ድሆች አስለቅሶ ግፍ የሚሰበስብ!!
በሰው ዘንድ ቢሟጠጥ ተስፋ እና ደስታ
በሰው ዘንድ ቢሟጠጥ ተስፋ እና ደስታ
እኛስ ፈጣሪ አለን ሁሉን የሚረታ
ተስፋ እንደሌላቸው አንሆንም ከቶ
ክርስቶስ አለልን የሚያሳይ አብርቶ

ያለቀሱ ሁሉ ይስቃሉ አይቀርም
ይለዋውጠዋል ጌታ መድኃኒዓለም
ማንም ያላሰበው ያልጠበቀውን ድል
ለእኛ ለምስኪኖች ጌታ ይሰጠናል

ማንም ያልጠበቀው ያልገመተውን ድል
ለእኛ ለምስኪኖች ጌታ ይሰጠናል

በሰው ዘንድ ቢሟጠጥ ተስፋ እና ደስታ
እኛስ ፈጣሪ አለን ሁሉን የሚረታ
ተስፋ እንደሌላቸው አንሆንም ከቶ
ክርስቶስ አለልን የሚያሳይ አብርቶ

ሰዎች ቢጠበቡ ገንዘብ ለመሰብሰብ
ይጠላለፋሉ ባልጠበቁት መረብ
እግዚአብሔርን ይዘው በቅን ካልተጓዙ
ክፋት እና ተንኮል ብዙ ነው መዘዙ

እግዚአብሔርን ይዘው በቅን ካልተጓዙ
ክፋት እና ተንኮል ብዙ ነው መዘዙ

በሰው ዘንድ ቢሟጠጥ ተስፋ እና ደስታ
እኛስ ፈጣሪ አለን ሁሉን የሚረታ
ተስፋ እንደሌላቸው አንሆንም ከቶ
ክርስቶስ አለልን የሚያሳይ አብርቶ

ድሆች አስለቅሶ ግፍ የሚሰበስብ
ምን ይመልስ ይሆን በጌታ ፊት ሲቀርብ
ለዚህች አጭር ዘመን የሚስገበገቡ
አይረኩም አይጠግቡም ድሆች እያስራቡ

በሰው ዘንድ ቢሟጠጥ ተስፋ እና ደስታ
እኛስ ፈጣሪ አለን ሁሉን የሚረታ
ተስፋ እንደሌላቸው አንሆንም ከቶ
ክርስቶስ አለልን የሚያሳይ አብርቶ

የእህል ሽታ ጠፍቶ መሶቡ ቢራቆት
ተስፋችን ሙሉ ነው እኛስ በጌታ ፊት
ይህን ክፉ ዘመን ያሻግራል ጌታ
ከሰራን በኋላ በጸሎት እንበርታ
በሰው ዘንድ ቢሟጠጥ ተስፋ እና ደስታ
እኛስ ፈጣሪ አለን ሁሉን የሚረታ
ተስፋ እንደሌላቸው አንሆንም ከቶ
ክርስቶስ አለልን የሚያሳይ አብርቶ


 

 
Share this article :

+ የተሰጡ አስተያየቶች + 1 የተሰጡ አስተያየቶች

Anonymous
November 15, 2013 at 12:03 PM

መጨካከን ባይኖር ኖሮ ዓለም ለሁሉም ትበቃ ነበር። በተለይ መንፈሳዊ እንደሆኑ የሚያስቡት ቅንነትና በጎነት ቢኖራቸው ኖሮ የፈጣሪ በረከት በተትረፈረፈ ነበር። ዳሩ ምን ያፈርጋል። በጎ ሰው ጠፋ። ሁሉ ተሳስቷል።

Post a Comment

አስተያየቶች

 
Support : | |
Copyright © 2011. ደጀ ብርሃን dejebirhan - All Rights Reserved

Proudly powered by Blogger