Monday, July 9, 2012

ክርስቶስ ሰምራ ዘብሔረ ቡልጋ በቀን ሦስት ሺህ ነፍሳት ከሲኦል ታወጣለች!

 መጽሐፍ ቅዱስ «መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደሆነ መርምሩ» ይላል። ምክንያቱም በዓለም ላይ ከእግዚአብሔር  ቃል ጋር የማይስማሙ ነገር ግን እውነትን የሚመስሉ ሀሰተኛ ትምህርትና ትንቢት በዓለሙ ገብተዋልና በማለት ጥንቃቄ እንድናደርግ ያስተምረናል። ነገር ግን እውነቱን ጋርደው እውነት የሚመስሉ አስተምህሮዎች ምን ጊዜም ከእግዚአብሔር መንፈስ የሚመጣ ሳይሆን ከሀሰት አባት መንፈስ የሚቀዳ ስለመሆኑ ቅዱስ ቃሉ «የሀሰት አባት ከራሱ አንቅቶ ሀሰትን ይናገራል» በማለት (ዮሐ 8፤44) እንዳስቀመጠው ዛሬም በስህተት ትምህርቶች ፍጥረቱ ተበክሏል።   ከስህተት ትምህርቶች አንዱ የሆነውን ገድል «ተስፋ» የተባለው ጸሐፊ በወንጌል ቃል ሽፍንፍኑን እየገለጠ ያሳየናል። ሰው ሃይማኖት ኖረው፤ አልኖረው ፤ እግዚአብሔርን ካደ፤ አልካደ ምንም ጥቅም የሌለው እንደሆነ የሚያደፋፍርና ከአምልኰ የለሽነትም ጭምር የሚታደግ  አስተማማኝ መጽሐፍ መገኘቱን በማብራራት እስኪገርመን ድረስ ገላልጦ ያሳየናል። ልብ ያለው ልብ ይበል! እንላለን።

የጽሁፋችን ምንጭ «አባ ሰላማ ድረ ገጽ» ነው።

«ወወሐባ ኪዳነ ከመ ታውጽእ ነፍሳተ እምሲኦል ሠለስተ እልፈ ነፍሳተ በበዕለቱ» ትርጉም "ጌታም በየቀኑ ከሲኦል ሦስት ሺህ ነፍሳትን እንድታወጣ ሥልጣን ሰጣት ወይም ቃል ኪዳን ሰጣት» ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘጥቅምት ቁ 61
ገድሉን ለማንበብ ( እዚህ ይጫኑ )

ክርስቶስ ሠምራ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የታወቀች ቅድስት ሴት ናት። በየዓመቱ ግንቦት 12 መታሰቢያዋ ይከበራል። በዚህ ቀን በርካታ ምዕመናን እርሷን ከሲኦል እንድታወጣው ለመማጸን ወደ ቤተ መቅደሷ በመሄድ ሲሰግድ ይውላል። ንፍሮ በመቀቀል፣ ዳቦ በመጋገር፣ ጠላ በመጥመቅና ገድሏን በማንበብ ልመናና ጸሎት ያቀርብላታል። እርሷ የኖረችበት ነው በተባለው በጣና አካባቢ በሚገኘው ገዳሟ የሚሰበሰበው ሕዝብ ብዙ ነው። በዚያ ሰንጣቃ አለት የሚገኝ ሲሆን አንድ ሰው መጽደቅ እና አለመጽደቁን ለማወቅ በሰንጣቃው አለት በማለፍ እራሱን ይፈትናል። በዓለቱ ሾልኮ ካለፈ ጸድቋል ይባላል ካላለፈ ግን ተኮንኗል ይባላል። በብልሃት እንደምንም ያለፈ ሰው ጸድቄያለሁ ብሎ እራሱን አዘናግቶ ይኖራል።

Sunday, July 8, 2012

የጉጂ ቦረና ሐገረ ስብከት ችግር መንስዔው እና አሁን ያለበት ሁኔታ!

