የፓትርያሪክ
ጳውሎስ ሞት ከአወዛጋቢነት አልፎ አስደንጋጭ ዜና እየተሰሙ ነው። ፓትሪያሪኩ ህይወታቸው ለህልፈት እስከተዳረገች
ዕለት ድረስ በተለይ የዕለቱ ውሎአቸው እስከ ሥርዓተ ቁርባን ድረስ ምንም ዓይነት ችግርና እንዲሁም የድካም መንፈስ
ያልታየባቸውና ያልተስተዋለባቸው ሲሆኑ “ቅዱስ” ቁርባኑን ከወሰዱበት ቅጽበት ጀምሮ ግን በሰውነታቸውን ላይ የመዛል፣ በሚታይ የሰውነት ክፍላቸውም በላብ የመጠመቅ ዓይነት ምልክት እንደታየባቸው በትናት ዕለት ካነጋገርኳቸው በዕለቱ አብሮአቸው ቤተ- መቅደስ ውስጥ ነበሩ ከተባሉ ካህናት ተጨባጭ ምስክርነት ለማግኘት ተችለዋል።
በሁኔታው
ግራ የተጋቡ የዓይን ምስክሮች ጨምረው እንዳወሱልኝም ከሥርዓተ ቁርባኑም ሆነ ከዚያ በፊት የነብሩ ቀናት ፓትሪያሪኩ
እንደ ወትሮ የዕለተ ዕለት ግዴታዎቻቸውን በሚገባ ሲያከናውኑ እንደሰነበቱና ምንም ዓይነት ለሞት ሊዳርግ የሚያስችል
ዓይነት ሕመም እንዳልነበራቸውም ለማወቅ ተችለዋል። ታድያ ገዳያቸው ማን ሊሆን ይችላል? ቤተ- ክርስቲያን
እነሆ ደመ ክርስቶስ ብላ ለስዎች ልጆች ሕብረት በምታቀርበው በጽዋ ላይ ገዳይ መርዝ ጨምሮ ጭቃኔ በተሞላበት
አረመንያዊ ድርጊት የሰው ነፍስ ለህልፈት ዳርጎ ሲያበቃ ተጠቃሚ የሚሆነው ማን ሊሆን ይችላል? የቤተ- ክርስቲያኒቱ አባቶችና ሊቃውንት መምህራን በመግደልስ የጥቅም መርበቡን በቤተ- ክርስቲያን ላይ የመዘርጋትና እውን የማድረግ ዓላማ አነግቦ የተነሳ ነፍሰ ገዳይ ማን ይሆን? ለሚሉና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎች በሰፊውና በተጠናከረ መልኩ ሳምንት እመለስበታለሁ።
በዛሬው ዕለት ግን ህልፈተ ሥጋ ፓትርያሪክ ጳውሎስ ተከትሎ በብዙሐን ዘንድ አነጋጋሪ ከሆኑት ርዕሰ ጉዳዮች መካከል በቀዳሚነት እያነጋገረ የሚገኘውን የፕትርክና መንበሩ/መቀመጫው ማን ይተካው? የሚለው ጥያቄ ዙሪያ ላይ አጭር መልስ/መፍትሔ
ለመጠቆም ነው። ስህትት በስህተት ለማረም ወይንም ደግሞ ለማስተካከል እንደማይቻል ከሌላው በተሻለ ኢትዮጵያውያን
ብዙ ማለት እንደምንችል አመናለሁ። ይኸውም ስህተትን በስህተት ለማስተካከበል በሞከርናቸው ዘመናት ሁሉ እርምጃዎቻችን
ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው አመዝኖ ዛሬ ምድራችንም ሆነ ሕዝባችን የሚገኝበት አሳፋሪ ገጽታና የተመሰቃቀለ ህይወት
ማየቱ በቂ ማስረጃ ነው ብዬ አምናለሁ።
እዚህ ላይ አጽንዖት ሰጥቼ ለማስተላለፍ የምወደው መልዕክት ቢኖር ቤተ- ክርስቲያን
በተለይ በሀገር ውስጥ የሚገኘውን ሲኖዶስ ከቀድሞ ስህተት ይልቅ የባሰ ስህተት እንዳይሰራ ከወዲሁ እርምጃዎችን
