Tuesday, August 8, 2023

የጾመ ፍልሰታ: የማርያም ትንሣኤና እርገት መንፈሳዊ መሰል ኢ—መጽሐፍ ቅዱሳዊታሪክ!

የዚህ ፅሑፍ ዓላማ የጌታን እናት ቅድስት ማርያምን የማሳነስ ወይም የመተቸት ዓላማ ግብ የሌለውና ሰዎች በማርያም ሽፋን የሚሰሩትን ኢ—መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሀሰት ትረካ ለአንባቢው ማሳየት ነው። ቅድስት ማርያም ቅድስትና ብጽዕት ናት። ጥንተ ጠላታችን በተንኮሉ "አምላኬና መድኃኒቴ" ካለችለት ውድ ልጇ ይልቅ ወደእርሷ እንዲመለከቱ አዚም ማድረጉን በማወቅ እውነቱን መግለፅ ግድ ስለሚለን ነው። ቅድስት ማርያም ዓለም ሁሉ እንዲድን እኔ ልሙት አላለችም። መድኃኒቷ መሆኑን የመሰከረችለት ልጇን ተክታ በእኔ ሞትና ትንሣኤ ሕይወት ይሆንላችኋል አትልም። ታዲያ ጾመ ፍልሰታ ምንድነው? በጾመ ፍልሰታ የሚገኝ ዘላለማዊ ሕይወት አለ ወይ? ብለን ስንጠይቅ መልሱን ለማግኘት ፅሑፉን በትዕግስት እንዲያነቡ ይመከራሉ። ሲወጣ እንዳየነው ሲመጣም የምንጠብቀው እሱን ነው።
ቅዱሳንን ስለማክበር ምንም ጥያቄ የለንም። መታሰቢያ ማድረግም የነገሮችን ሁሉ ባለቤት እስካልተካ ድረስ የሚደገፍ ነው። ነገር ግን «ጥቂት አሻሮ ይዞ፤ ዱቄት ወዳለው መጠጋት» የሚለውን ብሂል ለመተግበር መሞከር ግን ተቀባይነት አይኖረውም። በተለይም በሃይማኖታዊ አስተምህሮ ወቅት ወንጌል እንደዚህ ስለሚል፤ እኔም እንደዚህ ብል ችግር የለውም የሚለውን ራስን መሸሸጊያ ምክንያት በማቅረብ ለመከለል መሞከር አያዋጣም። ብዙ ጥያቄዎችን የሚያስነሱትና እነዚህ የመሳሰሉ የስህተት ችካሎች አልነቀል ያሉት በምክንያት ስር በመወሸቃቸው ነው። ራሱን የማርያምን እረፍትና ትንሣዔ ሳይሆን በማርያም እረፍት፤ ቀብር፤ ትንሣዔና እርገት ላይ ያሉ አስተምህሮዎችን ለመቃኘት እንሞክራለን። ስለማርያም እረፍት፤ ትንሣዔና እርገት አብያተ ክርስቲያናት አንድ ዓይነት የእምነት አቋም የላቸውም። እንዲያውም ስለማርያም ሞትና የእርገት ዕለት በግልጽ የሚታወቅ ማስረጃ እንደሌለ በ5ኛው ክ/ዘመን የኖረው የሳላሚሱ ኤጴፋንዮስ ተናግሯል። ዕረፍቷና እርገቷ በኢየሩሳሌም እንደሆነ የሚናገሩ ቢኖሩም ይህንን አባባል የማይቀበሉ አብያተ ክርስቲያናትና የቴኦሎጂ ምሁራን ሞልተዋል። በኢየሩሳሌም አርፋለች የሚለውን አባባል የማይቀበሉበትን ማስረጃ ሲያቀርቡም ዮሐንስ በወንጌሉ ላይ እንደተናገረው «እናትህ እነኋት አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት» ዮሐ19፤27 ባለው መሠረት ማርያም እስከ ሕይወቷ ፍጻሜ ድረስ ከዮሐንስ ጋር ስለኖረችና ወንጌላዊው ዮሐንስም ከጌታ ሞት በኋላ በኢየሩሳሌም ጥቂት ዓመታትን ከቆየ በኋላ በ37 ዓ/ም ገደማ ወደ ቤዛንታይን ከተማ ኤፌሶን ሄዶ ወገኖቹን ወንጌል እያስተማረ መቆየቱንና ማርያም በሞት እስከተለየችው ድረስ ከ48-52 ዓ/ም እዚያው እንደነበር ብዙ ተጽፏል። ከማርያም ክፍል ትይዩ ያለው የዮሐንስ መኖሪያ ቤት ፎቶ፤
በኋላም በቅርብ ርቀት ባለችው ደሴተ ፍጥሞም በግዞት መኖሩ ይነገራል ። አንዳንዶች ከዶሚኒሽን አገዛዝ ቀደም ብሎ የራእይ መጽሐፉን ከ55-65 ዓም ገደማ እንደጻፈም ይናገራሉ። ዋናው ነገር ማርያም በኤፌሶን ከዮሐንስ ጋር ኖራለች ወይስ አልኖረችም ነው ጥያቄው። በኢየሩሳሌም አርፋለች የሚሉ ሰዎች አንድም ጊዜ ከዮሐንስ ጋር በኤፌሶን ኖራለች ሲሉ አይደመጥም። ለምን? ዮሐንስ ማርያምን እንደእናት ሊይዛት አደራ ተሰጥቶታል የሚባል ከሆነ ከዮሐንስ ጋር ኤፌሶን ስለመቀመጧ የማይነገረው ለምንድነው? ዮሐንስ እስከ 96 ዓመቱ ድረስ ከኤፌሶንና ከደሴተ ፍጥሞ ውጪ ስለመኖሩ የተነገረ ነገር የለም። ማርያም ከዮሐንስ ጋር በኤፌሶን አልኖረችም ብሎ በመከራከርና በኢየሩሳሌም ኖራ፤ እዚያው ማረፏን በግልጽ በመናገር መካከል ልዩነት አለ። «እነኋት እናትህ» ባለው መሰረት አብረው ኤፌሶን ኖረው እዚያው ማረፏን የማይቀበሉና ኢየሩሳሌም ኖራ አርፋለች የሚሉ ሰዎች እንደልጅና እናት አብረው የመኖራቸውን የወንጌል ቃል መካድ ሊሆንባቸው የግድ ነው። ያ ደግሞ እስከ ሕይወቷ ፍጻሜ በኢየሩሳሌም ኖራ እረፍቷም፤ ቀብሯና እርገቷ ሆነ ከሚለው አስተምህሮአቸው ጋር «እነኋት እናትህ» የሚለው የወንጌል ቃል ስለሚጋጭባቸው ለዚህ ዓይነት ያፈጠጠ እውነት ምን እንደሚሉ አይታወቅም። ወይ ደግሞ ኤፌሶን ላይ እድሜውን ሙሉ የኖረው ዮሐንስና ኢየሩሳሌም ማርያምን ይዞ የኖረው ዮሐንስ የተለያዩ ናቸው ሊሉ ይገባል። ሮበርት ክሬው የተባለ የነገረ መለኮትና የታሪክ ጸሐፊ ዮሐንስ ወንጌላዊ ዘመኑን ሁሉ በኖረበት ከኤፌሶን ከተማ 8 ኪሎ ሜትር ወጣ ብላ ባለች ኰረብታ ላይ በተሰራ ቤት ውስጥ እንደኖረና ማርያምም እዚያ ማረፏን ጽፏል። ይህንን በኤፌሶን ያለውን የማርያምን መቃብር የዓለም ክርስቲያኖች እንዲሆም ሙስሊሞች ሳይቀሩ ይጎበኙታል፤ ይሳለሙታል። በቱርክ ግዛት ያለው ይህ ስፍራ በቱርካውያን ሙስሊሞች ዘንድ «ሜሪዬማና» ተብሎ ይጠራል። ቅድስት ድንግል ማርያም ከዚህ ዓለም የተለየችው መቼ ነው? ለሚለው ጥያቄ ጥንታዊያን አብያተ ክርስቲያናት የሚባሉት የምሥራቁና የምዕራቡ ጎራዎች የተለያየ አመለካከት አላቸው። በተወለደች በ58 ዓመቷ ዐርፋለች የሚሉ አሉ። በ72 እና 63 እድሜዋም አርፋለች የሚሉ መረጃዎች አሉ። እንደ ግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ግን የሚታመነው በ64 ዓመት እድሜዋ ማረፏ ነው። ኖረችበት ተብሎ ከሚገመተውና አርፋለች ከሚባለው ቦታ ያለው ልዩነት እንዳለሆኖ በጥር ወር ከዚህ ዓለም ተለይታ በ40ኛው ቀን ማረጓን የሚናገሩ አሉ። በነሐሴ ወር አርፋ ከተቀበረች በኋላ ትንሣዔዋን ሳያዩ መቃብሯ ባዶ ሆኖ ስላገኙት ሐዋርያት ሱባዔ ይዘውበሦስተኛው ቀን ተገለጸችላቸው የሚሉም አሉ። እንደኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ደግሞ በጥር ሞታ፤ በነሀሴ ተቀበረች የሚል ትምህርት አለ። በጥር ወር አርፋ፤ በነሀሴ ተቀብራለች የሚሉ ሰዎች ሥጋዋ በገነት ዛፍ ስር ለስምንት ወራት መቀመጡንና በሱባዔ ጸሎት በተደረገው ልመና የተነሳ ለመቀበር መቻሏን አስፋፍተው ይነግሩናል። በጥር ወር እንዳረፈች፤ ለመቀበር ያልቻለችውም ታውፋንያ የሚባል ሽፍታ፤ ጎራዴ ሲመዝባቸው ወደ ቀብር ሥጋዋን ተሸክመው ይሄዱ የነበሩት ሐዋርያት በመፍራት ጥለዋት በመሸሻቸውና ዮሐንስ ብቻውን ቀርቶ ወደ መቃብር ሳትገባ ወደ ገነት ዛፍ ስር በመወሰዷ እንደሆነ ይነገራል። ዮሐንስም ወደቤቱ ማምራቱንና ሸሽተው የነበሩትም ሐዋርያት ሥጋዋስ የታለ? ብለው ቢጠይቁት በገነት ዛፍ ስር መቀመጧን ስለነገራቸው ዮሐንስን ገነት ዛፍ ስር ሬሳዋ መቀመጡን አይቶ ለምን እኛስ ይቀርብናል በማለት ነሐሴ 1/ ቀን የጾም የጸሎት ሱባዔ ጀምረው በ15ኛው ቀን ትኩስ ሬሳ ከገነት ዛፍ ስር እንደመጣላቸውና እንደቀበሯት ይናገራሉ። ይህ እንግዲህ በ49 ዓ/ም ገደማ መሆኑ ነው። ዮሐንስ ግን ኤፌሶን መኖር ከጀመረ 10 ዓመት አልፎታል። ሌላው ጥያቄ የሚያስነሳው ነገር በጥር ወር አርፋ ከቀብር በፊት ወደገነት ዛፍ ስር ስለመወሰዷና ዮሐንስ ወደ ቤት ገብቶ ለሐዋርያት ከነገራቸው በኋላ እሱ ያየውን እነርሱም ለማየት ሐዋርያቱ ለስምንት ወር ያህል የቆዩበት ምክንያት ግልጽ አለመሆኑ ነው። ሐዋርያቱ የልባቸውን ተምኔት ለማሳካት ሱባዔ ባያደርጉ ኖሮ የማርያም ሥጋ ከገነት ዛፍ ስር አይንቀሳቀስም ነበር ማለት ነው? ሌላው ደግሞ ይህ የማርያም ሥጋ አርፎበታል የሚባለው የገነት ዛፍ ምንነትና የሙት ሥጋ ማረፊያ ተብሎ የሚመረጥ የገነት ዛፍ ስለመኖሩ እግዚአብሔር እንደዚህ ዓይነት አሰራር እንዳለው ለሰው ልጆች በመጽሐፍ ቅዱስ ያላሰፈረ አዲስ ግኝት የመሆኑ ጉዳይ ነው። በሌላ መልኩም የማርያም ሥጋ ለመቀበር የግድ የሐዋርያቱን ሱባዔ በተስፋ እየጠበቀ የመቆየቱ ነገር አስገራሚ ይሆናል። እንደሰዎቹ አባባል በጥር ወር አርፋ ሳይቀበር የቀረውን የማርያምን ሥጋ በስምንተኛው ወር ከገነት ወጥቶ ከተሰጣቸውና ከቀበሯትም በኋላ ቢሆን ሐዋርያቱ እርግቷን ለማየት አልቻሉም። ሐዋርያቱ ቀብረዋት ወደ ቤታቸው ከገቡ በኋላ ቶማስ ሐዋርያው በደመና ተጭኖ ከህንድ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ ማርያምን ሐዋርያት በቀበሯት በሦስተኛው ቀን ወደ ሰማይ ስታርግ የዳመናው ጎዳና ላይ ያገኛትና ቀድሞ የልጅሽን እርገት ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንቺን ሳላይ ልቀር ነው? ብሎ ቢያዝን ትንሣዔዬን ያላንተ ማንም አላየም ካለችው በኋላ የተገነዘችበትን ጨርቅ እና ሰበን ለምልክት ሰጥታው እንዳረገች ሰፊ ታሪክ ይነገራል። ሰዎቹ ነገሩን ሁሉ ለማጣፈጥ የሚጠቀሙበት ነገር አስገራሚ ነው። የሰው ልጅ ከትንሣዔው በኋላ የዚህን ዓለም ጨርቅና ልብስ እንደተሸከመ ወደ ሰማይ ይገባል ማለት ክርስቲያናዊ አስተምህሮ ነው ወይ? የሚል ጥያቄን ያስነሳልና ነው። ወንጌል ከትንሣዔ በኋላ ክርስቶስን ይመስል ዘንድ ሰው ይለወጣል ይላል እንጂ የመቃብሩን ልብስና ሰበን እየተሸከመ ያርጋል የሚል አስተምሮ የለውም። « 2ኛ ቆሮ 3፤18 እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን» ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን