ባለቤቴን አፈቅረዋለሁ ትዳራችንም ፅኑ ነው !!


ከዚህ በፊት ስለተከስተ ጌትነት የአሜሪካው አማርኛ ድምጽ አየር ላይ ካዋለው መረጃ ተነስተን ዐመጻውን በንስሐ እንዲተው የሚያሳስብ ዘገባ አውጥተን ነበር። በንስሐ ስለመመለሱ እየተናገረ ባለበት ሁኔታ የባለቤቱን ጽናትና ያላትን የይቅርታ ልብ ተመልክተን ወደፍቺና የግድያ ተግባር ላለመሄድ የተጓዘችበትን የክርስትና አርአያነት «አሌክስ አብርሃም» የዘገበውን ልናስነብባችሁ ወደድን።
 


ባለቤቴን አፈቅረዋለሁ ትዳራችንም ፅኑ ነው !!
 (አሌክስ አብርሃም )

ይቅርታ መቸም እንደሚወራው ቀላል ነገር አይደለም !! በተለይም በባልና በሚስት ማሃል በአንድኛው ወገን ለትዳር አለመታመን ሲከሰት የተበደለው አጋር ይቅር ለማለት ይቸገራል …እንዲህ አይነቱ ነገር ሲከሰት ሚስት ባሏን በመፍለጫ …በተኛበት አቅምሳው እጇን ለመንግስት የሰጠችበት ዜና ሰምተናል ….ባልም በገጀራ ሚስቱን አመሳቅሎ ዘብጥያ የወረደባቸውን በርካታ ዜናዎች በቲቪ ተመልክተን አማትበናል ! የራሱ ጉዳይ ያሉም ትዳራቸውን በትነዋል !
ይህን ነገረ ካለነገር አላነሳሁትም …. በዚያ ሰሞን ከወደአሜሪካ የሰማነው ዜና የሚታወስ ነው …..ዘማሪ ተከስተ ጌትነት ሚስቴን አማግጦብኛል ያለ አንድ ሰው በየሚዲያዎቹ ቀርቦ ፍረዱኝ ሲል ሁላችንም ሰምተን ጉድ ጉድ ብለናል ! ማገጠች የተባለችውም ሴት በየሚዲያው እንዴት ካንድ አይሉ ሁለት ሶስት ጊዜ ወዳረፈበት ክፍል ጎራ እያለች ‹‹ሳትፈልግ ›› አብረው እንደተኙ በዝርዝር መግለፅዋ ይታወሳል ….ፓስተር ተከስተ ጌትነትም ይህንኑ አምኖ ይቅርታ መጠየቁ እንደዛው ..ሚዲያውም እስኪበቃው አናፍሶታል !ዘማሪ /ፓስተር ተከስተ በሚያገለግልበት ቤተክርስቲያንም አገልግሎቱን እንዳቆመ ተዘግቦ ነበር !!
ታዲያ ያኔ አገር ይያዝ ያለው ሚዲያ ለዚችኛዋ ዜና ጭጭ ማለቱ ስለገረመኝ …ያው ችግሩን ካወራን መጨረሻውስ ምን ሆነ የሚለውን ዝም ማለቱ ተገቢ አይደለም በሚል ይችን ፅሁፍ እነሆ አልኩ ……. ትላንት ‹‹የእውነት ቃል ጎስፕል ሚዲያ›› ‹‹የእንደገና አምላክ›› በሚል ርእስ እንደዘገበው ከሆነ ዘማሪ ጌትነት ባለፈው ቅዳሜ በምእመኑ ፊት ቁሞ ስለሁኔታው ምስክርነቱን ሰጥቷል … ባለቤቱ የምስራችም የሆነውን ሁሉ ይቅር እንዳለች በሚገልፅ አጭር ቃል እንዲህ ብላለች ‹‹ ባለቤቴን አፈቅረዋለሁ ትዳራችንም ፅኑ ነው ›› ፓስተር ጌትነትም ወደአገልግሎቱ ተመልሷል !! መቸስ ይቅርታ ጥሩ ነው … መልካም የትዳርና የአገልግሎት ጊዜ ይሁን እያልኩ ….ምንም እንኳን የመጀመሪያ ተጎጅዋ እርሷ ብትሆንም እንዲህ በችግር ጊዜ የራሷን ብሶት ትታ ከባሏ ጎን የምትቆም ሚስት ማግኘት መታደል ነው የሚል የግል አስተያየቴን ጨምሬ ላብቃ !!

Share this article :

+ የተሰጡ አስተያየቶች + 1 የተሰጡ አስተያየቶች

Anonymous
September 6, 2015 at 5:26 AM

እውነት ከሆነ የክርስቶስ ልብ አለን የሚለው ይሄ ነው።በተለይ ለአበሻውና ይቅርታ ምን እንደሆነ ላልገባው ትልቅ ትምህርት ሰጥተውናል እንዲህ ቢሆን ኖሮ ምነው ስንት ትዳር በዳነ ከዚህ የበለጠ እኮ የሚያፋታ ነገር አልነበረም ግን ነገሩ በእዚህ ሁኔታ መቆረጡ ሰፋ ያለ ትምህርት ብትሰጥበት እህታችን መልካም የተባረከች ሚስት ናት ልባምን ሚስት ማንያገኛታል የሚለው ይህንን ነው እናንተም ደጀሰላሞች ይህንን ማስነበባችሁ የጥፋትን ሳይሆን የልማትንም መንገድ በግልጽ ማሳየታችሁ ብሎጋችሁን ያስመዘግባል።ሰላም ሁኑ ለዘማሪ ተከሰተና ለምሥራችም እንኳን ደስ ያላችሁ ሰይጣን ስላፈረ በሉልኝ እውነትም የምሥራች ነሽ !!
ኒቆዲሞስ

Post a Comment

አስተያየቶች

 
Support : | |
Copyright © 2011. ደጀ ብርሃን dejebirhan - All Rights Reserved

Proudly powered by Blogger