ግብረ ሰዶማዊነትና የእኛ ዘመን አገልጋዮች

( ከአቤኔዘር ተክሉ )

    ስለግብረ ሰዶማዊነት በሁለት የተለያዩ ክፍሎች መጻፌና በሁለቱ ክፍሎችም ለጊዜው የነበረኝን ሃሳብ ማጠቃለሌን አልዘነጋውም፡፡ ነገር ግን አሁንም ግብረ ሰዶማዊነት የቤተ ክርስቲያንን ቅድስና ከማርከስ፤ ምድራችንን ለከፋ ጉስቁልናና ርኩሰት አሳልፎ ከመስጠት ያላቆመ ፍጹም ወደመስፋፋት የሄደ ክፉ ርኩሰት ነውና ዳግም ይህንን ርዕስ ማንሳት አስፈልጎኛል፡፡ ለዚህ እውነታ ብዙ የቅርብ ጊዜ ማሳያ ብቻ ማንሳቱ በቂ ይመስለኛል፡፡

    ድርጊቱ የተፈጸመው በምስራቁ የሃገራችን ክፍል ነው፡፡ የሠላሳ ሁለት አመት አጐት የአራት አመት የወንድም ልጁን በእረኝነት ሥፍራ በመሄድ ጫት እንዲቅም ያግባባዋል፡፡ ህጻኑ እንቢ ቢልም ያስገድደዋል፡፡ ጫት እንዲቅም ካስገደደው በኋላ ልጁ ራሱን መቆጣጠር ሲያቅተው ልጁን የግብረ ሰዶም ጥቃት ይፈጽምበታል፡፡ የልጁ የሰገራ ማውጫ ሙሉ ለሙሉ ይቀዳዳል፡፡ ከሆዱ የወጣው የውስጠኛው የሰገራው ክፍል ሙሉ ለሙሉ የልጁን ጠረን ይለውጠዋል፡፡ ልጁ ፍጹም ራሱን ስቶ ሲወድቅ ከወደቀበት ቦታ ተሸክሞት ከወላጆቹ ጓሮ አምጥቶ ጥሎት ይሰወራል፡፡ ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የልጁ ህይወት ያልፋል፡፡

    ሌላም ብንጨምር፦ አንድ “ስመ ገናና” አገልጋይ እንዲህ ያለ ነውር እንደሚፈጽም በምስክር ይረጋገጥና ብዙዎች ተረባርበው ሊመክሩት ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን ከማስመሰልና የሽንገላ እሺታ ከማሳየት በቀር ከነገሩ ሳይታቀብ ይቀራል፡፡ በኋላ ይባስ ብሎ በአቋም፤ የሠራው ትክክል እንደሆነና ይቅርታ መጠየቅ እንደማያስፈልግ ከብዙ ደጋፊዎቹ ጋር በግልጥ በአቋሙ ይጸናል፡፡ ወንድሞቹን ይቅርታ ሳይጠይቅ በግልጥ ለሠራውና ሌሎችን ላሰናከለበት ኃጢአቱ ንስሐ ሳይገባ እንደዋዛ ዛሬም አለ፡፡ በድርጊቱ የተጠቁት ወንድሞች ግን “እንዲህ ያለ ነገር እያደረገ በአንድ የኃይማኖት ጥላ ሥር አንቀመጥም” በማለት ወደሌላ የእምነት ተቋም ራሳቸውን አገለሉ፡፡ (ርቀው ወደሌላ የኃይማኖት ተቋም እንዳይሄዱ ብዙ ርብርብ ቢደረግም አልተሳካም፡፡)

    በመንግስትም ደረጃ በዘንድሮው የይቅርታ መመሪያ ውስጥ ይቅርታ ከሚያሰጡ ወንጀሎች መካከል ግብረ ሰዶማዊነትም እንዲካተት ጥረቶች “መደረጋቸውና መሳካቱንም” ጭምጭምታዎች ይሰማሉ፡፡ ጉዟችን ወዴት ይሆን? እንዲህስ እስከምን ድረስ ነው የምንጓዘው?

      ግብረ ሰዶማዊነት እግዚአብሔር የፈጠረውን ፍጥረት ሙሉ ለሙሉ በመቃረን የሚፈጸም ርኩሰት ነው፡፡ ቃሉም “ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው”(ሮሜ.1፥24) እንዲል ቅዱሱን የእግዚአብሔር ፍጥረት በመቃረናችን ምክንያት የገዛ ኃጢአታችን “ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ እንደሰጠን” ትልቅ ምስክር ነው፡፡(ሮሜ.1፥26)

