ከወደ ጠቅላይ ቤተክህነት አካባቢ ሰሞኑን «ጉባዔ
አርድእት» የሚባል ጊዜያዊ ማኅበር ይቋቋማልን እንደማንኛውም ሰው ሰምተናል። እኛን ግራ የገባን ይህ «ጉባዔ አርድእት« የተባለው
መቋቋሙ ሳይሆን ከተቋቋመ 20 ዓመቴን ሞልቻለሁ የሚለው ጎረምሳው ማኅበር ማቅ ግን ሽብር የገባበት ምክንያት አስገራሚ መሆኑ ነው።
ሁለት ነገር እንድናነሳ ተገደድን። አንደኛ ማኅበሩ ከእኔ ወዲያ ሌላ ማኅበር አያስፈግም የሚል የጽንፈኝነት ጥግን የታጠቀና በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በእኔ በኩል ያላለፈ
መንፈስ ቅዱስ እንዴት እዚያ ይደርሳል? ስለዚህ እፍ! ያላልኩበት ማኅበር ሊኖር አይችልም የሚል ስግብግብነት የሞላው ጠባብ አስተሳሰቡ ነው።
በአንድ በኩል የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት እና
የቅድስት ሥላሴ ኰሌጅ ደቀመዛሙርት ማኅበራት መኖራቸውን እደግፋለሁ ሲል እየተደመጠ በሌላ በኩል ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንትና
አመራር ላይ ያሉ ሰዎች ስብስብ እንደሆነ የሚነገርለት «ጉባዔ አርድእት» መቋቋምን ስመለከት ዓይኔ ደም ይለብሳል ዓይነት ቅናት ከሰይጣን እንጂ ከመንፈስ ቅዱስ ሊሆን አይችልም።
ይህ ይቋቋማል የሚባለው የጉባዔ አርድእት ማኅበር
አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በሥራ ላይ ያሉ የቤተክርስቲያኒቱ ሰዎች
እስከሆኑ ድረስ ማኅበረ ቅዱሳንን ይህን ያህል ያስጨነቀው ለምንድነው? ቤተክርስቲያኒቱን
ይጥቀምም፤ አይጥቀምም ራሱ ማቅ እንደ ማኅበር የተቋቋመበትን መንገድ
ሌሎች የዚሁ መብት ተጠቃሚ የመሆን መብት እንዳይኖራቸው መጮሁስ ምን
ይባላል?
ማንም የሾመው ባይኖርም« ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ
ነው እንዲሉ» ራሱን በራሱ ሾሞ ከጉባዔ አርድእት አባላት መካከል
አንዳንዶቹን በተሐድሶነት ይወነጅላል። በተለመደ የድራማው ትወና አፈኞቹን ጉዳይ ፈጻሚዎቹን በደንብ ጭኖና አስፈራርቶ እነዚያ የሚወነጅላቸውን
ሰዎች በቀጣይ ጉባዔ እስኪያስወግዝ ድረስ የቤተክርስቲያኒቱ አባላት መሆናቸውን አምኖ መቀበል የግድ ይሆናል። ስለዚህ ጉዳይ ፈጻሚ
አባቶቹ የማኅበሩን ተልእኰ ተቀብለው ውግዘት እስኪያወርዱ ድረስ በሥራ ላይ ያሉ ሰዎች የቤተክርስቲያኒቱ አባላት ናቸውና
ማቅ ማኅበር ሆኖ እንደሚንቀሳቀሰው ሰዎቹንም ማኅበር እንዳያቋቁሙ የሚከለክላቸው ምንም አሳማኝ ነገር የለም።
ይልቁንም ማኅበርሩን እንደዚህ ሽብር ውስጥ የከተተውን ነገር ከማኅበሩ ግልጽና ስውር ዓላማ አንጻር ከታች የተመለከቱትን ነጥቦች ማንሳት እንችላለን።
1/
ጉባዔ አርድእት በቤተክርስቲያን ሙያ የበለጸጉ ምሁራንና በዘመናዊውም የበሰሉ ሰዎች ስብስብ እንጂ እንደ ማቅ አባላት የክብር ቅስና ያልተሸከሙና የንግድ ግዛት /ኢምፓየር/ ያላቋቋሙ በመሆናቸው፤
2/
የጉባዔ አርድእት አባላት ናቸው ተብለው የሚነገርላቸው ሰዎች አብዛኛዎቹ በቤተክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ የሚገኙና በሰንበት ት/ቤት ሽፋን አንድ እግራቸውን እንደማቅ ውጪ ያላደረጉ ስለሆነ፤
3/
በዚሁ በአዲሱ ማኅበር ውስጥ ይካተታሉ የሚባሉት ሰዎች አብዛኛዎቹን ማቅ ሲወጋቸውና ሲያደማቸው የቆዩ በመሆናቸው ውሎ አድሮ የእጄ ይከፈለኛል የሚል ፍርሃት ማቅን ስለሚያስጨንቀው፤
4/
በማኅበረ ካህናቱ ዘንድ «ማቅ፤ ጢም የሌለው አልቃኢዳ» እየተባለ መጠራቱ የሚታወቅ ሲሆን ጉባዔ አርድእት ህልው ሆኖ ከተቋቋመ በአባልነት ይሁን በተሳታፊነት ማኅበረ ካህናቱን ሁሉ ስለሚጠቀልል መንቀሳቀሻ ስፍራ ያሳጡኛል የሚል ስጋት፤
5/
በሕዝብና በመንግሥት ዘንድ አስቸጋሪነቴ ግልጽ ይወጣል ከሚል ፍርሃት፣
6/
ተሐድሶ ወይም ጴንጤ እያልኩ የዓይኑ ቀለም ያላማረውንና ለእኔ ያልተንበረከከውን ሁሉ ለማድቀቅ ይቸግረኛል ከሚል እሳቤ የተነሳ፤
7/
የታዛዦቼን ሊቃነ ጳጳሳት ቅስም በመስበርና በማስፈራራት ለአቡነ ጳውሎስ እንዲገዙ በማድረግ የሲኖዶስ ላይ ስውር ድምጼ ይታፈናል፤ አባ ጳውሎስም ጉባዔ አርድእትን እንደአንድ ኃይል ሊጠቀሙት ይችላሉ ብሎ በመስጋት፤
8/
አሁን ያለኝ እንቅስቃሴ ከጫፍ እጫፍ መድረሱ እክል ሊገጥመው ይችላል ብሎ ለእጀ ረጅምነቱ ከመጨነቅ አንጻር ሲሆን
ከብዙ በአጭሩ ሊነሳ የሚችል ውጥረቶቹ እንደሆኑ
እነዚህን ልንገምት እንችላለን። እንዲያውም ከግምት በዘለለ የማኅበሩ አፈቀላጤ የሆነው «ደጀ ሰላም» ማቅ ይደርስብኛል ብሎ ከሚያስበው
አንዱን ስጋት እንዲህ ሲል ተናግሯል።
«የአባ ጳውሎስን
ዐምባገነንት ለማጠናከር፣ መንፈሳውያን ማኅበራትን ለማፈራረስ፣ የግል እና የቡድን ጥቅሞቹን ለማስጠበቅ….» በማለት
በግልጽ አስቀምጧል።