በ2ኛ ሳሙ.11፤1 እንዲህም ሆነ በአመቱ መለወጫ-
-በ2ኛ ሳሙ.11፤1 እንድህም ሆነ በአመቱ መለወጫ ነገሥታት ወደ ሰልፍ በሚውጡበት ጊዘ ...ዳዊት ግን በእየሩሳሌም ቀርቶ ነበር።
ጥያቀ 1ኛ .የእሰራኤላዉያን የአመት መለወጫ የትኛው ወር ነው?ከ4ቱ ወቅቶች በየትኛው ውስጥ ይመደባል?እንደ እትዮጵያውያንሰ?
2ኛ.ነገሥታት ለሰልፍ የአመት መለወጫን ለምን መረጡ?
3ኛ.የእስራኤላውያን ግብርና ሁኔታስ ለስልፍ በሚውጡበት ጊዘ በምን ሁኔታ ላይ ይገኝ ነበር? ለግንዛቤ(4ቱ ወቅቶች winter,spring,summer,autumn)
አስተያዬት፦
ጥያቄ ካበዘሁባችሁ አስተዬታችሁን እፈልጋለሁ። እስካሁን እየጠየቅሁችሁ ላለው ጥያቄ አጥጋቢ መልስ እያገኘሁበት ሰላለ እ/ር አብዝቶ ይባርካችሁ።ቃሉን የሚገልጥ መንፈስ አብዝቶ ይጨምርላችሁ። Yonni Tibesso
(የደጀብርሃን መልስ)
የእብራውያን አዲስ አመት እንደኢትዮጵያውያን ወር አቆጣጠር በመስከረም ወር ላይ ነው። ወሩ በአብዛኛው በወሩ በ1ኛው ወይም በ2ኛው ቀን ላይ ይውላል።
በእብራይስጥም ሮሽ ሃሸና ראש השנהይባላል። «ሮሽ ሀሸና» ማለት የወሮች ሁሉ ራስ ማለት ነው። የኛው መስከረም ደግሞ «ትሽሪ» תִּשְׁרֵיይባላል። ከወቅቶች አቆጣጠር ደግሞ autumn ወይም በልግ የሚባለውን ይይዛል። ወርሃ ክረምት ከመግባቱ በፊት የሚመጣ ወር ነው።
እብራውያን አዲስ ዓመት አድርገው መስከረምን ያክብሩ እንጂ መስከረም የዓመቱ የመጀመሪያ ወር አይደለም። የዓመቱ
የመጀመሪያ ወር ሚያዚያ ነው። ሚያዚያ የመጀመሪያ ወር ሊሆን የቻለው እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ነጻ የወጡበት
በዚህ ወር ስለሆነ ነው።
«ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ ይሁናችሁ የዓመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ» ዘጸ 12፣2
«በመጀመሪያው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን ሲመሽ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው» ዘሌ 23፣5
እሱም ኒሳን נִיסָן ይባላል።
ኒሳን የመጀመሪያው ወር ስለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ያረጋግጥልናል።
« አስቴር 3፥7
በንጉሡም በአርጤክስስ በአሥራ ሁለተኛው ዓመት ከመጀመሪያው ወር ከኒሳን ጀምሮ በየዕለቱና በየወሩ እስከ አሥራ ሁለተኛው ወር እስከ አዳር ድረስ በሐማ ፊት ፉር የተባለውን ዕጣ ይጥሉ ነበር»
ወደጥያቄህ ስንገባ ነገሥታቱ በሚያዚያ ወር መጀመሪያ ላይ ከጠላቶቻቸው ጋር ይዋጉ የነበረው፤ የነገረ መለኰት ምሁራን ይህንን ያስቀምጣሉ።
