Sunday, April 7, 2013

እስልምና በኢትዮጵያ ታሪክ (ክፍል አምስት)



 የጽሁፉ ባለቤቶች (ለእስልምና መልስ አዘጋጅዎች ነው)
አንደኛው፡
የጥንቱ የመጨቆንና የማንቋሸሽ መንገድ እንደገና ተጀመረ፣ እነዚህ መንገዶች ከጣሊያን ወረራ ጥቂት ቀደም ብሎ በተከሰተው ምስጢራዊው የልጅ ኢያሱ ሞት አበቁ፡፡
ሁለተኛው፡
ሙሉ ለሙሉ አዲስ ወደ ሆነ አቀራረብ በድንገት ቀልበስ ማለት ነበር፡፡ ስለዚህም በ1935 በመጀመሪያዎቹ አካባቢ ንጉሱ ኃይለስላሴ እራሱን የተለያየ ማህበረ ሰብ አካላት መሪ አድርጎ ማቅረብ ጀመረ፡፡ እርሱም በተለያዩ ቦታዎች ላይ በታላቋ ኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት እኩልነት እንደሚኖር ንግግር አደረገ፡፡ አያይዞም በግንቦት 22 1935 ለሐረር የማህረሰብ መሪዎች ንግግርን አደረገ፡፡ የንጉስ ኃይለስላሴም ዋና መልእክት የነበረው ሁሉንም ሃይማኖቶች፣ ሁሉንም ጎሳዎች፣ በአዲሲቱ የኢትዮጵያ ሞዴል ማለትም “ክርስትያን ባልሆነው ነገር ግን ከልዩ ልዩ አካል በተውጣጣው የኢትዮጵያ ሞዴል” ውስጥ ለማካተት መሞከር ነበር፡፡ እርሱም የሁሉም ሃይማኖት እኩልነት ያለበት ህገ መንግስትን እንደሚያወጣ ቃል ኪዳንን ገባ፡፡ ሙስሊሞችን የማባበሉ የእርሱ አዲሱ ጥረት ያካተተው በአዲስ አበባ ውስጥ የአረብ ቋንቋ ጆርናል እንዲታተም እና በሚኒልክ ትምህርት ቤት ውስጥ አስተማሪ በነበረው ግብፃዊ አማካኝነት እንዲዘጋጅ የተደረገው እርምጃ ነበረበት፡፡ በመጨረሻም ቀደም ሲል በአፄ ሚኒሊክ በ1904 ቃል የተገባበትን የታላቁ መስጊድን ግንባታ ፈቀደ፡፡ በዚህም መሰረት እና በመሐመድ አሊ ኩባንያ ተፅዕኖ መሰረት የአረብ-እስላማዊ የንግድ ማዕከል በአዲስ አበባ መርካቶ ኢትዮጵያን በመደገፍ የድጋፍ መግለጫን አወጣ፡፡ በግንቦት 30 1935 በመሐመድ አል ሳዲቅ “የአገሪቱ የሙስሊም ኮሙኒቲ መሪ” በነበረው የተሰጠውን መግለጫ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በጋዜጣው ላይ አውጥቶታል፡፡
ሦስተኛው፡
በኃይለስላሴ ተደርጎ የነበረው ሦስተኛው እርምጃ በአረብ አገሮች ውስጥ እርዳታን መፈለግ ነበር፡፡ በ1935 ውስጥ ወደ ግብፅ፣ ሊቢያና አረቢያ መልእክተኞችን ላከ፡፡ የእርሱም ዓላማ የወታደርና ሌላም ዓይነት የቁሳቁስ እርዳታን ለመጠየቅ አልነበረም፡፡ እርሱ ፈልጎ የነበረው ለእርሱ የኢትዮጵያ አዲስ ሞዴል ማለትም የሐበሻ ሕዝቦች መንግስት የስምምነት (የተቀባይነት) ምልክት እንዲሁም ከሙሶሊኒ ጋር ለሚያደርገው ትግል የሙስሊም ሕዝቦችን ድጋፍ ለማግኘት ነበር፡፡ እርሱም የተደባለቀ ውጤት ነበረው፡፡ በሊቢያ የነበረው ሚሽን ያልተሳካ ነበር ምክንያቱም የሳኑሲ የፀረ ጣሊያን እንቅስቃሴ ተደምስሶ ነበርና፡፡ በጣም ጠቃሚው ደግሞ የግብፅ ሕዝብ ነበረ፡፡ በእርግጥ ግብፃውያን በሙሶሊኒ በኩል ሊከፈት ስላለው ጦርነት ያን ጊዜ አስታዋሽ አያስፈልጋቸውም ነበር፡፡ በ1935 የኢትዮጵያና የእርሷ እጣ ፈንታ፣ በግብፅ፣ እንዲሁም በሶርያ በኢራቅና በፍልስጥዔም ውስጥ የሕዝብን አመለካከት በመካፋፈል ዋና ጉዳይና አጀንዳ ነበር፡፡
