የማኅበረ ቅዱሳን የተሸፈነ ማንነት በአሜሪካ ተገለጠ!One of his loyal bishop
እንደስንዝሮ ታሪክ ሰኞ ቀን ዩኒቨርስቲ ተረከዝኩ፤ ማክሰኞ ብላቴ ላይ ተወለድኩ፤ ረቡዕ ዕለት በአቡነ ገብርኤል ማኅበረ ቅዱሳን በሚል የክርስትና ስም ተጠመኩ፤ ሐሙስ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ ልሰብር የነገር እንጨት ለቀማ ሄድኩ የሚለው ይህ ማኅበር ብዙዎቹን ለማሰለፍ ቢችልም የስንዝሮ ታሪኩ እየተገለጠና እየተገፈፈ በመታወቅ ላይ ይገኛል። በተለይም የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናት ይህንን ማኅበር በጭለማ መንፈስ የሚነዳ፤ የክፋት ኃይል አድርጎ በመመልከቱ ደረጃ ትልቅ ግንዛቤ እንዳለ ይታወቃል። ወጣቱ ትውልድም ቢሆን እየዋለ እያደረ የማኅበሩን እንቅስቃሴና እርምጃ ፤ የገንዘብ አቅሙን ማደርጀትና ወደንግዱ ዓለም ጎራ ማለቱን በማየት ከየት ተነስቶ ወደየት? ለመሄድ እንደፈለገ በተፈጠረበት ግርታ የተነሳ ባለበት ቆም ብሎ ለማስተዋል መገደዱን የምናገኛቸው ትዝብቶች ያስረዱናል። አንዳንዶቹም ርቀው ሲያዩት ወርቅ የመሰላቸው ይህ ማኅበር ቢቀርቡት የመዳሪያና የገንዘብ መሸቀጫ ስብስብ መሆኑን ተመልክተው አፍረውበት እርባና እንደሌለው ሲናገሩም ይደመጣል።  ይህ ማኅበር ከራሱ ከንግድ ተቋሙ ኃላፊዎችና የእንደጋሪ ፈረስ ከሚነዱለት ጥቂት ተከታዮቹ በስተቀር እንደመንፈሳዊና ጠቃሚ ማኅበር የመቆጠሩ ነገር እንደገለባ በመቅለል ላይ ይገኛል
በ1950 ዓ/ም የተቋቋመውና  ከሃይማኖት የለሹ የደርግ መንግሥት ጋር በመተባበር የጠቅላይ ቤተክህነት ሹማምንት በ1975 ዓ/ም እንዲፈርስ የኢሠፓአኮ ሠይፍ የመዘዙበት «ሃይማኖተ አበው» የተሰኘውን አንጋፋ ማኅበር ከደርግ ውድቀት በኋላ እንደገና ነፍስ ዘርቶ ሊቋቋም ሲንቀሳቀስ ከእኔ ሌላ ማንንም አልይ የሚለው የብላቴው የወታደሮች ማኅበር፤ ማኅበረ ቅዱሳንና ደጋፊዎቹ ሁለተኛ ጊዜ ሠይፍ አሳርፈውበት ከነአካቴው እንዳይኖር አድርገው አከርካሪውን እንደመቱት የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። ማኅበረ ቅዱሳን ከክፋቶቹ ሁሉ የላቀው ክፋት ከእርሱ በስተቀር አንድም ማኅበር ኅልውና አግኝቶ እንዳያንሰራራ በተለጣፊ ጳጳሳቶቹና በአገልጋዮቹ በኩል ማስመታት መቻሉ ነው። እንኳን ማኅበራት ጳጳሳሶቹ እንኳን ከፓትርያርኩና ከፌዴራል ፖሊስ በላይ የሚፈሩት ይህንን ማኅበር መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። በሹክሹክታ የሚያወሩትን የሚሰማቸው እስኪመስላቸው ድረስ ይህንን ማኅበር እንደሚከተላቸው ጥላ ይከታተለናል ብለው ይንቀጠቀጡለታል። ገሚሶቹም ነውራሞች ሳይወዱ እየሳቁ በታማኝ ሎሌነት ያገለግሉታል።