በመቃብሩ የተገነዘበትን ጨርቅ ትቶ መነሳቱን እንጂ ያንኑ ለብሶ መነሳቱን አላነበብንም። ዮሐ 20፤6-8 «ስምዖን ጴጥሮስም ተከትሎት መጣ ወደ መቃብሩም ገባ፤ የተልባ እግሩን ልብስ ተቀምጦ አየ፥ ደግሞም በራሱ የነበረውን ጨርቅ ለብቻው በአንድ ስፍራ ተጠምጥሞ እንደ ነበረ እንጂ ከተልባ እግሩ ልብስ ጋር ተቀምጦ እንዳልነበረ አየ» የሁላችን አማኞች ትንሣዔ የክርስቶስን ትንሣዔ መምሰል ካለበት በቀብር ወቅት ከዚህ ዓለም ጉድጓድ የገባ ጨርቅ ወደ ሰማይ አብሮን የሚያርግበት ምንም መንገድ የለውም። ስለዚህ ተጠራጣሪ እንደሆነ ሁል ጊዜ የሚነገርበት ቶማስን በማርያም ትንሣዔ ላይ ግን የተለየ ተጠቃሚ እንደሆነ አድርጎ ለማቅረብ ሲባል ማርያም ወደ ሰማይ ስታርግ የመቃብሯን ከፈን ተሸክማ የሄደች በማስመሰልና ለምልክት ይሆን ዘንድ ከፍላ ሰጠችው የሚለው አባባል በአንዳችም ነገር ከወንጌል እውነት የተጠጋ አይደለም። ሌላው ነገር በመንፈስ ቅዱስ በመነጠቅ፤ በሌላ ስፍራ ወዲያውኑ መገኘት ስለመቻል ለሐዋርያው ፊልጶስ ከተነገረው የወንጌል ቃል በተለየ በዳመና ላይ ተቀምጦ ስለመሄድ ግልጽ የሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ባይኖርም የቶማስን ከህንድ ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ እንደፊልጶስ መነጠቅ አድርገን ብንቆጥረው እንኳን የቶማስ ሰብአዊነትና የማርያም የእርገት ማንነት የተለያየና ፈጽሞ የማይገናኝን ነገር ለማቀራረብ መሞከር ነው። የቶማስን የዳመና ላይ ውይይትን ከረቂቅ ክርስቶሳዊ አዲስ ፍጥረት ጋር ለማገናኘት መሞከር የጥንቶቹን የግሪክ ወጎች/fable story/ እንድናስታውስ ያደርገናል። በሞትና በትንሣዔ እንዲሁም በእርገት መካከል እንደዚህ ዓይነት ነገሮችን እግዚአብሔር በሰውኛ ትረካ ይጫወታል ማለት እግዚአብሔር ስለሞትና ትንሣዔ በተናገረው መቀለድ ይሆናል። ከሁሉ የሚገርመው ደግሞ ማርያምን በጥር ሞታለች ያሉ ሰዎች፤ በመጀመሪያው ሞት ዮሐንስ ብቻ እድለኛ ሆኖ በገነት ዛፍ ስር ለማየት በመቻሉ፤ በኋለኛውም ቀብር ቶማስ ብቻ ተጠቃሚ የሆነበትን የእርገት እድል፤ ሌሎቹ ሐዋርያት ለማግኘት ባለመቻላቸው በቀጣይ ዓመት ነሐሴ አንድ ቀን ጀምረው ሱባዔ ለመያዝ መገደዳቸውንና በ16ኛው ቀን ሁለተኛ ትንሣዔና እርገትን ለማየት የመቻላቸው ነገር ነው። ቀብር ሳይኖር ትንሣዔዋንና እርገቷን እንዴት ማየት እንደቻሉ ግልጽ አይደለም። በምሳሌ ይሁን በምትሃት እርግጠኝነቱን ያብራራ ማንም የለም። ሁለት ጊዜ ትንሣዔና እርገትስ ማለት ምን ማለት ነው? ሌላው ደግሞ ማርያምን መንበር፤ ጴጥሮስን ንፍቅ ቄስ፤ እስጢፋኖስን ገባሬ ዲያቆን አድርጎ በመቀደስ አቁርቧቸዋል የሚለው ትረካ እርገቷን ተከትሎ የመጣ አባባል ነው። የማርያም ነፍስ እንዴት መንበር መሆን እንደሚችል? ምን የሚባለው ቅዳሴ እንደተቀደሰ? ለማወቅ የምናቀርባቸው ጥያቄዎችን ለጊዜው እንተዋቸውና፤ ሰራዔ ካህኑ ክርስቶስ የማንን ሥጋ እንደቆረበ? እንዲነግሩን ግን እንጠይቃቸዋለን። ለየትኛው ድኅነት/መዳን/ እሱ ይቆርባል? ክርስቶስ ቀደሰ እንጂ አልቆረበም አንድ ነገር ነው። ቆርቧል የሚባል ከሆነም ምክንያትና ውጤቱን የሚተነትን ትምህርት አያይዞ ማቅረብ የግድ ይላል። እሱማ የሕይወት ምግብ ሰጪ እንጂ ተቀባይ አይደለም የሚባል ከሆነም ሰራዔ ካህናት በዚህ ምድር መቅደስ ውስጥ ከመቀደስ ባሻገር መቁረብ አይጠበቅባቸውም በማለት አብነታዊ የክህነት አስተምህሮን አያይዞ ማቅረብ የተገባ ይሆናል። እንግዲህ ማርያምን መንበር አደረጋት፤ ክርስቶስ ሰራዔ ካህን ሆኖ ያልታወቀ ቅዳሴ ቀደሰ ማለት ስለማርያም ትንሣዔና እርገት ማጠናከሪያ በማቅረብ ትዕይንቱን ተአማኒ ለማድረግ ካልሆነ በስተቀር አንድም እውነትነት የለውም። / እንደተለመደው አባባል ቅዳሴ እግዚእ ነው የተቀደሰው የሚል ካለም ክርስቶስ ራሱን በሁለተኛ መደብ አስቀምጦ « ነአኩተከ አምላክ ቅዱስ፤ ፈጻሜ ነፍስነ፤ ወሀቤ ሕይወትነ ዘኢይማስን» ሲል አይገኝም። ራሱ ሕይወት ሰጪ ሆኖ ሳለ ሕይወት ይሰጠው ዘንድ አይለምንምና ነው። እንደዚህ ዓይነቱ አደገኛ ክህደት፤ ሰዎች ለማርያም ባላቸው ፍቅር ውስጥ ተደብቆ ለዘመናት ቆይቷል። በጉ መስዋእቱን ለህይወታችን ሰጥቷል። ከዚያ ውጪ እሱ በመንግሥቱ የፍርድ ሰዓት ዳግመኛ ሊመጣ ካልሆነ በስተቀር ከማእዱ አይካፈልም።«ሰዓቱም በደረሰ ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ጋር በማዕድ ተቀመጠ። እርሱም፦ ከመከራዬ በፊት ከእናንተ ጋር ይህን ፋሲካ ልበላ እጅግ እመኝ ነበር፤ እላችኋለሁና፥ በእግዚአብሔር መንግሥት እስኪፈጸም ድረስ፥ ወደ ፊት ከዚህ አልበላም አላቸው። ጽዋንም ተቀበለ አመስግኖም። ይህን እንካችሁ በመካከላችሁም ተካፈሉት» ሉቃ 22፤14-17 በጉ መስዋዕቱን ሕይወት ይሆናቸው ዘንድ ለሰዎች ከሰጠ በኋላ፤ በፍርድ ቀን የደሙን ምልክት ለተቀበሉት ሁሉ ዋጋቸውን ይሰጣቸዋል እንጂ እሱ የመስዋእቱ ተካፋይ ስላልሆነ፤ ክርስቶስ በቀዳሽነት ቆርቦ፤ ማቁረብ የሚባል ታሪክ ከወንጌል ቃል ሊመጣ አይችልም። ይህም በማርያም ሞትና ትንሣዔ ላይ የተጨመረ ሌላ አሳዛኝ ትረካ ነው። በግ ለተራቡ ምግብ እንጂ እራሱን ተመጋቢ ሊሆን አይደለምና። ወደዋናው ሃሳባችን ስንመለስ ለመሆኑ በማርያም ላይ ስንት ቀብር፤ ስንት ትንሣዔና ስንት እርገት ተደረገ? ብለን ብንጠይቅ እንደሚነገረው ከሆነ ፤ 1/ዮሐንስ ያየውና አፈር ያልነካው እርገት በገነት ዛፍ ስር 2/ አፈር የነካው የሐዋርያቱ ቀብር በነሐሴ 14 ቀን /ከስምንት ወር በኋላ/ 3/ ቶማስ ያየው የትንሳዔ እርገት፤ ከቀብር በኋላ በሦስተኛው ቀን ነሐሴ 16 4/ ከአንድ ዓመት በኋላ ሐዋርያት ያዩት የነሐሴ 16 ትንሣዔና እርገት ናቸው። እንግዲህ በማርያም ሞትና እርገት መካከል አራት ትእይንት መከሰቱን ዛሬም ድረስ ከሚሰጡት የቃል አስተምህሮዎችና የተዘጋጁ ጽሁፎች ውስጥ በግልጽ እናገኛለን። ማርያምን መውደድ አንድ ነገር ነው። ማርያምን ግን እየቀበሩና እያነሱ ለማረጋገጥ መሞከር ደግሞ ሌላ አሳዛኝ ክስተት ይሆናል። እንዲያውም ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት መሆን ከቻልኩ ሰባት ጊዜም ቢሆን እሞታለሁ ብላ ለልጇ ተናግራለች የሚሉትም ተረት ተያይዞ ይነገራል። የእሷ መሞት የዓለሙ ሁሉ መድኃኒት መሆን ከቻለ የክርስቶስ ከእሷ መወለድ አስፈላጊ አይደለም የሚል ሃሳብን የሚያንጸባርቀው ይህ አባባል ከአሳሳች ትረካዎች ውስጥ የሚደመር ከመሆን አያልፍም። እኛ ማርያምን ብንወዳትና ብጽእት ብንላት «እናትህንና አባትህን አክብር» ያለውን የአምላክ ቃል መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ለእርሷ የተነገረ ቃል ስላለም ጭምር ነው። ነገር ግን የዘላለማዊ አምላክ የክርስቶስ ፤ እናቱ ስለሆነች በማዳላት ወይም አምላካዊ ባህርይውን በሰውኛ ጠባይ በመለወጥ ከፍርድ ሚዛኑ በማጉደል የእሷን ሞትና ትንሣዔ የተለየ ያደርጋል ብሎ ማሰብ የዋሕነት ይሆናል። የእሷ ሞትም የመድኃኒትነትን ውክልና ለሰው ልጆች የያዘ እንደሆነ ማሰብ ክህደት ነው። ብቸኛው መድኃኒት አንዱ በግ ኢየሱስ ብቻ ነው። ማርያምም ይህንን ስለምታውቅ « ነፍሴ በአምላኬና በመድኃኒቴ ተስፋ ታደርጋለች» ብላ ነግራናለች።የትንሣዔ በኩር የሆነው ሁላችንም በሞቱ እንድንመስለው እንጂ የተለየ አድሎአዊ ጥቅምን/ faver/ ለተለዩ ሰዎች በመስጠት አይደለም።ወንጌል የሚናገረው ይህንን ነውና። ሮሜ 6፥5 «ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን» ስለዚህ ደጋግሞ መሞት፤ መነሳትና ደጋግሞ ማረግ አለ ከተባለ ያ ነገር ከክርስቶስ ትንሣዔ ጋር ያልተባበረ ስለሆነ አንቀበለውም። እንዲያውን ይህ ኑፋቄና ወንጌልን መካድ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስም የተናገረው ስለክርስቶስ ወንጌል በሞቱም ክርስቶስን እንዲመስል ነበር። ፊልጵ 3፥10-11 «እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ» ማርያምን እንወዳለን እያሉ በጥር ሞተች፤ ገነት ዛፍ ስር ስምንት ወር በሬሳ ቆየች፤ በስንት ሱባዔ ስጋዋ መጥቶ ነሐሴ ተቀበረች፤ እስከነ ምድራዊ ልብሷ አረገች፤ በዳመናው ጎዳና ላይ ከቶማስ ጋር ጨርቅ ተለዋወጠች፤ እድል ላመለጣቸው ሐዋርያት ዳግመኛ በስንት ሱባዔ በሌላ ትንሳዔና እርገት ተረጋገጠች፤ መንበር ሆና ተነጠፈች ወዘተ በማለት እየገደሉና እያነሱ በማርያም ላይ መጫወት ተገቢ ነው ብለን አናምንም። የክርስቶስን ሞትና ትንሣዔንም ማፋለስና መካድ ይሆናል። የማርያም ሞትና ትንሣዔ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ካዘጋጀው የትንሣዔው በኩር አንድያ ልጁ የተለየ አያደርገውም። ከመግቢያችን ላይ ጀምሮ ለመግለጽ እንደሞከርነው የኤፌሶኑና የኢየሩሳሌሙ ታሪክ እንዳለ ሆኖ አብያተክርስቲያናት ሁሉ የተለያየ የሞትና የትንሣዔ አስተምህሮ ከመያዛቸው አንጻር ኤጲፋንዮስ እንዳለው ትክክለኛው ታሪክ ቀን አይታወቅም። [2 ] አሁን የሚደረገው ግን ልምድና ትውፊት ነው። ይሁን እንጂ የሆነውን ቀን ወስኖ መታሰቢያ ማድረጉ ባይከፋም እየገደሉና እያነሱ ከመጽሐፉ ቃል በተጻጻሪ የትንሣዔንና የእርገትን ነገር ዋጋ ማሳጣት ተገቢ አይደለም።