   ጥቂት የማይባሉ አገልጋዮች “ለአገልግሎት” ወደክፍለ አገር ወይም ወደውጪ አገር ሲወጡና ጨርሰው ሲመለሱ ጥንድ ጥንድ እየሆኑ ሹልክ ብለው ለሴሰኝነትና ለዝሙት እንደሚገባበዙ ፀሐይ የሞቀው እውነት ሆኗል፡፡   በአቶ አስማማው ኃይሉ በተጻፈውና “ኢህአሠ” በተባለው ቅጽ አንድ መጽሐፍ ላይ ከትግል መልስ ደራሲው አንድ ታጋይ ነገረኝ ብሎ ሲጽፍ ፤ ታጋዩ ማደሪያ አገኘሁ ብሎ ወደ አንድ ቤተ ክርስቲያን ሊጠለል ጎራ ባለበት ወቅት ሌሊቱን ሙሉ  የገጠመው ሌላ ትግል ይኸው ከግብረ ሰዶማውያን ጋር ያደረገው ያለመደፈር ትግል እንደነበር በግልጥ አስቀምጦታል፡፡ በእርግጥ ዛሬ በገዳም ካሉት ጥቂት የማይባሉ መነኰሳትና መነኰሳይያት፤ እንዲሁም  በወንዶችም ሆነ በሴቶችም ዘማሪዎቻችን መንደርም የምንሰማው ነገር ጆሮን ጭው የሚያደርግ ነው፡፡ (እንደአገር ስናስብ ደግሞ በካርዲናሎቹና በፓስተሮቹም መካከል አጸያፊ የርኩሰት ነገር ጆሯችን ከመስማት አልታከተም!!)   

     ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ያሉ ኃጢአተኞችን በግልጥ ከመቃወም እየደከመች የመጣች ይመስላል፡፡ ምክንያቱም የግብረ ሰዶማውያን “አገልጋዮችን” የጨለማ ሥራን ከመግለጥ (ኤፌ.5፥11)፤ ሌሎች ሰዎችም ከክፋታቸው እንዳይተባበሩ ከማስጠንቀቅና መክራ እንዲመለሱ ከማድረግ ድምጿን አሰልላለች፡፡ ስለዚህም ሌሎች ብዙዎች ግብረ ሰዶማውያኑን  “በርቱ፤ እኛም ከጎናችሁ ነን” ከማለት አልፈው ለግብረ ሰዶማውያኑ ድጋፍ ሲሰጡና ሲሟገቱላቸው በአይናችን እያየን ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ኩልልና ጥርት ያለ የተቃውሞ ድምጿን ልታሰማ ግድ የሚላት ጊዜ አሁንና አሁን ነው፡፡ ከረፈደ በኋላ መሯሯጥ ድካም እንጂ ሚዛን የሚደፋ ትውልድ የማዳን ሥራ አይሠራም፡፡

    የሰዶም ሰዎች ያደርጉት የነበረው የክፋት ድርጊታቸውን እንደመልካም ከመቁጠር አልፈው እነርሱ የሚያደርጉትን ነውር የማያደርጉትን ሰዎች ይቃወሙ፤ የእነርሱን ነውር እንዲቀበሉ ያደርጉም ነበር፡፡ በአገሪቱ ካሉት ሰዎች ሁሉ ጋር ነውራቸውን ከፈጸሙ በኋላ  እንግዳ ሰዎች በመካከላቸው በተገኙ ጊዜ ከእንግዶቹ ጋር ሊፈጽሙ (በሎጥ ቤት የመጡትን መላዕክት ሲያዩ ወደአዲስ መጎምጀት መጥተዋልና!) የኃይልን መንገድ እንደተጠቀሙ፤ ጻድቁንም ሎጥ እንደተጋፉትና በሩን ሊሰብሩ እንደተገዳደሩ ታላቁ መጽሐፍ ይነግረናል፡፡(ዘፍ.19፥5-9) ሰው ለእግዚአብሔር ባህርይና ለተፈጥሮ እውነት መገዛት ሲሳነው የኃጢአት መሻቱ ድንበር አልባ ይሆናል፡፡ ሁሉንም ርኩሰት ከመፈጸም የሚያግደውም የለም፡፡

   ዛሬ ላይ ድሆች ሃገራትን ለመርዳት የሚዘረጉ ብዙ የእርዳታ እጆች ስውር አጀንዳቸው ግብረ ሰዶምና ሰዶማዊነት ለመሆኑ ብዙ ማስተንተኛ ማቅረብ አያስፈልግም፡፡ ግብረ ሰዶምን በግልጥ የተቃወመች ብቸኛይቱ አፍሪካዊት ሃገር ይህንን በግልጥ አይታዋለችና፡፡ እኛ “ከቃል ባልዘለለ” ክርስትናችን በከንቱ ስንመካ ከአገራችን ቀድማ ግብረ ሰዶማዊነትን በግልጥ አለም አቀፍ በሆነ ዕይታ ህግን አስደግፋ ተቃውሞ ያሰማችው አፍሪካዊት አገር ኡጋንዳ ናት፡፡ በእርግጥ የእኛ ወንጀል ህግ “ግብረ ሰዶማዊነት ወንጀል ነው” ይላል፤ ግን የአገሪቱን ትልልቅ ከተሞች ጎዳና እያጥለቀለቁ ያሉትና ቁጥራቸው የማይናቅ አገልጋዮችን እንደወረርሽኝ በሽታ እየወረሱት ያሉት “ሴት እንተኛ አዳሪዎች” ብቻ ሳይሆኑ ግብረ ሰዶማውያኑም ጭምር ናቸው፡፡ ህጉ ቢኖርም ለነዚህ ምድርን ለሚያረክሱ “ወገኖች” ግን ጥርስ የሌለው አንበሳ ሆኖ ተቀምጧል፡፡

