Friday, March 2, 2012

«አንድ ሳንቲም»

 
የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ!

አንድ ሳንቲም ሁለት ገጻት አለው። እንደሀገርኛው ቀደምት አባባል በአንደኛው ገጽ «አንበሳ» ሲሆን በሌላኛው «ዘውድ» ነው። አንበሳው ኃይሉን የሚገልጽ ሲሆን ዘውዱ ደግሞ ሥልጣኑን ያመለክታል።
እንደዚሁ ሁሉ ማኅበረ ቅዱሳን አንደኛውን ገጽ ልክ እንደአንበሳ «ደጀ ሰላም» ብሎ በሰላም ስም አንድም የሰላምን የወንጌል አስተምህሮ ሳይጽፍ እያጓራ ያስፈራራበታል ወይም ስም ያጠፋበታል። በዘውዱ በኩል ደግሞ የማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ በሚል ፊቱ የወንጌል ቃል ተናጋሪና አስተማሪ መሆኑን ያሳይበታል። እንደዚህ ነው በአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽ ማለት!! ይህ ማኅበር ደግሞ በጣም የገባው ነው። ሲሰራ እንደዚያ ነዋ!!
የሀገሬ ሰውም «ሁለት ባላ ትከል፣ አንዱ ሲነቀል ባንዱ ተንጠልጠል» ይል የለ!!
«ደጀ ሰላም» ብሎግ ስለጾም፣ ስለጸሎት፣ ስለቅዱሳን ወይም ስለወንጌል አስተምህሮ የተሰጠው የገጽታ ግንባታ ኃላፊነት ስለሌለው ለሌላኛው ገጹ ጠቅልሎ በማስረከብ ስራውን በትኩስ ዜና፣ በመርዶ ነገራ፣በተሃድሶ ዘመቻ፣ በትችትና በነቀፋ፣ በያዘው፣ ደረስኩብህ ሩጫ ላይ ተጠምዶ ይህንኑ ያከናውናል።
ሁለቱ ፊቶች አንዳንዴ እንደዚህ አንድ መሆናቸውን ይመሰክሩልናል። ሁለቱም ቆሮንቶስ ላይ ሱባዔ የያዙ ለመምሰል መልካቸውን ቀይረው አንድነታቸውን ያሳዩናል።
አቤት አንድ መሆናችሁ ሲያምርባችሁ! ግን ለምን ትከዳዳላችሁ?
ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ዓይነት ከእውነቱ መሸሽ ጥሩ አይደለምና እንደመልካችሁ አዋጅ ነግራችሁ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጻት መሆናችሁን አጠንክሩ! ምክራችን ነው።