Tuesday, March 7, 2023

ኬንያዊው "ኢየሱስ ክርስቶስ" ችግር ላይ ወድቋል‼

"ከ2000 አመታት በፊት በኢየሩሳሌም የነበርኩት ትክክለኛው ኢየሱስ እኔ ነኝ" የሚለው ኬንያዊው ፓስተር ሙአሊሙ የሱ ዋህ ታንጎሌ በኬንያ በርካታ ተከታዮችን አፍርቷል። አንድ ሚስት እና ስምንት ልጆች ያሉት ሙአሊም ተዓምራቶችን ሲፈጽም አይተናል በሚሉ በሺህ የሚቆጠሩ ተከታዮች ታጅቦ ሥርዓተ አምልኮ ያስፈፅማል። 12 ደቀመዝሙሮችን ሳይቀር የሰየመው እና "ዓለምን ለማዳን ከእግዚአብሔር የተላኩ መሲህ ነኝ" የሚለው ሙአሊም በሽተኞችን ከመፈወስ አንስቶ በሠርግ ላይ ውሃን ወደ ሻይ ሲቀይር አይተናል ይላሉ ተከታዮቹ። ተከታዮቹ የቡግማን ሰዎች ታዲያ መጪው ፋሲካ ከመድረሱ በፊት ትክክለኛው መሲህ መሆኑን ለማረጋገጥ የፈለጉ ይመስላል። ይህንን መሲህ ነኝ ባይ ፓስተር "እንሰቅለው ዘንድ ይገባል። ከዚያም በ3ኛው ቀን ከሞት ይነሳ እንደሆነ ማረጋገጥ አለብን።" በማለት ውሣኔ ላይ ደርሰው ዝግጅታቸውን ጀምረዋል። አሟሟቱም በመስቀል ላይ በሚስማር ተቸንክሮ እንዲሆን እና ከቀበሩት በኋላ ቀጣዩን 3 ቀናት ከሞት ይነሳ እንደሆነ ለመጠበቅ ወስነዋል። ይህንን የተረዳው እና ሃሳባቸው ምንም ያልጣመው ሙአሊም ወደ ኬንያ ፖሊስ በመደወል ከስቅላት እንዲያስጥሉት ተማጽኗል። ተከታዮቹ ግን በውሳኔያቸው ጸንተዋል፣"ፖሊስ በእምነታችን ጣልቃ እንዳይገባብን!! ይህ በእኛ እና በመሲሑ ሙአሊም መካከል የምንጨርሰው ጉዳይ ነው" ብለዋል!! ጋሼ ሙአሊም አላህ ይረዳህ እንደሆነ እስኪ ወደዚያ ጩህ!