በአጠቃላይ የመካከለኛው ምስራቅ የፓን አረብ አገሮች አገር ወዳድነት እንዲሁም የእስልምና በፖለቲካው መድረክ ውስጥ መነቃቃት፤ “የኢትዮጵያ ጥያቄ” እንዲሁም ከእርሱ ጋር አብሮ ያለው ያልጠራ አመለካከት ከዚህ እንቅስቃሴ ማዕከል ውስጥ እና የማንነት ትርጉም ውስጥ ገብቶ፤ የፖለቲካ መረጋጋት በሌለበት ሰዓት እንደገና ሊተረጎም ነበር፡፡ እጅግ ብዙ የሚሆኑት ግብፃውያን ብሪቴንን ከሚያዳክም ማንኛውም ነገር ጋር ተባብረው ነበር፡፡ ብዙዎች ሌሎች ደግሞ ሙሶሊንን በመደገፍ ዝግጁዎች ሆነው በክርስትያን ኢትዮጵያ ላይ መጥፎውን ሁሉ ይመኙ ነበር፡፡ መጽሐፎችና ጽሑፎች የኢትዮጵያን ወንጀል በመግለፅ ተጻፉና በጊዜው የነበረውን የንጉሱን የኃይለስላሴ የመጨረሻ ደቂቃ ንቃት ላይ ማላገጣቸውን ቀጠሉ፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያን ይደግፉ የነበሩትም ቀላል ቁጥር አልነበራቸውም በተለይም ሳይጠቀስ የማይቀረው እና የአገሪቱን ጠቃሚ እገዛ ያመጣው በግብፅ ውስጥ “ኢትጵያን የሚመክት ኮሚቴ” መቋቋሙና መንቀሳቀሱ ነበር፣ እርሱም ሊበራሎችና አክራሪ ያልሆኑ የካይሮ ሙስሊሞች አንድነት ድርጅት ነበር፡፡ 


ኢትዮጵያን ይደግፉ ከነበሩት ውስጥ የሳላፊያ እንቅስቃሴ መሪ የነበረው ሼክ መሐመድ ራሺድ ሪዳ፣ የፀረ ኮሎኒያሊስቶች አመለካከት ስለነበረው አፄ ሚኒሊክ በጣሊያን ላይ የነበራቸውን ድል በጣም የሚያደንቅና እንደምሳሌ ይመለከት የነበረ ሰው ነው፡፡ ይህ ሰው የሳውዲው ንጉስ ወዳጅ ስለነበረ ፕሮፌሰሩ እንደጠቀሰው የሳውዲው ንጉስ ግብፅን በጎበኘበት ወቅት ኢትዮጵያን መደገፍና ጣሊያንን መቃወም እንዳለበት እንደወተወተው ደብዳቤዎችንም በጥር 1935 እንደጻፈለት ጠቅሷል፡፡ ከዚያም ባሻገር ለሶርያዊው ድሩዝ ለአሚር ሻኪብ አርስላ በጥር 24 1935 በጻፈው ደብዳቤ ላይ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ለሚሄደው ለሙሶሊኒ ምንም ድጋፍን ከማድረግ እንዲቆጠብ አሳስቧል፡፡ በኋላ ቆይተን እንደምናየው ይህ አርስላ ከፍተኛ የሆነ ፀረ ኢትዮጵያ አቋም የነበረውና ኢትዮጵያ እንድትጠቃ ቢቻልም እንድትወድም ቅስቀሳ ያደረጉ ብዙ ጽሑፉችን የጻፈ ሰው ነው፡፡