   የኡጋንዳ መሪዎች ያንን የመሰለ ቁርጥ ያለ አቋማቸውን በግብረ ሰዶማዊነት ላይ ሲያሰሙ፤ ሰለጠን ያሉቱ ምዕራባውያን የኡጋንዳን ድርጊት “የሰይጣን ድርጊት” አድርገው ለማቅረብ ጊዜ አልወሰደባቸውም፡፡ (እግዚአብሔርስ ይቅር ሰይጣን እንኳ እንዴት ታዝቦን ይሆን?!)  የእኛ አገልጋዮች ግን ዛሬም ግብረ ሰዶማዊነትን በመካከላችን ያሽሞነሙኑታል፡፡ ከዓመታት በፊት ግብረ ሰዶማውያኑም አለም አቀፍ ስብሰባ አፍንጫችን ስር ባለችው አዲስ አበባ አድርገው አባላታቸውን መልምለው ሲሄዱ እንኳ ዝም ጭጭ ሆኗል ክርስትናችን፡፡ እንኪያስ ወርቁ ለምን ይሆን የደበሰው?
   ግብረ ሰዶማውያንን ለመቃወም የአገልጋዮች “ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ” ማለት ከበለጠብን እንኪያ እኛስ ከእነርሱ በምን እንሻላለን? መንፈሳዊነት መለኪያው የአገልግሎት ስኬት ሳይሆን የህይወት ጥራት ነው፡፡ ጌታ ጥራት ከሌለው ሸንጋይ መንጋ ጋር ህብረት እንደሌለውና ጥራት ካለው ጥቂት አማኝ ጋር ብቻ ህብረት እንዳለው በጌዴዎንና በሐዋርያት ህይወት አይተናል፡፡ ምክራችን፣ ጩኸታችን፣ ተግሳጻችን፣  ቁጣችን … “ምክር ለምኔ” ያሉ ግብረ ሰዶማውያን አገልጋዮች በንስሐ ተመልሰው የበደሏቸውንና ያሰናከሏቸውን ወንድሞች ይቅርታ በመጠየቅ እንዲመለሱ ነው እንጂ በመካከላችን ተቀምጠው ሌሎችን ለማጥቃት እንዲያደቡ አይደለም፡፡

    የእግዚአብሔርን ምህረት የሚያሸንፍ ወይም የሚበልጥ ኃጢአት የለም፡፡  እንዲህ የምንለው ግን በንስሐ ለሚመለሱ እንጂ ልብን ለሚያደነድኑ አመጸኞች አይደለም፡፡ ጌታ ለምድሪቱ ምህረትና የንስሐን ልብ ያውርድላት፡፡ አሜን፡፡
Share this article :

+ የተሰጡ አስተያየቶች + 23 የተሰጡ አስተያየቶች

Anonymous
November 17, 2014 at 2:47 PM

ሰላም ወንድሞች
የዚህ አሸናፊ መኮንን የሚባል ግሰለብ ወሬ ደረሳችሁ? ግብረ ሰዶም ነው ኤተባለ ከተማው ውስጥ ይወራል።

Anonymous
November 23, 2014 at 8:28 PM

ስለ አለቆቻችሁ፣

TO GET HUSBANDS, PASTOR UNDRESSES AND KISSES FEMALE CHURCH MEMBERS ASSES AT BEACH.


http://udumakalu.wordpress.com/2014/11/19/to-get-husbands-pastor-undresses-and-kisses-female-church-members-asses-at-beach/

Anonymous
November 24, 2014 at 9:20 AM

ስማ የጴንጤውም ፓስተር ተሳስቷል። ያንተም ዲያቆን ተሳስቷል። ኃጢአትን ኃጢአት በማለት እና ማካካሻ ኃጢአት በመፈለግ ሽፋን መስጠት መንፈሳዊነት አይደለም። እንደምንሰማው አዲስ አበባ ከተማ የግብረ ሰዶማውያን መናሐሪያ እየሆነች ነው። ይህ ደግሞ ፓስተሩንም ዘማሪውንም ዲያቆኑንም መነኩሴውንም ይጨምራል። ሁሉም በጌታ ፊት ኃጢአትን ሰርተዋል። ሁሉም ንስሀ ካልገቡ እንደሚጠፉም እንናገራለን። በተረፈ ለዲያቆኑ ኃጢአት የፓስተሩ ኃጢአት ማካካሻ አይሆንም ለፓስተሩም ኃጢአት የመነኩሴው ኃጢአት ማካካሻ አይሆንም። ጌታ ሁሉን ይፈውስ