ደጋግመን እንዳልነው ማኅበረ ቅዱሳን ዓላማውና ግቡ ቤተ ክርስቲያንን በራሱ ሰዎች መረከብ ነው እንጂ ወንጌልን የማስፋፋት ብቃት፤ ችሎታና ማንነት ቅንጣት ታህል እንደሌለው እሙን ነው። ማኅበሩ በምንም ዓይነት መልኩ የወንጌልን እውነት የማይቀበል የጨለማ መንፈስ አገልጋይ ነው። ይባስ ብሎ የወንጌሉን እውነት አለመቀበል ብቻ ሳይሆን ወንጌሉን ደፍጥጦ ለተረት፤ ለእንቆቅልሽ፤ ለቅዠትና ለህልም ታሪኮች ከፍተኛውን ቦታ በመስጠት ሰው ሁሉ በዚያ መንገድ እንዲነጉድ የሚያመቻች የጥፋት ኃይል ነው። የቤተ ክርስቲያን ልጆችን ያሳድዳል፤ ያስወግዛል፤ ያሳድማል። ማኅበሩ ባለበት ቦታ ሁሉ ሁከት አለ። በደቡብ ኢትዮጵያ ከሀዋሳ እስከቦረና ረጅም እጁ እስካሁን አልተሰበሰበም። በሐረርና በድሬዳዋ፤ በቅድስት ሥላሴ ኮሌጅና በየአድባራቱ የሁከት መንፈሱን ጊዜ እየጠበቀ ይረጫል። ጎጋ አባላቱ ነፍሳቸውን እንኳን ለመገበር እንደማይመለሱ ብናውቅም ብዙዎቹ የማኅበሩ አባላት እውነቱን እያወቀ  ከእውነቱ ጋር ለመታረቅ ያሰገራቸው መንፈስ እድል ስለማይሰጣቸው ምንም የሌላቸው ባዶዎች፤ ከሚታየው ከፍታ መውረድ የማይፈልጉና ከሚበላው ሠርከ ኅብስት ጋር ሆዳቸውን አስታርቀው የሚኖሩ የአእምሮ ደሃዎች ሆነው ቀርተዋል።
ይህ ማኅበር እውነት ምን እንደምትመስል ቢያውቅ እንኳን ከእውነት ጋር ለመስማማት ተፈጥሮው አይፈቅድለትም። ራሱን እያገዘፈና ተጠሪ የሆነ ያህል ሰይሞ በየቦታው ራሱን የሚያስገባው ይህ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ ብዙ ብጥብጥ አስነስቶ ቆይቷል። ለምሳሌም በላስቬጋስ ሐመረ ኖኅ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪውን ቄስ አባሮ በራሱ ምልምል ጢም አልባ መነኩሴ ቤተ ክርስቲያኑን መረከቡ አይዘነጋም። በሲያትል፤ በኒውዮርክ፤በዳላስና በካሊፎርንያ ለማስነሳት የሞከረው ብጥብጥና በአንዳንዶች ቦታም  ምዕመናን ከፍሎ በመገንጠልና በሥነ ምግባር ጉዳይ በቅዱስ ሲኖዶስ በሚፈለገው ጳጳስ በኩል እያስባረከ የራሱን ንግድ እያጧጧፈ ይገኛል። ይህንን ተግባሩን ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል። ይህንን መሠሪ አድራጎቱን የተመለከቱ የሰሜን አሜሪካ አድባራት ሰሞኑን በዚህ ማኅበር ዙሪያ ሰፊና ጥልቅ ውይይት አድርገዋል። በማኅበሩ ማንነትና አቋም ዙሪያ አንድ ውሳኔ በማሳለፍ ማኅበሩ ከተሸሸገበት ከቤተ ክርስቲያን ጉያ እንዲወጣ ለመምከር በተሰበሰበው ጉባዔ ላይ የተገኙ የማኅበሩ አባላት ጨርቃቸውን ጥለው እስኪሄዱ ድረስ እብደት ቃጥቷቸው እንደነበር ተሳታፊ የማኅበሩ አባላት በምሬት ሲናገሩ ተደምጧል። ስለማኅበሩ ቅዱስ መሆን ለማስረዳት እድል የጠየቁትና ማንንም ሰሚ ሳያገኙ ከንፈራቸው ደርቆ የቀሩት እነዚህ ሰዎች ማኅበሩ እርቃኑን እየቀረ መሄዱንና እዚህ ድረስ ያደረሳቸው የአክራሪ ተሐድሶዎች ሴራ እንደሆነ ሲለፈልፉም ተሰምቷል። ይሁን እንጂ የማኅበሩን ማንነት እያጋለጠ ያለው ሌላ ማንም ሳይሆን የማኅበሩ ግብር ራሱ ነው። በሰሜን አሜሪካ የማኅበሩ አባላትና ደጋፊዎች ባሉበት ቦታ ሁሉ አድባራቱ ይታወካሉ፤ ይታመሳሉ ወይም የተገነጠለ አዳራሽ ያቋቁሙባቸዋል። ይህንን የማኅበሩን ሴራ ለመቋቋም የመከሩት የሰሜን አሜሪካ አድባራት ሊመሰገኑ ይገባል። ከእንግዲህ በሰሜን አሜሪካ የራሱን ሦስተኛ ሲኖዶስ ከሚያቋቁም በስተቀር በየአድባራቱ ውስጥ ስፍራ እንደሌለውና ማንነቱ በደንብ በመገለጹ የክስረት ጎዳናውን የመጀመሩ ምልክት ተደርጎ ተወስዷል።
በኢትዮጵያ ውስጥም በዚህ ማኅበር ዙሪያ ትልቅ ግንዛቤ ተይዟል። ይሁን እንጂ ከማኅበሩ ጋር እንዳይጋጩ በነውሬን ሸፍንልኝ ቃለ መሃላ የተያዙ ጳጳሳት አንዳንዶቹ በፍርሃት፤ ገሚሶቹም በጥቅም ተደልለው እስትንፋሱ እንዲቆይ እየረዱት ይገኛሉ። ይህም ቢሆን ለጊዜው ነው። ይዘገይ እንደሆን እንጂ እውነት በአናቷ ቢቀብሯት እግሯ ትወጣለች። አሁንም እያየነው ያለው ያንን ነው። በሰሜን አሜሪካ ያሉ አድባራት በዚህ ማኅበር ዙሪያ ያደረጉት ምክክር የሚያሳየው በማኅበረ ቅዱሳን ማንነት ዙሪያ እየተሠራ የቆየው ሥራ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን ነው።
Share this article :

