መጽሐፍ ቅዱስ «መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደሆነ መርምሩ» ይላል። ምክንያቱም በዓለም ላይ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የማይስማሙ ነገር ግን እውነትን የሚመስሉ ሀሰተኛ ትምህርትና ትንቢት በዓለሙ ገብተዋልና በማለት ጥንቃቄ እንድናደርግ ያስተምረናል። ነገር ግን እውነቱን ጋርደው እውነት የሚመስሉ አስተምህሮዎች ምን ጊዜም ከእግዚአብሔር መንፈስ የሚመጣ ሳይሆን ከሀሰት አባት መንፈስ የሚቀዳ ስለመሆኑ ቅዱስ ቃሉ «የሀሰት አባት ከራሱ አንቅቶ ሀሰትን ይናገራል» በማለት (ዮሐ 8፤44) እንዳስቀመጠው ዛሬም በስህተት ትምህርቶች ፍጥረቱ ተበክሏል። ከስህተት ትምህርቶች አንዱ የሆነውን ገድል «ተስፋ» የተባለው ጸሐፊ በወንጌል ቃል ሽፍንፍኑን እየገለጠ ያሳየናል። ሰው ሃይማኖት ኖረው፤ አልኖረው ፤ እግዚአብሔርን ካደ፤ አልካደ ምንም ጥቅም የሌለው እንደሆነ የሚያደፋፍርና ከአምልኰ የለሽነትም ጭምር የሚታደግ አስተማማኝ መጽሐፍ መገኘቱን በማብራራት እስኪገርመን ድረስ ገላልጦ ያሳየናል። ልብ ያለው ልብ ይበል! እንላለን።
የጽሁፋችን ምንጭ «አባ ሰላማ ድረ ገጽ» ነው።
ክርስቶስ ሠምራ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የታወቀች ቅድስት ሴት ናት። በየዓመቱ ግንቦት 12 መታሰቢያዋ ይከበራል። በዚህ ቀን በርካታ ምዕመናን እርሷን ከሲኦል እንድታወጣው ለመማጸን ወደ ቤተ መቅደሷ በመሄድ ሲሰግድ ይውላል። ንፍሮ በመቀቀል፣ ዳቦ በመጋገር፣ ጠላ በመጥመቅና ገድሏን በማንበብ ልመናና ጸሎት ያቀርብላታል። እርሷ የኖረችበት ነው በተባለው በጣና አካባቢ በሚገኘው ገዳሟ የሚሰበሰበው ሕዝብ ብዙ ነው። በዚያ ሰንጣቃ አለት የሚገኝ ሲሆን አንድ ሰው መጽደቅ እና አለመጽደቁን ለማወቅ በሰንጣቃው አለት በማለፍ እራሱን ይፈትናል። በዓለቱ ሾልኮ ካለፈ ጸድቋል ይባላል ካላለፈ ግን ተኮንኗል ይባላል። በብልሃት እንደምንም ያለፈ ሰው ጸድቄያለሁ ብሎ እራሱን አዘናግቶ ይኖራል።
የጽሁፋችን ምንጭ «አባ ሰላማ ድረ ገጽ» ነው።
«ወወሐባ ኪዳነ ከመ ታውጽእ ነፍሳተ እምሲኦል ሠለስተ እልፈ ነፍሳተ በበዕለቱ» ትርጉም "ጌታም በየቀኑ ከሲኦል ሦስት ሺህ ነፍሳትን እንድታወጣ ሥልጣን ሰጣት ወይም ቃል ኪዳን ሰጣት» ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘጥቅምት ቁ 61
ገድሉን ለማንበብ ( እዚህ ይጫኑ )