ወቅት
-ከታምራት ውቤ ከተባሉ ባልድረባቸው ጋር በመሆን
ሀ 200 ሺ ብር ለካህናት ማስቀየሪያ
ለ 100 ሺ ብር ለቀድሞው ፓትርያሪክ የልብስ ስጦታ መግዣ
ሐ 150 ሺ ብር ለቀበሌ መስተዳድሮች ጉቦ በሚል
መ 200 ሺ ለባንዲራ መግዣ
ሠ 450 ሺ ብር ለቀድሞው ፓትርያሪክ ለህዳርና ለጥር ማርያም የምሳ ግብዣ
ረ ንብረትነቱ የደብሩ ጸሀፊ የሆነውና በደብረ ዘይት ከሚገኘው የዕጸዋት ማዕከል 10.000 ብር ለማያወጣ ተክል 45.219 ብር ለትራንስፖርት የወጣ ሲሆን ነገር ግን ለነፍሳቸው ያደሩ የቤተክርስቲያኑ ምእመናንን በማስተባበር ተክሉን እንዲያመጡ አድርጎዋል
በድምሩ 1.145.219 (አንድ ሚልየን አንድ መቶ አርባ አምስት ሺ ሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ) ብር በላይ አጭበርብሮ በመውሰድ ባሁኑ ሰአት

ባሁኑ ሰዐት ከደብሩ ጸሀፊ፣ ሂሳብ ሹም ና በወቅቱ የሰበካ ጉባኤው ምክትል ሊቀመንበር የነበረው ከታምራት ውቤ ጋር በመሆን
-የመኪና አስመጪ ና ላኪ ፈቃድ በማውጣት 8 ቪትስ መኪና ገዝተው ከልይ በጠቀስነው ግለሰብ ቤት በር ላይ የሚገዛቸው አጥተው ጸሀይ ሲሞቁ ይውላሉ
- አልታድ ሚካኤል አካባቢ የሴቶች የመዋቢያ መሸጫ ከፍተዋል
- ካሳንችስ መናሀሪያ አካባቢ የመጠጥ ገሮሰሪ የከፈቱ ሲሆን


ከዚህም በተጨማሪ
ከደብሩ ሂሳብ ሹም፡- ጋር በመሆን ተክለሀይማኖት አካባቢ ወደ ሲኒማ ራስ መሄጃ ጋር ግሮሰሪና ጫት ቤት ከፍተዋል
ከደብሩ ጸሀፊ፣ ጋር በመሆን ሲመሲ የአሸዋ መደብር ከፍተዋል
እናም ይሄን ሁሉ ወንጀል የፈጸሙ ግለሰብ ሆነው ሳለ በውሸት የሰውን ስም ማጥፋታቸው በጣሙን ይገርማል
ከላይ የተጠቀሰውን ለማረጋገጥ ማንናውንም የጉርድሾላ አካባቢ የሚኖር ወደ 40 ሺ የሚቆጠር ህዝብ መጠየቅ ይቻላል ከብዙ በጥቂቱ በአቶ አቤል አሰፋ በኩል የተገለጹት ሲሆኑ የሌሎቹን በሚቀጥሉት ጊዜያት እናቀርባለን

Anonymous
March 18, 2014 at 2:49 PM

የደጀ ብርሀን ብሎግ ለሙሰኞች ብቻ የወገነ መሆኑን በግልጽ ያሳያል በተደጋጋሚ የሚያወጣው ሪፖርት በተለይ ስለሰዓሊተ ምህረት በጽንፈኝነት የተተበተበ ነና ወደ ሙሰኞቹ ግሩፕ ያደላ ነው ለእውነት የማይወግን ብሎግ

Anonymous
March 18, 2014 at 5:42 PM

እውነተኛ ከሆናችሁ በሰዓሊተ ምህረት ቅ/ማርያም ቤ/ክ ለ3 ዐመታት ሙሉ የሚካሄደውን የምዝበራ ወንጀል በተለይም ታምራት ውቤ ና አቤል አሰፋ የተባሉት ግለሰቦች ከደብሩ አስተዳደር አካላት ጋር በመሆን እየፈጸሙት ያሉትን ምዝበራ ወንጀል ለምን አታቀርቡም ፡፡

