Wednesday, December 7, 2011

የጴንጤ መዝሙር ያዳመጠስ?

የበጋሻው ግጥም ስህተት የለውም!
በጋሻው ደሳለኝን በተመለከተ አንዴ ጻድቅ ነው፣ አንዴ ደግሞ ኀጥእ ነው እንደሚለው ማኅበረ ቅዱሳንና ልሳኖቹ በሆኑት ደጀሰላም፣ አንድ አድርገን  በመሳሰሉት እንደሚናገሩት ኀጥኡን ለመኮነን ወይም ጻድቁን ለማጽደቅ የኛ ድርሻ ስላልሆነ እንዲሁም  ቃለእግዚአብሔር አይፈቅድልንምና በዚህ ዙሪያ የምንለው ነገር አይኖርም።
ሁለተኛው ደጀሰላም የሆነው «አንድ አድርገን» የበጋሻውን ከሀዲነት የሚገልጽ የግጥምና የመዝሙር ቅንብር በማቅረብ ለማጋለጥ ሞክሯል። እስኪ በዚያ ላይ ተንተርሰን ጥቂት ሃሳብ እንስጥ። ለፍርድ ያመች ዘንድ ግጥሙን ለማሳያነት በጥቂቱ ኮፒ አድርገነዋል።

የፕሮቴስታት                                                                  የኦርቶዶክስ
ካልባረከኝ አለቅህም ካልባረከኝ አለቅህም-                      ካልባረከኝ አለቅህም ካልባረከኝ አለቅህም
 አምላኬ ነህ ለዘላለም                                                 -አምላኬ ነህ ለዘላለም
ጌታዬ ነህ ለዘላለም                                                       ጌታዬ ነህ ለዘላለም
ለብቻዬ ልኖር ፈቃድህ ከሆነ                                           ሊነጋ ሲጀምር ሰማዮ ሲቀላ
ሌላው አይገደኝም ህይወቴ ከዳነ                                      ወዴት እሔዳለው ነፍሴ እንዲህ ዝላ
ሲሆን እስከ ንጋት ልታገልህና                                           እያለቀስሁ ሁሉ እከተልሀለሁ
ስደደኝ ጌታዬ ሆይ ሕይወቴን ባርክና                                   እጅህን ዘርጋልኝ በረከት እሻለሁ
በመንበርከክ ብዛት በጸሎት ትግል                                        ለብቻዬ ልኖር ፈቃድህ ከሆነ
ፈቃድህ ከሆነ ጉልበቴ ይዛል                                               ሌላውን አልሻም ሕይወቴ ከዳነ
እያለቀስኩ ሁሉ እከተልሀለሁ                                           ሲሆን እስከ ንጋትታግለሃልና ል                                                                              
እጅህን ዘርጋልኝ በረከት እሻለሁ                                       ስደደኝ ጌታዬ ሕይወቴን ባርክና

የግጥሙን መመሳሰል ወደኋላ ላይ እናቆየውና የሚታየውን እውነት ኢአመክንዮያዊ (fallacy)በመስጠት በጋሻውን ከሃዲ ለማድረግ የተሞከረበትን ስነ ሞገት እንመርምር።


