Friday, July 20, 2012

የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ማኅበረ ቅዱሳን በስራዬ ጣልቃ እየገባ ስላስቸገረ አደብ ይያዝልኝ አለ

(ሐምሌ 13 2004 ዓ.ም. ፣አውደ ምህረት/www.awdemihret.blogspot.com)ማኅበረ ቅዱሳን በማን አለብኝነት ወዋቅራዊ አሰራርን በመጣስ በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሥራ ላይ ጣልቃ በመግባት በስሩ የሚገኙ ገዳማትንና አድባራትን ሰበካ ጉባኤ ስብሰባ እየጠራ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠውን ከሶስተኛ ወገን የሚገናኝበትን መመሪያ እየጣሰ ይገኛል ሲል የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት አስታወቀ፡፡ ለተጻፈው ደብዳቤ ( እዚህ ይጫኑ )
ይህ የመዋቅር ጥሰት አግባብ ያልሆነ ስለሆነ ሃገረ ስብከቱ “…ማኅበሩ በሃገረ ስብከታችን ጣልቃ እየገባ የሚያስተላልፋቸውን ጥሪዎችና የመዋቅር ጥሰቶች እንዲያቆም…”የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት አካሄዱን የሚያተካክልበት መመሪያ እንዲሰጥልን እናሳስባለን ብሏል፡፡
ከፅንሰቱ ጀምሮ አመጽ በቀል የሆነው ማኅበር እኔ ያልጣድኩት ድስት አያስፈልግም እያለ በተለያየ ሥራዎች ላይ ጣልቃ በመግባት ለቤተክርስቲን የሚጠቅም ሥራ ከመስራት ይልቅ የማኅበሩን ገጽታ በመገንባት ሥራ ላይ ተጠምዶ ይገኛል፡፡  ህዝብ ወደ እግዚአብሔር እውነት የሚደርስበትን መንገድ ከማመቻቸት ይልቅ ቤተክርስቲያን ያለህዝብም ቢሆን በማኅበሩ ቁጥጥር ሥር የምትውልበትን ስራ በመስራት ላይ ያለው ማኅበር ባልተፈቀደለት የስራ መስኮች እየገባ በማን አለብኝነት እየበጠበጠ ነው፡፡
ደፋሩ ማኅበር ለመምሪያዎች ከተለያዩ አካለት የሚመጡ በየስልጠና ጥሪዎችን መምሪያዎች ውስጥ ባሉ ሰዎቹ አማካኝነት ደብዳቤ እያስከፈተ መምሪያው ሳያውቅ በመምሪው ስም ስልጠናዎችን የማኅበሩ ሰዎች እንዲወስዱ እያስደረገ መሆኑ ሲታወቅ ከዚህ በፊት እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲከሰት ከማዘን ያለፈ ተቃውሞ ሳይሰማ ቀርቶ ነበር፡፡ ይህም የልብ ልብ እየሰጠው በሃገረ ስብከቶችና በአጠቃላይ በቤተክኅነቱ ስራዎች ላይ ጣልቃ በመግባት ማኅበረ ቅዱሳን ወይም ሞት ፉከራን እያሰማ ይገኛል፡፡
እንደ አንድ አለሌ ሽፍታ የተወሰኑ እበላ ባይ ጳጳሳትን ማስገበሩ የልብ ልብ እየተሰማው ምንስ ባደርግ ምን እሆናለሁ ያሻኝን ሰርቼ ወጥቼ እገባለሁ እያለ በአንድ መጠምሻ ጎረምሳ ስሜት የሚንቀሳቀስ ማኅበር መሆኑ ለቤተክርሰቲኒቱ አደጋ እየሆነ መምጣቱን ያሳያል፡፡
የቤተክርሰቲያንን ክፍተት ለመሙላትና አደጋዋን ለመቅረፍ በሚል አባባይ ቃል የታገዘው የማኅበሩ አካሄድ ግቡ ቤተክርስቲኒቱን በማኅበሩ መተዳደሪ ደንብ እንድትመራ ማድረግ ሲሆን ዶግማዋም ቀኖናዋም ማኅበሩ እንዲሆን የሚያስገድድ አካሄድ እየተከተለ መሆኑ የአደባባይ ሚሥጢር ሆኗል፡፡
የአንድ ተቋም ትክክለኛነት ከሚለካበት መንገድ አንዱ ህጋዊ መዋቅሮችን አክብሮ መንቀሳቀስ መቻሉ ነው፡፡ ያለ ሕጋዊ መዋቅር ህግ እና እውነት የበላይነት ይዘው መቀጠል የማይችሉ መሆናቸው እውነት ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ግን ህግ የት እንዳለ የሚያስታውሰው ሌሎችን ለመምቻ የሚጠቅመው ከሆነ ብቻ ነው፡፡ የማኅበሩን ፍላጎት ለማስጠበቅ  ግን እስካዋጣው ድረስ በህጋዊ አሰራር እሱም ካላዋጣ የወንጀል ድርጊቶችን ጨምሮ የትኛውንም ህገ ወጥ አካሄድ ለመጠቀም ወደ ኋላ የማይል ድርጅት መሆኑን እስካሁን ያሉት ተሞክሮዎቹ ያስረዳሉ፡፡