በ2ኛ ሳሙ.11፤1 እንዲህም ሆነ በአመቱ መለወጫ-
-በ2ኛ ሳሙ.11፤1 እንድህም ሆነ በአመቱ መለወጫ ነገሥታት ወደ ሰልፍ በሚውጡበት ጊዘ ...ዳዊት ግን በእየሩሳሌም ቀርቶ ነበር።ጥያቀ 1ኛ .የእሰራኤላዉያን የአመት መለወጫ የትኛው ወር ነው?ከ4ቱ ወቅቶች በየትኛው ውስጥ ይመደባል?እንደ እትዮጵያውያንሰ?
2ኛ.ነገሥታት ለሰልፍ የአመት መለወጫን ለምን መረጡ?
3ኛ.የእስራኤላውያን ግብርና ሁኔታስ ለስልፍ በሚውጡበት ጊዘ በምን ሁኔታ ላይ ይገኝ ነበር? ለግንዛቤ(4ቱ ወቅቶች winter,spring,summer,autumn)
አስተያዬት፦
ጥያቄ ካበዘሁባችሁ አስተዬታችሁን እፈልጋለሁ። እስካሁን እየጠየቅሁችሁ ላለው ጥያቄ አጥጋቢ መልስ እያገኘሁበት ሰላለ እ/ር አብዝቶ ይባርካችሁ።ቃሉን የሚገልጥ መንፈስ አብዝቶ ይጨምርላችሁ። Yonni Tibesso
(የደጀብርሃን መልስ)
የእብራውያን አዲስ አመት እንደኢትዮጵያውያን ወር አቆጣጠር በመስከረም ወር ላይ ነው። ወሩ በአብዛኛው በወሩ በ1ኛው ወይም በ2ኛው ቀን ላይ ይውላል።
በእብራይስጥም ሮሽ ሃሸና ראש השנהይባላል። «ሮሽ ሀሸና» ማለት የወሮች ሁሉ ራስ ማለት ነው። የኛው መስከረም ደግሞ «ትሽሪ» תִּשְׁרֵיይባላል። ከወቅቶች አቆጣጠር ደግሞ autumn ወይም በልግ የሚባለውን ይይዛል። ወርሃ ክረምት ከመግባቱ በፊት የሚመጣ ወር ነው።
እብራውያን አዲስ ዓመት አድርገው መስከረምን ያክብሩ እንጂ መስከረም የዓመቱ የመጀመሪያ ወር አይደለም። የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ሚያዚያ ነው። ሚያዚያ የመጀመሪያ ወር ሊሆን የቻለው እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ነጻ የወጡበት በዚህ ወር ስለሆነ ነው።
«ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ ይሁናችሁ የዓመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ» ዘጸ 12፣2
«በመጀመሪያው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን ሲመሽ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው» ዘሌ 23፣5
እሱም ኒሳን נִיסָן ይባላል።
ኒሳን የመጀመሪያው ወር ስለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ያረጋግጥልናል።
« አስቴር 3፥7
በንጉሡም በአርጤክስስ በአሥራ ሁለተኛው ዓመት ከመጀመሪያው ወር ከኒሳን ጀምሮ በየዕለቱና በየወሩ እስከ አሥራ ሁለተኛው ወር እስከ አዳር ድረስ በሐማ ፊት ፉር የተባለውን ዕጣ ይጥሉ ነበር»
ወደጥያቄህ ስንገባ ነገሥታቱ በሚያዚያ ወር መጀመሪያ ላይ ከጠላቶቻቸው ጋር ይዋጉ የነበረው፤ የነገረ መለኰት ምሁራን ይህንን ያስቀምጣሉ።
1/ ከግብጽ ባርነት ነጻ የወጡበት ወር በመሆኑ፣ በዚህ ወር ድል ሁሉ የእነሱ እንደሆነ ያምናሉ።
2/ የሀገራቸው ክረምት የሚያልቅበት ጊዜ በመሆኑ፣ከጭለማና ከአረንቋ ይልቅ ብርሃኑ ሲገልጥ ውጤታማ እንደሚሆኑ ስለሚያምኑ፤
3/ ጠላቶቻቸውም ይህንን ሰማይና ምድሩ የሚገፍበትን ጊዜ ጠብቀው ስለሚያጠቋቸው አስቀድሞ መምታት እንደሚገባቸው በማመን፣
ጥንት ጠላቶቻቸው ሲመክሩ እንዲህ ሲሉ ይጠጠቡባቸው ነበርና እስራኤላውያንም ሲጠበቡባቸው ይህንን ወር ይመርጡት ይሆናል።
«እንዳይበዙ፥ ሰልፍም በተነሳብን ጊዜ ጠላቶቻችንን አግዘው እንዳይወጉን ከምድሪቱም እንዳይወጡ፥ ኑ እንጠበብባቸው አለ» ዘጸ 1፣10
ስለዚህ እስራኤላውያንም በመጠበብ ይህንን ወቅት ይመርጡታል።