በ4ኛው ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ የሚመራው የአሜሪካው ሲኖዶስ ጠንከር ያለና መሠረታዊ የልዩነት ነጥቦችን የሚያመላክት
መግለጫ አውጥቷል። የሀገር ቤቱ ሲኖዶስ ሕጋዊ እንዳልሆነና ሕጋዊ ሊባል የሚቻለው በአቡነ መርቆሬዎስ የሚመራው ሲኖዶስ እንደሆነ
ሕገ ቤተክርስቲያንን አጣቅሶ ያቀረበ ሲሆን ከመንበር ላይ በመሰደድ ቅዱስነታቸው በቤተክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያ እንዳልሆኑ በማመልከት
ሁሉም ስደቶች የአባቶች ጥንካሬና የምእመናን ብርታት አሰዳጆችን እምቢ በማለት አንድነትና ኅብረትን ያሳየ ሆኖ ከማለፉ በስተቀር
ለመኳንንቱ ፍላጎት ይሁንታን በመስጠት ኅብረታቸውን በታትነው እንደዚህ እንደዛሬው አለመታየታቸውን በመግለጽ መግለጫው ሰፊ ሀተታ አቅርቧል።
ወደ 6ኛ ፓትርያርክ ምርጫ ለመግባት ጥቂት የሥልጣን ጥመኞች ጳጳሳት መንግሥትን ተገን አድርገው ያቀናበሩት እንደሆኑ
በማመልከት በቤተክርስቲያናችን ታሪክ ሌላኛውን ስህተት ለመፈጸም በመቋመጥ
ወደምርጫ የመሄድ አድራጎቱን በውግዘት ኮንኖታል።
ከአባ ሰላማ ብሎግ ላይ ያገኘነውን ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ
እዚህ ላይ( Click here )