Friday, April 22, 2022

ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶልናልና 1ኛ ቆሮ 5፣7

ዕብራውያን פֶּסַח» ፔሳኽ» ይሉታል። ፋሲካ ማለት ነው። በወርኀ ኒሳን በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን ይከበራል። ሥርዓቱ የሚጀመረው በዐሥራ አራተኛው ቀን ዋዜማ ሲሆን በፋሲካው ሳምንት እርሾ የገባበት ምንም ዓይነት ምግብ መመገብ ክልክል ነው።ዕለቱን ተቦክቶ ወዲያው የሚጋገር እንጂ የኮመጠጠ ወይም የቦካና የዋለ፤ያደረ መመገብ በሕጉ እንደተቀመጠው ከእስራኤል አንድነት ያስወግዳል። ከማንኛውም እርድ ላይ ጥሬ መብላት ወይም ከበሉትም አስተርፎ ማሳደር አይፈቀድም። ለመስዋዕት የሚቀርበው የበግ ወይም የፍየል መስዋዕትም እድሜው ከአንድ ዓመት ያልበለጠ ጤናማና የተመረጠ መሆን ይገባዋል። በዐሥራ ዐራተኛው ቀን ምሽት መስዋዕቱ ይታረዳል።ሥጋውን ደግሞ ሌሊት ከመራራ ቅጠል ጋር ቀላልቅለው ይበሉታል። ደሙን ደግሞ የበሩን ሁለት መቃንና ጉበኑን ይቀቡታል። ሁለቱን ቋሚ መቃንና የላይኛውን ጉበን ሲቀቡት ይህንን ቅርጽ ይይዛል።
ይህ ቅርጽ የዕብራውያን ስምንተኛውን ፊደል «ኼ» የተባለውን ይወክላል። (እንደአማርኛው በጉሮሮ ሳይሆን በላንቃ የሚነበብ ነው) «ኼ» ማለት በዕብራውያን ትርጉም «ሕይወት» ማለት ነው። ዕብራውያንም በፊደላቸው በ«ኼ» ቅርጽ በሚቀቡት ደም የተነሳ ወደፈርዖናውያን ሠፈር የሚያልፈው ሞት አይነካቸውም። ምክንያቱም ሕይወት የሚል ማኅተም በራቸው ላይ ታትሟልና። ፋሲካ ማለት ይህ ነው። በደሙ ምልክት የተከለሉ በሕይወት ለመቆየት ዋስትና የያዙ ሲሆን ይህንን ማኅተም ያላገኙና ምን እየሆነ እንዳለ የማያውቁ ደግሞ በሞት የሚወስዱበት የፍርድ ምልክት ነው። ደሙ የሞትና የሕይወት መለያ ምልክት ሆኖ አገልግሏል። ይህ ሥርዓት እስራኤላውያንን ከባርነት፤ ከጠላት አገዛዝና ከመገደል የታደገ የዋስትና መንገድ ነበር። እንደዚሁ ሁሉ የአዲስ ኪዳኑ ፋሲካ ሕዝብና አሕዛብን ከሰይጣን ባርነትና ከዘላለም ሞት የታደገ በመሆኑ ሐዋርያው ጳውሎስ «እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና» 1ኛ ቆሮ 5፤7 በማለት የሚነግረን። የእስራኤል ዘሥጋ ፋሲካ መጻጻና የቦካ ይከለክል እንደነበረው ሁሉ የአዲስ ኪዳኑ ፋሲካም እንዲሁ ይከለክላል። በኃጢአትና በዐመጻ የቦካ የውስጣችንን ሆምጣጣ እርሾ ካላስወገድን በስተቀር በፋሲካው የሚገኘውን ሕይወት በፍጹም አናገኝም። የቀደመው ፋሲካ እርሾ ያለውን ነገር ከቤቱ ያላጠፋ ከእስራኤል ጉባዔ ተለይቶ ይጥፋ የሚል ሕግ ነበረው። ምድራዊው ፋሲካ ይህንን ያህል ከከበረ ሰማያዊውማ እንደምን የበለጠ አይከብር? ፋሲካን መናገርና ፋሲካን አውቆ መኖር የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ስለፋሲካ ብዙ ማስተማርና መናገር ይቻል ይሆናል። ስለፋሲካ የመልካም ጊዜ መግለጫና ስጦታም መለዋወጥ ይቻል ይሆናል። ፋሲካ ግን በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ አይገኝም። ፋሲካ በስግደትና በወይራ ቅጠል በመጠብጠብ የሚገኝም ጸጋ አይደለም። ፋሲካ የአንድ ወቅት ራስን ማስገዛትና በጽኑ እሳቤና ጭንቅ ማለፍ ውስጥ የሚመጣም አይደለም። ፋሲካ በልባችን መቃንና ጉበን ላይ የደሙን ምልክት በመያዝ ዕብራውያን ከሞት እንዳመለጡበት የ «ኼ» ምልክት ማኅተም በመያዝ ብቻ ነው የምንድነው። ያን ጊዜ ብቻ ነው ሞት በራችን ላይ ያለውን የአዲስ ኪዳኑን ፔሳኽ አይቶ የሚያልፈን። ይህንን የደም ማኅተም ለመያዝም ከክፋት፤ ከሀሰት፤ ከግፍና ከዐመጻ እርሾ መለየት የግድ ነው። ከዝሙት፤ ከስርቆት፤ ከጉቦ፤ ከምኞትና ከኃጢአት ሁሉ እርሾ ሳንለይ ውስጣችን የሞላውን መጻጻ ተሸክመን የፋሲካ ሕይወት አይገኝም። ጳውሎስም እንዲህ አለን። «ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾም አይደለም» 1ኛ ቆሮ 5፤8 እንግዲህ ከፋሲካው ተስፋ የምናደርግ ሁላችን እስኪ ራሳችንን እንመርምር። እንደመጽሐፍ ሊያነበን በሚቻለው ከፋሲካችን ክርስቶስ ፊት እስኪ ራሳችንን እናንብበው። በእውነት እነዚህ እርሾዎች በውስጣችን ከሌሉ ከ2000 ዓመት በፊት ለሕይወት የፈሰሰውን ደም ይዘናል ማለት ነው። ያኔም ሞት በኛ ላይ ምንም ሥልጣን እንደሌለው አረጋግጠናል። እስራኤላውያን የበራቸውን ጉበንና መቃን በቀቡ ጊዜ ሞት እንደማይነካቸው እርግጠኞች እንደነበሩ ሁሉ እኛም የበለጠውንና የተሻለውን የሕይወት ደም በእምነት ስለያዝን ለዘላለማዊ ሕይወት እርግጠኞች መሆን እንችላለን። ከዚያ ባሻገር በየዓመቱ በሚመጣ በዓል የሚገኝ የደም ምልክት የለም። በጥብጠባና በስግደትም የሚገኝ የሕይወት ዋስትናና የሚሻር ኃጢአት የለም። የተደረገልንን ማሰብ አንድ ነገር ሆኖ ሰው ግን ዓይኑን በዚያ በዓል ላይ ተክሎ የዓመቱ ኃጢአት ወይም ሸክም እንደሚወድቅ ማሰብ ስህተት ነው። ዓመቱን ሙሉ ከክፋትና ከግፍ እርሾ በመላቀቅ፤ አንድም ሰከንድ የማይለይ የልባችንን ጉበንና መቃን ላይ ደሙን በእምነት ይዘን መገኘት የግድ ይሆንብናል። ያኔ ነው ፋሲካችን ታርዷል የምንለው። ያኔም ነው ሁልጊዜ በሕይወት መንገድ ላይ እንዳለን የምናውቀው። መንፈሳዊ ሕይወት እንዲኖረን፤ መንፈሳዊ ጉዞ እንዲሰምርልን ዕለት፤ ዕለት መታደስ መታደስ ይገባዋል እንጂ በዘልማድ መንገድ አንመላለስ! «ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል» 2ኛ ቆሮ 4፤16 ፋሲካችን የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ያደረገልንን ውለታ እያሰብን ውስጣችንን መፈተሽ የግድ ነው። በአምናው እኛነታችንና በዘንድሮው እኛነታችን መካከል የሕይወት ለውጥ ከሌለን ሞት በመጣ ጊዜ ምንም የመዳን ምልክት እንደሌላቸው ፈርዖናውያንን ወደዘላለማዊ ሞት መሄዳችን እውነት ነው። በወይራ በመጠብጠብ 30 እና 40 ለመስገድ ከመሽቀዳደም ይልቅ፤ ከሞት የማምለጫ የፋሲካው ዓርማ ክርስቶስን ከኃጢአት በጸዳ ማንነታችን ውስጥ ዘወትር ይዘነው እንኑር። የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን እሁድ ነው። ከእሁድ እስከ እሁድ 8 ቀናት አሉት። ዕብራውያን የበራቸውን ጉበንና መቃን የቀቡት ቅርጽ ከዕብራውያን አሌፋት መካከል የ «ኼ» ስምንተኛው ፊደል አምሳል ነው። «ኼ» ደግሞ ትርጉሟ «ሕይወት» ማለት ነው። ይህ የደም ምልክት ነው ሕይወት የሆናቸው። በሳምንቱ የመጀመሪያው ቀን የአዲስ ኪዳኑ ሕይወት በክርስቶስ ትንሣዔ ለዓለሙ ሁሉ ታደለ። ይልቅስ ይህንን ደም በልባችንን ጉበንና መቃን ላይ እንደንጹሕ መስዋዕትለመቀባት እንሽቀዳደም። ያኔምክርስቲያኖች እግዚአብሔርን ፍለጋ የት መሄድ ይገባናል? የእግዚአብሔር መገኛው የት ይሆን? ከምድራዊት ቤተ መቅደስ? ከገሪዛን፤ ከጌባል? ወይስ በኢየሩሳሌም? አንዳንዶች ኢየሩሳሌምን የተሳለመ የ40 ቀን ሕጻን ይሆናል ይላሉ። የቆረበ ደግሞ የበለጠ የ40 ቀን ሕጻን እንደሚሆንም ይሰበካል። ከተሳለመ የ40 ቀን ሕጻን በመሆንና ከቆረበ የ40 ቀን ሕጻን በመሆን መካከል ያለው ልዩነት አይገባኝም። ኢትዮጵያ በመቁረብና ኢየሩሳሌም ከጎልጎታ ሄዶ በመቁረብ መካከልስ ያለው ልዩነት ምንድነው? ሰዎች ክርስትናን እንደሕግ ሥርዓት ማክበር ሲጀምሩ የሕግ የብልጫ ልዩነት ክርስትናውን መውረስ ይጀምረዋል። ኢየሩሳሌም ሄዶ በመሳለም ወይም በመቁረብና ኢትዮጵያ በመቁረብ መካከል ልዩነት የሚመጣውም ለዚህ ነው። መቱ ባለች ቤተ ክርስቲያን ጓሮ በመቀበርና ደብረ ሊባኖስ በመቀበር መካከል ያለው የመብት ልዩነትም ውጤቱ የሕግ ተፋልሶ ክርስትናውን በመዋጡ የመጣ ነው። የወንጌል እውነት ግን ያንን እንድንል አይነግረንም። እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቦታና በሥፍራ የሚወሰን አምላክ አይደለም። ስለዚህም እግዚአብሔር በመንፈስ ይመለካል፤ በእምነትም፤ የመንፈስ የሆነ ሥራ በሕይወታችን ላይ ሊገለጥ ይገባዋል። ያኔ ዲላ ሚካኤል ተቀበርን፤ ደብረ ሊባኖስ፤ ደሴ ቆረብን አውስትራሊያ በማንነታችን ላይ ለውጥ የለውም። በሕይወቱ የክርስትና ማንነት የሌለው ሰው ደብረ ሊባኖስ ጓሮ መቀበሩ በፍርድ ወንበር ፊት ለውጥ አያመጣለትም። ሰው ሲሞት ይዞት የሚሄደው በምድር የነበረውን ሥራ እንጂ በሰማይ የሚፈጸም የክርክር ዳኝነት የለም። «እስመ አንተ ትፈድዮ ለኩሉ በከመ ምግባሩ» እንዳለ ዳዊት በመዝሙር 62፤12 ስለዚህ እግዚአብሔር በመንፈስ ይመለካል፤ በመንፈስ ይሰገድለታል፤ በመንፈስ ይታመናል እንጂ በቦታና በሥፍራ አይደለም። እሱን ይይዝ ዘንድ የሚችል ምድራዊ መቅደስ የለንም። «ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ? ይላል ጌታ» የሐዋ 7፤50 «ወትቤሎ፤ አበዊነሰ በዝንቱ ደብር ሰገዱ፤ ወአንትሙሰ ትብሉ ከመ በኢየሩሳሌም መካን ውእቱ ኀበ ይሰግዱ። ወይቤላ ኢየሱስ፤ እመንኒ ብእሲቶ ከመ ትመጽእ ሰዓት አመ ኢበዝንቱ ደብር፤ ወኢበኢየሩሳሌም ዘይሰግዱ ለአብ፤ አንትሙሰ ትሰግዱ ለዘኢታአምሩ፤ ወንሕንሰ ንሰግድ ለዘናአምር፤ እስመ መድኃኒት እምነ አይሁድ ውእቱ። ወባሕቱ ትመጽእ ሰዓት፤ ወይእዜ ይእቲ፤ እመ እለ በርቱዕ በአማን ሰጋድያን፤ ይሰግዱ ለአብ በመንፈስ ወበጽድቅ እስመ አብኒ ዘከመዝ የኀሥሥ እለ ይሰግዱ ሎቱ። እስመ እግዚአብሔር መንፈስ ውእቱ፤ እለሂ ይሰግዱ ሎቱ በመንፈስ ወበጽድቅ ሀለዎሙ ይሰግዱ ሎቱ» ትርጉም፤ «አባቶቻችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እናንተም፦ ሰው ሊሰግድበት የሚገባው ስፍራ በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ አለችው። ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ አንቺ ሴት፥ እመኚኝ፥ በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ ይመጣል። እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ መዳን ከአይሁድ ነውና ለምናውቀው እንሰግዳለን። ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል» ዮሐ 4፤20-24 የኢየሱስ ስቅለት የሚታሰበው በመንፈስ መሆኑን ለማመልከት ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች እንዲህ አላቸው። ኢየሱስ የተሰቀለው ኢየሩሳሌም እንጂ ገላትያ አለመሆኑን እያወቀ ለገላትያ ሰዎች ግን «በዓይናችሁ ፊት እንደተሰቀለ ሆኖ ተስሎ ነበር» እያለ ይወቅሳቸዋል። ምክንያቱም ስቅለቱ በአማኞች ፊት የሚታየው በየዓመቱ ለሁለት ወር በሚደረግ ጾምና ለአንድ ሳምንት በሚታሰብ የሕማማት ሳምንት ሳይሆን በየትኛውም ቦታ ብንሆን ያለምንም ዕረፍት በዘመናችን ሙሉ ነውና። የሕማማቱ ሳምንት ካለፈ በኋላስ? በዓለ ፍስሐ ወሀሴት፤ በዓለ ድግስ ወግብዣ፤ በዓለ ምግብ ወመጠጥ ነው? የኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ለሁለት ወር ከምግብ የመከልከል ማዕቀብና ለሁለት ወር ተከልክለው የነበሩ ምግቦች በተራቸው ድል የሚቀዳጁበት በዓል አይደለም። ዓመቱን ሙሉ በፊታችን እንደተሰቀለ ሆኖ የምናስብበት፤ በመንፈስና በእውነት የምንሰግድለት ቋሚ የሕይወታችን መርህ እንጂ በአርብ ቀን የወይራ ጥብጣብ የሚያበቃ ዓመታዊ ልምምድ ካደረግነው ከገላትያ ሰዎች በምን እንሻላለን? ለዚህም ነው፤ ብዙ ክርስቲያኖች ከነገሠባቸው የሥጋ ሥራ ሳይላቀቁ ፋሲካን እያከበሩ ዘመናቸውን ሁሉ የሚፈጽሙት። ጋብ ብሎ የነበረው የሥጋ ሥራ ከፋሲካ በዓል በኋላ ይደራል። ዝሙቱ፤ ውሸቱ፤ ስርቆቱ፤ ማጭበርበሩ፤ ሃሜትና ነቀፋው ያለማንነት ለውጥ እንደነበረው ይቀጥላል። ዓመቱን ሙሉ ያጠራቅሙትን ኃጢአት የፋሲካ ጾም ሲመጣ ለማራገፍ እንደሚቻልበት አመቺ ጊዜ ጠብቀው ብዙ ሰዎች ጥሬና ቆሎ ቋጥረው በየዋሻውና ፍርክታው ልክ እንደሽኮኮ ይመሽጋሉ። ሀብት ያላቸው ኢየሩሳሌም ሄደው ለመሳምና ለመቁረብ ገንዘባቸውን በየዓመቱ ይከሰክሳሉ። የክፉ ቃል ምንጭ የሆነውን አንደበቱን ሳይዘጋ ሥጋ መሸጫ ቤቱን የሚዘጋ የት የለሌ ነው። ከተማውን ሁሉ የወረረው የሚዛን መሥፈሪያ በፈሪሃ እግዚአብሔርና ያለማጭበርበር ሳይሰሩበት ጾም የሚሉትን ፈሊጥ የሚጠብቁት ለምንድነው? አቤት! የዘንድሮ ሚዛን የሚባለው የድሮና የዚህ ዘመን ሚዛን ልኬታ የተለየ ሆኖ ይሆን? የሕዝብና የመንግሥት ሀብት የሚዘርፉ የሕግ ፋሲከኞች ቁጥራቸው ብዙ ነው። የቤተ ክርስቲያን ደወል ሲደወል የሚከንፉ ነገር ግን የቤታቸውን የፍቅርና የሰላም ደወል የተነጠቁ ቤቱ ይቁጥራቸው። ሠራተኞቻቸውን የሚያስጨንቁ፤ በፍትህ አደባባይ ፍርድን የሚጨፈልቁ፤ በመማለጃም የእንባን ዋንጫ የሚጎነጩ የሁለት ወር ጸዋሚዎችና ተሃ ራሚዎች አያሌ ናቸው። የልምድ ክርስቲያኖች የሕይወት ምስክርነት በሥራቸው ሊታይባቸው አይችልም። ስለዚህም ይመስለኛል፤ በክርስቲያን ቁጥር ብዙ ሆነን በበረከት መትረፍረፍ አቅቶን እድሜ ልካችንን ከእምነት የለሾች ምጽዋት ጠባቂ ሆነን የቀረነው። እንደእምነት የለሾቹ፤ እምነት የለሾች ብንሆን ያለእምነት ስለሚፈረድብን በሥጋ ረሃብ ባልተገፋንም ነበር። እግዚአብሔርን እየጠራን፤ እንደፈቃዱ ለመኖር ባለመቻላችን በራሳችን የእምነት ጉድለት በሥጋችን እንቀጣለን። ብዙ ባወቅህ ቁጥር ብዙ ሥራ ይጠበቅብሃል። ካልሰራኸው ግን ባታውቅ ቢቀርብህ ይሻልህ ነበር። ስለዚህ ማወቅህ ለመዳንህ ዋስትና የሆነውን ነገር ካላትርፈረፈልህ ክርስትናህ ምንድነው? ኢየሱስ በባዶ ተስፋ አልተወንም። እኛ ግን አስሮ በያዘን በገላትያውያን አዚም ፈዘን ሳለ ስለገላትያ አዚም እናስተምራለን። የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለትና ትንሣኤ በየዓመቱ እየዞረ የሚመጣ በዓል ሳይሆን ዕለት፤ ዕለት በፊታችን ተስሎ የሚታየን የሕይወታችን አካል ነው መሆን ያለበት። በቦታ፤ በሥፍራና በጉዞ ብዛት የሚከበር ሳይሆን በእውነትና በመንፈስ እንድናመልከው የተደረገልን የማዳን ሥራ ነው። በአዲስ ሰውነት ለውጥ እንጂ በሕግ ሥነ ሥርዓት ልናሳልፈው አይገባም። ሰላምና እርጋታ በውስጡ መኖሩን መንፈስ ቅዱስ የሚመሰክርለት አማኝ ሀገር ለሀገር፤ ተራራ ለተራራ ትንሣኤውን ፍለጋ ሲዞር አይገኝም። ምክንያቱም፤ ሁል ጊዜ በዓይኑ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ይታየዋልና»! ከተያዝንበት አዚም ተላቀን በልባችን የተሳለውን ትንሣኤ፤ በኑሮአችን ፍሬ የሚታይበት እንዲሆን እግዚአብሔር ይርዳን! አሜን።