March 19, 2014 at 7:24 PM

ምላሽ ያላቸውንና መረጃቸውን ሊያካፍሉ የፈለጉትንም እናስተናግዳለን።

Anonymous
March 28, 2014 at 2:28 PM

ተሃድሶ ተጋለጠ
ቅድስት ማሪያም የመዳን ምክንያት ያደረጋት ጌታ ኢየሱስ ነው፣ ፃድቃንን ሐዋሪያትን መርጦ ያከበራቸው ጌታ ኢየሱስ ነው
ለሐዋሪው ዮሐንስ እና ለመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የመሰከረው ጌታ እየሱስ ነው ፣ በመፀሐፍ ቅዱስ እውነተኛ ፃድቃን ካሉ ለእንርሱ ስል ለሕዝቡ ምህረት እሰጣለሁ ያለው ጌታ እየሱስ ነው፣ በፃድቀን ሥም የሚደረግ በጎነገር ዋጋ እንዳለው የተናገረው ጌታ እየሱስ ነው፣ ቅዱሳን መላዕክት ከፈጣሪ በተሰጣቸው ፀጋ የሰውን ልጅ ከመከራ እንደሚታደጉ በመፀሃፍ ቅዱስ ተመስክሯል
ታዲያ ይህቺ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በዕውቀት የተሞላች ምንጎሎባት ነው መታደስ አለባት የሚባለው ቅዳሤው እረዘመ፣ ፆሙ በዛብን፣ ፃድቃንን ፣ ቅድስት ማሪያምን ማመስገን አያስፈልግም ፣ እንደፈለግን እንብላ እንጠጣ፣ እንጨፍር እንዝናና ፣ ፃድቃንን ማክበር አያስፈልግም፣ ስንቱን ፆርና ተጋድሎ በድል የተወጡትን በምድር ላይ እራሳቸውን የካዱትን ፃድቃን ሰማዕታት ከእራሳቸው ሕይወት ጋር የሚያወዳድሩ ነውረኞች ፋሽን ቲሸርት ቀበቶና መነፅር ለመግዛት በየሱቁ ሲሻሙ የሚውሉ የስጋቸውን ፍላጎት መግታት የተሳናቸው አቅመቢሶች ቢያንስ አስከ 6 ሰአት እንኮን መፆም የማይችሉና አብዝቶ መስገድን የሚፈሩ በየካፍቴሪው በርገር እንደ አሳማ ሲሰለቅጡ የሚውሉ ሆዳቸው አምላካቸው የሆኑ ተሃድሶ መናፍቃን ከቤተክርስቲያን ይመነጠራሉ በቤተክርስቲናችን እድል ፋንታ የላቸውም በተጨማሪም ከላይ ከሰማይ ተሰጥኦ ሳይታደሉ ለቢዝነስ/ ለሆዳቸው መሙያ ስባሪ ሳንቲም ለማግ ኘት/ በኦርቶዶክስ ስም የሚዘምሩ ሐያሉን እግዚሃቤር አቃለው በማይገባ ቃል የሚጠሩ/ ፍቅሬ፣ውዴ፣…../ መዝሙራቸው ዜማው ከአለማዊ ዘፋኞች የተሰረቀ እና ተራ ምንም መልዕክት የሌለው ሕይወታቸው በምሳሌነት የማይቀርብና የማያስተምር፣ የሰውን ብሶት መሰረት ያደረገ ስብከት አይሉት ፉከራ በመንዛት ሲደ በማሳተም ሆዳቸውን የሚሞሉ ማፈሪያዎች በምድራዊ ሕይወታቸው ሰነፎችና ታካቾች በመሆናቸው ዘለግ ያለ የትምህርት ደረጃ የሌላቸው ለመኖር ሆዳቸውን ለመሙላት አማራጭ ስለሌላቸው ይህችው ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው የሚቃትቱ ሰነፎች በእግዚአብሄር እገዛና በእራሳቸው ጥረት በሁለት ወገን የተሳለ ቢላዋ ሆነው/በምድራዊ ትምህርታቸው የመጠቁና የላቁ ዶክተሮች፣ ዳኞች፣ መምህራን፣ ኢንጂነሮች፣ሳንቲስቶች እንዲሁም በመንፈሳዊ ህይወታቸው በማይታመን ሁኔታ የላቁ አስከ ቅስና ድረስ የዘለቁ / ወንድሞች የመሰረቱትን ማህበር የመናፍቃንና የተሃዱሶዊያን ጠላት የሆነውን ማህበረ ቅዱሳን መናፍቃን በብሎጋቸው ስሙን ጥላሸት ለመቀባት ሲፍጨረጨሩ ይውላሉ ሆኖም ማህበሩ እውነተኛው ዳኛ እግዚሃብሄር የመሰረተውና በሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን ልብ ውስጥ ሰርፆ የገባ በመሆኑ ምንም ማምጣት አይቻላቸውም እኛም/የኦርቶዶክስ ልጆች/ በፀሎት፣ በዕውቀት፣ በገንዘባችን ማህበሩን መርዳት አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡መስቀል መሳለም፣ የንስሃ አባት፣ የቃልኪዳኑ ታቦት፣ እጣኑ የቅዱሳንን ስም መጥራትና ማመስገን ኤስፈልግም የምትሉ እንዲሁም ስግደትን፣ ፆምን፣ ቅዳሴን የምትፈሩ ሰነፎች እና ሆዳም ተሃድሶዊያን አርብና እሮብ ሳገለግል ይርበናል ስለዚህ አልፆምም መብላት ያስፈልገኛል የምትሉ አጉራ ዘለል ሰባኪያን ከቤተክርስታኒያችን ውጡ ልቀቁ ምክንያቱም ቤተክርስታኒያችን ለሰነፎችና ለሆዳሞች ቦታ የላትም አትመችም ፣ በመዝሙር ሥም ጭፈራ እና የስጋ ድሎት ወደሚፈቀድለት በአዳራሽ ውስጥ ሴሰኝነት ወደ ነገሰበት የዘመኑ መናፍቃን መሰባሰቢያ ሂዱ እንደወደዳችሁም የሥጋችሁን ፈቃድ ፈፅሙ አታለቃቅሱ የፃድቃንን ተጋድሎ በምን አቅማችሁ ትችላላችሁ ወዝ የሌላችሁ ሀሰተኞች አስመሳዮች ጌታ ያከበራቸውን ከእኛ በምን ይበልጣሉ የምትሉ ማፈሪዎች ቅዱሳን ከመወለዳቸው በፊት በእግዚያብሄር እንደሚመረጡ እንኮን የማታስተውሉ ሰነፎች ሀሳባችሁ ምድራዊ የሆነ "መዝሙርና "ስብከታችሁ" ሰውን የማይለውጥ ባዶ የቆርቆሮ ጩኽት አሁንማ ተነቃባችሁ ሲዲ መቸብቸብ ቀረ በመዝሙር ስም ትዝታ፣ አምባሰል ……… እየዘፈናችሁ፣ ሁሉም ነቃ ትንሽ ትልቁ …. ቡዝነስ ቐረ ቦሌ ካፍቴሪያ እያማረጡ ሆድ መሙላት ቀረ ገና እውነተኛ ጌት እየሱስ ክርስቶስ በስሙ የሚነግዱትን ያዋርዳቸዋል፣