1/ ከግብጽ ባርነት ነጻ የወጡበት ወር በመሆኑ፣ በዚህ ወር ድል ሁሉ የእነሱ እንደሆነ ያምናሉ።
2/ የሀገራቸው ክረምት የሚያልቅበት ጊዜ በመሆኑ፣ከጭለማና ከአረንቋ ይልቅ ብርሃኑ ሲገልጥ ውጤታማ እንደሚሆኑ ስለሚያምኑ፤
3/ ጠላቶቻቸውም ይህንን ሰማይና ምድሩ የሚገፍበትን ጊዜ ጠብቀው ስለሚያጠቋቸው አስቀድሞ መምታት እንደሚገባቸው በማመን፣
ጥንት ጠላቶቻቸው ሲመክሩ እንዲህ ሲሉ ይጠጠቡባቸው ነበርና እስራኤላውያንም ሲጠበቡባቸው ይህንን ወር ይመርጡት ይሆናል።
«እንዳይበዙ፥ ሰልፍም በተነሳብን ጊዜ ጠላቶቻችንን አግዘው እንዳይወጉን ከምድሪቱም እንዳይወጡ፥ ኑ እንጠበብባቸው አለ» ዘጸ 1፣10
ስለዚህ እስራኤላውያንም በመጠበብ ይህንን ወቅት ይመርጡታል።
እ/ር ለሳኦል ያልመለሰበት ምክንያቱ ምንድነው?ማነው ትክክል?-
-1ኛ ሳሙ. 14፤ 37 በሚገኘው ክፍል እ/ር ለሳኦል ያልመለሰበት ዮናታን ከወለላው ስለ በላ ነው?የሳኦልስ ዉሳኔ ትክክል ነበር?1ኛ
ሳሙ. 14፤24 ሳኦል ጾምን አወጀ ቁጥር 27 ላይ ዮናታን ስላልሰማ ከወለላው በላ አይኑም በራ ቁ.30 ህዝቡም
ሁሉ ቢበሉ ይበረቱ ነበር ነገርግን ለሳኦል መልስ ማጣት ምክንያት ሆኖ የተገኘው ዮናታን ሆነ እጣ ስለወደቀበት ግን
በህዝቡ ድምጽ ዮናታን ከመሞት ዳነ.
ትክክል ያደረገው ሳኦል ነው ወይስ ዮናታን ወይስ ህዝቡ? የተጠቀሱትን ጥቅስ በማስታረቅ ብታብራራው። እ/ር ይባርክህ።
በyoni Tibesso
መልስ በደጀብርሃን
ይህ ጥያቄ ሰፊ ነገሮችን ወደመዳሰስ ይወስደናል። ስለሆነም ወደጥያቄህ ጭብጥ ከማምራታችን በፊት እስኪ ሕዝቡን፣ ሳኦልንና ዮናታንን ለየብቻቸው እንመልከታቸው።
ሕዝቡ፣
1/ ሕዝቡ ለእግዚአብሔር አልገዛም በማለቱ ታቦተ ጽዮን ተማርካ ነበር። በኋላም ተመልሳ አቢዳራ ቤት ተቀምጣ ሳለ ሕዝቡ ከጣዖት አምልኮ እንዲወጣ ሳሙኤል አስጠንቅቋቸዋል።
«ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ። በሙሉ ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር ከተመለሳችሁ እንግዶችን አማልክትና አስታሮትን
ከመካከላችሁ አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ እግዚአብሔር አቅኑ፥ እርሱንም ብቻ አምልኩ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ያድናችኋል
ብሎ ተናገራቸው» 1ኛ ሳሙ 7፣3
ሕዝቡም ያለ ንጉሥ በሳሙኤል ነብይነትና ፈራጅነት ይተዳደሩ ነበር።
2/ የእስራኤል ሕዝብ ነብይና ፈራጅ ሆኖ ሳሙኤል ለብዙ ዓመታት ቆይቷል። ሳሙኤል እርጅና እየተጫጫነው በመሄዱ
በእርሱ ምትክ ልጆቹን ኢዮኤልና አብያን ሾሞላቸዋል። ይሁን እንጂ የነብዩ ሳሙኤል ልጆች ጉቦ እየተቀበሉ ፍርድን
እያጣመሙ ሕዝቡን አስመረሩ እንጂ በአባታቸው መንገድ አልሄዱም።(1ኛ ሳሙ8፣2-3)
