Wednesday, December 14, 2011

ማደናገር ይቁም! የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መ ድረገጽ


«ADOBE OF GOD»በሚል ርእስ የክርስቶስ ኢየሱስን የማዳን ስራ የሚያጥላላና ፍጹም ክህደት የተሞላበት ፊልም ኢትዮጵያ ውስጥ ሊሰራ እንደነበር በባለፈው ወር የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። በእርግጥም ከ75% በላይ ሕዝብ ክርስትናን በአንድም በሌላ ምክንያት ተቀብሎ የሚኖርና በአብዛኛውም ይህንኑ የእለት ከእለቱ መመሪያ አድርጎ በሚቀበል ሀገር ላይ ይህንን መሰሉን ፊልም መስራት መርገም ካልሆነ በረከት ያመጣል፣ ተብሎ አይታሰብም። ክርስቶስን ለማዋረድ መፈለግ ከክርስቶስ ማንነት ላይ አንዳች የሚያጎለው ነገር ባይኖርም
«የማያምኑ ቢኖሩ አለማመናቸው የእግዚአብሔርን ታማኝነት ያስቀራልን?» ሮሜ 3፣3 እንዳለው ክርስቶስ ዛሬም፣ ነገም ያው እሱ መሆኑ ሳይጎድል አምልኰና ክብር በሚገባው ቦታ ተሳልቆና ክህደት ሲተካ ግን የረድዔትና የበረከት እጁን ላለመቀበል በፈለግነው ልክ የዚህ ዓለም ገዢን ማስተናገድ በመሆኑ ሊያስደነግጠን እንደሚገባ ለአፍታ መዘናጋት የለብንም። ይህንን ድርጊት ለምእመናንና ምእመናት በማዳረስ በመረጃው ላይ የወል ግንዛቤ ወስዶ አቋማችንን ለሚመለከተው ለማድረስ ሚዲያዎች ሰፊ ዘገባቸውን ሰጥተው ሰርተዋል። ይህ ሊመሰገን የሚገባው መንፈሳዊ ተግባር ነው። ይሁን እንጂ አንዳንዶች ራሳቸውን የዚህ ጥረትና ትግል ዋነኛ አካል አድርገው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ማእከላዊ ጽ/ቤት ግን «ፊልሙ እንዲሰራ ፈቅዷል» በማለት ድካምና ጥረቱን ውሃ በመቸለስ ከችግሩ ጎን ለጎን የችግሩ ዋነኛ ምህዋር እንደነበር ለማሳየት መሞከራቸው አስገራሚ ሆኗል። ከነዚህም መካከል የማኅበረ ቅዱሳኑ ሌላኛው እጅ የ«ደጀሰላም» ድረገጽ ከለጠፈው በኋላ ቤተክህነቱን የወነጀለበትን ጽሁፍ ያውርድ እንጂ ወንድሙ የሆነው «አንድ አድርገን» ለማንበብ ይህን ይጫኑ
እስካሁን ያስነብበናል። «ማኅበረ ቅዱሳን የቤተክህነት እዳ» በተሰኘው መጽሐፍ እንደተጠቆመው «እንቁ» መጽሔት የማኅበረ ቅዱሳን የእጅ አዙር መጽሔት መሆኑን ለመረዳት ብንችል ሁሉም በአንዴ ተቀባብለው ቤተክህነቱን ያለስራው ስም ሰጥተው «ADOBE OF GOD» ለተሰኘው የክህደት ፊልም ትብብሩን ሰጥቷል ሲሉ መጻፋቸው ካንድ ወንዝ መቀዳታቸውን እንደሚነግሩን እንገነዘባለን። የቤተክህነቱ ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ነገሩ እጅግ ቢያስመርረው በድረገጹ ለተባለው ፊልም ከታቃውሞ ውጪ ድጋፍ አለመስጠቱን አስነብቦናል።
ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