ማኅበረ ቅዱሳን ማለት ለተረት፤ ለእንቆቅልሽ፤ ለልማድና ለባህል እምነት ጥብቅና የሚቆም፤ የወንጌል ቃል ጆሮውን የሚያሳክከው፤ በኢየሱስ ክርስቶስ የእውነት መንገድ ላይ ቆሞ እንዳይገለጥ መጋረጃ የሚጋርድ የጠላት መልእክተኛ ማለት ነው። ማኅበረ ቅዱሳን በሀገሪቱ ላይ የብርሃን ወንጌል እንዳይበራ የጭለማ ሥራ የሚሰራ፤ ሰዎች በእጃቸው ያለውን እውነት እንዳያዩ ወደገደል የሚመራ እውር መሪ ማለት ነው።
ማኅበረ ቅዱሳን ማለት በአንድ ወቅት የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለው እስራኤል በእግዚአብሔር ላይ ያለውን እምነት ትቶ የራሱን የልብ መሻትና ምኞት በተከተለበት ወቅት እንደሆነው ዓይነት በተመሳሳይ መልኩ በሀገራችን በኢትዮጵያም ከፊት ሆኖ በሀሰት እየመራ በእውነት የሚፈርድ እንዲታጣ ያደረገ፤ በሀሰትም የሚያስተምር እንዲበዛ የፈለፈለ፤ ልቡን ያደነደነ ትውልድ እንዲበረከት ሚና የተጫወተ ማኅበር ነው።
ያንን የእስራኤል ዐመጽ ነቢዩ ኤርምያስ እንዲህ ሲል ተናግሮት ነበር።
«እናንተ ሰነፎች ልበ ቢሶች፥ ዓይን እያላችሁ የማታዩ፥ ጆሮም እያላችሁ የማትሰሙ ሕዝብ ሆይ፥ ይህን ስሙ። በውኑ እኔን አትፈሩምን? ከፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንዳያልፍ አሸዋን በዘላለም ትእዛዝ ለባሕር ዳርቻ አድርጌአለሁ፤ ሞገዱም ቢናወጥ አያሸንፍም፥ ቢጮኽም አያልፍበትም። ለዚህ ሕዝብ ግን የሸፈተና ያመፀ ልብ አላቸው፤ ዐምፀዋል ሄደውማል። በልባቸውም፦ የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በጊዜው የሚሰጠውን፥ ለመከርም የተመደቡትን ወራት የሚጠብቅልንን አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ አላሉም። በደላችሁ እነዚህን አስቀርታለች፥ ኃጢአታችሁም መልካምን ነገር ከለከለቻችሁ። በሕዝቤ መካከል ክፉዎች ሰዎች ተገኝተዋል፤ እንደ አጥማጆችም ያደባሉ፥ ወጥመድንም ይዘረጋሉ ሰዎችንም ያጠምዳሉ» ኤር 5፤21-26
ማኅበረ ቅዱሳን በዘመናት ብዛት ማን እንደጻፋቸውና ማን እንዳስገባቸው የማይታወቁ የተረትና የእንቆቅልሽ መጻሕፍት እንዳይነኩ ዘብ የቆመ የጠላት ወታደር ነው። ብዙዎች እውነት በመናገራቸውም ያወገዘና ያስወገዘ ማኅበር ነው። ለምሳሌ አንድ አስረጂ እናንሳ!
መስተብቍእ ዘመስቀል በተባለው የቤተክርስቲያን የጸሎት ክፍል ውስጥ እንዲህ የሚል ክህደት ተሰንቅሮ ይገኛል።
«ለእሉ ክልዔቱ ፍጡራን/ለማርያም ወለመስቀል/ ስብሐተ ፈጣሪ ይደልዎሙ፤ እስመ ተዐረዮሙ በክብሮሙ»
ለነዚህ ሁለቱ ፍጡራን (ለማርያምና ለመስቀል) ለፈጣሪ የሚሰጠው ምስጋና ይገባቸዋል። በክብር ፈጣሪያቸውን ተካክለዋልና!
እግዚአብሔር ቢከብር ክብር የባህርይው እንጂ አክባሪ የሚጨምርለትና የሚቀንስለት ነገር የለም። ማንም የቱንም ያህል ቢከበር ከእግአብሔር ፈቃድ አንጻር እንጂ በራሱ ብቃት በሚያመጣው ችሎታ አይደለም። ደግሞም በክብር እግዚአብሔርን የሚስል፤ የሚያክልና አቻ የሚሆን ፍጥረት ፈጽሞ የለም። «በልዑል እመሰላለሁ» ካለው ከሰይጣን በስተቀር ከፍጥረታት ውስጥ በክብር እግዚአብሔርን የሚተካከል የለም።
«ከዳመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፥ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ» ኢሳ 14፤14
ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚመስለው ማንም የለም? በማንም ልንመስለውና ከማንም ጋር ልናስተካክለው አይገባም። ራሱ እግዚአብሔር በነቢዩ አንደበት እንደዚህ ሲል ተናግሮናልና።
«እንግዲህ እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ? ይላል ቅዱሱ። ኢሳ 40፤25»
ማኅበረ ቅዱሳን ማለት እንደነዚህ ዓይነት ተረቶችና ክህደቶች እንዳይነኩ ለእውነት ሁሉ ጠላት ለሆነው ለሰይጣን ጥብቅና ቆሞ የሚከራከር ማኅበር ነው። መንፈሳዊ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች የእውቀትና የማስተዋል ተቋማት እንደመሆናቸው መጠን ጥያቄ የሚጠይቁና ከእግዚአብሔር ቃል የተገናዘበ አሳማኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው የሚተጉትን በክህደትና በምንፍቅና እየወነጀለ መቆሚያና መቀመጫ የሚያሳጣ፤ ወይ ከእውቀቱ ወይ ከእውነቱ አንዱንም ያልያዘ ድርጅት በመሆኑ ነው።
ስለዚህ ፓትርያርክ ማትያስ ለመንፈሳዊ ኮሌጆች ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ ደብዳቤ ለመጻፍ የተገደዱት ከኮሌጆቹ ተማሪዎች ጥያቄ አንጻር ብቻ ሳይሆን ፓትርያርኩ ለሚያደርጉት ትግል የሊቃነ ጳጳሳቱ ድጋፍ አናሳ ሆኖ በመገኘቱ ቢያንስ የትግላቸው አጋር የተማረውን ክፍል ለመያዝ ከመፈለግ የተነሳ ይመስላል።
በዚህ አጋጣሚ የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችና የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳይ ግድ የሚለው ሁሉ ከፓትርያርኩ ጋር በመቆም የያዙትን ትግል ከግብ ለማድረስ በጸሎትና በሃሳብ እንዲያግዝ ለማሳሰብ እንወዳለን።
ደብዳቤዎቹን ለማንበብ ሊንኩን ከከፈቱ በኋላ ለማስፋትና በደንብ ለማንበብ ጽሁፉን ይጫኑት!
እዚህ ይጫኑ 1
እዚህ ይጫኑ 2
እዚህ ይጫኑ 3
እዚህ ይጫኑ 4