Anonymous
March 31, 2014 at 2:40 PM

የደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል የሰንበቴ ማኅበራት ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተወከለውን ኦዲተር የኦዲት መርኃ ግብር በመቃወም ህገወጥ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ???? በጣም ገራሚ እርዕስ ነዉ የሰጣችሁት ለፅኁፋችሁ፡፡ አረጋግጣችሁ ነዉ ወይስ ፖስት አድርጉልን ስለተባላችሁ ነዉ ዜና አድርጋችሁ የምታወሩት ይሆ በእዉነቱ በጣም በጣም ያስተቻችሁልና በማጣራት ብትሰሩ መልካም ነዉ መረጃ ከሆነ ደግሞ ሊቀርብላችሁ ይችላል ደግሞ የሙስናና የምዝበራ ለደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል አዲስ እኮ አይደለም አሁን በዛ አይን አወጣ ተብሎ ነዉ ምእመኑ ጥያቄ ያቀረበዉ ጥያቄ ማቅረብ ደግሞ ተገቢ ነዉ ማንም ቤቱ ሲጠፋና የግለሰቦች መበልፀጊያ ሲሆን ማየት አጥፈልግም፡፡ ትክክልና ማስረጃ የተገኘበት ስህተት እየሰሩ ሊጋለጡ ሲሉ ደግሞ ምዕመኑን ሌላ ተልዕኮ አንግበዉ ነዉ ብለዉ ማደናገር ግን ተገቢ አይደለም፡፡ ተአምራት ዉቤ፣ አቤል አሰፋ እንዲሁም ፀሃፊዉ ሩፋኤል በቤ/ክርስቲያናችን ላይ የሚያደርጉት ሙስናና ዝርፊያ ይቁም ብሎ ጥያቄ ማቅረብ ትክክል ነዉ አቤል አሰፋ የተባለዉ ግለሰብ ትምህርቱን ጨረስ ዩንቨርስቲ ገባ ማስተርሱን ተማረ ቀጥሎ የትም ድርጅት ሳይቀጠር ከምን ተነስቶ መኪና አስመጪ ሆነ? ሲሆን አንደኛዉ ጥያቄ ታምራት ዉቤ ከመኪና መኪና እየቀየረ በራሱም ባይሆን በሌላ ስም ቤት መግዛቱ ከየት መጣ? ሶስተኛዉ ደግሞ ፀሃፊዉ በጋብቻላይ ጋብቻ መፈፀሙና ቅስናን ተቀብያለሁ በማለት ስጋዎ ደሙ ማቀበል መረጃዎች ሲኖሩ ሶስቱም በመሆን ደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል ብር እንደፈለጉ እያወጡ ይመዘብራሉ ብለዉ መጠየቅ ሌላ ያስብላል?? ብቻ ደጀ ብርሃን ዜና የሚሆን አለን ስለተባላችሁ ሳይሆን እዉነተኛ መረጃ በመያዝ ብትፅፋ መልካም ነዉ ለሌላም ቢሆን የሚያስተምር እንጂ የስድብ አምድ አታድርጉት ለእናንተም ጥሩ አይደለም እሰዚህ እርምት ዉሰዱ