ይመረምር ዘንድ ነው የሚጠየቀው። ፓትሪያሪክ ጳውሎስ አልፈዋልና አዲስ መሾም ያስፈልጋል በማለት በጥድፍያ የሚሆን
ነገር እንደሌለ በመገንዘብ በተለይ በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች መካከል የተጀመረውን የዕርቀ ሰላም አጀንዳ
በሁለቱም አካላት በጎ ተነሻሽነት በአስቸኳይ ፋይሉን በመክፈት ቤተ -ክርስቲያኒቱ
አንድ የምትሆበትና ወደ ቀድሞ አንድነትዋ የምትመለስበት እንዲሁም የቀድሞ ፓትሪያሪክ ወደ መንበራቸው የሚመለሱበት
መንገድ በርትቶና ተግቶ መስራት እንደሚጠበቅበት ነው የማምነው። ይህን አይነቱ እርምጃ ደግሞ ከየትኛውም አቅጣጫ
ለማየት ቢሞከር ሀገራዊም ሆነ መንፈሳዊ ጠቀሜታውም የጎላ ነው።
በተጨማሪም የመንፈሳዊያን መሪዎችም ሆነ የቤተ- ክርስቲያን አጀንዳ ሰላምና ሰላም እስከሆነ ድረስ ለዓመታት የዘለቀውን ቀውስና ትርምስ መግታትና ማስቆም የሚቻለው መንበሩ ከፖትሪያርክ መርቆርዮስ አልፎ ለማንም ሊሆን እንደማይችልና እንደማይገባ በማመን ፓትሪያሪክ መርቆሪያስ ወደ ቀድሞ መቀመጫቸው ለመመልስ በሚሳየው በጎ ተነሳሽነት ነው። ይህም የምለው ያለ ምክንያት አይደለም። በቤተ- ክርስቲያኒቱ ጉዳይ ላይ የሚመለከተውም የማይመለከተውም አፉን በከፈተ ቁጥር ለዚህ ሁሉ ዕንቅፋትና መሰናክል መዋቹ ፓትሪያሪክ ጳውሎስ ብቸኛ ተጠያቂ ያደርግ እንደነበረ ማናችንም አንስተውም። ታድያ አሁን ማንን ተጠያቂ ልናደርግ ነው? በህይወት ባሉ ፓትሪያሪክ ላይ ፓትሪያሪክ ለመሾም አይደለም ሊሞከር ፈጽሞ ሊታሰብም አይገባውም። ፓትርያሪክ መርቆሪዮስ ወደ መንበራቸው ይመለሱ!
መቀመጫው አሜሪካ ላያደረገ የአበው ጉባኤ (ሲኖዶስ):
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሆይ! ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕ 12 :17 “በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ። ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።“ ሲል
እንደ ጻፈላቸው ዛሬ ደግሞ እኛ ባለተራዎች በእኩል ኃይል ሥልጣንና መንፈስ ቃሉ ከፍ ባለ ድምጽ ሰላምን እናወርድ
ዘንድ አፍ አውጥቶ እየጮኸ ይገኛል። ሳሙኤል ገና ብላቴና በነበረበት ዘመን እግዚአብሔር በስሙ ይጠራው ነበር።
ሳሙኤልም ገና የእግዚአብሔር ድምጽ ለይቶ ካለማወቁ የተነሳ እግዚአብሔር በጠራው ቁጥር ብድግ እያለ ወደ ኤሊ በመሄድ
“እነሆ የጠራኸኝ” ይለው ነበር። ታድያ ከዕለታት አንድ ቀን ነገሩ የገባው ሊቀ ካህን ሳሙኤልን “ሄደህ ተኛ ቢጠራህም አቤቱ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር በለው“ በማለት አሰናብቶታል።