አቡነ ሳሙኤል ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ውስጥ ሽምቅ ውጊያ መጀመራቸው ተሰማ
በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ለጳጳሳት ማረፊያ በተሰራው ህንጻ ውስጥ ሳይሆን፣ ተምረው
ባላለፉበት በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ የሚኖሩት የልማት ኮሚሽን የበላይ ጠባቂ አቡነ ሳሙኤል ከማህበረ ቅዱሳን የተሀድሶ
መናፍቃንን ዘመቻ ለመከላከል በሚል ከሰበሰበው ገንዘብ ላይ እንደተለቀቀላቸው በሚታመነው ገንዘብ አንዳንድ የኮሌጁን ተማሪዎች በማባበልና
ከብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው የሚባሉ ተማሪዎችን በመዋጋት በውስጣቸው ተዳፍኖ አልወጣላቸው
ያለውን መፈንቅለ ፓትርያርክ እንደገና ለመሞከር ሽምቅ ውጊያ መጀመራቸው ተሰማ፡፡
አቡነ ሳሙኤል ከማህበሩ ጋር በመቀናጀት ለጀመሩት ሽምቅ ውጊያ አንዱ የቤት ስራቸው
በኮሌጁ ውስጥ ከዚህ ቀደም በደጀሰላም ድረገጽ ላይ ወጥቶ የነበረውና ማህበረ ቅዱሳን ‹‹ተሀድሶ ናቸው ይባረሩልኝ›› ብሎ
ያለባለቤትና አድራሻ የላከውንና በኮሌጁ አስተዳደር ውድቅ የተደረገውን ክስ እንደአዲስ ማንቀሳቀስና የተባሉትን ደቀመዛሙርት
ከኮሌጁ ማስወጣት ነው፡፡ ከሰሞኑም ያው ስም አጥፊ ደብዳቤ እንደ ተለመደው ያለባለቤትና አድራሻ ተልኮ ለኮሌጁ አስተዳደር
ከደረሰ በኋላ ፍሬከርስኪ ሆኖ በመገኘቱ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ምክንያቱም ባለቤት የለውም አድራሻም የለውም፡፡
ከማህበረ ቅዱሳን ጋር በማበር ማህበሩ የሰጣቸውን ተልኮ ለመፈጸምና ጎን ለጎንም
ማህበሩ የገባላቸውን የመጨረሻና ትልቅ ተስፋ (ፓትርያርክ መሆን) ለማሳከት ሽምቅ ውጊያ የጀመሩት አባ ሳሙኤል ከስላሴ ግቢ
መልቀቅ እንዳለባቸው አንዳንዶች እየተናገሩ ነው፡፡ በስላሴ ኮሌጅ ውስጥ መሆን የመረጡት እንደ ጳጳስ ሳይሆን እንዳሻቸው ለመኖር
ስለሚመቻቸው ነው የሚሉት እነዚሁ ታዛቢዎች፣ ይሄው ታውቆ የኮሌጁን ግቢ እንዲለቁ መደረግ አለበት ሲሉ ይናገራሉ፡፡
ምንጭ፤ http://awdemihret.blogspot.com/