አንዳንዶች ስለማኅበረ ቅዱሳን ሽፍታነት ስንናገር ከሜዳ አንሰተን የጥላቻ ስም የምንለጥፍበት አድርገው ይቆጥሩናል። ነገር ግን አጣፍቶ ከሚለብሰው ነጠላ ጀርባ የሽፍታነት መገለጫ ያለበት የመሠሪ አባላት ስብስብ መሆኑን የሚያሳያቸው ግብራት ከምንም በላይ ማረጋገጫዎች ናቸው። /ይህንን ስንል ግን በቅንነትና በየውሃት መንፈስ ያሉትን አባላቱን ሳንጨምር ነው/ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ እስካሁን ያልበረደው የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢ ሀገረ ስብከቶች እየታመሱ ከቆዩ ሁለት ዓመት ያለፋቸው መሆኑ ነው። የማኅበረ ቅዱሳን ተላላኪ አገልጋይ የሆነው ሲያምር ተ/ማርያም በመንበረ ፓትርያርክ ውሳኔና በሥራ አስኪያጁ ደብዳቤ ወደ ትንሣዔ ዘጉባዔ ማተሚያ ቤት መዛወሩን ከአንዴም ሦስቴ ደብዳቤ ተጽፎለት ሳለ እሱ ጫንቃውን ያሳበጠውን ማኅበር ተተግኖ ሽፍትነቱን በማጠናከር በእምቢታው ከጸና ሁለት ዓመት አልፎታል። ቤተክርስቲያን ስታዘው ያልተቀበለ ሽፍታ፤ ሃዋሳ ሆኖ የማንን ቤተክርስቲያን ሊመራ ይፈልጋል? ብለን ብንጠይቅ ያልጨረሰው የማኅበረ ቅዱሳን ስራ ስላለ ያንን ሳይፈጽም እንዳይመለስ ኅሊናውን ስላሳመነ እንደሆነ ግልጽ ይሆንልናል። የሀገረ ስብከቱን መኪና ይዞ ጠፋ፤ ማኅተምና የጽ/ቤት ንብረቶችን አላስረክብም አለ፣ በህግ ተጠየቀ፤ ከዚህ ሁሉ ሽፍትነቱ ይባስ ብሎ ከደጅ ሆኖ በማኅተሙ እየጻፈ ሰው ያግድ ጀመር። እንግዲህ እነዚህ የሽፍቶች አባላት ስብስብ ናቸው ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉት! አሸባሪ ማለት ከዚህ ውጪ ምን ሊመጣ ነው? እንኳን በበላይ አካል ተዛውረሃል የተባለ ግለሰብ ይቅርና ጠንካራ ሠራተኛ የሆነ ሰው እንኳን አታስፈልግም ከተባለ ጥያቄውን በሕግና በሕግ ብቻ ለማስፈጸም ይፈልጋል እንጂ ቀሚስ ለብሶ ይሸፍታል እንዴ? ሽፍትነት የተፈጥሮው የሆነው ማቅ አንድ አባሉን «ግብረ ጥፉን በስም ይደግፉ» እንድንል ሆኖ ለክፋት የጥበብ መግቦቱ፤ «መጋቤ ጥበብ»፤  ለክፋት ስማዊ ግብሩ «ሲያምር» የተሰኘው «መጋቤ ጥበብ ሲያምር ተ/ ማርያም» ያደረሰው ግፍና ዐመጻ እንድታነቡ ከታች አቅርበነዋል። የጽሁፋችን ምንጭ «ዓውደ ምሕረት» ብሎግ ነው።

Friday, July 6, 2012

በዓለመ መላእክት ቤተክርስቲያን የሚባል አልነበረም!



 
 
ክርስቲያን የሚለው ስም የተጀመረው ከክርስቶስ ሰው መሆን በኋላ ነው። ክርስቶስ ሰው ሳይሆን ክርስትና አልበረም። ባልነበረ ክርስትና እንዴት ሆኖ ነው በዓለመ መላእክት ቤተ ክርስቲያን  ነበረ የሚባለው? ማኅበረ ቅዱሳን ግን በድረ ገጹ ላይ ከክርስቶስ ሰው መሆን አስቀድሞ ቤተክርስቲያን በዓለመ መላእክት ነበረ ይለናል። ይህ አዲስ ግኝት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያልተጻፈ ነገር ግን በማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር የተገኘ። ሰይጣን በዐመጽ ሳቢያ የነበረበትን ስፍራ ለቀቀ ማለት አንድ ነገር ነው፤ ነገር ግን ሰይጣን ቤተክርስቲያንን መፈታተን የጀመረው በሰማይ ነው ማለት የማንን ክርስትና ለማስተጓጎል የሚል ጥያቄን ያስነሳልና ነገር ዓለሙ አማረልን ብሎ ያለ የሌለውን ለማስመሰል መሞከር ትክክል አይደለም። ወይም ከክርስቶስ ሰው መሆን በፊት በሰማይ ክርስትና ተሰብኳል በሉንና እስከወዲያኛው አስገርሙን። ያለበለዚያ የሌለ ነገር በመፍጠር ልታሞኙ ሳይሆን ልታሳስቱ አትሞክሩ።