Monday, November 24, 2025
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስለተቀየረ ሰይጣን ውጊያውን አያቆምም!
gg
(ከመሥፍን ግርማ)
እኔ ከወንጌላውያን አማኞች ነኝ። አዎ ኦርቶዶክስ ብዙ የአስተምህሮ መፋለስ አለባት። ነገር ግን ይሄንን ቄስ በማጣቷ ምንም አልተጎዳችም። እንዲያውም እየተጎዱ ያሉት ይሄን ሰውዬ የተቀበሉ ወንጌላውያን ናቸው። ሰውየው ወንጌል አልገባውም። ከገባውም እየኖረበት አይደለም። መዋሸትና ማጭበርበር መደበኛ ስራው አድርጓል። ኦርቶዶክስን መሳደብ እውቀት መስሎታል። የትኛውም ቦታ አፉን የሚያሟሸው ኦርቶዶክስን በመሳደብ ነው። ይሄንን ቄስ ተረጋጋ የሚለው ዘመድ እንዴት ይጥፋ? የተቀበሉት ወንጌላውያንም የላንቃህን ቶን ትንሽ ቀነስ አድርግ ማለት ለምን አቃታቸው? በጣም መልፍለፍ አበዛ። ሰውየው ቀራንዮ አካባቢ ሚስቱ አስወልዶ እንደጣላት ስትከሰው ሰምተናል። ያስወለዳቸውን ልጆች ያላሳደገ አሁን ስለ ዘመን አቆጣጠር መለፍለፍ እውቀት መስሎታል። በትክክል ድኖ ከሆነ የዳነ ሰው ሕይወትን ይኑር። ንግግሩ የታረመ ይሁን። ትምሕርቱ ወንጌልን ይግለጥ፣ ሰዎች ወደመዳን እንዲመጡ ይትጋ። ከዚያ ውጪ ስድብ፣ ኃይለ ቃልና ከንቱ ልፍለፋውን ያቁም።
አሁን ኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠሯን ወደአይሁድ ዘመን ብትቀይረው እንንእስራኤል ሀብታም ትሆናለች ማለት ነው? ወደአመተ ሂጅራ ብትቀይረው እንደአረቦቹ ነዳጅ በነዳጅ እንሆናለን? ወደፖፕ ጎርጎርዮስ ቀመር ብንቀይረው እንደኢጣሊያ ወይም አውሮፓን ልንሆን ነው ማለት ነው? ከኛ የተሻሉ ሀገሮች ሀብታም የሆኑት በዘመን አቆጣጠራቸው የተነሳ ነው? ከእግዚአብሔር ለሰው ልጆች የጽድቅና የቅድስና ዘመን ተብሎ የተሰጠው የትኛው የዘመን አቆጣጠር ነው? ይሄ ሰውዬ፣ የዚያ የእውቀት ድሃው የትዝታው ሳሙኤል ወንድም ነው። በግሌ ዘመን ቢቀየር፣ ባይቀየር በኔ ላይ የሚያመጣው ልዩነት እንደሌለ አምናለሁ። ነገር ግን ከሰኞ እስከ እሁድ ያሉትን ቀናት በስም መጥራት ብንተወውና ወይም ከዛሬ ጀምሮ 1,2,3,4, ብለን በቁጥር ብንለውጠው ወይም ከመስከረም እስከ ነሀሴ ያሉትን ወራት በእጽዋት ወይም በእንስሳት ስም ብንቀይረው የዘመኑ መለወጥ ኢትዮጵያን ሀብታም አያደርጋትም፣ ህዝቦቿንም ጻድቅ አይሆኑም ብዬ አምናለሁ። መለወጥ ያለበት በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ወደመዳን መድረስ ያለበት ህዝቡና ቢያምንም፣ ባያምንም ጠንክሮና ተግቶ በመስራቱ ብቻ ነው ከድህነት መውጣት የሚቻለው። ጃፓንና ቻይና ሀብታም የሆኑት ይሄ ደንቆሮ መንፈስ የያዘው ቄስ እንደተናገረው ዘመን ስለቀየሩ ሳይሆን የስራ ባህላቸውን ስለቀየሩ ነው። እነዚህ ደናቁርት ግን የሚለፈልፉት ለኛ መዳንና ባለጸጋ መሆን መፍትሄው የዘመኑ መለወጥ ይሉናል። ይሄ ዲስኩር ተልእኮ ያለው ሲሆን ከኋላ ሆኖ push የሚያደርጋቸው ሃይል መኖሩን ያሳያል። ዘመኑን ወደአይሁድ ወይም ወደፖፕ ጎርጎርዮስ ዘመን ስለቀየርን ሰይጣን አይጠፋም። የአጋንት ውጊያም አይቀርም። መለወጥ ያለበት ይሄንን ቄስ የመሰሉ ደንቆሮ መንፈስ የያዛቸው ሰዎች ናቸው። በዚህ ሰው የሚመገቡ ምዕመናን ምን እንደሚመግባቸው ባይገባንም መጋቢ ነኝ ባዩ ሶፎንያስ ሞላልኝ በዩቱብ አካውንቱ የሚያቀርባቸው አብዛኛዎቹ ሰዎች እብዶች፣ ከበሽታ መፈወስ ያለባቸው ሰዎችን ልክ ጤናማና የተመሰከረላቸው አስተምህሮ ያላቸው አስመስሎ ማቅረብ ከጀመረ ጊዜያት ተቆጥረዋል። ጉዳዩ ስለወንጌል ሳይሆን ከዩቱብና ከሌሎች የሚዲያ ምንጮች የሚቀራርማትን ሽርፍራፊ ሳንቲም ስለመለቃቀም ነው። ለሁሉም ፈውሱን ይላክላቸው!
