Friday, July 6, 2012

በውኑ፣ ክርስቶስ ያማልዳልን?


 አንዳንዶች ስለክርስቶስ የማማለድ ሥራ ለመቃወም ሲሉ መጽሐፍ ቅዱስን እስከመደለዝ ደርሰዋል። ሰብዓ ሊቃናትና ዐበይት የአብያተ ክርስቲያናት ጉባኤያት ያጸደቋቸውን የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ትርጓሜ በመሰረዝ የራሳቸውን ክልላዊ መጽሐፍ ቅዱስ እስከማሳተም የደረሱት የክርስቶስን ሥጋ የመልበስን ምስጢርና አሁንም በአብ ቀኝ የተቀመጠበትን አምላክ ሰው የሆነበትን ማንነት ለመጠበቅ ሲሉ የግሪኩንና እብራይስጡን ትርጉም ሰርዘውታል። በአንድ በኩል መናፍቃን ለራሳቸው እንዲያመቻቸው የወንጌል ቃልን ይሰርዛሉ፤ ይደልዛሉ እያልን በሌላ መልኩ ወቃሾች፤ የተወቃሾችን ታሪክ መድገም መደለዝ በመሠረቱ አሳዛኝ ነገር ነው። አበው ያቆዩትንና የተጻፈልንን እውነት ይዞ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ቃል ግልጽልጽ አድርጎ መመለስ ሲገባ፤ የተጻፈውን ሰርዞ፤ ከማስተማር ለመደበቅ መሞከር አስደንጋጭ ነው። ይህንን ከእውነት የመሸሽ ተግባር በማብራራት ከታች የቀረበው ጽሁፍ አንድ ነገር ይጠቁመናል። መሰረዛቸውን የማይክዱ ግን በመሰረዛቸው ከሲኖዶሳውያት ጉባዔያት ጋር ለምን እንደተለያዩ ማሳመን የማይችሉ ሰዎች ይህን ጽሁፍ ሲያነቡ ጆሮአቸውን ሊያስክክ፤ ዓይናቸውንም ሊያጨልም ይችላል።
የጽሁፉ ባለቤት «አድነው ዲሮ» ይሰኛሉ። መልካም ንባብ ይሁንልዎ!

I. መግቢያ፡- የሰው ልጅ ውድቀት

የዚህ ጽሁፍ አቢይ አላማ በየዕለቱ ስለ ሚገጥሙን የሕይወት ውጣ ወረዶች አንጻር፣ ስለታመሙ ሰዎች፣ በእስር ስላሉ ሰዎች፣ ስለ መሪዎች፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን፣ ስለ አገር፣ ስለ አገልግሎት፣ ወዘተ አንዱ ለሌላው ወደ ፈጣሪው የሚያደርሰው የምልጃ ጸሎት፣ ክርስቶስ ለእኛ ባደረገው የማማለድ ሥራ ላይ ጥላውን እንዳያጠላበት ጥንቃቄ እንድናደርግ ለማሳሰብ ነው፡፡ እንደነዚህ አይነቶቹ - አንዱ ስለ ሌላው የሚጸልየው ጸሎት - ክርስቶስ ለእኛ ከፈጸመው የምልጃ ሥራ ጋር ምንም ዝምድና እንደሌለው ማሳሰብና እነዚህ ሁለት ነገሮች ሊነጻጸሩም ጭምር እንደማይገባ ማሳየት፣ የማንም ሰው የጸሎት ምልጃ የክርስቶስን የመስቀል ላይ ምልጃ ሊተካው እንደማይችል መግለጽ፣ እንዲያውም አንዳችን ለአንዳችን የመጸለይ (የመማለድ) ፈቃድ ያገኘነው በክርስቶስ የምልጃ ሥራ ከእግዚአብሔር ጋር ስለታረቅንና ከተቆጣን ፈጣሪ ጋር ሰላም ስለፈጠርን መሆኑን ማስገንዘብ የዚህ ጽሁፍ ዋነኛ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ይህንን አሳብ ለመገንዘብ ይረዳን ዘንድ ከችግሩ መነሻ ማለትም ከሰው ልጅ የውድቀት ታሪክ እንነሳና ጉዳዩን በጥልቀት እንመልከት፡፡ 

