Sunday, July 1, 2012

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን፤ ተመራቂ ተማሪዎችን ማደሪያ ከለከሉ!

             
   የጽሑፍ ምንጭ፤ ዓውደ ምሕረት

በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን ከመመደባቸው በፊት ተማሪዎች ግቢውን መልቀቅ የለባቸውም የሚለውን መመሪያ ጥሰው ተማሪዎቹን ከግቢ አስወጡ፡፡ መነኮሳትን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ማደሪያ አጥተው እየተንከራተቱ ይገኛሉ፡፡ እስከአሁን ደረስ ባለው ሕግ መሰረት ተመራቂ ተማሪዎች ምደባ እስኪደረግላቸው ድረስ በኮሌጁ ውስጥ ማደር መብታቸው ነበር።ተማሪዎቹ ችግራቸውን ለቅዱስ ፓትርያርኩ ያስረዱ መሆናቸው ሲታወቅ እሳቸውም የኮሌጁ የበላይ ጠባቂ እንደመሆናቸው በቤታችሁ ማደር መብታችሁ ነው፡፡ መመሪያውን ማፍረስም አይቻልም ስለዚህ ሂዱ እቤታችሁ እደሩ ብለው ቢያዙም የኮሌጁ ዲን ግን ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡
   በርካታ መነኮሳት ያሉበት ተማሪች ማደሪያ አጥተው እየተንገላቱ መሆኑ የኮሌጁን ማህበረሰብ ጨምሮ በርካቶችን ያሳዘነ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ባለፈው ሐሙስ ምደባ እንደሚደረግ ተነግሮ የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ምደባው ለማክሰኞ መዞሩ በጠቅላይ ቤተክህንት ምክትል ሥራ አስኪያጅ በኩል ተነግሮዋቸዋል፡፡
ነገሩ ግራ የገባቸው ተማሪዎች መብታችን ተነክቷል በማለት ለፖሊስ ጣቢያ ያመለከቱ ሲሆን ፖሊሶች ችግሩን መፍታት ከተቻለ ብለው አቡነ ጢሞቲዎስን ለማነጋገር ቢሞክሩም አቡኑ ግን ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡
የኮሌጁ የአስተዳደር ዲን / አባ ሃይለ ማርያምን ችግሩ መፍትሔ ሊያገኝ የሚችልበትን መንገድ ካለ እንዲፈልጉ እንደ አስተዳደር ዲንነታቸውም አንድ ነገር ማድረግ የሚችሉ እንደሆነ ተጠይቀው የነበረ ሲሆን እሳቸውም ከአባ ጢሞቲዎስ ያልተሻለ ምላሽ ሰጥተዋል።መምህራንና  ሌሎች የኮሌጁ ሰራተኞች ከተማሪዎች ጎን ቢቆሙም አቡነ ጢሞቴውና አባ ሃይለማርያም ስላልተስማሙ ግን ተማሪዎቹ ማደሪያ በማጣት በመንገላታት ላይ ይገኛሉ።
ምክንያቱ ይህ ነው ብለው ባልጸገለጹበት ሁኔታ መመሪያንን ሸሮ ቤተክርስቲያን ባሳደገቻቸው ልጆችዋ ላይ ይህን ያህል መጨከንዋ አሳዛኝ መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