Saturday, April 16, 2022

ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር ማቴ ፳፩፣፱

«ሆሳዕና» ቃሉ ከሁለት አረማይክ ቃላት የተሰራ ሲሆን ትርጉም «እባክህ እርዳ፣ አሁን አድን» ማለት ነው። እብራይስጡም ይህንኑ ቃል ወርሶ «הושענא » ሆሻአና ሲል ይገኛል። አዎ «አሁን አድን፣ እባክህ እርዳን» ብሎ የአዳም ዘር ያጣውን ልጅነትና የደረሰበትን ሞት ለመላቀቅ የሚያሰማው የጩኸት ድምጽ ነው፣ «ሆሳዕና»!!! ዳዊት ነቢይ በመንፈስ ቅዱስ ተመልክቶ ማዳኑን ሲጣራና አሁን ናልን ሲል ከዘመናት በፊት አድምጠነዋል። የውስጥ ዓይኖቹ ሩቅ አይተዋል። ማዳኑንም ሽተው እንዲህ ሲል ዘምሮለታል። «አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና» መዝ ፻፲፰፣፳፭ ያ ማለት ደግሞ « אָנָּ֣א יְ֭הוָה הֹושִׁ֘יעָ֥ה נָּ֑א אָֽנָּ֥א יְ֝הוָ֗ה הַצְלִ֘יחָ֥ה נָּֽא » አና ያኽዌ ሆሳአና አና ያኽዌ ሆስሊኻ ና» የሚለው የእብራይስጡ ቃል ነው። አበው የማዳኑን ነገር አስቀድመው አይተው በተስፋ «ሆሳዕና» እያሉ ዘምረዋል። የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ በክርስቶስ ኢየሱስ እስኪገለጥ ዘወትር በእንባና በዝማሬ ወደ ተስፋው ፍጻሜ ድምጻቸውን ያሰሙ ነበር። አዎ ንጉሥ ክርስቶስ ከዘጠና ዘጠኙ በጎች መካከል የጠፋውን አንዱን በግ ፍለጋ ንጉሥ ሆኖ ሳለ እንደንጉሥ ያይደለ በአህያ፣ ለዚያውም በውርንጫ ተቀምጦ «የአሁን አድን (ሆሳዕና)» ጩኸት ሊመልስ በጽዮን ከተማ ይመጣል፤ ይህንንም ዘካርያስ ከዘመረው ዘመናት ተቆጥረው ነበር። «አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል» ዘካ ፱፣፱ ምንኛ ይደንቅ? ምንኛስ ይረቅ? ንጉሥ ስለመምጣቱ አስቀድመው የተናገሩለትና ከዘመናት በፊት ማዳኑን አይተው በእልልታ የዘመሩለት!! ሰማያዊ ንጉሥ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለዘርዓ ብእሲ ከስጋችን ተዛምዶ ማዳኑን ሲጠብቁ፤ ከሩቅ አይተው ሲጣሩ፣ ሲዘምሩለትና አንድ ቀን ማዳኑ እንደሚሆን ተስፋ ሲያደርጉት የነበረው ሰዓቱ ደርሶ በመካከላቸው ሲገኝ ይጠብቁት የነበረው ዓይነት ሳይሆን ውበት የሌለውን ንጉሥ ለመቀበል የገዛ ወገኖቹ ተቸግረው ነበር። አዎ የደም ግባት ብቻ ሳይሆን የንጉሥ ወግ የሌለው፣ በአህያ ለዚያውም በውርንጫ የሚመጣ ንጉሥ እንዴት ይቀበሉት? «በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል። መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም» ኢሳ ፶፫፣፪ አባቶቻቸው ለዘመናት «ሆሳዕና፣ ማዳንህ አሁን ይሁን» ያሉለትና የዘመሩለት በዕለተ ቀጠሮው ማዳኑን ሊያሳይ ከጽዮን ደጃፍ ቀርቦ ሳለ የማያውቁት፣ ያልሰሙት፣ ትንቢቱን ያላነበቡት «ሆሳዕና» ሲሉ ትልልቆቹ ዕብራውያን ግን ዝም አሉ፣ ዝም በሉም አሉ! «ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም፣ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው፣ እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት» የማዳኑ ጌታም፣ «እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን? አላቸው» ማቴ ፳፩፣ ፲፭-፲፮ ኢየሱስ ክርስቶስ የእነዚህን ሕፃናት ዝማሬና ምስጋናን የሰማው ከቤተ ፋጌ ወደ ኢየሩሳሌም ማዳኑን ሊፈጽም በመጣ ጊዜ ነበር። ቤተ ፋጌ ከኢየሩሳሌም ከተማ ምሥራቃዊ አቅጣጫ በቢታንያና በደብረ ዘይት ተራራ መካከል የምትገኝ መንደር ነበረች። ቤተ ፋጌ ማለት በአረማይክ «ያልበሰለ በለስ ቤት» ማለት ነው። ርቀቱም ከኢየሩሳሌም የሰንበት ያህል ምዕራፍ ነበር። ጌታ ኢየሱስም ከኢያሪኰ ከተማ ወደኢየሩሳሌም ሲወጣ ካረፈባት ከቤተ ፋጌ መንደር ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ልኰ ውርንጫይቱን ከታሰረችበት ፈትተው እንዲያመጡለት አዟል። «ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ፥ ያንጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከ፥እንዲህም አላቸው፦ በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርስዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ» ማቴ ፳፩፤፪ ያን ጊዜም በቀደምት አበው የተነገረው ትንቢትና ዝማሬ ፍጻሜ አገኘ ማለት ነው። «የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም። ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር» ማቴ ፳፩፣፱ ይሁን እንጂ ኢየሩሳሌም ለሆሳዕና አልተዘጋጀችም ነበር። ይልቁንም ቤተ መቅደሱ አካባቢ ስለማዳኑ ዝማሬ በማቅረብ ፋንታ የጦፈ የንግድ ገበያ ደርቶበት ነበር። ቤተመቅደሱ የጸሎት ሥፍራ መሆኑ ቀርቶ የሻጮችና የለዋጮች መድረክ ሆኖ ነበር። ያኔ ማዳኑ የቀረበላት ኢየሩሳሌም በመቅደሱ በራፍ ስትሸጥ፣ ስትለውጥ መድኃኒቱን ሆሳዕና እያለች መቀበልን እንዳልቻለች ሁሉ የዛሬዋ ቤተክርስቲያንስ ንግድና ሸቀጥ የሌለበትን «ሆሳዕና» እያከበረች ነው ወይ? ብለን ብንጠይቅ ራስን ማታለል ካልተጨመረበት በስተቀር፣ መሸጥ መሸቀጡ የሌለበትን «ሆሳዕና» የሚያከብር የለም ነው መልሱ። ዐውደ ምሕረቱ ሱቅ በደረቴ ያልሆነበትን ሥፍራ ማግኘት ከባድ ነው። ኢየሱስ ማዳኑን ከመፈጸሙ በፊት እነዚህን ነጋዴዎች አስወግዷል። ገበታቸውን ገልብጧል። እየገረፈ አስወጥቷል። የወንበዴዎች ዋሻ የሆነውን የጸሎት ቤት ጠራርጓል። ዛሬስ ቤቱ ስንት ወንበዴ መሽጎበት ይሆን? ወንበዴዎቹ ይዘምራሉ፣ ሆሳዕና ይላሉ፣ የዘንባባ ዝንጣፊ ይይዛሉ፣ በጣታቸው፣ በግንባራቸው ያስራሉ። ወንበዴዎች ናቸው ተብለው እንዳይርቋቸው የአምልኰ መልክ አላቸው። ቤተመቅደሱን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁ ያለው በግብር ውንብድና በመልክ ግን አገልጋይ ይመስሉ የነበሩትን የመቅደሱን ሰዎች ነበር። ዛሬም እንደዚያው!! በሌላኛው ቀንም በዚያው በመቅደሱ ሲያስተምር ዋለ። የወይኑ ጌታ ስለወይኑ ደኅንነት የላካቸውን አገልጋይ ሠራተኞች ታሪክ አወጋቸው። የሕይወት ለውጥ ለወይኑ ባይሆንለት ይፈሩት እንደሆነ አንድ ልጁን ቢልክም ገበሬዎቹ ወራሹ ይህ ነው እንግደለው ብለው መከሩበት፣ መክረውም አልቀረም፣ ከወይኑ አውጥተው ገደሉት። ስለዚህ የወይኑ ጌታ ገዳዮቹን ምን የሚያደርግ ይመስላችኋል? ሲል ይጠይቃቸዋል። እነሱም መልስ መለሱ። መልሱ ግን በራሳቸው ላይ የሚሆን የምስክርነት ፍርድ ነበር። «ፍታሕ በርእስከ» ማለት ይህ ነው። እነሱም እንዲህ ሲሉ በራሳቸው ፈርደው ተናገሩ። «እርሱም፦ ክፉዎችን በክፉ ያጠፋቸዋል፥ የወይኑንም አትክልት ፍሬውን በየጊዜው ለሚያስረክቡ ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጠዋል አሉት» ማቴ ፳፩፤፵፩ የአይሁድ ፋሲካ ከመሆኑ ሶስት ቀን ቀደም ብሎ ደብረ ዘይት ተራራ ላይ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ይነጋገር ነበር። ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይወድቅ የማይቀረው ለምድነው አሉት? ስለረገማት በለስና ስለኢየሩሳሌም ጥፋት ተናገረ። ኋላም በሮማዊው ጥጦስ ትንቢቱ ተፈጸመ። ፍሬ አልባዋ በለስ እስራኤል ጠፋች። ጴጥሮስ ደብረ ዘይት ላይ ሌላ ጥያቄ አነሳ። «እርሱም፦ መምህር ሆይ፥ እንግዲህ ይህ መቼ ይሆናል? ይህስ ይሆን ዘንድ እንዳለው ምልክቱ ምንድር ነው? ብለው ጠየቁት» የቅርቡን ጊዜና መጨረሻውን ዘመን ምልክቶች ነገራቸው። የቅርቡ ጊዜ የኢየሩሳሌም መከበብ የበለስ መድረቋ ጊዜ መሆኑን እንዲህ አለ። «ኢየሩሳሌም ግን በጭፍራ ተከባ ስታዩ በዚያን ጊዜ ጥፋትዋ እንደ ቀረበ እወቁ» ሉቃ ፳፩፤፳ በዚህ የኢየሩሳሌም የመጥፊያ የፍርድ ቀን መድረሱን አሳይቷል። እንደገናም የኋለኛውንም ዘመን ትንቢት ደግሞ ይህች የተረገመች በለስ ስታቆጠቁጥ በጋ እንደ ደረሰ ታውቃላችሁ፤ ያኔ ደግሞ የመጨረሻው የፍርድ ቀን እንደደረሰ ምልክት ይሆናል አላቸው። «ምሳሌንም ነገራቸው እንዲህ ሲል፦ በለስንና ዛፎችን ሁሉ እዩ፣ ሲያቈጠቍጡ ተመልክታችሁ በጋ አሁን እንደ ቀረበ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።እንዲሁ ደግሞ እናንተ ይህ ሁሉ መሆኑን ስታዩ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ቀረበች እወቁ» ሉቃ ፳፩፤፳፱-፴፩ አዎ ! የመጨረሻው ዘመን ዋናው ምልክት ፍሬ አልባዋና የደረቀችው በለስ ማቆጥቆጥ መጀመሯ ነበር። ያኔ የአጨዳው መከር ስለመድረሱ ጫፏ ሲለሰልስና ማቆጥቆጥ ሲጀምር በጋ እንደደረሰ እወቁ« ተብሏል። እናም የምንዘምረው ዝማሬ ትልቅ ትርጉም አለው። ማዳኑን አይተናል። «ሆሳዕና በአርያም » እያሉ መዘመር ብቻውን ግን ዋጋ የለውም። ኢየሩሳሌም ተዘምሮባት ነበር። ግን ፍሬ የሌለባት በለስ በመሆኗ ደረቀች። በሚያምር ውብ ድንጋይ ፵፮ ዘመን የታነጸውን መቅደስ ማዳን አልቻለም። ተራሮችን ውደቁብን እስኪሉ ድረስ የወረደውን መከራ መሸሸግ የቻለ ዝማሬ አልተገኘም። መቅደሱ በወንበዴዎች ተሞልቶ ነበር። ወንበዴዎቹ ልጁን አልተቀበሉትም። የተቀበሉትም ፍሬ አላፈሩም። ስለዚህ በጭፍራ ተከበው ለሺህ ዘመናት ጠፉ። ዛሬ በኛ የሚሆን ፍሬ አልባነት ጥፋቱ ለሺህ ዘመን አይደለም። ለአልቦ ማኅለቅት እንጂ!! በእድሜአችን ስንት «ሆሳዕና በአርያም» አሳለፍን? ማዳኑ በተደረገለት ማንነታችን ውስጥ ስንት ፍሬ አፈራን? የተራበው ኢየሱስ ከእኛ የሚፈልገውን ፍሬ ይዘናል? ወይስ ፍሬ አልባ ሆነን ለቁጣ የተዘጋጀን እንሆን? «ሆሳዕና በአርያም» ማለቱ ብቻውን አያድንም፣ ማዳኑንም አያመጣም። የወንበዴ ዋሻ ማንነታችንን እናጽዳ። ከዚህ ዓለም ሽቃጭና ልዋጭ ማስመሰያ ማንነት እንውጣ! በጎ ፍሬ እንዲያፈራ ለተላከው የወይኑ ባለቤት ወራሽ እንገዛ! ያኔ «ሆሳዕና በአርያም» ስንል ማዳኑ ፈጥኖ ይሆንልናል። ከኢየሱስ በቀር ማዳን የሚቻለውና ተስፋ የሚሆነን ማነው? ከሥጋ ለባሽ ማንም የለም። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በሰው የሚታመን፣ በሥጋ ለባሽ የሚመካ፣ ልቡንም ከእግዚአብሔር የሚያርቅ የተረገመ ነው። አዎ ሆሳዕና በአርያም! በዚህም አንተ ብቻ መታመኛ ነህ፣ በወዲያኛውም አንተ ብቻ! ሆሳዕና በአርያም። ሃሌ ሉያ!!!!!!!!