+ የተሰጡ አስተያየቶች + 14 የተሰጡ አስተያየቶች

Anonymous
August 4, 2013 at 9:57 PM

ዛሬ በለጨ ነው የቃምከው ማለት ነው? የምታወራው ሁሉ በምርቃና ነው። እንደ ሙሉጋኔን ወልደ ሰይጣን። ኸረ እንደሱ አይደለም ራስህ ሙሉጋኔን ነህ። ለመሆኑ የት ጠፍተህ ተገኘህ? በለጨ ከሌለ አይንህ አይከፈትም ማለት ነው? አይ ሙሉጋኔን። ይልቁኑ ለአባ ጳውሎስ ጣዖት ያቆሙ የወንጌል ነገዴ ጓዶችህ ለቅዱስ መለስ መታሰቢያ ሲያደርጉ የት ነበርክ? ስለሱ አታወራም ስላልተከሰተ ነገር ከምትዘበዝብ። የዘበዘብከው ነገር ሁሉ የተከሰተው ያቺው የማትረባ አእምሮህ ውስጥ በምርቃና ነውና ንቃ።

Anonymous
August 5, 2013 at 5:54 AM

አይ ጉድ መቼም ውሸትን አሳምሮ እውነት አስመስሎ ማቅረብ በጣም ቀላል ነው። አንድም ያላችሁት ነገር እውነት ነገር የለውም። የሚገርመው ስለ ማኅበሩ የጠላትነት ወሬ ስታወሩ ዓመታት አልፈዋል። የማኅበሩ የእለት የእለት እንቅስቃሴ ከምንጊዜውም የበለጠ በእግዚአብሔር እርዳታ እየተራመደ ነው። የእናንተ ወሬ ከምቀኝነትና ከዋልጌነት የመነጨ ለመሆኑ ከመልክታችሁ መረዳት ይችላልና ምንም አታመጡምና አትልፉ። እርግጥ ከዚህም የተሻለ ነገር ለማድረግ ችሎታውም ብቃቱም የላችሁምና ብዙም አያስገርምም።

Anonymous
August 5, 2013 at 8:38 AM

ለደጀ ብርሃን ብሎግ አዘጋጆች
የብሎጋችሁ ጥቁር ቀለም በነጭ ጽሁፍ ለዓይን አይመችም፡፡
በአብዛኛው የምናየው/የምናነበው/ ነጣ ያለ ገጽ ላይ በመሆኑና ወደ እናንተ ብሎግ ስንመጣ ሙሉ ለሙሉ ተቃራኒ/ጥቁር/ ሲሆን ለማየት ወይም ለማንበብ ይከብዳል፡፡
እንዲሁም በእናንተ ብሎግ/ ደጀ ብርሃን/ ጥቁር ገጽ ላይ እያነበብን ቆይተን ወደ ሌላ በአብዛኛው ነጣ ወዳሉት ገጾች ለማንበብ ስንሄድ ለማየት ይከብዳል፡፡ በአይን ላይ ተጽዕኖ ስላለው ነው ይህን አስተያየት የጻፍኩላችሁ፤….ከሌሎች ወንድሞችና እህቶች አስተያየት ተቀብላችሁ ብታስተካክሉት መልካም ነው፡፡
አመሰግናለሁ