በዚያን አንገብጋቢ ወቅት ቀዳማዊ ኃይለስላሴ በተለያየ ጊዜ ወደ ሳውዲው ንጉስ የተከበሩ የመንግስት ልዑካንን ቢልኩም ያገኙት የቀናነት ምንም ትብብር እንዳልነበረ ጥናቱ ዝርዝር ሁኔታዎችን እና መልእክተኞችን በመጥቀስ ያስረዳል፡፡ በሚያዝያ 7 1935 የኢትዮጵያ ልኡካን ወደ ጅዳ በመሄድ ንጉሱን እንዲያነጋግሩና ከኃይለስላሴ የተላከውን ደብዳቤ እንዲያቀርቡ ተልከው ነበር፣ በሚያዝያ 10 1935 የኃይለስላሴም ጥያቄ ሆኖ የቀረበው “በነቢዩ በነጃሺ መንፈስ የወዳጅነት ምስረታን” መጠየቅ ብቻ ነበር፡፡ ንጉሱ የመለሰው ይህንን ለማድረግ ጊዜው አሁን እንዳይደለ ምንም ዓይነት ስምምነትም እንደማይደረግ ነበር፡፡ ኢብን ሳውድ ለጥያቄው በተጨማሪ የመለሰው እርሱ ለኢትዮጵያም ለጣሊያንም ወዳጅ እንደሆነና የእነርሱ ግጭት የሆነ ደረጃ ላይ ሳይደርስ ወይንም ፍፃሜ ላይ ሳይደርስ ማንኛውንም ሊወግን እንደማይችል ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በወቅቱ ከልዑካኑ መካከል ለነበረው ለኢትዮጵያዊው ሙስሊም ለአህመድ ሳሊክ ንጉሱ ሳውድ የተናገረው፣ “ኢትዮጵያ ለራሷ ሙስሊሞች የምታደርገውን ሁሉ እንደሚያውቅ ነበር፡ ቀጥሎም ለልዑኩ የነገረው “አባ ጅፋር ተወግዷል ልጁም ተሰዷል፡፡ በጅማ ለብዙ መቶ ዓመታት የነበረው እስላማዊ መንግስት ተደምስሷል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ጠቃሚ ቦታ ላይ የተቀመጠ ወይንም ጠቃሚ ቦታ የያዘ ማንም ሙስሊም የለም፡፡ እኔ ለኢትዮጵያ ምንም ነገርን ላደርግ አልችልም” ነበር ያለው፡፡ ስለዚህም ሚያዝያ 15 ልዑካኑ ባዶ እጃቸውን ተመለሱ፡፡ ይህም ነገር ሙሶሊንን በከፍተኛ ደረጃ አስደስቶት ነበር፡፡
የአርሰላን እጅ በታሪኩ ውስጥ
በኢትዮ-ጣሊያን ጦርነት ላይ የሳውዲ አረቢያውን ንጉስ ኢብን ሳውድን ከጣሊያኖች ጋር እንዲተባበርና የኢትዮጵያን ጥያቄ ችላ እንዲል እንዲያውም እንዲዘጋ እንዲያውም በጠላትነት እንዲቆም ለማድረግ መሳሪያ በመሆን የቆሙ ሁለት ግለሰቦች እንደነበሩ የፕሮፌሰሩ ጥናታዊ ጽሑፍ ያሳያል፡፡
ከ1920 ጀምሮ የኢብን ሳውድ የውጭ ጉዳይ አማካሪዎች የነበሩት አንደኛው ግብዊው ሃፊዝ ዋህባ፣ ሁለተኛው ሶርያዊው ዩሱፍ ያሲን እና ሦስተኛው ደግሞ ሊባኖሳዊው ድሩዝ ሃምዛ ነበሩ፡፡ ግብፃዊው ዋህባ የሳውዲ የብሪቴን አምባሳደር ስለ ነበር ከኢትዮጵያ ሳውዲ ጉዳይ ውጭ ሲሆን ሁለቱ ማለትም ሶሪያዊውና ሊባኖሳዊው ግን በጥልቅ ተሳትፈውበታል፡፡ ሁለቱም በርዕዮተ ዓለማዊ አቋማቸው ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ከተቋቋመው ከ”ሶርያ ፍልስጥኤም ኮንግረስ” የአረቦች ህብረት ጋር ግንኙነት ነበራቸው፡፡ የዚያም ኮንግረስ መሪዎች ውስጥ አርስላንና ቀደም ብሎ የተጠቀሰው ግብፃዊው ሪዳ ይገኙበታል፡፡ ሪዳ እስከሚሞትበት ዕለት ድረስ ሙሶሊንን ይቃወም የነበረ ሲሆን ሦስቱ ግን ከጣሊያን ጋር የቅርብ ትስስርን አድርገዋል፡፡