1/የጽሁፉ መሠረት
የጽሁፉ መሠረት መጽሐፍ ቅዱስ ነው። በኦሪት ዘፍጥረት 32፣26 ላይ ተጽፎ እናገኘዋለን። ባለቤቱ ያዕቆብ ያደረገውም እግዚአብሔር! በአንድ አድርገን (ማኅበረ ቅዱሳዊ) ቤተዘመቻ ይህ ጽሁፍ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌለው ስለሆነ ነው የምንቃወመው ብሎ ከሆነ ለይቶላችሁ ክዳችኋል ማለት ነው።
2/የጽሁፉ ይዘት
ጽሁፉ መጽሐፍ ቅዱሱን መሠረት አድርጎ በዝማሬ መልክ ተዘጋጅቶ ቀርቧል። ይዘቱ፣ መሠረቱን አልሳተም። የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ተከትሎ ጽሁፎችን በዝማሬ ወይም በግጥም ወይም በቅኔ መልክ ማቅረብ ክልክል አይደለም። 
«በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ»       ኤፌ 5፣19 እነዚህ አሳጪዎች የግጥሙ ይዘት የመጽሐፍ ቅዱሱን መሠረት ያፈረሰ ስለሆነ የምንቃወመው የሚሉ ከሆነ ይህንኑ በግልጽ ይናገሩና ክህደታቸው በአደባባይ ይለይ!!
3/ የጽሁፉ ባለቤት
የጽሁፉ መሠረት መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑን ካየን ባለቤቱ ራሱ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። የትኛውም ወገን የኔ የብቻዬ ነው ሊል አይችልም። ምክንያቱም ማንም ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለውን ጽሁፍ የኔ የብቻዬ ብሎ የባለቤትነት መብት(proprietorship)ሊይዝበት አይችልም። የኮፒ ራይት ህግ ፈጠራው ወይም የሥራው ምንጭና ባለቤቱ ራሱ ሲሆን እንጂ በሌላ የራሱ ባልሆነ ነገር ላይ የተመሰረተን ነገር የሚከላከል አይደለም። ከዚህ አንጻር መሰረቱ፣ይዘቱና ባለቤቱ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሆነ አቶ አንድ አድርገን አፈቀላጤ ምን እንደሚል ግልጽ አይደለም። በጋሻውን ለመቃወም ወይም ጴንጤ ነው ለማለት ማድረግ የሚጠበቅበት ጽሁፉ መሰረቱም፣ይዘቱም፣ባለቤቱም መጽሐፍ ቅዱስ አይደለም የሚለውን ሥነ አመክንዮ(logic)ሊያሳየን ይገባል። ከዚያ ባሻገር ፋላሲ ሃሳቦችን ወደእውነት እንድንመነዝርለት ቢፈልግ ለሰውዬው ያለው ጥላቻና እስከመጨረሻው ለመጣል ምን ያህል እንደተዘጋጀበት ከሚያሳይ በስተቀር እውነቱን እየገለጸ መሆኑን አያረጋግጥም። ይህንን ስንል በጋሻው ስህተት የሌለበት ወይም ስህተት የተሞላ ነው የሚልን የሁለት ወገን ፍርድን ለመስጠት  እንዳልሆነ በመግቢያችን ላይ አጽድቀንና ኰንነን እንደማንጽፍበት ለማስረዳት የፈለግነው ከግንዛቤ ይያዝልን።
አቶ አንድ አድርገን ወይም አቶ ማኅበረ ቅዱሳን ከሰውዬው የተሻሉ ጻድቅና ፍጹም ክርስቲያኖች መሆናቸውን እየነገሩን በሰውዬው ላይ የሚሰጡትን ፍርድ በጅምላው አጨብጭበን እንድናጸድቅላቸው መፈለጋቸው ምክንያታዊ ማስረጃ የላቸውም እንላለን። ለዚያውም ማን ጴንጤ፣ ማን ተሃድሶ ወይም ማን ከሃዲ እንደሆነ መርምሮ ውሳኔ ለሚሰጥ አካል የውሳኔ ሃሳብ ማቅረብ የሚችል አካል ቤተክርስቲያን ስላላት ወደዚያ ከመሄድ ይልቅ አስቀድሞ በውሸት መፍረድ አግባብ አይደለም።
4/ሥነ ግጥሙና ዝማሬው