Anonymous
November 24, 2014 at 9:23 PM

ዲያቆኑማ ያንተ ነው እኮ። የተሃድሶ ጴንጤ ተከፋይ ስለሆነ አይደለ እንዴ ስሙን መጥራት የከበደህ? አንተንና ድርጅትህን ካልታደሳችሁ ብለህ ግትር ስትል ተሃድሶ ጴንጤ ናችሁ ስለተባልክ አይደል እንዴ እዚህ የስንቱን አባት ሰመሪ ስታጠፋ የምትውለው? አድሳለሁ ብለህ ከመነሳትህ በፊት መጀመሪያ ፓስተሮችህነው ተመልከት። ወደ ልበወግ ተመልሰህ ኦርቶዶክስ ስትሆን የመናገር የሞራል ብቃት ይኖርሃል።

Anonymous
November 27, 2014 at 6:38 AM

እውነት ነው እኮ የምን መሸፋፈን ነው። ይህ ብሎግ አይደል እንዴ ጳጳሱን ሰዶማዊ ብሎ የጻፈው!! ታድያ ለምንድን ነው ዲያቆኑን ስመ ገናና ብላችሁ የምታልፉት? ተሃድሶ ስለሆነ ነው? ለእውነት ከቆማችሁ ከምር ለእውነት ቁሙ። እንደሆነ "ስመ ገናና" ብላችሁ የጻፋችሁለት ዲያቆን አሸናፊ መኮንን ለመሆኑ ጸሀይ የሞቀው እውነት ነው። ወሬው እንደሆነ በደንብ ተሰምቷል። እሱም እን ፈሳ ዝንጀሮ ከተሀድሶው አካባቢ ተገልሎ ለብቻው ከአጨብጫቢዎቹ ጋር ተቀምጧል። ሚኒስትሪውን ሲመሰርት መስራች ከነበሩት መካከል አንዳንዶቹ ሰዶማዊ ስለሆነ ከዚህ ልምምድ እንዲወጣ ያደረግነውም ስህተት ስላልተሳካ ለቀናል ብለው ፌደራል ጉዳዮች ያስገቡትንም ደብዳቤ አይተነዋል። ኃጢአት ወገን ስለሌለው ማንም ያድርገው ማን ሀጢአቱን ማውገዝ ይገባል። እንደ አሸናፊ አይነቱን ታረም ተመለስ ለማለት ካልደፈራችሁ እናንተም ለእውነት መቆማችሁ ያጠራጥራል። እንደ አባ ሰላማ ብሎግ ከብሎጉ ላይ የአሸናፊ መኮንንን ብሎግ ሊንክ በማንሳት ብቻ ስህተቱን ተቃውመናል ማለት አይቻልም። ችግሩን በግልጽ የሰውየውን ስም በመግለጽ መቃወም ያስፈልጋችሁዋል። ኃጢአት በእናንተ መካከል እንኳ ብትሰራ ለመቃወም ድፍረት እንዳላችሁ ካሳያችሁ በእውነት ክርስቲያን ትባላላችሁ። ሰውየው እንደሆነ አይኑን በጨው አጥቦ መስበክ ጀምሯል። እሱ ካላፈረበት ለምን ታፍሩለታላችሁ?

Anonymous
November 27, 2014 at 6:59 AM

የአሹን ነገር ተወው ባክህ በጣም ያሳዝናል። እንደ ድመት የወለዳቸውን ልጆች እኮ ነው የበላው። የት ይደርሳል የተባለ በሬ ሉካንዳ ተገኘ የተባለው ይህ ነው።ደግሞ ሊረዱት የሚፈልጉትን ወገኖች ሁሉ አይናችሁን አያሳየኝ እያለ ነው ይባላል። የመጨረሻው ዘመን እንደዚህ ነው።

Anonymous
November 27, 2014 at 7:31 AM

ሰውየው አሁንም እደግምልሀለሁ። ፓስተሩም ሰራው ዲያቁኑ ኃጢአት ኃጢአት ነው። ማስረጃ እስካለ ድረስ እና በኃጢአቱ ንስሀ አልገባም ካለ ሰው እንዲጠነቀቅ ሲባል የማንም ሰው ስም ቢጠቀስ በግሌ የምቃወመው አይደለም። ስማ ከጳውሎስ ጋር እኮ ዴማስ ነበር ከተሀድሶ ጋር ሰዶማዊ የሆነ ሰው መኖሩ ቢታወቅ ችግሩ የሰውየው እንጂ የተሃድሶነት አይደለም።ከማኅበረ ቅዱሳንም ጋር ሰዶማውያን እንዳሉ ይወራል። ስለዚህ ስም ቢገለጥም አያሳፍረኝም። ተሃድሶ ለቤተክርሰቲያን ጠቃሚ መሆኑንም አያስቀረውም። የብሎጉን አዘጋጆች መሞገት የምትፈልገው ነገር ካለህ የእኔን አስተያየት ተለጥፈህ አትንጫጫ ቀጥታ ለእነሱ ጻፍ። እኔ ኃጢአትን እንጂ የሰውየውን ሃይማኖት አልተቃመምኩም። ፓስተርም ሰራው ዲያቆን ነቢይ ነኝ ባይም ሰራው ጳጳስ ኃጢአት ኃጢአት ነው። ጽሁፉን ካነበብከው እኮ የተሀድሶነት ስሞ ባልተወራበት ገጠር ላይ ነው የኢህአፓውን ታጋይ መነኮሳት ሊደፍሩት የነበረው። ደግሜ ልንገርህ የኔ አቋም ኃጢአትን ኃጢአት ማለት ነው። ያንተም አቋም ይህ ከሆነ የሚያጋጨን ነገር የለም። ካልሆነ ደግሞ ግለጠው እና እንነጋገር እስክንግባባ ድረስ ምላሽ ለመስጠት አልሰንፍም።