Friday, April 8, 2022

ቻት ላይ ነን አትረብሹን!

ዮሐንስ 10 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹¹ መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል። ¹² እረኛ ያልሆነው በጎቹም የእርሱ ያልሆኑ ሞያተኛ ግን ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም ይነጥቃቸዋል በጎቹንም ይበትናቸዋል። ¹³ ሞያተኛ ስለ ሆነ ለበጎቹም ስለማይገደው ሞያተኛው ይሸሻል።

Wednesday, March 9, 2022

የቤተ ክርስቲያኒቱ ጠላቶች በጉያዋ ናቸው!

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በሦስት መንገድ ችግር ውስጥ ናቸው። 1ኛ/ ወደው ባልተወለዱበት ዘር ትግሬ በመሆናቸው በኦሮሙማው ኃይል የሚታዩት እንደጠላት ነው። 2ኛ/ የራሳቸው የአመራርና የሥልጣን አጠቃቀም ድክመት የተነሳ የመፈራትና የመከበር አቅማቸው አናሳ መሆኑ ሌላኛው ችግር ነው። 3ኛ/ ሊቃነ ጳጳሳቱ በራሳቸው የግል ኑሮ ምቾትና ምንግዴለሽነት የተነሳ ቤተ ክርስቲያኒቱን ስለረሷት ከፓትርያርኩ ጋር መቆም አልቻሉም። ወደፊትም ቢሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አሁን ባለችበት መንገድ ከተጓዘች በውስጥና በውጪ ጠላቶቿ እየተገዘገዘች የመውደቋ ነገር የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር መፍረሷ አይቀርም። የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ሦስት ምክር ያቀርባል። 1/የቀድሞው ፓትርያርክ ከዚህ ዓለም ስላረፉ አሁን ያሉት ፓትርያርክ ከእድሜ: ከህመምና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች የተነሳ በቂ ውሳኔ እየተሰጠ ባለመሆኑ ችግሮቹ ተደራራቢ እየሆኑ በመገኘታቸው ለቤተክርስቲያኒቱ ፈጣን አመራር መስጠት የሚችል ሰው በራሳቸው በፓትርያርኩ አቅራቢነት እንደራሴ ቢሾም: 2/ አጠቃላይ የሰበካ ጉባኤ ስብሰባ በዓመት ሁለት ጊዜ መሆኑ ከድግስና ከተጋነነ ሪፖርት ውጪ ችግር ፈቺ ስላልሆነ የየአህጉረ ስብከቶቹን ችግር የሚያጠናና ለእንደራሴው ቢሮ የሚያቀርብ ቡድን ተሰይሞ በየችግሮቹ ዘርፍ ፈጣን ውሳኔ ቢሰጥባቸው: 3/ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የሚቆረቆሩ በሙያ: በልምድና በችሎታ ከልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የአማካሪ ቦርድ ቢቋቋም የተሻለ ይሆናል። ይህ አሰራር በግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያና ተግባራዊ ሆኖ ብዙ ችግር መቃለል ተችሏል። ከዚህ ውጪ አሁን ባሉት ጳጳሳት የሚፈታ የቤተ ክርስቲያን ችግር የለን። አይኖርምም። ራሳቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ችግሮች ናቸው። ፈሪሃ እግዚአብሔር የነበራቸውና በጥብዓት ይታገሉ የነበሩት ሁሉ በዐረፍተ ዘመን ሁሉን ትተው ሄደዋል። አሁን ካሉት ጳጳስ ተብዬ ወመኔዎች አንዱ የሆነው ቅዱስ ፓትርያርኩ ለመናገር ያሰቡትን ሃሳብ እንዳያስተላልፉ የዱርዬ ስራውን እንዴት ይሰራ እንደነበር ይህ ቪዲዮ ያሳያልና ተመልክታችሁ ፍረዱ! በፕሮቶኮል ደረጃ ከፓትርያርኩ ፊት መነጋገሪያ ማይክ አይነሳም። ማፊያው ጀነራል ሦስት መነጋገሪያ ፓትርያርኩ እንዳይነጋገሩ ሲያሸሽና ለአዳነች አቤቤ ሲሰጥ ተመልከቱ።

Friday, February 4, 2022

የኦሮሙማ ህልመኞችና የኦርቶዶክስ ጳጳሳት!