የሰው ልጅ፣ አጽናፈ ዓለሙ፣ የምድር አራዊት፣ የሰማይ ወፎች፣ የባሕር ዓሶች ከተፈጠሩ በኋላ በፈጣሪው አምሳል በስድስተኛው ቀን የተፈጠረ ልዩ ፍጥረት ነው፡፡ ከእርሱ ቀድሞ የተፈጠሩትን ይገዛና ያስተዳድር ዘንድ ሃላፊነት ጭምር የተሰጠው ይህ ሰው፣ ይኖርበት ከነበረው ኤደን ገነት የአንዲቷን ዛፍ ፍሬ እንዳይበላ ከፈጣሪው ትእዛዝ ተሰጠው፡፡ በፈጣሪው ላይ መታመን ያልፈለገው የሰው ልጅ በትዕቢት ከፍሬዋ ቀጥፎ በላ፡፡ ከፍሬዋ በበላህ ጊዜ ሞትን ትሞታለህ ያለው አምላክም ጻድቅ ፈራጅ እንደ መሆኑ፣ የጽድቅ ብያኔውን በራሱ ላይ ተደግፎ ለመኖር በወሰነው በዚህ የሰው ልጅ ላይ አስተላለፈ፡፡ ከብያኔዎቹ መካከል አንዱ እንዲህ ይነበባል - «... የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፣ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም በልተሃልና፣ ምድር ካንተ የተነሳ የተረገመች ትሁን፤…´ (ዘፍ. 317)፡፡

የሰውና የፈጣሪ ጠብ እንግዲህ ከዚህ መጥፎ ጊዜ ይጀምራል፡፡ ከዚህች ቀንና ሰዓት ጀምሮ ሰውና ፈጣሪው ጥለኞች ሆኑ፡፡ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያዘጋጀውም መልካም ሃሳብ በሰይጣን ፈታኝነት፣ በሰው ልጅ ተባባሪነት እንቅፋት ገጠመው፡፡ አግዚአብሔር ሕግ ሰጠ፣ የሰው ልጅ ተላለፈው፣ ፈጣሪም የጽድቅ ፍርድ አስተላለፈ፡፡ ይህም ፍርድ ሞት ይባላል፡፡ የሰው ልጅ በሞት ፍርሃት ውስጥ እየማቀቀ ለበርካታ ዓመታት በምድር ላይ የስቃይ ኑሮ መግፋት ጀመረ፡፡

ይህን ፍርድ ያስተላለፈው አምላክ ጻድቅ ብቻ ሳይሆን የፍቅር አምላክ በመሆኑ፣ ከእስትንፋሱ የተካፈለው ሰው በምድር ላይ ሲሰቃይ ማየት አላስቻለውም፡፡ በዚህም ምክንያት ጻድቅ ፈራጅነቱንና የፍቅር አምላክነቱን አዋህዶ የሚያሳይ ሌላ የደኅንነት መንገድ ለሰው ልጅ አዘጋጀ። ይህ የደኅንነት መንገድ ጽንፍ የሚመስሉትን የአምላክ ሁለት ባሕሪያት (ፍርድና ምሕረት) በአንድ መስመር ያገናኘ አስገራሚ ክስተት ነበር፡፡ እግዚአብሔር በሰው ዘር ሁሉ ላይ ያሳለፈው ሊታጠፍ የማይችል የሞት ፍርድ ሳይቀለበስ የሰው ልጅ ከተቆጣው አምላኩ ጋር ታረቀ፡፡ የአገራችን የእምነት ሊቃውንት ይህንን ሁኔታ ግሩም በሆነ መንገድ እንዲህ በማለት ይገልጹታል፡፡ «እግዚአብሔር ሰውን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ ያዳነበት ጥበቡ ተጠበበች፡፡´ የዚህ አስገራሚ ትእይንት ጀማሪና ፈጻሚው ደግሞ ምንም በደል ያልተገኘበት ኢየሱስ ነበር፡፡ እግዚአብሔር በሰው ልጅ ላይ የተቆጣውን ቁጣ በኢየሱስ ላይ አሳረፈው፤ ፍርዱን አሳየ፡፡ ኢየሱስ ስለ ኃጢአተኞቹ ስለ እኛ ሞተ፡፡ በእርሱም ምክንያት የሰው ልጅ ምሕረትን ተቀበለ፡፡ ከፈጣሪውም የፍርድ ቁጣ ተረፈ (ሮሜ. 59)፡፡