Anonymous
March 31, 2014 at 2:42 PM


ዉድ ደጀ ብርሃን በእናንተ ስም የወጣ ፅሁፍ አንብቤ በጣም ነዉ ያዘንኩት እዉነቱን ለመናገር ይህ አምድ የተከፈተዉ ሃይማኖታዊ ስርዓትን በተላበሰ ትምህርት ለመማማር ነዉ ወይስ አባቶችን ለመሳደብ ነዉ፡፡ ሰሞኑን በደብረ ምጥማቀቅ ሳሊተምህረት ቤተክርስቲያን ዉስጥ ስለተፈጠረዉ ሁኔታ በስድብ በዘለፋና በማንቋሸሽ የሰፈር አዛዉንቶችን በመሳደብ የቀረበዉ ፅሁፍ በጣም የሚያሳዝን ነዉ፡፡ ወይስ ማንም ባለጌ እየተነሳ አምዳችሁ ላይ ይፅፋል፡፡ አንድ ፅሁፍ ፅፎ ለአንባቢ ማቅረብ በቅድሚያ ሳንሱርድ መደረግ ያለበት ይመስለኛል፡፡ እንዴት በአንድ ቤ/ክ ዉስጥ በሶስት ሰዎች ትመዘበራለች፤ ከምንም ተነስቶ አንድ ሰዉ የመኪና አስመጪ ይሆናል፤ቤት ይገዛል፤ እንዲሁም በቤ/ክርስቲያን ብር በመዝረፍ ያላግባብ እየበለፀጉ ስለሆነ አካሄድ ይስተካከል እነዚህ ሰዎች ከቤተክርስቲያን አገልግሎት መዉጣት አለባቸዉ የሚሄዱት አካሄድ ጥሩ አደለምና እርምት ይወሰድ ብሎ የአጥቢያ የቤተክርስቲያኗ ምእመን ጥያቄ ማቅረብ ነዉር ነዉ፡፡ በፍፁም በዚህ ምክንያት ምእመኑን የእንጨት ሽበት፤ ጡረተኛ፤ ጋለሞታ ሁሉ፤ ዝሙተኛ ብቻ ለመፃፍ አይደለም ለማንበብ የሚያሥጠላ ፅሁፍ መፃፍ ለቤተክርስቲያኑም ለምእመኑም መልካም አይደለምና እርምት ማድረግ፣ ካልሆነም የቤተክርስቲያንን ችግር ፈቺ ነን የምትሉ ከሆነም ቦታዉ ላይ ድረስ በመምጣት ያለዉን ነገር በማጣራት እዉነታዉን ማዉጣት እንጂ እንደዚህ አይነት አፀያፊ ቤተክርስቲያንን የሚያሰድብ ስራ ባትሰሩ መልካም ነዉ እላለሁ፡፡

Post a Comment

አስተያየቶች

 
Support : | |
Copyright © 2011. ደጀ ብርሃን dejebirhan - All Rights Reserved

Proudly powered by Blogger