Friday, September 7, 2012

የግብጽ ኦርቶዶክስና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት መጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር ለምን ተለያየ?

የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለ1600 ዓመትያህል  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የበላይ ሆና ስትመራ መቆየቷ እርግጥ ነው። በዚህ ረጅም ዓመታት ውስጥ ለቤተክርስቲያኒቱ ያበረከቱት እድገትና መንፈሳዊ ልማት እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ይልቁንም በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ለመግባትና በቤተክርስቲያኒቱ የወርቅና የልዩ ልዩ ስጦታዎች ሀብት ማጋበስ እድል ሰጥቷቸዋል። ራሷን በቻለች ጊዜም መሪዋና ኃላፊዋ የመሰረታት ክርስቶስ ነው፤ ከማለት ይልቅ በእኛ አመራርና ኃላፊነት ስር ካልሆናችሁ ፕትርክናውን አንፈቅድላችሁም ሲሉ አስቸግረው እንደነበር የቅርብ ጊዜው ታሪክ ይነግረናል። እንደዚያም ሆኖ በብዙ ነገራችን የመመሳሰላችን ነገር እንዳለ ሁሉ ዋና በሚባለው በመጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር ላይ ግን ትልቅ ልዩነታችንን በ1600 ዓመት ውስጥ ለምን እንደሆነ አልነገሩንም፤ ወይም እኛም አልጠየቅናቸውም። በጅምላ የኦሪየንታል/ምስራቃዊ/ አብያተክርስቲያናት ሁላችንም አንድ ዓይነት እምነትና አስተምህሮ አለን እያልን በረጅም ታሪካችን ውስጥ እስክንድሪያ እናታችን፤ ማርቆስ አባታችን ከማለት ውጪ አንድ ሊያደርገን በሚገባው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እስከዛሬ ባለን ልዩነት የሚነገር ምንም ነገር አለመኖሩ አስገራሚ ነው። እውነቱ ግን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና በኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መካከል የሃይማኖቱ መመሪያ በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሁለቱም ቤተክርስቲያን የቁጥር ልዩነት እንዳላቸው እርግጥ ነው። ለምን? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ የሊቃውንት ጉባዔ ካለ ለመስማት ዝግጁ ነን። እስከዚያው የልዩነትም ደረጃ ለማየት እዚህ ላይ እንዘረዝራቸዋለን።



የግብጽ/ኮፕቲክ/ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍት ዝርዝር፤
የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት

1/ Genesis     ዘፍጥረት                
2/ Exodus    ዘጸአት
3/ Leviticus  ዘሌዋውያን
4/ Numbers ዘኁልቈ
5/ Deuteronomy ዘዳግም
6/ Joshua  ኢያሱ ወልደ ነዌ
7/ Judges  መሣፍንት
8/ Ruth   ሩት
9/ 1 Samuel  1ኛ ሳሙኤል
10/ 2 Samuel  2ኛ ሳሙኤል
11/ 1 Kings   1ኛ ነገ
12/ 2 Kings 2ኛ ነገ
13/ 1 Chronicles  1ኛ ዜና
14/ 2 Chronicles  2ኛ ዜና
15/ Ezra     እዝራ
16/ Nehemiah  ነህምያ

17/ Tobit  ጦቢት
18/ Judith   ዮዲት
19/ Esther   አስቴር
20/ Job    ኢዮብ
21/ Psalms  መዝሙር
22/ Proverbs   ምሳሌ
23/ Ecclesiastes  መክብብ
24/ Song of Solomon  መሐልይ
25/ Wisdom   ጥበብ
26/ Sirach  ሲራክ
27/ Isaiah  ኢሳይያስ
28/ Jeremiah   ኤርምያስ
29/ Lamentations   ሰቆቃ
30/ Baroch    ባሮክ
31/ Ezekiel    ሕዝቅኤል
32/ Daniel   ዳንኤል
33/ Hosea   ሆሴዕ
34/ Joel   ኢዩኤል
35/ Amos   አሞጽ
36/ Obadiah  አብድዩ
37/ Jonah   ዮናስ
38/ Micah  ሚክያስ
39/ Nahum   ናሆም
40/ Habakkuk   እንባቆም
41/ Zephaniah   ሶፎንያስ
42/ Haggai    ሐጌ
43/ Zechariah   ዘካርያስ
44/ Malachi   ሚልክያስ
45/ 1 Machabees   1ኛ መቃቢስ
46/ 2 MachabeesPhilemon  2ኛ መቃቢስ ዘፊልሞና



************************************************



የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት
1/ Matthew  ማቴ
2/ Mark ማር
3/ Luke  ሉቃ
4/ John  ዮሐ
5/ Acts of Apostles  የሐዋ
6/ Romans   ሮሜ
7/ 1 Corinthians  1ኛ ቆሮ
8/ 2 Corinthians  2ኛ ቆሮ
9/ Galatians   ገላ
10/ Ephesians  ኤፌ
11/ Philippians  ፊልጵ
12/ Colossians  ቆላስ
13/ 1 Thessalonians 1ኛ ተሰ
14/ 2 Thessalonians  2ኛ ተሰ
15/ 1 Timothy   1ኛ ጢሞ
16/ 2 Timothy   2ኛ ጢሞ
17/ Titus   ቲቶ
18/ Philemon  ፊልሞ
19/ Hebrews ዕብ
20/ James  ያዕ

21/ 1 Peter  1ኛ ጴጥ
22/ 2 Peter  2ኛ ጴጥ
23/ 1 John  1ኛ ዮሐ
24/ 2 John  2ኛ ዮሐ
25/ 3 John  3ኛ ዮሐ
26/ Jude ይሁዳ
27/ Revelation  ራእይ

 46+27= 73 ጠቅላላ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር ነው።  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ በተለምዶ 81 ወይም ሰማንያ ወአሐዱ ተብሎ የሚጠራው ምንም እንኳን ከሰማንያ አንድ ቢበልጥም የተባለውን እንዳለ ብንቀበል ከግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጋር በ8 /ስምንት/ መጻሕፍት የብልጫ ልዩነት አለ።

በመጽሐፍ ቅዱስ አምላካዊ መጽሐፍ ቁጥር ላይ አንድ ካልሆንን እንዴት አንድ ዓይነት ዶግማና ቀኖና አለን ሊባል ይችላል? በመቃብያን መጻሕፍት ላይ ደግሞ በጭራሽ መጻሕፍቱ አንድ ዓይነት አይደሉም።  ለምን ልዩነቱ ተፈጠረ? በቅርጣግና /Chartage/ ጉባዔ  ላይ እነ ቅዱስ አትናቴዎስ ከቅዱሳት መጻሕፍት ዝርዝር ውስጥ ያላስገቧቸው መጻሕፍት ለምን እንደመጽሐፍ ቅዱስ አካል ተቆጥረው በ2000 ዓ/ም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ገቡ? የምላሽ ያለህ!!!!!!!!!!!!
  ለተጨማሪ መረጃ እዚህ ላይ ተጭነው ይመልከቱ