ሊባኖሳዊው ሐምዛ እንደ አርስላን የተማረ ሰው ሲሆን የሳውዲው ኢብን ሳውድ አድናቂና እርሱንም የአረባ ባህረሰላጤ አረብ እስላም ታሪክ ማዕከል አድርጎ የሚቆጥርና የእርሱም ሰራተኛ ለመሆን በ1924 የመጣ ነው፡፡ ይህንንም ፅንሰ ሐሳቡን በ1933 ባሳተመው መጽሐፉ “The Heart of the Arab Peninsula’ በሚለው መጽሐፉ ውስጥ አስቀምጦታል፡፡ በዚያ መጽሐፉ ውስጥ ለኢትዮጵያ የሰጠው ግልፅ የሆነ እጅግ መጥፎ ገፅታ ነው፡፡ የነቢዩ መሐመድን ታሪክ ሲያወሳ ወደ ኢትዮጵያ የተደረገውን ጉዞ ጠቅሶ ለሳሃባዎቹ ኢትዮጵያ ያደረገችውን ነገር ፈፅሞ አልጠቀሰውም (ገፅ 262-271}፡፡ በአንፃሩ (በተቃራኒው ግን) ቀደም ብሎ ኢትዮጵያውያን የመንን እንደወጉና ካዓባን ለማጥፋት እንደዛቱ በጣም በሰፊው ዘግቧል (ገፅ 252)፡፡ በዚያ አንቀፅ ውስጥ ያስተላለፈው መልእክት አረቦች ከወራሪ ክርስትያን ኢትዮጵያ ቅዱሳን ቦታዎቻቸውን ለማዳን ሲሉ አንድ መሆን አለባቸው የሚለውን መልእክት ነው፡፡ በዚያን ጊዜ የነበረውን የአቢያን ባህረ ሰላጤ ሲገልጠው ሐምዛ የሰጠው ነጥብ ውስጥ “ንፁህ አረብ” እና 435,000 “አረብ ያልሆኑ” በግምት አረቢያ ውስጥ እንደሚኖሩ ነበር ከእነዚህም ውስጥ 200,000 ዎቹ ጥቁሮችና ኢትዮጵያውያን ናቸው በማለት ነበር፡፡ የኋለኞቹ ምንም እንኳን ሙስሊሞችም ቢሆኑ እንኳን በሐምዛ መሰረት ግን እነርሱ የባርያ ዝርያዎች ወይንም ወራሪዎች ናቸው የሚል ገለፃ ነበራቸው (ገፅ 85፣ 96-97)፡፡ ይህ ሰው ነው በሳውዲው ንጉስ በኢብን ሳውድ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሮ የነበረው፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ ልኡካን ባዶ እጃቸውን እንዲመለሱና ለጣሊያን ጦርነት መሰረታዊ የሆኑ ምቹ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ አድርጎ በዚያን ጊዜ ለተከሰተው የኢትዮጵያ ውድቀት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡
አርስላንም ከፍተኛ ሚናን ተጫውቷል ፕሮፌሰር ኢርሊች እንደሚለው ከሐምዛ የበለጠ እርሱ በዓለም ውስጥና በአረብ አገር ሁሉ ይዞርና የእስላማዊ አረብ አንድነትን ሚሊታንታዊ አንድነት ያደራጅ ነበር፡፡ በእርሱም ዓይን ውስጥ እስላምና እና አረብነት የማይነጣጠሉ ነገሮች ነበሩ፡፡ አርስላን ከዚህም የተነሳ የአረቡን ዓለም አንድ በማድረግ በኩል የሚቀጥለው ካሊፍ ኢብን ሳውድ እንደሆነ በተለያየ መንገድ ይናገርና ይገልፅ ስለነበር፣ እራሱ ኢብን ሳውድ ሐሳቡን በግልፅ ባይቃወመውም ከአርስላን ጋር በጣም የቀረበ ግንኙነትን መስርቷል፡፡ አርስላንም የኢብን ሳውድን ስም ታላቅ ለማድረግ እጅግ በጣም ጥረትን ያደርግ የነበረ በመሆኑ በ1929 የሳውዲ ዜግነት ፓስፖርት እንዲሰጠው ንጉሱ አድርጓል፡፡
