Saturday, August 11, 2012

ብሎጋችንን ኢትዮጵያ ውስጥ አንዳትታይ መደረጉ አሁንም ቢሆን እውነት ነው፡፡


 የማቅን ውስጠ ምስጢር ፈልፍላ በማውጣት ከፍተኛ መደናገጥን በመፍጠር ላይ ያለችውን ዓውደ ምሕረት ብሎግ በኢትዮጵያውስጥ እንዳትታይ ከተደረገች ሳምንታት ተቆጥረዋል። አባ ሰላማ ብሎግ የችግሩን ግዝፈት በመጥቀስ በገጹ ካወጣው በኋላም ቢሆን  የዓውደ ምሕረት መዘጋት እስካሁን መፍትሄ አላገኘም። ይህንን ጉዳይ የማቅ ብሎጎች በሬ ወለደ ለማለት ጊዜ ባይፈጅባቸውም የአዘጋገባቸው ቃና ያስገነዘበን ነገር ቢኖር ለምን ድርግም ብላ አትቀርም የሚል ምኞትን ያረገዙ ይመስላል። ምክንያቱም በእውነት «ዓውደ ምሕረት» እንዳትታይ ከተደረገ ሳምንታትን ያስቀጠሩ ሆነው ሳለ ነገረ ስላቅን ማቅረብ የጠላት አሰራር ጥልቅ መሆኑን ያመላክታል። መረዳት የሚገባን ነገር ቢኖር «እውነት አናቷን ሲቀብሯት በጭራዋ ብቅ እንደምትል ማወቅን ለአፍታም መዘንጋት አይገባንም።

የዓውደ ምሕረት ዘገባ ከታች ቀርቧል።

ብሎጋችንን ኢትዮጵያ ውስጥ አንዳትታይ መደረጉ አሁንም ቢሆን እውነት ነው፡፡
የሀገር ውስጥ አንባቢያን አዲሱን አድራሻ www.awdemihret.wordpress.com ተጠቀሙ፡፡
(ነሐሴ 5 2004 .. ዐውደ ምሕረት/ www.awdemihret.blogspot.com / www.awdemihret.wordpress.com )  ብሎጋችን አውደ ምህረት በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳትታይ ከተደረገች ዛሬ ሁለት ሳምንት ሆናት፡፡ አድራሻችንን ማለትም www.awdemihret.blogspot.com ማንም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ሰው ለመክፈት ቢሞክር የሚያገኘው መልስ No data received Unable to load the webpage because the server sent no data.  የሚል ነው፡፡ ይህ ማለት በግልጽ አማርኛ ብሎጉ እንዳይከፈት ተደርጓል ማለት ነው፡፡ ይህንን እውነት አባ ሰላማ በመዘገብዋአቤት ውሸትሲል አንድ አድርገን ለመተቸት ሞክሯል፡፡ የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ እንደሚባለው ሳልዋሽ ቀኑ እንዳይመሽብኝ እያለች የምትሰጋው አንድ አድርገን የምትዋሽበት ጉዳይ ስታጣ ፍጥጥ ካለው እውነት ጋር መታገል ጀምራለች፡፡ ብሎጋችን ኢትዮጵያ ውስጥ አለመስራትዋን አሁንም ቢሆን ማንም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ሰው ሊያየው የሚችለው ሀቅ ነው፡፡
አንድ አድርገንብሎጉ ሳይዘጋ ተዘግቷል ይላሉስትል ጽፋለች፡፡ ማንም አንባቢ እንደሚያስተውለው ግን ብሎጋችን ተዘግቷል የተባለው ስለተዘጋ ነው፡፡ እኛ እንደእናንተ ልናገኝ የምንችለው ፖለቲካዊ ትርፍ ስለሌለን እንዲህ ያለ ውሸት አንዋሽም ስለማኅበረ ቅዱሳን የምንጽፈው የሆነውን ነው፡፡ እኛን ዋሻችሁ ለማለት ምክንያት ያገኛችሁ መስሎዋችሁ ነበር ነገር ግን እናንተ የራሳችሁን ውሸታምነት ነው የገለጻችሁት፡፡

በሬ ወለደ የእናንተ ስም እንጂ የእኛ አይደለም፡፡ ብዙ ብዙ ብዙ በሬዎችን አስወልዳችኋል በርካታ ግመሎችን በመርፌ ቀደዳ አሳልፋችሁኋል፡፡ አላማችሁ ሀሳባችሁ መንፈሳዊነታችሁ ሁሉ የተመሰረተው በውሸት ነው፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ብሎጋችን ላይ የሚወጡት ዜናዎች ራስ ምታት ስለሆኑበት መረጃ የሚሰጠው ማነው እያለ በስብሰባ ራሱን እንደሚያደክም እናውቃለን፡፡ የብሎጉ ባለቤት እገሌ ነው እገሌ ነው የለም እገሌ ነው እያለ ወሬ የሆነመረጃእንደሚያሰባስብም እናውቃለን፡፡ ብሎጉን ለማዘጋት አይደለም ሌላም እድል ቢኖረው ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም፡፡
ብሎጎችን ኢንሳም ይዝጋው ማንም ማኅበረ ቅዱሳን እዛ ውስጥ ሰው አያጣም፡፡ እነዛን ሰዎች ተጠቅሞ ብሎጉን ከማዘጋት ወደ ኃላ አይልም፡፡ በዛ ላይ ብሎጉ ለምን ተዘጋ ብሎ ጥያቄ የሚያቀርብ አካል እንደማይኖርም ያውቃል፡፡ ስለዚህ እንዲህ ያለውን ብሎግ ማዘጋት ከባድ አይደለም፡፡