Anonymous
November 29, 2014 at 5:44 AM

"ሰውየው አሁንም እደግምልሀለሁ። ፓስተሩም ሰራው ዲያቁኑ ኃጢአት ኃጢአት ነው።" ዋው እንዴት አይነት እውቀት ነው ባክሀ? ልክ እኮ ኃጢአት አይደለም የተባለ ይመስል ባልተባለ ጉዳይ ላይ ታወራለህ:: የሌለ ክርክር ለፍጠር ትላለህ:: ይልቅ ያልተባልከውን ትተህ የተጠየከውን ሳትዘላብድ መልስ:: አንተ አይደለህ እንዴ ትናንት ጳጳሱን ሰዶማዊ ብለህ የጻፈውከው!! ታድያ ለምንድን ነው ዲያቆኑን ስመ ገናና ብለህ የምታልፈው? ጳጳሱን በየትኛው ማስረጃህ ነው ስም ጠርተህ የከሰስከው? ይህኛው ተሃድሶ ስለሆነ ነው?

Anonymous
November 29, 2014 at 11:16 PM

በመጀመሪያ እኔ የብሎጉ አዘጋጅ አይደለሁም እንደ አንተ አስተያየት ሰጪ ብቻ ነኝ። ስለዚህ ምን ገዶኝ የዲያቆኑን ስም እደብቅሀለሁ? በዚህ ብሎግ ጳጳሱ ግብረ ሰዶማዊ መባላቸውን አንብቤያለሁ ዲያቆንም ይሁን ጳጳስ ንስሀ አልገባ እና አልመለስ ካለ ሌሎች እንዲጠነቀቁ ሲባል ስሙ ተጠቅሶ ተጠበቁ በመባሉ እስማማለሁ። በበኩሌ ስለ ጳጳሱ የቀረበው ማስረጃ በጣም አሳማኝ እንደነበር አውቃለሁ። የተጻፈው ጽሁፍ በግልጥ አስቀምጦታልና። ዲያቆኑም ተሀድሶ ሆነ አልሆነ ሰዶማዊ ከሆነ ሰዶማዊ ነው ተብሎ ተገልጦ ሊጻፍበት ይገባል እላለሁ። ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች አሸናፊ መኮንን መሆኑን እኮ ገልጠውልሀል። በርግጥ ስለዚህ ሰው ብዙ መደነቅ የነበረን ሰዎች ሁሉ ባለፉት ጥቂት ወራት ድንጋጤ መትቶናል። እሱም ይሁን መጽሀፎቹ ግን ከእግዚአብሔር እውነት ስለማይበልጡ በግልጥ ቢጻፍበት ቅር አይለኝም። ብትመለስ ተመለስ ባትመለስ አፈር ልበስ ይላሉ የአገርህ ሰዎች ጌታም "እናንተም ንስሀ ባትገቡ እንዲሁ ትጠፋላችሁ" ብሏል። አጅሬውም ለመካሪ ያስቸገረ ወዳጆቹን ያስመረረ ሀኬተኛ ሰው መሆኑን በበቂ ሁኔታ ስላወኩ እያዘንኩም እያፈርኩም ሰዎች ከሱ እንዲለዩ በሰዶማዊ ምግባሩም እንዳይታለለሁ እመክራለሁ። ይህን የምለው ግን አንተን ደስ እንዲልህ አይደለም ሰውየውን ማዳን ካልቻልክ በዙሪያው የተከማቹትንና ሊከማቹ የሚችሉትን መጠበቅ ክርስቲያናዊ ግዴታ ስለሆነ ነው። እህሳ እንቀጥል?

Anonymous
November 30, 2014 at 9:19 PM

yekazanchisu debtera ashenafi mekonnen sedomawinetu eko zare yejemere aydelem gena duro sebeta abron sale yeminawekiwe new.

Anonymous
December 1, 2014 at 2:07 AM

እኔ ደሞ የጳጳሱ ስም ማጥፋት እንደሆነ ባየሁት ማስረጃ መሰረት እርግጠኛ ነኝ። የናንተ ስም ማጥፋት ነበረችና። በተረፈ ማስረጃ እስካለህ ድረስ ከስምምነት ማጥፋት ወጥተህ የጳጳሱን ስም እንደጠራህ ሁሉ የሱንም(የዲያቆን ተብዬ ጴንጤውንም) ስም ሳትሳቀቅ ጥራው። የብሎጉ ፀሃፊ አይደለሁምን ጨዋታ ተዋት።
በአጠቃላይ ማንኛውም ሃጢያት ያንተ ፓስተሮችና የሃገር ልጆች ሲያደርጉት ጽድቅ ሌሎች ሲያደርጉት ኃጢአት የሚሆንበት ምክንያት የለም። ማንም ያድርገው ማንም ሃጥያት ነው። ይሄ የሚያነጋግር ጉዳይ አይመስለኝም። ሁልጊዜም ነገሮችን በሁለት ሚዛን አትመዝን ነው ቁምነገሩ። ትቀጥል ታዲያ?