በዚህም የተነሳ ሕዝቡ ሳሙኤልን ንጉሥ በላያቸው ላይ እንዲሾምላቸው ግድ ብለው ያዙት።
«እነሆ፥ አንተ ሸምግለሃል፥ ልጆችህም በመንገድህ አይሄዱም አሁንም እንደ አሕዛብ ሁሉ የሚፈርድልን ንጉሥ አድርግልን አሉት» (ቁ፣5)
3/ እግዚአብሔርም ለሳሙኤል ተናገረው። እኔን አላከበሩኝም እንጂ የአንተን ነብይነት ስላልዘነጉ እንደጥያቄያቸው ሹምላቸው አለው።
«እግዚአብሔርም ሳሙኤልን አለው። በእነርሱ ላይ እንዳልነግሥ እኔን እንጂ አንተን አልናቁምና በሚሉህ ነገር ሁሉ የሕዝቡን ቃል ስማ» 1ኛ ሳሙ 8፣7
እንደሕዝቡ ጥያቄ ሳኦል በነሱ ላይ በሳሙኤል ተቀብቶ ነገሰ።
«ሳሙኤልም የዘይቱን ብርሌ ወስዶ በራሱ ላይ አፈሰሰው፥ ሳመውም፥ እንዲህም አለው፦ በርስቱ ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ
እግዚአብሔር ቀብቶሃል የእግዚአብሔርንም ሕዝብ ትገዛለህ፥ በዙሪያውም ካሉ ጠላቶቻቸው እጅ ታድናቸዋለህ» 1ኛ ሳሙ
10፣1
ስሙ ያልገለጸ ጠያቂ፣
እንደ ሮም፣ምዕራፍ 8 ሃሳብ ልጅነት ምንድን ነው?ስንት አይነት ልጅነትስ አለ?
የደጀብርሃን መልስ፣
ሰው ሁለት ልደት እንዳለው መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። መጀመሪያ ከእናትና ከአባት የምንወለድበት ሥጋዊ ልደትና ቀጥሎም ከእግዚአብሔር የምንወለድበት መንፈሳዊ የእግዚአብሔር ልጅነት ናቸው።
«ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው» ዮሐ 3፣6
ሥጋዊውን ልጅነት አይሁዳዊው ይሁን አረማዊው፤ ግሪካዊ ይሁን ሲሮፊኒቃዊ ሁሉም ይህን የሥጋ ልደት ያለ ልዩነት ያገኙታል። መንፈሳዊውን ልጅነት ግን በእምነት ብቻ የሚያገኙት ስጦታ ነው።
ሥጋዊው ልደት ምድራዊ ሲሆን መንፈሳዊው ልደት ሰማያዊ ነው። ሥጋዊውን ልደት የእግዚአብሔርን ሕልውና ቢያውቅም
ባያውቅም፣ ቢያምንም ቢያምንም ሊያገኝ ይችላል። መንፈሳዊውን ልደት ግን በአንድያ ልጁ ያላመነ ማንም ቢሆን ሊያገኘው
የሚችለው ልጅነት አይደለም።
«ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው» ዮሐ 3፣3
ሰው ይህንን መንፈሳዊ ልጅነት እንዴት ሊያገኝ ይችላል?
እስራኤላውያን ከምድረ ግብጽ ከወጡ በኋላ የሖር ተራራን አልፈው ወደ ከነዓን ምድር ሲደርሱ እንዲህ ሲሉ በእግዚአብሔር ላይ አጉረመረሙ።
«ሕዝቡም በእግዚአብሔርና በሙሴ ላይ። በምድረ በዳ እንሞት ዘንድ ከግብፅ ለምን አወጣችሁን? እንጀራ የለም፥ ውኃ የለም ሰውነታችንም ይህን ቀላል እንጀራ ተጸየፈ ብለው ተናገሩ» ዘኁ 21፣5
ይህን ቀላል እንጀራ ሰውነታችን ተጸየፈ አሉ። ሳያቦኩና ሳይጋግሩ የሚበሉትን የሰማይ እንጀራ የሆነውን መና
ተጸየፉት። ከሰማይ የወረደውን መና የጠሉ ሁሉ መጨረሻቸው ሞት ነውና በእነዚህ ሰዎች ላይ የሞት መርዝ ያለው ጠላት
እባብ ገባባቸው።