ካሉት ሁኔታዎች አንጻርም ማቅ እንዲህ ያለውን ተግባር አይደለም የከፋ ወንጀልም ከመፈጸም ወደ ኋላ አይልም፡፡ ለሀይማኖት ሲባል ምንም ማድረግ ትክክል ነው ከሚለው የማቅ ወንጌል መሰረት የሰው ሕይወት እስከማጥፋት የደረሰ ወንጀል መፈጸሚያ ኮሚቴ ያቋቋመ ድርጅት እንዲህ ያለውን ነገር አያደርግም ተብሎ አይታሰብም፡፡ በደንብ ያደርጋል፡፡ ሰርቆ ሌባ ሌባ እያለ እንደሚሮጥ ሰው ዋሽታችሁ ስታበቁ ውሸታም እያላችሁ አትጩሁ፡፡ ባትጽፉዋቸው ምንም የማይቀርባችሁን ነገሮች እያነሳችሁ ተራ ሰዎች መሆናችሁን እስገደዳችሁ አትንገሩን፡፡ እኛ የሆነውን ሆኗል ስንል ያልሆነውን ሆነ የምትሉት እናንተ ናችሁ፡፡  የተዘጋውን ብሎጋችን ተከፍቶ የእናንተን ጫጫታ እውነት ቢያደርግልን ደስታችን ነው፡፡ አንባቢዎቻችን በለመዱት አድራሻችን ያገኙናልና ነው፡፡ ብሎጋችን ከእናንተ ያነሰ ዕድሜ እንዳላት ታውቃላችሁ፡፡ አንባቢዎቻችን ግን ከእናንተ አያንሱም፡፡ እኛም ብንጠቅሰው በሚያኮራን በርካታ አንባቢያን ብሎጋችን ተጎብኝታለች፡፡
ዋሽተዋል ብላችሁ ለማሳመን የምትፈልጉት ከኢትዮጵያ ውጭ ያለውን ወገን እንደሆነ እናውቃለን፡፡ የአገር ቤቱ አንባቢ በቀላሉ ሞክሮ የሚያውቀው እውነት ስለሆነ አይደንቀንም፡፡ እኛም እውነቱን መግለጽ የፈለግነው እናንተ ልታልሉት ያሰባችሁት ለውጩ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ አገር ውስጥ ያለው እማ ሞክሮ የሚያውቀው እውነት ነው፡፡
        ለእናንተ የአምላክ ያህል የምታጥኑለት ማኅበራችሁን ስህተቶች በመግለጣችን በምሰትሰጡን ስም አይደንቀንም፡፡ ለእናንተ የክርስትና ጥግ ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑን እናውቃለን፡፡ ብሎጋችሁን ማን እንድትፈጥሩ አደረጋችሁ ብትባሉ ቢያንስ በልባችሁ   ኅበረ ቅዱሳን ማለታችሁ አይቀርም፡፡ እኛ የምንፈራው ግን እንዲህ እንደ አምላክ እንከን አልባ ያደረጋችሁት ማኅበር እኛንም ፈጥሮናል ብላችሁ ለማኅበረ  ቅዱሳን መስገድ እንዳትጀምሩ ነው፡፡ አካሄዳችሁ ወደዛ ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን የሚባል ሃይማኖት ፈጥራችኋል፡፡ ጥቂት ቆይታችሁ ደግሞ ማኅበረ ቅዱሳን የሚባል አምላክ ለራሳችሁ ማበጀታችሁ አይቀርም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን የሚባል ሀይማኖት ባትፈጥሩ ኖሮማ ማኅበረ ቅዱሳን አልሆንም ያለውን ሁሉ ሌላ ቅጽል አታበጁለትም ነበር፡፡ የማህበረ ቅዱሳንን ችግሮች ስለገለጥን እንዲህ እና እንዲያ ናችሁ አትሉንምም ነበር፡፡
ለማንኛውም አንባቢያን እንዲያውቁልን የምንፈልገው እውነት ብሎጋችን እስካሁን ድረስ የተዘጋ መሆኑን ነው፡፡ ብሎጋችንን ኢትዮጵያ ውስጥ የምትነበበብበት በአዲሱ  ተጨማሪ አድራሻችን  www.awdemihret.wordpress.com ነው፡፡