Anonymous
August 5, 2013 at 4:09 PM

hey some time don't tarnish the good pictures of good young Christians who did a lot in the rural part of Ethiopia, for example those who teach kids their history and bible under the umbrella of Mahiber kidusan. If Mahiber Kidusan members were not invested their time and money to teach college and high school students at that dark ages may be The churches have been struggle to reach all the their members. We Ethiopians have a problem to encourage good things rather we like to condemn every organization and groups if their idea or the way they work is not liked by us. I think the good thing for the church and the Christian community at large is correcting the wrong thing rather than destroy the whole organ of the group.

Anonymous
August 5, 2013 at 4:10 PM

ahun yiheni tsihuf yetsafikewu sewuye mallet yemifeligewu ye ewunet chrisitiyan kehonik kemezalef ena abatoch enikuwan mesirat yalichalutin eyeseru yalutin wetat ye betekirisitiyanun lijoch bejimila moral kemitineka be adebabay, wusit honewu mahiberun kedimo yetenesabetin alam ""wenigel masifafat"" yizewu kefitegna tiret eyaregu yalutin bitagiz yimeretal. Lelawu linegerih sewu yemisasatewu sisera newu. sihitetun enidiyarim madireg degimo yemahiberesebu hulu dirisha newu.

Anonymous
August 5, 2013 at 11:49 PM

hello Deje Birhan,
Why your blog background is 'chelema'? Is that represent real you??

Anonymous
August 6, 2013 at 6:11 AM

አይ ጉድ መቼም ውሸትን አሳምሮ እውነት አስመስሎ ማቅረብ በጣም ቀላል ነው። አንድም ያላችሁት ነገር እውነት ነገር የለውም። የሚገርመው ስለ ማኅበሩ የጠላትነት ወሬ ስታወሩ ዓመታት አልፈዋል። የማኅበሩ የእለት የእለት እንቅስቃሴ ከምንጊዜውም የበለጠ በእግዚአብሔር እርዳታ እየተራመደ ነው። የእናንተ ወሬ ከምቀኝነትና ከዋልጌነት የመነጨ ለመሆኑ ከመልክታችሁ መረዳት ይችላልና ምንም አታመጡምና አትልፉ። እርግጥ ከዚህም የተሻለ ነገር ለማድረግ ችሎታውም ብቃቱም የላችሁምና ብዙም አያስገርምም። ይህንን መልእክት ትናንትና አስፍሬው ነበረ ነገር ግን የሌላውን እንደ ጉድ አድርጋችሁ ማውራት እንጂ ስለራሳችሁ ግን ማየት መስማት እንደማትችሉ እያረጋገጣችሁ ስለሆነ ለማስነበብ ፍላጎታችሁ አለመሆኑን ያሳያል። እባካችሁ ውሸት እየለመደባችሁ ስለሆነ ነግሮችን ማጤን ብትጀምሩና እንደ ሰው ከህሊናችሁ ጋር ለመኖር ብትሞክሩ መልካም ነው። እግዚአብሔር ይርዳችሁ።

Anonymous
August 7, 2013 at 12:23 PM

ውሾች ይጮሃሉ ግመሎች ግን ኮራ ብለው ይሄዳሉ

Anonymous
August 8, 2013 at 7:38 AM

Haleluya, Elelelelllllllllllllllllllllllllll

Anonymous
August 9, 2013 at 9:13 PM

ይበል ብለናል ነፍሰ ገዳዩን ማህበር በጋራ እንዋጋ የእውነት ባለቤት ይርዳን::

