ከ12, 000 ሺህ ዓመት በፊት የኩሾች ፈርዖን፤ የሰማይና ጸሐይ ፤
«አስራ» የተባለው
አምላክ ሦስት ልጆችን ወለደ።
የመጀመሪያ ወንድ ልጁ «ሴቴ»፤ ሁለተኛው ልጁ ደግሞ «ኦራ» ሲባል የመጨረሻ ሴት ልጁ ደግሞ «አቴቴ» ወይም አድባር የምትባል ነበረች። ከጸሐይና ከሰማይ አምላክ «አስራ»
ልጆች መካከል ሴቴ የተባለው የመጀመሪያ ልጁ ታናሽ ወንድሙን ኦራን በድንጋይ ገደለው። በወንድሟ ሞት እጅግ ያዘነችው «አቴቴ»
ዐባይ ወንዝ ዳርቻ ባረፈው በሟች በወንድሟ መቃብር ላይ «ኦዳ» የተባለውን ዛፍ ለመታሰቢያነት ተከለች።
አቴቴ (አድባር) በመቀጠልም ያደረገችው ነገር በገዳይና በሟች ወንድሞቿ ቤተሰቦች መካከል በቀልና ጥላቻ እንዳይኖር ወደሰማይና ጸሐይ አምላክ አባቷ
ወደ አስራ በማመልከቷ የሰላም ምልክት እንዲሆን ከሰማያት ዝናብ ዘንቦ የተከለችውን «ኦዳ» የተባለውን በማለምለም ሰላም እንዲሰፍን አድርጎላታል።
ሟች ኦራም በኦዳ ዛፍ ልምላሜ የተነሳ በጸሐይና በሰማይ አምላክ አባቱ ሥልጣን ምክንያት ከሞት የተነሳና ያረገ ሲሆን ይኸው በኦዳ ዛፍ ስር ሟች ኦራን በማስታወስ የሚደረገው የሰላምና የምህረት አከባበር ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ ቀጥሏል። በቀደምት ኑቢያውያን የሚደረገው አከባበር
በጥንታውያን የአክሱም ስርወ መንግሥትም ዘመን የኦራ መታሰቢያን የሚያመለክት ቋሚ ድንጋዮችን በመትከል ሲታሰብ ኖሯል።