December 1, 2014 at 6:35 AM

ደጀ ብርሃን መካነ ጦማር በራሷ ስምና መለያ ምልክት ስም መልስ ይሁን አስተያየት ትሰጣለች። ከዚህ በላይ በተደረጉት ምልልሶች ውስጥ አልተሳተፈችም። የአስተያየት ምልልሶችን ተመልክተን ይህንን ለማስረዳት ወደድን።
ስለግብረ ሰዶም ክፉ አሠራር ስንናገር ዋናው ዓላማችን የግለሰቦችን ኃጢአት ለማውጣት ሳይሆን የችግሩን አሳሳቢነት በማሳየት፤ ራሳቸውን ደብቀው ድርጊቱን የሚያስፋፉትን ቢቻል አስቀድሞ በንስሐ እንዲመለሱ በግል ማሳሰብ፤ ካልተቻለም ያልታወቀባቸው መስለው በተግባራቸው እንዳይቀጥሉ ለሌሎች ለማስገንዘብ ሲባል መሆኑን መታወቅ አለበት። «የጳጳሱን አውጥተህ የዲያቆኑን ተውከው» የሚለው አባባል ከመረጃውና ከድርጊቱ እውነተኛነት ጋር ሳይሆን «እኔ ያልኩት ለምን ቀረ?» የሚል ቁጭት የወለደው ስሜት ይመስላል። ስለጳጳሱ የወጣው ድርጊት ከተጠቂዎቹ ጋር በተደረገ ንግግርና ጉዳዩን በቅርብ በሚያውቁ ሰዎች ማስረጃነት የተረጋገጠ እንጂ በስሚ ስሚ አይደለም። ለዚያውም ነገሩ በደል በደረሰባቸው ሰዎች በኩል የተረጋገጠ እውነት ቢሆንም ለቤተ ክርስቲያን ክብር ሲባል ብቻ ያወጣነውን ጽሁፍ ከመካነ ጦማራችን ላይ አንስተነዋል። ስለዲያቆን አሸናፊ የሚወራውን ነገር ከወሬ ባለፈ የሰውም፤ የሰነድም፤ የተበዳይም ማስረጃም ይሁን መረጃ አላገኘንም። ስለዚህ ወሬ ብቻውን እውነት ስለማይሆን በመረጃ የተደገፈ ጽሁፍ ከደረሰን ቅድሚያ ግለሰቡ ንስሐ እንዲገባና ድርጊቱን እንዲተው እድል በመስጠት፤ ተመክሮ ካልተመለሰ ሌሎች እንዲጠነቀቁት ለብዙዎች መዳን ሲባል ለማውጣት ዝግጁዎች ነን። መሰረታዊ ዓላማችንም ማሳሰብ፤ ማስተማርና ማስጠንቀቅ ስለሆነ ለዚህ ግዴታ ምን ጊዜም ተግተን እንሰራለን።
በቅርቡ በናይጄሪያ ራቁታቸውን ያጎነበሱ የአንስት መቀመጫ ይስማል ስለተባለው ፓስተር ያገኘነው መረጃ የተሟላ ስላልሆነ በወሬነቱ አልፈነዋል። ማን የሚባል ፓስተር? በየትኛው የናይጄሪያ ከተማ ባለች ቤተ ክርስቲያን? መቼ? ለሚለው ነጥብ ምንም መረጃ አይሰጥም። ስለዚህ ለወደፊትም ወሬንና መረጃን ለይተን እንወቅ!

Anonymous
December 3, 2014 at 9:45 AM

ledeje birhane
if u r honest enough and did what you wrote, you will get full document about ashenafi mekonnen soon. he is a sodomy and he believe it for several people he is sodomy. then he change his mind and fight for survival. does he survive by talking lies to his friends and fellow peoples? we will see.

Anonymous
December 3, 2014 at 3:48 PM

ሃሃ ይቺ ጨዋታህ እኮ ናት የምትገርመኝ። አንተ የሰውን አስተያየት ቆርጠህና የራስህን ጨምረህ ያወጣህ ሰው እኮ ነህ። አለማውጣት እየቻልክ። ልክ ስለ አፍ መክፈት የፃፍኩልህን እንዳላወጣኸው ማለት ነው። እና እኔ አይደለሁም ብለህ ለምን እንደምትደክም እኮ ነው የሚገርመኝ።
የጳጳሱን ሰረዝከውም አልሰረዝከውም ስም ማጥፋት እንደሆነ በደንብ ታውቀዋለህ። ሆነ ብለህ ያደረከው አይደል እንዴ? ካለበለዚያማ ለተሃድሶው የስራ ባልደረባህ የሰጠኸውን ላይሆን ይችላል መጠራጠርን እኩል ትጠቀም ነበር። (መቼም አንሶላ አጋፍፌአለሁ አትልም)
የድርጊቱን ሃጢያትነት የካደ ሰው እስከሌለ ድረስ ስለ ሃጥያትነቱ ማውራት ጉንጭ አልፋ ነው የሚሆነውና ትኩረትህን መጀመሪያ ወደራስህ የእምነት ድርጅት መልሰህ እየው። ከዛ እኛም እኛም ጋር እኮ እንደዚህ አለ እንልሃለን። ካለዛ ስለተከፈለህ ብቻ ወሬህን እንዳወራህ ትኖራለህ።

