Monday, June 4, 2012

መምህር ዘበነ ለማ መመሪያ አክብሮ እንዲሠራ ደብዳቤ ተጻፈለት !

                       ምንጭ፦ ዓውደ ምሕረት ብሎግ
የስብከተ ወንጌልን አገልግሎት አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነውንና ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የተሰጠውን መመሪያ ጥሰዋል ያለፈቃድም ሰብከዋል በሚል ለመምህር ዘበነ ለማ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተጻፈ። ደብዳቤውን የጻፈው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሲሆን፣ ዘበነ መኖሪያውን በአሜሪካ ቢያደርግም በእናት ቤተክርስቲያን ውስጥ እያገለገለ ለመሆኑ የሚያስረዳ ደብዳቤ በአሜሪካ ከሚገኘው ሀገረ ስብከት ይዞ መምጣት ሲገባው እርሱ ግን ያለ ፈቃድ እየተዘዋወረ በመስበክ የስብከተ ወንጌል መምሪያ ውሳኔዎቹን ለማስፈጸም በሚያደርገው ጥረት ላይ አፍራሽ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ደብዳቤው ገልጾ፣ ከዚህ በኋላ ከሚኖርበት ሀገረ ስብከት በእናት ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ካላመጣና እንደለመደው እሰብካለሁ ቢል ለሚመለከተው አካል ሪፖርት በማድረግ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ የሚያደርግ መሆኑን ገልጾአል።

መምህር ዘበነ ነዋሪነቱን በአሜሪካ አድርጎ ከሁለቱም ሲኖዶሶች ውጪ ነኝ በሚል በገለልተኛነት የሚኖር ሲሆን፣ እንዲህ ያደረገውም ወደ አገር ቤት ብቅ እያለ በስብከተ ወንጌል ስም ቢዝነሱን የሚሰራበት በር እንዳይዘጋበት ሲሆን፣ በሌላም በኩል በውጪ ያለው ዳያስፖራ ማህበረሰብ ደግሞ ከአገር ቤቱ ሲኖዶስ ጋር ነው የሚሰራው እንዳይለው በማሰብ ነው። 
ዘበነ በአገር ውስጥና በውጭ አገር አክራሪነትን የሚሰብክና ክርስቲያኖች ተቻችለውና ተከባብረው እንዳይኖሩ የሚያደርጉ ርእሶችን በማንሳት፣ በስብከት ንግድ ለመክበር የሚሠራ ሰው እንደሆነ አሜሪካ ውስጥ በሬዲዮ ከሚያስተላልፋቸው ፕሮግራሞችና አልፎ አልፎ ከአሜሪካ ወደ አገር ውስጥ የሚያስገባቸው ገበያ ተኮር ርእሶች፣ በአገር ውስጥም የሚያገኛቸው አንዳንድ በመለያየት ላይ የሚያጠነጥኑ ርእሶች ምስክር ናቸው። ዘበነ የወንጌልን ዓላማ ስላልተረዳና እንዲረዳም ስለማይፈልግ፣ ይሸጥልኛል ብሎም ስለማያስብ እስካሁን የወንጌልን እውነት የሚገልጥ የቪሲዲም ሆነ የካሴት ስብከት አላቀረበም።

 ድብዳቤውን ለማንበበብ ( እዚህ ይጫኑ )

ዘበነ በትምህርት ቤት ሳለ የስብከት ዘዴ የሚያስተምሩት የነበሩት የእህት አብያተ ክርስቲያን መምህር የትምህርቱ ይዘት ተማሪዎቻቸው ምን ያህል እንደገባቸው በሚገመግሙበት የሙከራ ስብከት ጊዜ ገና ስብከቱን ሲጀምር እየጮኸ ስለሚያስቸግራቸው ስብከት ጩኸት አይደለም እያሉ የሙከራውን ስብከት እያቋረጡ ያስቆሙት እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። አዋቂ ነኝ ከሚል እሳቤ ውጭ መማር የሚፈልግ ማንነት ስለሌለው አሁንም ስብከት ካልጮኸ የማይደምቅ እንደሚመስለው የሚታይ እውነት ነው።
ዘበነ ከማን እንደተማረውና ከየት እንዳገኘው ባይታወቅም ክብርን ለራሱ በማከማቸት የሚታወቅ ሲሆን ከአሜሪካን ሲመጣ ለሚያውቃቸው ሰባኪያን እየደወለ ልመጣ ነውና ቀሚስ ለብሳችሁ ተቀበሉኝ በማለት እየደወለ በመጥራት የታወቀ ሰው ነው። ለስብከት ከቦታ ቦታ ሲዘዋወር ያለ አጃቢ የማይዘዋወር ሰው መሆኑ አላማው ምንድን ነው? የሚያሰኝ ነው። በአንድ ወቅት ከአሜሪካ ሲመጣ ከስብከት በኃላ እንደ ዘፋኝ እየፈረመ ረዥም ጊዜ ይወስድ እንደነበር የምናስታውሰው እውነት ነው።
አላማው ሕዝቡ እውነትን እንዲያውቅ ሳይሆን፣ እርሱ የሚያውቀውንና ሁሌ ከአፉ የማይለየውንአውሬውየሚለውን ስም ብቻ እንዲያጠናና በስጋት እንዲሞላ ለማድረግ ነው። ይህም ፍሬ አልባ ትምህርቶቹ የሚጠቀምበት እውነቱ ያልገባቸውና እንደዘበነ ያሉ ጆቢራዎች ያቀረቡላቸው ሁሉ እውነት የሚመስላቸው ወገኖች ገዝተው የእነዘበነን ኪስ እንዲሞሉና እነርሱ ግን የወንጌሉ ዓላማ ሳገባቸው እንዲሁ ስለ ልዩነት ብቻ በማሰብ በእነርሱ ጉንጭ አልፋ ክርክር ውስጥ ጠፍተው እንዲኖሩ ለማድረግ ነው።

የወንጌሉን ዓላማ ከተረዱ ግን የእነርሱን የተሳሳተ አስተምህሮ እንደማይቀበሏቸውና የስብከት ገበያቸው እንደሚቀዘቅዝ  ስለሚያውቁ፣ ሁሌ ስለመለያየት በሚሰብክ አመለካከት ስለተጠመዱ፣ የዕውር መሪዎች መሆንን መርጠዋል። በእውነትም ለሕዝቡ የወንጌል እውነት ማለትም «የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ።» (2 ቆሮንቶስ 44) ተብሎ እንደተጻፈው ሰይጣን ብቻ ሳይሆን ለሆዳቸው ያደሩ አንዳንድ ሰባኪዎችም ለጥቅማቸው ሲሉ ሕዝቡን ማሳታቸውን በመቀጠላቸው የስብከተ ወንጌሉ መመሪያ ተግባራዊ መሆኑ ጠቃሚ ነው።