Sunday, June 10, 2012

የአዶላ ከተማ የማኅበረ ቅዱሳን ተጠሪ የተማሪዎችን ፈተናና የፈተና ጣቢያውን ኃላፊ አገቱ

                       ምንጭ፤ ዓውደ ምሕረት ብሎግ
ማኅበረ ቅዱሳን በተለያየ የአገሪቱ ክፍሎች ሁከት ማነሳሳትን አላማው አድርጎ ተያይዞታል። ጭር ሲል አልወድም በሚል ባህሪው የሚታወቀው ይሄ አሸባሪ ማኅበር አባላቱ በሄዱበት ቦታ ሁሉ ሁከት እያነሳሱ ይገኛሉ። የዋልድባን ጉዳይ እነደ መንግስትን ማዳከሚያ ስልት እየተጠቀመበት ያለው ማቅ ደመቅ ባለበት ቦታ በቤተክርስቲያን ውስጥ፤ ምዕመኑ አነስተኛ በሆነበት ቦታ ደግሞ ባሉ ክፍተቶች ተጠቅሞ አመጽ ማነሳሳቱን ስራዬ ብሎ ተያይዞታል። 
 ሰሞኑን ይህን እውነት የሚያጎላ ክስተት በጉጂ ዞን በጨንቤ ወረዳ ተከስቷል። የአዶላ ወረዳ የማቅ ተጠሪ የሆነውና ባለፈው የካቲት 16 በነበረው ግርግር አመጽ በማነሳሳት ታስሮ በገደብ የተለቀቀው ስምንት ስልጣን ደራርቦ በያዘው ቀሲስ መኮንን ጉተማ አስተባባሪነት ሌሎች የማኅበሩ አባላት በሆኑ መምህራን አጋዥነት ክፍያ አነሰን በሚል ሰበብ የተማሪዎቹን ፈተናና የፈተና ጣቢያውን ኃላፊ ለሁለት ቀናት አግተው ቆይተዋል። የክብረ መንግስት ከተማ የሀገር አቀፍ ፈተናዎች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን ግለሰቦቹ የዕርምት ዕርምጃ እንዲወስድባቸው ለጉጂ ዞን ት/ቢሮ ደብዳቤ የጻፉ ሲሆን ለኦሮሚያ መንግስትና ለሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት በግልባጭ አሳውቀዋል። 
ደብዳቤውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


ግለሰቦቹ ከመምህር የማይጠበቅ የተማሪዎችን ቀጣይ እድል በሚያጨልም ራስ ወዳድነት ተነሳስተው ያደረጉት ሕገ ወጥ ተግባር መሆኑም በደብዳቤው ተገልጿል።  ስምንት ስልጣን ደራርቦ የያዘው ቀሲስ መኮንን ከክብረ መንግስት 30 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ጨንቢ ወረዳ ሄዶ ሰውንና የፈተና ውጤትን ለሁለት ቀናት ለማገት የሚረዳውን ጊዜ እንዴት እንዳገኘ ግራ የሚያጋባ እውነት ሆኗል።
የወረዳ ቤተክህነት ጸሐፊ፣ የወረዳ ስብከተ ወንጌል ኃላፊ፣ የመድሀኒዓለም ደብር አስተዳዳሪ፣ የዘንባባ ማርያም አስተዳዳሪ፣ የዘንባባ ሚካኤል አስተዳዳሪ፣ የጨንቢ ሚካኤል አስተዳዳሪ፣ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ተጠሪ፣ የማኅበረ ሥላሴ ሰብሳቢ እና የማኅበረ ቅዱሳን የአዶላ ወረዳ ተጠሪ፣ የሆነው ቀሲስ መኮንን በነዚህ ስምንት ስልጣኖቹ ተጠቅሞ ቤተክርስቲያንን እየመዘበረ በክብረ መንግስት ከተማ የሰራው ቤት ከተማው ውስጥ ያለ እኔ ነኝ ያለ ነጋዴ እንኳ ሊሰራው ያልቻለው እንደሆነ ይታወቃል። ቤተክርስቲያኔን “በነፃ” ነው የማገለግለው በማለት የዋሁን የአካባቢውን ህዝብ የሚያጭበብረው መኮንን በአስተማሪ ደሞዝ እንዲህ ያለውን ቤት እንኳን ለመስራት ለማሰብ እንኳ የማይቻል መሆኑ ግልጽ ነው። የዘንባባ ማርያም ገንዘብ አንድም ቀን እንኳ አስቆጥሮ የማያውቀው እና ብሩን ሰብስቦ ወዴት እንኳ እንደሚወስደው አይታወቅም የሚባልለት ቀሲስ መኮንን በአፍ “የትሩፋት” ሠራተኛ ነኝ ቢልም በተግባር ግን የዘራፊዎች አለቃ ነው። ለምን ብሎ የሚጠይቀው እንዳይኖር ከዘረፈው የሚያካፍላቸው ሁለት ዋና ሰዎች ያሉት ሲሆን እነርሱም የሻኪሶ አዶላና ዋደራ ወረዳ ቤተክህነት አስተዳዳሪ የሆነው በማቅ አባልነቱ የሚመፃደቀው ፍትቶ በማግባቱ ክህነቱን ያፈረሰው ሊቀስዩማን ልሳነ ወርቅ ሁንዴና ሊቀጠበብት ሲያምር ተክለማርያም ናቸው።
እንደ በርካቶቹ የማቅ አባለት ቅስናው የክብር የሆነለት መኮንን ሊቅ ነኝ በማለት የሚመፃደቅ ቢሆንም ቅዳሴ እንኳ በቅጡ የማይችል ሰው ከመሆኑም በላይ፤ የክርስትና አላማው የተናቁትን ማንሳት መሆኑን ስለማያውቅ መስቀል እንኳ ለማሳለም ከሰው ሰው እንደሚለይና በራሱ መመዘኛ ሀጢያተኞች ብሎ የሚያስባቸውን ሰዎች መስቀል የማያሳልም እና የአዲስ ኪዳኗን ክርስትና በፈሪሳውያን የአምልኮ ዘይቤ ሊመራት የሚፈልግ ሰው መሆኑ ይታወቃል።
አበል አነሰኝ ብሎ ሰውንና የተማሪዎችን የፈተና ውጤት ሁለት ቀን ሙሉ ያገተው ቄስ ነኝ ባዩ መኮንን ለቁርጥራጭ ሳንቲም እንዲህ ያለ ግፍ የፈጸመ ያለከልካይና ያለተቆጣጣሪ የሚያገኘውን የቤተክርስቲያን ገንዘብ በዝምታ ያልፋል ማለት የማያስኬድ ነገር ነው። በአስተማሪ ደሞዜ በነፃ ቤተክርስቲያንን አገለግላለሁ ያለው የማቁ ባላባት መኮንን የሰራውን ቤት እንዴት እንደሰራ እንዲጠየቅና ምንጩ ያታወቀን ንብረት ለመንግስት እንዲሆን በሚያዘው ህግም እንዲዳኝ ለማሳሳብ እንወዳለን።