የጽሁፉ ባለቤቶች (ለእስልምና መልስ አዘጋጅዎች ነው)
አንደኛው፡
የጥንቱ የመጨቆንና የማንቋሸሽ መንገድ እንደገና ተጀመረ፣ እነዚህ መንገዶች ከጣሊያን ወረራ ጥቂት ቀደም ብሎ በተከሰተው ምስጢራዊው የልጅ ኢያሱ ሞት አበቁ፡፡
ሁለተኛው፡
ሙሉ ለሙሉ አዲስ ወደ ሆነ አቀራረብ በድንገት ቀልበስ ማለት ነበር፡፡ ስለዚህም በ1935 በመጀመሪያዎቹ አካባቢ ንጉሱ ኃይለስላሴ እራሱን የተለያየ ማህበረ ሰብ አካላት መሪ አድርጎ ማቅረብ ጀመረ፡፡ እርሱም በተለያዩ ቦታዎች ላይ በታላቋ ኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት እኩልነት እንደሚኖር ንግግር አደረገ፡፡ አያይዞም በግንቦት 22 1935 ለሐረር የማህረሰብ መሪዎች ንግግርን አደረገ፡፡ የንጉስ ኃይለስላሴም ዋና መልእክት የነበረው ሁሉንም ሃይማኖቶች፣ ሁሉንም ጎሳዎች፣ በአዲሲቱ የኢትዮጵያ ሞዴል ማለትም “ክርስትያን ባልሆነው ነገር ግን ከልዩ ልዩ አካል በተውጣጣው የኢትዮጵያ ሞዴል” ውስጥ ለማካተት መሞከር ነበር፡፡ እርሱም የሁሉም ሃይማኖት እኩልነት ያለበት ህገ መንግስትን እንደሚያወጣ ቃል ኪዳንን ገባ፡፡ ሙስሊሞችን የማባበሉ የእርሱ አዲሱ ጥረት ያካተተው በአዲስ አበባ ውስጥ የአረብ ቋንቋ ጆርናል እንዲታተም እና በሚኒልክ ትምህርት ቤት ውስጥ አስተማሪ በነበረው ግብፃዊ አማካኝነት እንዲዘጋጅ የተደረገው እርምጃ ነበረበት፡፡ በመጨረሻም ቀደም ሲል በአፄ ሚኒሊክ በ1904 ቃል የተገባበትን የታላቁ መስጊድን ግንባታ ፈቀደ፡፡ በዚህም መሰረት እና በመሐመድ አሊ ኩባንያ ተፅዕኖ መሰረት የአረብ-እስላማዊ የንግድ ማዕከል በአዲስ አበባ መርካቶ ኢትዮጵያን በመደገፍ የድጋፍ መግለጫን አወጣ፡፡ በግንቦት 30 1935 በመሐመድ አል ሳዲቅ “የአገሪቱ የሙስሊም ኮሙኒቲ መሪ” በነበረው የተሰጠውን መግለጫ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በጋዜጣው ላይ አውጥቶታል፡፡
ሦስተኛው፡
በኃይለስላሴ ተደርጎ የነበረው ሦስተኛው እርምጃ በአረብ አገሮች ውስጥ እርዳታን መፈለግ ነበር፡፡ በ1935 ውስጥ ወደ ግብፅ፣ ሊቢያና አረቢያ መልእክተኞችን ላከ፡፡ የእርሱም ዓላማ የወታደርና ሌላም ዓይነት የቁሳቁስ እርዳታን ለመጠየቅ አልነበረም፡፡ እርሱ ፈልጎ የነበረው ለእርሱ የኢትዮጵያ አዲስ ሞዴል ማለትም የሐበሻ ሕዝቦች መንግስት የስምምነት (የተቀባይነት) ምልክት እንዲሁም ከሙሶሊኒ ጋር ለሚያደርገው ትግል የሙስሊም ሕዝቦችን ድጋፍ ለማግኘት ነበር፡፡ እርሱም የተደባለቀ ውጤት ነበረው፡፡ በሊቢያ የነበረው ሚሽን ያልተሳካ ነበር ምክንያቱም የሳኑሲ የፀረ ጣሊያን እንቅስቃሴ ተደምስሶ ነበርና፡፡ በጣም ጠቃሚው ደግሞ የግብፅ ሕዝብ ነበረ፡፡ በእርግጥ ግብፃውያን በሙሶሊኒ በኩል ሊከፈት ስላለው ጦርነት ያን ጊዜ አስታዋሽ አያስፈልጋቸውም ነበር፡፡ በ1935 የኢትዮጵያና የእርሷ እጣ ፈንታ፣ በግብፅ፣ እንዲሁም በሶርያ በኢራቅና በፍልስጥዔም ውስጥ የሕዝብን አመለካከት በመካፋፈል ዋና ጉዳይና አጀንዳ ነበር፡፡
በአጠቃላይ የመካከለኛው ምስራቅ የፓን አረብ አገሮች አገር ወዳድነት እንዲሁም የእስልምና በፖለቲካው መድረክ ውስጥ መነቃቃት፤ “የኢትዮጵያ ጥያቄ” እንዲሁም ከእርሱ ጋር አብሮ ያለው ያልጠራ አመለካከት ከዚህ እንቅስቃሴ ማዕከል ውስጥ እና የማንነት ትርጉም ውስጥ ገብቶ፤ የፖለቲካ መረጋጋት በሌለበት ሰዓት እንደገና ሊተረጎም ነበር፡፡ እጅግ ብዙ የሚሆኑት ግብፃውያን ብሪቴንን ከሚያዳክም ማንኛውም ነገር ጋር ተባብረው ነበር፡፡ ብዙዎች ሌሎች ደግሞ ሙሶሊንን በመደገፍ ዝግጁዎች ሆነው በክርስትያን ኢትዮጵያ ላይ መጥፎውን ሁሉ ይመኙ ነበር፡፡ መጽሐፎችና ጽሑፎች የኢትዮጵያን ወንጀል በመግለፅ ተጻፉና በጊዜው የነበረውን የንጉሱን የኃይለስላሴ የመጨረሻ ደቂቃ ንቃት ላይ ማላገጣቸውን ቀጠሉ፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያን ይደግፉ የነበሩትም ቀላል ቁጥር አልነበራቸውም በተለይም ሳይጠቀስ የማይቀረው እና የአገሪቱን ጠቃሚ እገዛ ያመጣው በግብፅ ውስጥ “ኢትጵያን የሚመክት ኮሚቴ” መቋቋሙና መንቀሳቀሱ ነበር፣ እርሱም ሊበራሎችና አክራሪ ያልሆኑ የካይሮ ሙስሊሞች አንድነት ድርጅት ነበር፡፡