ይህም ብቻ ሳይሆን አርስላን በአረቡ ዓለም ውስጥ የጣሊያንም ወኪል ሆኖ ይሰራ ነበር፡፡ አርስላን አርቦች በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ ድል እንዲያደርጉ ከተፈለገ ጣሊያንን መጠጋት እንዳለባቸው ብዙ ይቀሰቅስ የነበረ ሲሆን በዚህም ቅስቀሳው ኢትዮጵያ የምትባለው አገር ሙሉ ለሙሉ ብትወድም ምንም ቅር እንደማይለው ነበር፡፡ እርሱ እራሱ በ1928 ለራስ ተፈሪ በጻፈው ደብዳቤ ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሙስሊሞች መሰረታዊ መብት እንዲጠበቅ ጥያቄን አቅርቦ ነበር፡፡ ለጥያቄውም ምንም የደብዳቤ መልስም ስላልተሰጠው (እንደ በቀል አድርጎ) በ1930ዎቹ ሁሉ ውስጥ ንጉሱን ኃይለስላሴን ይጠራ የነበረው ተፈሪ በማለት ነበር፡፡ በ1933 ላይ ደግሞ “የኢትዮጵያ ሙስሊሞች” በሚል ርዕስ ስር እጅግ ረጅም ጽሑፍን ጽፎ ነበር በዚያም ውስጥ ከአረብ ምንጭ የተወሰዱትን የግራኝ መሐመድን የጦርነት ዘገባዎች በማስቀመጥ የአፍሪካ ቀንድ እራሱን የቻለ ክብርና ድልን ይጋራል ብሎ ነበር፡፡
ከዚያም በፍጥነት በመቀጠል፣ ወዲያውኑ ሙሶሊኒን በማድነቅ እርሱ (ሙሶሊኒ) እስልምናን ከኢትዮጵያ ጭቆና ነፃ የሚያወጣ ነው በማለት እንደ እስልምና አዳኝ አድርጎ ማቅረቡን ቀጠለ፡፡ በ1934 ጥቅምት ላይ አርስላን ኤርትሪያን ጎብኝቶ ከተመለሰ በኋላ በ”La Nation Arabe’ ላይ ሙሶሊኒ እስልምናን በጥሩ ሁኔታ እንደያዘው በማድነቅ ረጅም ጽሑፍን ጽፎ ነበር፡፡ በ1935 ጥር ላይ ደግሞ እንደገና በዚያው በ”La Nation Arabe’ ላይ ለሕትመት ያቀረበው ሌላው ጽሑፍ ላይ ለኢትዮጵያ ማስጠንቀቂያን አስቀምጦ ነበር ይህም ለጅማና ለሐረር የራስን በራስ ማስተዳደር ስልጣን እንድትሰጥ አለበለዚያ ግን እንደምትወድም አስጠንቅቆ ነበር፡፡ ይህ ሰው ጣሊያንን፣ ኢትዮጵያንና፣ እስልምናን በተመለከተ ከጻፋቸው እጅግ በጣም ብዙ ጽሑፎች መካከል፤ ኢትዮጵያ በጣሊያኖች እጅ ውስጥ ከወደቀችም በኋላ እንኳን የጻፈው አስገራሚ ነበር ለመጥቀስም ያህል በAl-Jami’a al-Arabiyya በፍልስጥኤም ጋዜጣ ላይ ያወጣው ጽሑፍ በመጋቢት 4 1935 “ኢትዮጵያን ለመደገፍ የሚፈልጉ ሁሉ በመጀመሪያ መመልከት ያለባቸው ሙስሊሞች እንዴት በአገሪቱ ውስጥ እንደሚኖሩ፤ ከኢትዮጵያውያን እጅ ምን እንደሚቀበሉና፤ እነርሱ (የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በኢትዮጵያ ማለቱ ነው) እዚያ እንደሚሰቃዩት ማንም ሙስሊም በየትኛውም አገር ተሰቃይቶ አያውቅም” በማለት ነበር፡፡ ቀጥሎም በአገሪቱ ውስጥ ያሉት ስድስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በጭቆና