የብሉይና የሐዲስ ኪዳናት መሰረታዊ ጭብጥም ይኸው ታላቅ ሥራ ነው፡፡ ብሉይ ኪዳን የሐዲሱ ኪዳን ጥላ/ምሳሌ እንደ መሆኑ፣ የሰው ልጅ የደኅንነት መሰረት የሆነው (1ቆሮ. 310-11) ክርስቶስ ዘመኑ ደርሶ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እስኪመጣ ድረስ፣ የሰው ልጅ በታላቅ ምጥ ውስጥ ነበር፡፡ ጥላ የነበረውንና የሰውን ልጅ ፍጹም ሊያደርገው የማይችለውን የእርቅ ሥርዓት (ዕብ. 9910) እየፈጸመ ከአምላኩ ጋር ሊያስታርቀው የሚችለውን የደኅንነት ተስፋ መጠበቅ ጀመረ፡፡ አንዳንዶች ይህን ተስፋ በሩቅ ተሳለሙት (ዕብ. 1113 114940) ሊሎች ደግሞ ይህን ተስፋ በዓይናቸው አዩት (ሉቃስ 229-32)፡፡ የዚህ ጽሑፍ አንባቢ እርስዎና እኔ ደግሞ በዚህ የምሕረት ዘመን ውስጥ ለመገኘት የእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ሆነ፡፡
የሰው ልጆች ሁሉ ተስፋ የነበረው፣ የዓለሙን ሁሉ ኃጢአት የሚቤዠው፣ ሰውንና እግዚአብሔርን የሚያስታርቀው፣ የተዋረደውንና በውድቀት ከእግዚአብሔር ቁጣ ስር ለሞት የሚጠበቀውን የሰውን ዘር የሚታደገው ብቸኛ አዳኝ እስኪመጣ ድረስ፣ የሰው ልጅ የዚህን ፍጹም ተስፋ ጥላ እየተከተለ አካሉን ናፈቀ፡፡ ጥላው የነበረውን የብሉይ ሥርዓት እየፈጸመ የአካሉን መገለጥ ለእልፍ ምዕት ዓመታት በናፍቆት በጠበቅ ግድ ሆነበት፡፡ ከዚህ በታች ባሉት ጥቂት አንቀጾች ከሰው ውድቀት አንስቶ እስከ መሲሁ መምጣት ድረስ የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር ተቀባይነት ያለውን ሕብረት ለማድረግ፣ የኃጢአት ሥርየትን ለማግኘትና የምስጋና መሥዋዕት ለማቅረብ ምን ነገሮችን ይፈጽም እንደነበረ አለፍ አለፍ እያልን እናያለን፡፡ ይህ የብሉይ ሥርዓት ሊመጣ ያለው እውነተኛ አካል ጥላ/ምሳሌ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይበል፡፡ በዚህ ስር የምናያቸው ቁም ነገሮች ግልጽ ከሆኑ፣ ኋላ ላይ የምናየው የሐዲስ ኪዳኑ አካል ፍሬ አሳብ ፍንትው ብሎ ይታየናል፡፡

Wednesday, July 4, 2012

"ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ"