የኦሮሙማ ሀገር ምስረታ ህልመኞች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን የሚቆጥሯት የአማራና የትግሬ ንብረት እንደሆነች አድርገው ነው። የሁለቱ ብሄሮች ደናቁርት የፖለቲካ ኤሊቶች ደግሞ ለስልጣን ካላቸው ጉጉት አንዱ ለአንዱ ጠላት መሆን ከጀመረና በሴራና ተንኮል መተላለቅ ከጀመረ ግማሽ ክፍለ ዘመን ተቆጥሯል። ሰርቶ ከመኖር በስተቀር ስለፖለቲካው ምንም እውቀት የሌለው ደሃው ህዝብ በማያውቀው የፖለቲካ እሳት እየተጠበሰ ህይወቱን እየተነጠቀ: ሀብትና ንብረቱ ወድሞ ባዶ እጁን ቀርቷል። ይሄ እድል እጁ ላይ የወደቀው የኦሮሙማ መንግስት ከአማራና ከትግራይ እልቂትና ውድመት በኋላ ስልጣኑን አደላድሎ የተረፈችው ኦርቶዶክስን ሰባብሮ ለማጥፋት በቅጥረኞቹ በአባ ገዳ በላይ መኮንንና ወታደራዊ ሹመት ብቻ በቀረው ጀነራል አባ ዮሴፍ (እንኳን ጳጳስ የተመሰከረለት ወንበዴ ለመባል ይበዛበታል) በኩል ወጥሮ ይዟታል። ፊደል ተራራው አባ ወ/ኢየሱስ እና ቄሮ ኃይሉ ጉተታ የኦሮሙማው መንግስት ጉዳይ አስፈፃሚዎቹ ናቸው። ቤተክርስቲያኒቱ በአፄው ዘመን የአፄዎቹ አጋፋሪ ነበረች። በዘመነ ኢህአዴግ የህወሀት አለቅላቂ እንደነበረች ይታወቃል።  በደርግ ዘመን ፓትርያርኩ አባ መርቆርዮስ የሸንጎ አባል ነበሩ።
ዛሬ ደግሞ የኦሮሙማው መንግስት የብልፅግና ወንጌል አራማጅ ስለሆነ ቤተክርስቲያኒቱን ለቀብር እየገነዛት ነው። 
ይህ ሁሉ ሲሆን ጳጳሳቱ በየወሩ ረብጣ ደመወዝ እየበሉ በወንበራቸው ላይ ተቀምጠዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ጉዲትን ቢሮአቸው ድረስ ብትጠራቸውም ሆቴል እንገናኝ ብላ አላግጣባቸዋለች። ሀገሪቱ አሁን ለደረሰችበትና ኦርቶዶክስ እየፈራረሰች ለምትገኝበት ሁኔታ ግንባር ቀደም ተጠያቂዎቹ በመንፈስ ቅዱስ እየመራናት ነው ብለው በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚሳለቁ እነዚህ ጳጳሳት ናቸው። መቼም ቢሆን በነዚህ ምንደኞች ቤተ ክርስቲያን ፈውስ አታገኝም። ምንደኛ ስለደመወዙ እንጂ ስለበጎቹ አይገደውምና በነዚህ ጳጳሳት ኦርቶዶክስ ከሞት አትድንም። የበጎች እውነተኛ እረኛና ስለበጎቹ ራሱን አሳልፎ የሰጠ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው!


 

Sunday, August 22, 2021

በድንግል ማርያም የትንሣኤና የእርገት ታሪክ ላይ ችግር አለ!

ቅዱሳንን ስለማክበር ምንም ጥያቄ የለንም። ለቅዱሳንም መታሰቢያ ማድረግ የነገሮች ሁሉ ባለቤት የሆነው ኢየሱስን እስካልተካ ድረስ ችግር የለውም። ለክርስትና አስተምህሮና ለተጋድሎ ጽናት አርአያ ይሆኑናልና ታሪካቸውን እንናገራለን። ነገር ግን በሃይማኖታዊ አስተምህሮ ወቅት በወንጌል ላይ ብዙ ጥያቄዎችን የሚያስነሱትና የስህተት ችካሎች አልነቀል ያሉት በመታሰቢያና በአክብሮት ምክንያት ስር ተወሽቀው ኢየሱስን እየጋረዱ ስላስቸገሩ ነው። ከነዚህ የስህተት አስተምህሮዎች መካከል አንዱ የሆነው በማርያም እረፍት፤ ቀብር፤ ትንሣኤና እርገት ላይ ያሉ አስተምህሮዎች ሰዎች ዓይናቸውን ከኢየሱስ ላይ አንስተው ወደሌላ የመዳን መንገድ እንዲመለከቱ ያደረገው ተጠቃሽ ነው።

ስለማርያም እረፍት፤ትንሣዔና እርገት አብያተ ክርስቲያናት አንድ ዓይነት የእምነት አቋም የላቸውም። እንዲያውም ስለማርያም ሞትና የእርገት ዕለት በግልጽ የሚታወቅ ማስረጃ እንደሌለ በ5ኛው ክ/ዘመን የኖረው የሳላሚሱ ኤጴፋንዮስ ተናግሯል። ዕረፍቷና እርገቷ በኢየሩሳሌም እንደሆነ  የሚናገሩ ቢኖሩም  ይህንን አባባል የማይቀበሉ አብያተ ክርስቲያናትና የቴኦሎጂ ምሁራን ሞልተዋል። በኢየሩሳሌም አርፋለች የሚለውን አባባል የማይቀበሉበትን ማስረጃ ሲያቀርቡም ዮሐንስ በወንጌሉ ላይ እንደተናገረው «እናትህ እነኋት አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት» ዮሐ19፤27 ባለው መሠረት ማርያም እስከ ሕይወቷ ፍጻሜ ድረስ ከዮሐንስ ጋር ስለኖረችና ወንጌላዊው ዮሐንስም ከጌታ ሞት በኋላ በኢየሩሳሌም  ጥቂት ዓመታትን ከቆየ በኋላ በ37 ዓ/ም ገደማ ወደ ቤዛንታይን ከተማ ኤፌሶን ሄዶ ወገኖቹን ወንጌል እያስተማረ መቆየቱንና  ማርያም በሞት እስከተለየችው ድረስ  ከ48-52 ዓ/ም እዚያው እንደነበር ብዙ ተጽፏል።
በኋላም በቅርብ ርቀት ባለችው ደሴተ ፍጥሞም  በግዞት መኖሩንና በመጽሐፍ ቅዱሳችን የተጻፈውን ራእይ የተመለከተውም እዚያ እንደሆነ ይታወቃል ። አንዳንዶች ከዶሚኒሽን አገዛዝ ቀደም ብሎ የራእይ መጽሐፉን  ከ55-65 ዓም ገደማ እንደጻፈም በታሪክ አስቀምጠዋል።