እንደሚኖሩ ነበር ይህም ከአውሮፓውያን ኮሎኒያሊዝም በከፋ ሁኔታ ነው በማለት አስቀምጦት ነበር፡፡ አርስላን ከኢብን ሳውድ ጋር በጣም ቅርብ ስለነበር ኢብን ሳውድ ኢትዮጵያን በተመለከተ መጥፎ ሐሳቡን ያገኘው ከ”አብድ አል ዋሃብ’ ብቻ ሳይሆን ከአርስላንም ጭምር ነበር ማለት ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ተደማምረው ነበር ኢብን ሳውድ ከዚህ በፊት የተጠቀሰውን የቁጭት ንግግር በመናገር በሚያዝያ ወር ለወዳጅነት ግንኙነት ምስረታ የተላከውን የኢትዮጵን ቡድን አሳፍሮ ባዶ እጃቸውን እንዲመለሱ ያደረገው፡፡
ኢብን ሳውድና ሙሶሊኒ
የኢትዮጵያ ልኡካን ከተመለሱ አንድ ወር በኋላ ነበር የሳውዲ ልኡካን ወደ ሮም በጣሊያን ልዩ መርከብ ጉዞ አደረጉ፣ ልዑል ሳውድ እና ሐምዛ ነበሩበት፡፡ ግንቦት 20 ሮም ደርሰው ከፍተኛ አቀባበል ተደረገላቸው፣ ልዑል ሳውድ ከጣሊያን ንጉስና ከሙሶሊኒ ጋር እንደተገናኘ ሙሶሊኒ በአድናቆት የተናገረው ነገር የኢትዮጵያን ልዑካን እንዴት አሳፍረው እንደመለሷቸው ነበር፡፡ ከዚያም የተወሰኑ ስምምነቶች ተደርገዋል በመሆኑም ሙሶሊኒ፡
የእስላሞች ወዳጅ እና በኢትዮጵያ ውስጥ በክርስትያን መንግስት የጭቆና ቀንበር ስር ያሉት ሙሰሊሞች (የበላይ) ጠባቂ እንደሆነ፡፡
ሳውዲ ከየትኛውም አቅጣጫ የሚመጣውን ፀረ ጣሊያን ቅስቀሳን እንድታግድ እንዲሁም በሶማሊያና በኤርትሪያ የሚደረገውን የጣሊያንን ወታደራዊ ግንባታ በሰራተኞች ምልመላና በበጎ ፈቃደኞች እንድትረዳ፡፡
 ሳውዲዎች ለጣሊያን ሰራዊት ምግብን እንደሚሸጡ፡፡
 ለዚህም ምላሽ ጣሊያን የሳውዲን የአየር ኃይል እንደምትገነባ እንዲሁም ለሳውዲዎች ክፍያዋን በጦር መሳሪያ እንደምታደርገው፣ በተለይም ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ጦርነት ካለቀ በኋላ፡፡
 በመጨረሻም ሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያና በጣሊያን መካከል ያለውን ግጭት የሁለት ክርስትያን አገር ግጭት እንደሆነ አድርጋ እንድታየውና በስተውጭው በሁለቱ አገሮች መካከል ባለው ጦርነት ላይ ገለልተኛ እንደሆነች እንደሚታይ ተስማሙ፡፡ ከዚህም የተነሳ ማንኛውንም ዓይነት የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ሳውዲ አረቢያ ከኢትዮጵያ ጋር እንደማታደርግ ተስማማ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ጦርነቱም ከተጀመረ በኋላ እንኳን ከሳውዲ ጋር ግንኙነትን ለማድረግ ብዙ ያልተሳካ ሙከራዎችን አድርጓል በተደጋጋሚም ሳውዲ አረቢያ ከኢትዮጵያ ጋር የወዳጅነት ግንኙነት ለማድረግ ያሳየችው ምንም ዝንባሌ አልነበረም፡፡
To be continued....