መጀመሪያ ሥነግጥሙን በዝማሬ የተጠቀመው የፕሮቴስታንት ሰው ይመስላል። ያንን ስነግጥም በኦርቶዶክሳዊ ዘይቤና ዜማ ለማቅረብ የሞከረው በጋሻው ደሳለኝ መሆኑ ተገልጿል። ከላይ እንደተቀመጠው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቱን፣ይዘቱንና ባለቤቱን እስካልለቀቀና ትርጉሙ ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ጋር ልዩነት እስከሌለው ድረስ ግጥሙን መውሰድ ስህተቱ የቱ ላይ ነው? የብሉይ ኪዳን መጻህፍት እኮ የአይሁዳውያን ነው። አይሁዳውያን ዛሬም የኛ ነው ብለው ይከተሉታል። ክርስቲያኖችም የአይሁዳውያን መጽሐፍ መሆኑን አምነን ተቀብለነው፣ ለእኛ ለአዲስ ኪዳን ሰዎች የሕይወት ቃል እንዳለበት አውቀን እንመራበታለን። የአይሁዳውያን መጽሐፍ መቀበላችን አይሁዳውያን መሆናችንን ያመለክታል ማለት ነው?
ሰይጣን እኮ በአዲስ ኪዳን ዘመን ጌታችንን ሲፈታተን ከብሉይ ኪዳን ጠቅሷል(መዝ 91፣10) ይህንን ጥቅስ ዛሬ ብናነብ እኛ ሰይጣን ሆነናል ማለት ነው? ወይስ ይህ ጥቅስ በሰይጣን ስለተጠራ መዘለል ይገባዋል?
ጴንጤ ይሁን ካቶሊክ፣ አድቬንቲስት ይሁን ሜቶዲስት መጽሐፍ ቅዱስን እንቀበላለን ብለው የሚጠቅሱትን፤ የሚጽፉትንና የሚናገሩትን ማስቆም የሚቻለው መጽሐፍ ቅዱስን እንዳያነሱ መከልከል ሲቻል ብቻ ነው። ከዚያ ውጪ ግን መጽሐፍ ቅዱስን ይዘው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባለው ጽሁፍ ቢመሳሰል ወይም ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ያልወጣውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል የተጠቀመ ሁሉ የሰይጣን ቃልና የከሃዲነት ትብብር ተደርጎ የሚታይ ከሆነ ብሉይ ኪዳንን ለባለቤቶቹ ለእብራውያን እንመልስ እንደማለት ይቆጠራል። እኛንና እነሱን የሚያለያየው አንድ ዓይነት መጽሐፍ መያዛችን ሳይሆን በያዝነው አንድ ዓይነት መጽሐፍ የተለያየ አስተምህሮ መያዛችን ነው።
ስለሆነም የበጋሻው ግጥም የሚለካው ከጴንጤ ግጥም ጋር መመሳሰሉ ሳይሆን ግጥሙ ከቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ጋር ያለው የትርጉም ልዩነት ነው።  ኬንያ በጴንጤዎች ድጋፍና ማተሚያ ቤት የታተመውን መጽሐፍ ቅዱስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተቀብላ አከፋፍላለች። ዛሬም በሁላችን እጅ ይገኛል። ያ ማለት ግን ጴንጤ ተሆነ ማለት አይደለም።  ነገረ ሥራችሁ ሁሉ በዚያ በከሳሽ ወኪልነት ለመክሰስ የጥፋትና የስህተት ቀዳዳ ብታገኙበት ከመድከማችሁ በስተቀርና የምታሳዩት አንድም ክርስቲያናዊ መታያ የሌላችሁ መሆናችሁን ተረድተናል። እንዲያው ለመሆኑ ከስንት ሺህ የጴንጤ መዝሙሮች መካከል ከበጋሻው ጋር የሚመሳሰለውን ለማግኘት ስንቱን አዳመጣችሁ? ግጥሙን ለመጻፍ ስንት ደጋገማችሁት?
የበጋሻውን ኃጢአት ለመጻፍ ስትፈልጉ የጴንጤን መዝሙር እንደምታዳምጡ እግረ መንገዳችሁን ነገራችሁን። ካዳመጣችሁት ብዙው የጴንጤ መዝሙር መካከል ከምታውቁት በጋሻው ጋር የሚመሳሰል ላይ ስትደርሱ ገረማችሁና ግጥሙን ጽፋችሁ በጋሻው የጴንጤዎችን ግጥም ይቀዳል ብላችሁ ግጥሙን ከነዜማው ኢንተርኔት ላይ አወጣችሁት። በእናንተ ዘንድ ያዳመጠ ኦርቶዶክሳዊ ነው?
የጴንጤ መዝሙርስ የሚያዳምጥ ምን ይባላል?