Anonymous
August 9, 2013 at 10:05 PM

በነዋይ ፍቅር የሰከረው ማቅ መቀመቅ ይውረድና በቅዱሳንና በእመቤታችን ሥም በቤተክርስቲያናችህን የሚነግደው አልበቃ ብሎት አሁን ደግሞ የእግዚአብሔርን ሥራ መቀማት ፈልጎ እንደ ሳጥናኤል እየዞረና እያገሳ እኔ ሁሉን አዋቂ ነኝ፣ ከኔ በላይ ለቤተክርስቲያን የቆመ የለም በማለት ውዥንብሩን አየነዛ ይገኛል። የአንድን ሰው እምነት የሚለካውና የሚመረምረው ቅዱስ እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ የቤተክርስቲያናችንን ብርቱ ሰባኬ ወንጌላዊያንና ሊቃውንት ወንድሞቻችንን መናፍቅና ሌላም ሌላም ስም በመስጠት ከህዝበ ክርስቲያ ጋር ማጣላት፣ ማቃቃር፣ እምነት ማሳጣትና ማባላትን ሲኪያሂድ የቆየ ሲሆን፤ ይህ የሳጥናኤል ሥራው ለትንሽ ጊዜ የሠራለት መሆኑን አየና ይህንኑ የሰይጣን ስራውን ተያያዘው። ደስ የሚለው ነገር ግን ጌታችን ሁልጊዜም አሸናፊ በመሆኑ የጠላት ወሬውን እያጋለጠ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው። ግን ጌታችን እድሜ ለንስሃ ስለሰጣቸውና ስለታገሳቸው፣ ትክክል የሰሩ መሰላቸው። እንኩአን ኃያሉ ጌታ፣ ህዝበ ክርስቲያኑም አሁን ተንኮላቸውን አውቆ ተቀባይነት ካጡ አመታት አስቆጥሩአል። የወንድሞች ከሳሽ ማቅም እያፈረ ስለመጣ ሌላ ግድግዳ መጫር ጀምሩአል፡ እግዚአብሔር ደግሞ የራሱ የሆኑትን እሱ ያውቃልና ምስማር ሲመቱት እንደሚጠብቀው

Anonymous
August 10, 2013 at 10:24 PM

The sytan mahber mk; gena, gena, bezu yigaletal
bechelema yemiserawm be-Kerestos Berhan yitayal
Keber Le-Amlakachen yihun.

Anonymous
August 11, 2013 at 10:58 AM

ማህበረ ቅዱሳን እስከ መቼ እንደ ቀበሮዋ የበግ ለምድ ለብሰህ ትኖራለህ፡፡ አንተ ከተቋቋምክ ጀምሮ ከ7000000(ሰባት ሚሊዮን) ኦርቶዶክስ አማኞች በአንተ ክስና ተንኮል በመናፍቃን እንደተበሉ አልሰማህም፡፡ አሁን ወጣቱ ወደ ቤተክርስቲያኑ ተመልሶ ስታይ አይንህ ለምን ደም ይለብሳል፡፡ በአንድ ሐጥእ መመለስ በሰማይ መላእክት ዘንድ ደስታ ከሆነ በወጣቶች ወደ ቤተክርስቲያን መመለስ ከተናደድክ ግብርህ እንደ ስምህ ከቅዱሳን ጋር ሳይሆን የሰዉን ልጅ መጥፋት ከሚመኘዉ ከዲያብሎስ ጋር ነዉ፡፡ ስለዚህ ያ የአንተ ክፉ ዘመን አብቅቶአል፡፡ ፤ቤተክርስቲያናችን ብሩህ ዘመን በእዉነተኛዉ እረኛ በክርስቶስ የተበሰረላትን እየጠበቀች በመሆኑ አንተ ከዚህ በሁዋላ በቤ/ክ ስፍራ የለህም፡፡ ስፍራህ አሁን እየኖርከዉ እየተለማመድከዉ ባለዉ ድቅድቅ ጨለማ ነዉ፡፡ ግን ግዜ አለህ ንስሀ ለመግባት ምክንያቱም የክርስትና ማእከሉ ሰዉ ነዉ፡፡ እግዚአብሔር የሚያድነዉ ሰዉን ነዉ እናንተ የጠላችሁት ደግሞ ሰዉን፡፡ ስለዚህ #የጠቢብ አይኑ በራሱ ነዉ$ ስለሚል ጠቢቡ ሰለሞን ወደራሳችሁ ተመልሳችሁ እራሳችሁን እዩ ለዚህም እግዚአብሔር ይርዳችሁ፡፡ አሜን!!!

Anonymous
November 1, 2013 at 4:55 PM

you always preach devil things, not Jesus Christ.

Post a Comment

አስተያየቶች

 
Support : | |
Copyright © 2011. ደጀ ብርሃን dejebirhan - All Rights Reserved

Proudly powered by Blogger