                                         የጽሁፍ ምንጭ፤ ዓውደ ምሕረት

ማኅበረ ቅዱሳን ደጀ ሰላም በተባለው አሸባሪ ብሎጉ ጉባኤ አርድእት የተባለ ማኅበር ተቋቋመብኝ ይህ ማኅበር ደግሞ አያያዙ በሞኖፖል ይዠው የነበረውን የቤተክህነት ሥልጣን ሊነጥቀኝ ነው። የተሰበሰቡት ሰዎችም ከኔ ጨዋና ጥራዝ ነጠቅ አመራሮች የተሻሉ ስለሆነ ግርማ ሞገሳቸው አስፈርቶኛል የሚል አንድምታ ያለው ባለ 9 ገጽ ጽሁፍ ከለቀቀ በኃላ ይህ ገና ከመቋቋሙ ማኅበሩን በጥላው ያሸበረው ጉባኤ አለማው ምንድን ነው? በማለት በቤተክህነት አካባቢ ያለውን ነገር እያጣራን ሳለ gubae ardiet የሚል የፌስ ቡክ ገጽ ላይ አላማውን የሚያስረዳ ጽኁፍ ስላገኘን አላማውን ታውቁት ዘንድ ልናቀርብላችሁ ወድደናል።
ማኅበረ ቅዱሳን በአንድ እግሩ ፖለቲካ በሌላኛው እግሩ ሃይማኖት እየረገጠና በሁለት ሀሳብ እያነከሰ ያለ እኔ ቤተክርሰቲያን ዋጋ የላትም እያለ ቤተክርስቲያንን ለዘመናት ሲጠብቅ የነበረውን መንፈስ ቅዱስን ስፍራ ልቀቅ በማለት ያለአቅሙ እየተውተረተረ በየአቅጣጫው አቧራ በመበተን ቤተክርሰቲያንን እየረበሸ በመገኘቱ ያሳዛናቸው የቤተክህነት ሠራተኞች የመምሪያ ኃላፊዎችና የደብር አለቆች የተሰባሰቡበት ጉባኤ አርድእት አላማው በጽሁፉ እንደሚነበበው ቤተክርስቲያንን ከምንደኞችና ከእበላ ባዮች ለመታደግ እና አባቶችን በሚያስፈልገው ሁሉ ለመርዳት ነው።
እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ሁላችንም የምናውቅ ኦርቶዶክሳዊ ጋብቻ የሚባሉ የቤተከርስቲያኒቱ አባለት እርስ በርስ በተገቢው የቤተክርስቲያን ሥርዓት ሲጋቡ ነው። ማኅበረ ቅዱሳን እራሱን ከማኅበርነት ወደ ቤተክርሰቲያንነት ስለቀየረ ማህበረ ቅዱሳን ያልሆነ ሰው እንዳታገቡ የሚል ቀጭን ትእዛዝ ለአባላቱ አስተላልፎል። እንዲህ ያለው በቤተክርስቲያን ላይ የተቋቋመው የአንጃነት ስሜት በሙስሊሙ እንደተቋቋመውና አውነተኛ ሙስሊም ሰለፊ ነው እንደሚለው የሰለፊያ አስተሳሰብ  ሁሉ ኦርቶዶክሳዊነት ማለት ማኅበረ ቅዱሳንነት ነው ወደሚል አባዜ መቀየሩ አስጊነቱን የተረዳው መንግስት ከሁለት ሳምንት በፊት መንገድ ትራንስፖርት በማህበሩ ዋና ሰው በሆነው አቶ ካሳሁን ቢሮ የባለስልጣን መስሪያ ቤት ሠራተኞችን ሰብስቦ  “ማኅበረ ቅዱሳን ከሚባል ሃይማኖት ተጠበቁማለቱ የሚታወስ ነው። 
አሁንም ህዝቡ ማኅበረ ቅዱሳን ከሚባል ሃይማኖት እራሱን እንዲጠብቅ እና በቤተክርስቲያን ጥላ ውስጥ ብቻ እንዲሰባሰብ ኃላፊነት ያለባቸው በትምህርትም በአገልግሎትም የተመሰከረላቸው እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆች የሆኑ የመምሪያ ኃላፊዎች ሌሎች በቤተክርስቲያኒቱ በኃላፊነት ቦታ ላይ ያሉ አገልጋዮች ያቋቋሙት ይህ ጉባኤ በጥላው ማኅበሩን እንዲህ ያስበረገገ ሥራ ሲጀምርማ ምን ውጤት እንደሚያመጣ በጉጉት የሚጠበቅ ሆኗል። አለማውን በተመለከተ የተዘጋጀውን ጽኁፍ እንድታነቡት አቅርበናል። መልካም ንባብ ይሁንላችሁ።
ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት
ሐዋርያት በሰበሰቡአት፣ ከሁሉ በላይ በሆነች በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡
"ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ"
"የአርድእት መንፈሳዊ ኅብረትን ለመመሥረት የቀረበ መነሻ ጽሑፍ"
"ወንድሞች በኅብረት ቢኖሩ እነሆ መልካም ነው፤ እነሆም ያማረ ነው" (መዝ 132(133) 1)

Tuesday, July 3, 2012

ትውልድ ያላወቀው ኢትዮጵያዊው ሰው!