Anonymous
December 3, 2014 at 3:49 PM

ሃሃ ይቺ ጨዋታህ እኮ ናት የምትገርመኝ። አንተ የሰውን አስተያየት ቆርጠህና የራስህን ጨምረህ ያወጣህ ሰው እኮ ነህ። አለማውጣት እየቻልክ። ልክ ስለ አፍ መክፈት የፃፍኩልህን እንዳላወጣኸው ማለት ነው። እና እኔ አይደለሁም ብለህ ለምን እንደምትደክም እኮ ነው የሚገርመኝ።
የጳጳሱን ሰረዝከውም አልሰረዝከውም ስም ማጥፋት እንደሆነ በደንብ ታውቀዋለህ። ሆነ ብለህ ያደረከው አይደል እንዴ? ካለበለዚያማ ለተሃድሶው የስራ ባልደረባህ የሰጠኸውን ላይሆን ይችላል መጠራጠርን እኩል ትጠቀም ነበር። (መቼም አንሶላ አጋፍፌአለሁ አትልም)
የድርጊቱን ሃጢያትነት የካደ ሰው እስከሌለ ድረስ ስለ ሃጥያትነቱ ማውራት ጉንጭ አልፋ ነው የሚሆነውና ትኩረትህን መጀመሪያ ወደራስህ የእምነት ድርጅት መልሰህ እየው። ከዛ እኛም እኛም ጋር እኮ እንደዚህ አለ እንልሃለን። ካለዛ ስለተከፈለህ ብቻ ወሬህን እንዳወራህ ትኖራለህ።

Anonymous
December 5, 2014 at 9:09 PM

አንተ ታማኝ ስላልሆንክ ሌላውንም አታምንም። የብሎጉ አዘጋጅ እደለሁም ያልኩህ ስላልሆንኩ ነው። ያንተ ያልካቸውን ፓስተሮች እኔ አላውቃቸውምም።ባይደንቅህ ላውቃቸውም አልፈልግም። እኔ የክርስቶስ ወንጌል አገልጋይ ነኝ እንጂ የእገሌ ማኅበር አሊያም ፓስተር አገልጋይ አይደለሁም። በቤተክርስቲያኔ በኦርቶዶክሳዊቷ የኢየሱስ ክብር ሲልቅ ማየት የምፈልግ ሰው ነኝ። በተረፈ ዲያቆኑ የኢየሱስ ወንጌል አገልጋይ ከሆነ አከብረዋለሁ። የኢየሱስ ወንጌልን ትቶ ሰዶም ከትሞ ራሱን የሚያገለግል ከሆነ ደግሞ እቃወመዋለሁ። ወደ ሰዶም የጨው አምድ የሆኑ ዘመዶቹን ጥየቃ ከሄደ እኮ በቃ አከተመ ተለያየን። ብሎጉ የኔ ቢሆን አሳይህ ነበር። ለጳጳሱ እንደተጳፈው ያለ አሳማኝ መረጃ ጠቅሼ እከትብልህ ነበር። ከኃጢአቱ ንስሀ ገብቶ አልመለስ ላላ ፋናኝ የዲያቢሎስ አገልጋይ ተሀድሶ ሆነ ማኅበረ ቅዱሳን ዲያቆን አሸናፊ ሆነ አባ እገሌ ህዝቡን ተጠበቁ ለማለት አልሰንፍም። ለማንኛውም እኔና አንተ ለምን አብረን ብሎግ አንጀምርም? ሀሳቦቻችንን በነጻነት እየገለጥን እንጻጻፍ። አንተም ዘመዶችህ ያስጠጉህ አልመሰለኝም

Anonymous
December 6, 2014 at 7:27 PM

አይ ጴንጤው በቃ ውሸትህ ራስህን አሳምኖሃል አይደል? የትኛው መታመንህ? ኸረ አታስቀኝ።
የሁለት ደሞዝ ነገር ሆኖብህ አይታይህም እንጂ ቤተክርስቲያኔማ አንተና ዘመዶችህ የምትንቁትን ኢየሱስ ታከብረዋለች። እኔን ለሁለት ደሞዝ መመልመልህ ከሆነ ከንቱ ድካም ይሆነብሃልና አትለፋ። ለምን ከዘመዶችህ ጋር አዳራሽህ ውስጥ አትጨፍርም።

Anonymous
December 6, 2014 at 7:27 PM

አይ ጴንጤው በቃ ውሸትህ ራስህን አሳምኖሃል አይደል? የትኛው መታመንህ? ኸረ አታስቀኝ።
የሁለት ደሞዝ ነገር ሆኖብህ አይታይህም እንጂ ቤተክርስቲያኔማ አንተና ዘመዶችህ የምትንቁትን ኢየሱስ ታከብረዋለች። እኔን ለሁለት ደሞዝ መመልመልህ ከሆነ ከንቱ ድካም ይሆነብሃልና አትለፋ። ለምን ከዘመዶችህ ጋር አዳራሽህ ውስጥ አትጨፍርም።

