ትክክለኛ እድሜ የትኛው ነው?
[መንገሥ በጀመረ ጊዜ አካዝያስ የሀያ ሁለት ዓመት ጕልማሳ ነበረ በኢየሩሳሌምም አንድ ዓመት ነገሠ። እናቱም ጎቶልያ የተባለች የእስራኤል ንጉሥ የዘንበሪ ልጅ ነበረች] 2ኛ ነገ 8፡26
[አካዝያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ዕድሜው አርባ ሁለት ዓመት ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም አንድ ዓመት ነገሠ እናቱም ጎቶሊያ የተባለች የዘንበሪ ልጅ ነበረች] 2ኛ ዜና 22፣2 (በደጀብርሃን፣ የተጠየቀ)

በደጀብርሃን የተመለሰ፣
ይህ ጥያቄ ብዙ ጊዜ ሲቀርብ አይቻለሁ። ምናልባትም እናንተም አጋጥሟችሁ
ይሆን ይሆናል። ከዚህም የተነሳ እዚህ ላይ ፖስት በማድረግ እኔ ከማውቀው የተለየ ምላሽ ካለ ለማየት ጠብቄ ነበር።
እስካሁን ምላሽ የሚሰጥ ስላላገኘሁ እኔ ያገኘሁትን መረጃ በምላሽነት ላስቀምጥ ወደድሁ። ወደፊት የተሻለ ምላሽ
የሚሰጥ ካለ እጠብቃለሁ።
በእብራይስጥ አኀዝ የሚጻፈው በፊደል (alphabet) ነው። በዚሁ መሠረት የአካዝያስ እድሜ በቀደሙት የሱርስትና የዐረቢያ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሁሉም ቦታ 22 እድሜ እንደነበረው ተጽፎ ይገኛል። የሰባ ሊቃናት ትርጉም በተባሉት መጻሕፍትም ውስጥ 22 ዓመት ስለመሆኑ በዜና መዋእል ውስጥ ሳይቀር ተጽፎ ተገኝቷል። በአንዳንዶች ውስጥ ደግሞ 42 ዓመት እንደሆነ ተቀምጦ ይገኛል። ይህ የሚያሳየው ተርጓሚዎች ከአንዱ ቋንቋ ወደ ሌላ ቋንቋ ሲገለበጡ ያመጡት ክስተት መሆኑን ነው። ከላይ እንደተገለጸው የእብራይስጥ ቁጥር አኀዝ ሳይሆን ፊደል ስለሆነ 20 ለማለት כ የሚጻፍ ሲሆን 40 ለማለት ደግሞ מ ይጻፋል።
እነዚህ ፊደላትን አስማምቶ በቁጥር ካለማስቀመጥ የመጣ ሊሆን እንደሚችልና አካዝያስም ሲነግስ እድሜው ከአባቱ ከኢዮራም ኖሮ ከሞተበት እድሜ በሁለት ዓመት ሊበልጥ ስለማይችል (ኢዮራምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሠላሳ ሁለት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ስምንት ዓመት ነገሠ 2ኛ ነገ 8፣17) በማለቱ የትርጉሙን ስህተት ማየት ይቻላል። የእብራይስጡን ב +כ =22 በማለት እንደማስቀመጥ 42=ב מ+ በማለት ስህተቱን መገንዘብ ይቻላል። ለተጨማሪ መረጃ ፤(ይህንን ይጫኑ)