ሊቀ ትጉሃን ተሾመ ኃይለ ማርያም በ"ማኅበረ ቅዱሳን" ሤራ በፖሊስ ተይዘው ወደ ነጌሌ ቦረና ተወሰዱ
በቆሞስ መልአከ ገነት አባ ሙሉጌታ ታዬ የክብረ መንግሥት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ላይ የተቃጣው የግድያ ሙከራ ከሸፈ
የካቲት
16 ቀን 2004 ዓ.ም በክብረ መንግሥት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ የሚከበረውን የቅድስት ኪዳነ
ምሕረት በዓለ ንግስ በመረበሽ ያስተጓጎሉት ሃያ አምስት የማኅበረ ቅዱሳን አባላትና አፍቃሬ ማኅበረ ቅዱሳን ተከሳሾች
ለመጋቢት 19 ቀን 2004 ዓ.ም ቀነ ቀጠሮ ቀርበው እንዲከላከሉ ተበይኖባቸዋል፡፡ ዐቃቤ ሕግ አሥራ ሦስት
ምሥክሮችን ያሰማ ሲሆን ክሱን በጽሑፍ፣ በሰውና በምስል ማስረጃ አጠናቅሮ አስረድቷል፡፡ በተጨማሪም ሰባት ምሥክሮች
ቃለ መሐላ ከፈጸሙ በኋላ ዐቃቤ ሕጉ በቃኝ ሳይሉ ምክንያቱ በግልጽ ባልታወቀ ምክንያት ዳኛው አቶ ጉዩ እንዳይመሠክሩ
አስቁመዋል ተብሏል፡፡
በዚህም
ሳቢያ ስምንት ቀንደኛ በጥባጮች በዚያው ዕለት 29/6/2004 ዓ.ም በነፃ አሰናብተዋቸዋል ተብሏል፡፡ ከነዚህ
ስምንት ቀንደኛ መሪዎች ውስጥ መሪጌታ መዝገቡ ጌታነህ፣ ቄስ መኮንን ጉቴሳ (የአንድ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የታሪክ
መምህር)፣ ወ/ሮ ሃይማኖት ጥላሁን፣ ወ/ሮ መቅደስ፣ ዲ/ን እንዳሻው፣ ዲ/ን ብንያም፣ ዮናስና ጌትነት የተባሉት
መሆናቸው ታውቋል፡፡ በተለይም የእነዚህ ቀንደኛ በጥባጮች መለቀቅ፣ የከተማውን ኅብረተሰብ፣ የፍትሕና የፀጥታ
አካላትን ማስቆጣቱ ተመልክቷል፡፡