ብዙዎቻችን ኢትዮጵያዊ መሆን ማለት ኢትዮጵያ ውስጥ መወለድ ብቻ አድርገን እንቆጥራለን። ያ ግን ከእውነታው ብዙ የራቀ አስተሳሰብ ነው። በምንም መመዘኛ ኢትዮጵያ ውስጥ መወለድና ኢትዮጵያ ዜጋ መያዝ ማለት ኢትዮጵያዊ ማለት አይደለም የሚል አቋም አለኝ። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ ማለት በኑሮው፤ በባህሉ፤ በወጉ፤ በቋንቋው፤ በእምነቱ፤ በታሪኩ፤ በድርጊቱ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ሆኖ መገኘት ነውና። ባህሉን፤ አኗኗሩን፤ ወጉን፤ ቋንቋውን ታሪኩንና እምነቱን፤ትውፊቱን ሁሉ ከኢትዮጵያዊነት አተያይ ውጪ ያደረገ ትውልድ እንደ ሸቀጥ /Made in………/ ተብሎ ኑረቱ የሚገለጽበትን የባእድ ሀገር የማንነት ስያሜ ይሰጠዋል እንጂ ኢትዮጵያዊ ሰው ሊባል የተገባው አይደለም። ኢትዮጵያዊ ሆኖ ከመኖር ውጪ ኢትዮጵያዊነት ሊኖር አይችልምና። ያ ማለት ግን ከሌላው ዓለም ሚዛን ጋር ራሱን እየጠበቀ፤ የጎደለውን እየሞላ፤ የጎዳውን እያረመ አይሄድም ማለት ሳይሆን ማንነቱን በሌሎች ማንነት ውስጥ በመለወጥ፤ በመተካት ወይም በመደረት  ኢትዮጵያዊ መባል እንዳይቻል  ለማሳየት ተፈልጎ ነው።

ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የተጻፉ ሰፋፊ ጥናቶች እንደተጠበቁ ሆነው በዚህ ጽሁፍ ለመዳሰስ የተፈለገው በርእሱ ላይ የተጠቀሰውን «ትውልድ ያላወቀው ኢትዮጵያዊውን ሰው» በተመለከተ በአጭር ምልከታ ለማብራራት ነው።
«ትውልድ ያላወቀው ኢትዮጵያዊ ሰው» በብዙዎች ዘንድ መምሩ/መምሬ/ ወይም ቄስ ተብሎ በማእረገ ክህነቱ የሚጠራው የኢትዮጵያው የገጠር ቤተክርስቲያን አገልጋይ /ካህን/ ነው። በእርግጥ ዘመኑ መምሩ/ መምሬ/ ወይም ቄስ የሚለውን ስመ ተጸውኦ ሲያዘምነው በከተሜው ዘንድ «ቀሲስ» መባሉ ቢታወቅም ያ የገጠሩ ቄስ/ መምሩ/፤ ከዚህ እንግዳ የዝመና ጥሪ ጋር ብዙም ትውውቅ ስለሌለው ያችን ከምንም በላይ የሚያከብራትን፤ የሚወዳትንና የሚጠብቃትን የ«መምሬ» እገሌን ጥሪ እስከዛሬ ሳይለቅ እንደያዘ ይገኛል። ቄስ እገሌ ወይም መምሬ እገሌ ተብሎ መጠራታቸው ለእነርሱ ኩራታቸውና ክብራቸው  ስለመሆኑ በቅርብ የምናውቃቸው ዘመዶቻችን እንደሚናገሩ  ለዚህ ዋቢዎች ነን።


እነ መምሩ/መምህሩ/ የሚከበሩትና  የሚወደዱት ገጠር ስለኖሩ ሳይሆን ለነግህ ኪዳን፣ ለሰርክ ጸሎት የሚተጉ ከመሆናቸው ባሻገር እንደ ተራው ህዝብ ኑረትን ኖረው፤አርሰው ቆፍረውና ጎልጉለው የሚተዳደሩ፤ የተጣሉትን አስታርቀው፤ የታመሙትን ጠይቀው፤ በቤታቸው፤ በጎረቤታቸውና በአካባቢያቸው ፈሪሃ እግዚአብሔርን ኖረውትና አስተምረው፤ ሕዝቡ በግብረ ገብነትና በመከባበር ማኅበራዊ ኑሮውን በኅሊና ዳኝነት እንዲገፋ በማድረግ ከማንም በላይ ኢትዮጵያዊነት የሚታይባቸው የሕብረተሰብእ አንጓዎች በመሆናቸው ነው።
እነመምሩ በቀደሙት ዘመናት ከቤተክርስቲያን የምትሰጣቸውን 10 ብርና 20 ብር ወይም በቁና የምትሰፈርላቸውን የእህል  የድርጎ መዋጮ እንደክፍያ ቆጥረው ሳይሆን ኃላፊነትና ግዴታቸውን አውቀው በማኅሌቱ፤ በሰዓታቱ ቆመው ሲያድሩ ብርታታቸውና ጥንካሬአቸው በእውነቱ ያስገርማል። የሀገር ዳኛ ሳለ እነመምሩ የምእመናን ዳኛ ናቸው። ቃላቸው ይፈራል፤ ይከበራል። ምክራቸውና ተግሳጻቸው በሁሉም ዘንድ ቅቡል ነው።