Anonymous
December 7, 2014 at 1:17 AM

To the blog organizers of Deje Birhan:
If your goal is to raise awareness for people about this issue and you said you don't post without hard evidence, what was the need of mentioning of “ስመ ገናና” አገልጋይ prior to getting that hard evidence? Have you thought about what this article can do if it strays people away from hearing the Word of God? Jesus said in Mark 9:42 በእኔም ከሚያምኑት ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለው ነበር። God has touched so many lives through the teachings of Deacon Ashenafi, there is no need to look far - search for his name on Google, and you will find the evidence of that. This is the devil's work and its obvious 2 Corinthians 2:11 በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና። I hope and pray you will think twice before posting this kind of information in the future and stray people in the wrong direction, amen.

Anonymous
December 8, 2014 at 9:36 PM

ለእርስዎ
ለዲያቆን አሸናፊ ያለዎትን አድናቆት ጥሩ ነው። ግን ለስሜትዎ ወይም ደግሞ ለሰውየው ላሎት አክብሮት ከመቆምዎት በፊት ነገሩን በእግዚአብሔር ቃልና በማስተዋል ቢመዝኑት ጥሩ ነበር። ለምን ይመስልዎትዋል ዲያቆኑ ይመራው ከነበረው ሚኒስትሪ ግማሽ ያህሉ ሰው ለቆ የወጣው?
ለምን ይመስልዎታል እሱ "ካገለገላቸው" ልጆች መካከል የተወሰኑትየግብረ ሰዶም ድርጊት ሰለባ ነን እያሉ ያሉት?
ለምን ይመስልዎታል ከሚኒስትሪው መስራች አባላት መካከል የተወሰኑት ግብረ ሰዶማዊ ስለሆነ መስራችነቱን ትተናል ብለው ከሚኒሰትሪው ለመንግስት አሳውቀው የለቀቁት?
ለምን ይመስልዎታል በተሀድሶ አገልግሎት ዙሪያ ያሉ ሰዎች ሁሉ ሊያገኙት ሲፈልጉ እምቢ ብሎ የተደበቀው?
ለምን ለምን ለምን?
አንድ ነገር ልንገርዎት እኔ የዚህ አስተያየት ጸሀፊ ደግሞ አሸናፊ ግብረ ሰዶማዊ ለመሆኑ 100 % እረግጠኛ ነኝ።
ሰውን ለማሰናከል ሳይሆን ለመታደግ የሱን ድርጊት በዝርዝር መግለጥ የግድ ይላል። ያኔ ሲገለጥ ወይጉድ ይሉና አርፈው ይቀመጣሉ። ግን አገልጋይ ቢሳሳት ጌታ አይሳሳትም። የክብሩን ወንጌል ለስጋ ጥቅም የሚሸቅሉትን ሁሉ ጌታ በጊዜው ጊዜ ይገልጠዋል።
ክርክሩን ትተው ንስሀ እንዲገባ ቢመክሩት ጥሩ ነው።

Anonymous
December 9, 2014 at 8:36 AM

በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና
ለዚህ እኮ ነው አሸናፊ የሰይጣን መሳሪያሆኖ ብዞዎችን እያሳተ መሆኑን እና በግብረ ሰዶም ሀጢአት እየበከለ ስለሆነ ከሰይጣን ሀሳብ ተጠበቁ ማለት ያስፈለገው። ኢየሱስን ተከልሎ በተለወጠ አእምሮ በሻገተ መንፈስ እውነተኛውን መንፈስ ማገልገል አይቻልም።
አሸናፊ ሰዶማዊ ነው እንዲድን እርዱት ካልፈለገ ደግሞክርስትናን ለክርስቲያኖች ትቶ የሰይጣንን መቅደስ ሰርቶ ከተከታዮቹ ጋር ያደንክር። አሁንም ለነገሩ አልመለስ ካለ ያው የሰይጣን መቅደስ ነው።

Anonymous
December 10, 2014 at 2:09 PM

ato ashenafi mekonen yemibalo tabot zare ``yikeberalu``. ATO ashenafi bzare elet gebersedomawiyanena sdnakiwocachewen sebesebe yeledet bealacewen liyakebru defa kena eyal;u new yimiyasazenaewe yaderebachwe yegeberesedome menfese lneseha alatega belowachewe baltetochenena almeawi menfes yaderebachewen sewoch sebsebewe ersachwen lemasemesegen ena yeamarega yekene fukera liyademtu zegeju nachew. wey sedomawinet.

Anonymous
December 16, 2014 at 9:13 AM

hahahahaha it is true. he is really tabot. i am so soory for those people who follow him.

Post a Comment

አስተያየቶች

 
Support : | |
Copyright © 2011. ደጀ ብርሃን dejebirhan - All Rights Reserved

Proudly powered by Blogger