ዋናው ነገር  ማርያም በኤፌሶን ከዮሐንስ ጋር ኖራለች ወይስ አልኖረችም? ነው ጥያቄው። በኢየሩሳሌም አርፋለች የሚሉ ሰዎች አንድም ጊዜ ከዮሐንስ ጋር በኤፌሶን ኖራለች ሲሉ አይደመጥም። ለምን?  ዮሐንስ ማርያምን እንደእናት ሊይዛት አደራ ተሰጥቶታል የሚባል ከሆነ ከዮሐንስ ጋር ኤፌሶን ስለመቀመጧ የማይነገረው ለምንድነው?  ዮሐንስ እስከ 96 ዓመቱ ድረስ ከኤፌሶንና ከደሴተ ፍጥሞ ውጪ ስለመኖሩ የተነገረ ታሪክ የለም። ማርያም ከዮሐንስ ጋር በኤፌሶን አልኖረችም ብሎ በመከራከርና በኢየሩሳሌም ኖራ፤ እዚያው ማረፏን በግልጽ በመናገር መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። «እነኋት እናትህ» ባለው መሰረት አብረው ኤፌሶን ኖረው እዚያው ማረፏን በሚያምኑና ኢየሩሳሌም ኖራ እዚያው አርፋለች በሚሉት ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት የማይታረቅ ነው።
ሮበርት ክሬው የተባለ የነገረ መለኮትና የታሪክ ጸሐፊ ዮሐንስ ወንጌላዊ ዘመኑን ሁሉ በኖረበት ከኤፌሶን ከተማ 8 ኪሎ ሜትር ወጣ ብላ ባለች ኰረብታ ላይ በተሰራ ቤት ውስጥ እንደኖረና ማርያምም እዚያ ማረፏን ጽፏል።  ይህንን በኤፌሶን ያለውን የማርያምን መቃብር የዓለም ክርስቲያኖች እንዲሆም ሙስሊሞች ሳይቀሩ ይጎበኙታል፤ ይሳለሙታል።  በቱርክ ግዛት ያለው ይህ ስፍራ በቱርካውያን ሙስሊሞች ዘንድ «ሜሪዬማና» ተብሎ ይጠራል።
ቅድስት ማርያም ከዚህ ዓለም የተለየችው መቼ ነው? ለሚለው ጥያቄ ጥንታዊያን አብያተ ክርስቲያናት የሚባሉት የምሥራቁና የምዕራቡ ጎራዎች የተለያየ አመለካከት አላቸው።
በተወለደች በ58 ዓመቷ ዐርፋለች የሚሉ አሉ። በ72 እና 63 እድሜዋም አርፋለች የሚሉ መረጃዎች አሉ። እንደ ግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ግን የሚታመነው በ64 ዓመት እድሜዋ ማረፏ ነው።  ኖረችበት ተብሎ ከሚገመተውና አርፋለች ከሚባለው ቦታ ያለው ልዩነት እንዳለሆኖ በጥር ወር ከዚህ ዓለም ተለይታ በ40ኛው ቀን ማረጓን የሚናገሩ አሉ። ይህም ሞትና ትንሣኤዋን ከልጇ ጋር ለማመሳሰል የተደረገ ጥረት ነው። በነሐሴ ወር አርፋ ከተቀበረች በኋላ ትንሣዔዋን ሳያዩ መቃብሯ ባዶ ሆኖ ስላገኙት ሐዋርያት ሱባዔ ይዘው በሦስተኛው ቀን ተገለጸችላቸው የሚሉም አሉ። እንደኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ደግሞ በጥር ሞታ፤ በነሐሴ ተቀበረች የሚል ትምህርት አለ። በጥር ወር አርፋ፤ በነሐሴ ተቀብራለች የሚሉ ሰዎች ሥጋዋ በገነት ዛፍ ስር ለስምንት ወራት መቀመጡንና በሱባዔ ጸሎት በተደረገው ልመና የተነሳ ሥጋዋ ከሰማይ ወርዶ ለመቀበር መቻሏን አስፋፍተው ጽፈዋል።
በጥር ወር እንዳረፈች ያኔውኑ ለምን አልተቀበረችም?፤ ተብለው ሲጠየቁ ወደ ቀብር ሥጋዋን ተሸክመው ይሄዱ የነበሩት ሐዋርያት ላይ ታውፋንያ የሚባል ወንበዴ ጎራዴ ሲመዝባቸው ዮሐንስ ብቻ ሲቀር ሐዋርያቱ ጥለዋት በመሸሻቸውና ዮሐንስ ብቻውን ቀርቶ ወደ  መቃብር ሳትገባ ወደ ገነት ዛፍ ስር በመወሰዷ እንደሆነ ይነገራል።  ዮሐንስም ወደቤት በተመለሰ ጊዜ ሸሽተው የነበሩት ሐዋርያት ሥጋዋስ የታለ? ብለው ቢጠይቁት በገነት ዛፍ ስር መቀመጧን ስለነገራቸው ዮሐንስን ገነት ዛፍ ስር ሬሳዋ መቀመጡን አይቶ ለምን እኛስ ይቀርብናል በማለት ነሐሴ 1/ ቀን የጾም የጸሎት ሱባዔ ጀምረው በ15ኛው ቀን ትኩስ ሬሳ ከገነት ዛፍ ስር እንደመጣላቸውና እንደቀበሯት ይናገራሉ።
እዚህ ላይ ይሄንን ታሪክ የሚያፈርሰውና ተረት እንደሆነ የሚያሳየንን ነገር እናንሳ!
ገነት ውስጥ የሰው ሬሳ የሚቀመጥበት ዛፍ ስለመኖሩ ማስረጃችን ምንድነው? ሬሳውን ተሸክመው ገነት የገቡት ኃይሎች ታውፋንያ የተባለውን ሽፍታ ማስወገድ ለምን አልቻሉም? እጁን ቆረጡት የተባለው ተረት ለምን አንገቱን አልሆነም? ከሐዋርያቱ ተለይቶ ብቻውን የቀረው ዮሐንስ ከሽፍታው ሰይፍ እንዴት ተረፈ?  ይሄ ሁሉ ውጣ ውረድ ሲከናወን ሐዋርያቱ: መላእክቱ: ኢየሱስም አብረዋት ከነበሩ ከማርያም ሥጋ መንከራተት ጋር ምን ትርፍ አላቸው? 
ታሪኩን በሚያማልልና ልብን በሚቦረቡር ተረት መቀባባት ያስፈለገው ሰዎች ከወንጌል እውነት እንዲወጡና ልብን በተረታ ተረት በመሙላት በከንቱ ሃሳብ ውስጥ አስጥሞ ለማስቀረት ነው።
ሌላው ጥያቄ የሚያስነሳው ነገር  በጥር ወር አርፋ  ከቀብር በፊት ወደገነት ዛፍ ስር ስለመወሰዷና  ዮሐንስ ወደ ቤት ገብቶ ለሐዋርያት ከነገራቸው በኋላ እሱ ያየውን እኛም ማየት አለብን ያሉትና የጾም: የጸሎት ሱባኤ የገቡት ነሐሴ 1 ቀን ነው ይባላል። በጥር ወር  ገነት ገባ ለተባለ ሬሳ ምላሽ ለማግኘት ሐዋርያቱ ለምን እስከነሐሴ መቆየት አስፈለጋቸው? ሥጋዋስ 8 ወር ሙሉ ለምን ሳይቀበር ቆየ?  ሐዋርያቱ ሱባዔ ባያደርጉና እንዲቀብሯት ሬሳዋ ባይሰጣቸው ኖሮ የማርያም ሥጋ ከገነት ዛፍ ስር አይንቀሳቀስም ነበር ማለት ነው?
ለማርያም ሥጋ መቀበር ምክንያት የሆነው የሐዋርያቱ ሱባኤ መያዝ እንጂ ከቀብር ተለያይቶ የሚቀር ሆኖ ነበር ማለት ነው።
እንደሰዎቹ አባባል በጥር ወር አርፋ ሳይቀበር የቀረውን የማርያምን ሥጋ በስምንተኛው ወር ከገነት ወጥቶ ከተሰጣቸውና ከቀበሯትም በኋላ ቢሆን ወደሰማይ ስታርግ ሐዋርያቱ ለማየት አልቻሉም። የተረቱ ባለቤቶች እርገቷን ያየው ቶማስ ብቻ ነው ካሉን በኋላ ለተረቱ የታሪክ ፍሰት ውበት ሲሰጡት እንዲህ ነበር ይሉናል። ሐዋርያቱ ማርያምን ቀብረዋት ወደቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ቶማስ በደመና ተጭኖ ከሀገረ ስብከቱ ከሕንድ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ በሦስተኛው ቀን ወደ ሰማይ ስታርግ የዳመናው ጎዳና ላይ ማርያም ስታርግ አገኛት። ቀድሞ የልጅሽን እርገት ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንቺን ሳላይ ልቀር ነው? ብሎ ቢያዝን ትንሣኤዬን ያላንተ ማንም አላየም ካለችው በኋላ የተገነዘችበትን ጨርቅ እና ሰበን ለምልክት ሰጥታው እንዳረገች በሰፊው ይተረታል።
ሰዎቹ ነገሩን ሁሉ ለማጣፈጥ የሚጠቀሙበት ተረት አስገራሚ ነው። የሰው ልጅ ከትንሣኤው በኋላ የዚህን ዓለም ጨርቅና ልብስ እንደተሸከመ ወደ ሰማይ ይገባል የሚል ክርስቲያናዊ አስተምህሮ አለ ወይ?
ወንጌል ከትንሣኤ በኋላ ክርስቶስን እንመስል ዘንድ እንለወጣለን ይላል እንጂ የመቃብሩን ልብስና ሰበን እየተሸከመ ሰው ወደሰማይ ያርጋል የሚል አስተምሮ የለውም።
« 2ኛ ቆሮ 3፤18
እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን»
ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን በመቃብሩ የተገነዘበትን ጨርቅ ትቶ መነሳቱን እንጂ  ያንኑ ለብሶ መነሳቱን አላነበብንም።
ዮሐ20፤6—8 
«ስምዖን ጴጥሮስም ተከትሎት መጣ ወደ መቃብሩም ገባ፤ የተልባ እግሩን ልብስ ተቀምጦ አየ፥ ደግሞም በራሱ የነበረውን ጨርቅ ለብቻው በአንድ ስፍራ ተጠምጥሞ እንደ ነበረ እንጂ ከተልባ እግሩ ልብስ ጋር ተቀምጦ እንዳልነበረ አየ»
የሁላችን አማኞች ትንሣዔ የክርስቶስን ትንሣዔ መምሰል ካለበት በቀብር ወቅት ከዚህ ዓለም ጉድጓድ የገባ ጨርቅ ወደ ሰማይ አብሮን የሚያርግበት ምንም መንገድ የለውም።
ተጠራጣሪ እንደሆነ ሁል ጊዜ የሚነገርበት ቶማስ በማርያም እርገት እሱ ብቻ የተለየ ተጠቃሚ እንደሆነ አድርጎ ለማቅረብ ሲባል የማስረጃ ጋጋታ ሲፈለግ የማርያም የግንዘት ጨርቅ ተገኘና ወደሰማይ ከማረጉ በፊት ቶማስ ተቀበለ የሚል ተረት  አቀረቡልን። ሌላው አስገራሚው ነገር በደመና ተጭኖ የመሄድ ተረት ነው።  በመንፈስ ተነጠቀ የሚል መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት በደመና ተጫነ ከሚለው ጋር የትርጉም አንድነት የለውም። (የሐዋ 8:39)
ቶማስ በደመና ተጭኖ ሲጓዝ የሚለውን አባባል እንደፊልጶስ መነጠቅ አድርገን ብንቆጥረው እንኳን የቶማስ ሰብአዊ ማንነትና የማርያም ሰማያዊ የእርገት ማንነት የተለያየና ፈጽሞ የማይገናኝን ነገር ነው።  የቶማስን የዳመና ላይ ውይይትን ከረቂቅ  ክርስቶሳዊ አዲስ ፍጥረት ጋር ለማገናኘት መሞከር የጥንቶቹን የሮማውያን የቬነስ ወጎች/fable story/ እንድናስታውስ ያደርገናል።

በሞት: ትንሣዔና በእርገት መካከል እንደዚህ ዓይነት ተረቶችን በሰውኛ ትረካ መጫወት እግዚአብሔር ስለሞትና ትንሣዔ በተናገረው ላይ መቀለድ ነው። ከሁሉ የሚገርመው ደግሞ ማርያምን በጥር ሞታለች ያሉ ሰዎች፤  በመጀመሪያው ሞት ዮሐንስ ብቻ እድለኛ ሆኖ በገነት ዛፍ ስር ለማየት በመቻሉ ይሄንን እድል እነርሱም ለማግኘት ሐዋርያቱ ሱባኤ ነሐሴ 1 ቀን ገቡ ያሉን ሰዎች ማብቂያ በሌለው ተረታቸው እንዲህ በማለት ሆዳችንን በተረት ይነፉናል።  ከቀበሯት በኋላ ቶማስ ብቻ ያየውን እርገቷን እኛም ማየት አለብን ብለው ሐዋርያቱ በድጋሚ በዓመቱ ነሐሴ 1 ቀን ሱባኤ ገቡ ይሉናል። ሐዋርያቱ ነሐሴ ወር ላይ ሙጭጭ ያሉበት የሱባኤ የፍቅር ጊዜ ለምን ይሆን? ደግሞስ እርገቷን ለሁለተኛ ጊዜ ለማረጋገጥ ለምን አንድ አመት መቆየት አስፈለጋቸው? 
ማርያም አንዴ ካረገች በኋላ በሱባኤ የሚደገም ሁለተኛ እርገት አለ ወይ?  እንደዚህ ዓይነት ተደጋጋሚ ሞትና እርገት እንዲደረግላቸው ሐዋርያቱ ይጠይቁ ነበር ብሎ ለመቀበል ይቸግራል። ከጌታ የተማሩት ትምሕርት በእንደዚህ ዓይነት ጥያቄ እንዲዋከቡ የሚያደርግ አልነበረም። ማርያምን በመቅበር: በማንሳትና በማሳረግ ጣጣ ውስጥ ሐዋርያቱ ለምን እንዲህ ተጨነቁ? የተረት አባቶቹ ለዚህ ጥያቄ መልስ ባይኖራቸው ሐዋርያቱ ወንጌልን ለዓለም ያዳርሱ ዘንድ የተሰጣቸውን ሰማያዊ ተልእኮ ትተው ዋሻ ተወሽቀው የሆነ ሥጋ ከሰማይ እስኪወርድላቸው ጊዜያቸው ፈጁ የሚለውን ተረት  ሰይጣን ለሚያዳምጡት ከሚረጨው  በስተቀር የክርስቶ አማኝ የሆነ ሰው እውነት ነው ብሎ በጭራሽ ሊቀበል አይችልም።
የሚያሳዝነው ነገር ሐዋርያቱ ሱባኤ ከገቡ በኋላ የማርያም ሥጋ ከሰማይ እንደገና ወረደ የሚሉን አሳፋሪ ታሪክ ነው። እንዲያውም ኢየሱስ ራሱ ማርያምን ሥጋ መንበር (የቁርባን መቀመጫ) አድርጎ ጴጥሮስን ንፍቅ ቄስ፤ እስጢፋኖስን ገባሬ ዲያቆን ሆነው ቀደሱና ቆረቡ ይሉናል።  የማርያም ሥጋ እንዴት መንበር መሆን ቻለ? ምን የሚባለውን ቅዳሴ ቀደሱ? ኢየሱስ ሰራዔ ካህን ሆኖ ከቀደሰ የማንን ሥጋ ቆረበ? የራሱን?  ለየትኛው ድነት ይሆነው ዘንድ ሊቆርብ ይችላል? 
አልቆረበም የሚባል ከሆነም ሰራዔ ካህናት በዚህ ምድር መቅደስ ውስጥ ከመቀደስ ባሻገር መቁረብ አይጠበቅባቸውም በማለት አብነታዊ የክህነት አስተምህሮን አያይዞ ማቅረብ  የተገባ ይሆናል።
ኢየሱስ የቀደሰው ቅዳሴ ከ14ቱ ቅዳሴያት መካከል የትኛውን ይሆን? ያኔ ቅዳሴያት ተደርሰው ነበር? ወይስ የመጀመሪያው ደራሲ ኢየሱስ ነው?
  እንደተለመደው አባባል ቅዳሴ እግዚእ ነው የተቀደሰው የሚሉ ቢኖሩም ክርስቶስ ራሱን በሁለተኛ መደብ አስቀምጦ « ነአኩተከ አምላክ ቅዱስ፤ ፈጻሜ ነፍስነ፤ ወሀቤ ሕይወትነ ዘኢይማስን»  (ትርጉም) "የማይጠፋ ሕይወት የሰጠኸን: የነፍሳችን ፈጻሚ: ቅዱስ አምላክ እናመሰግንሃለን" ብሎ እንደእሩቅ ብእሲ ( እንደምድራዊ ሰው ሲማፀን አይገኝም። የማይጠፋ ሕይወት ራሱ ሰጪ ሆኖ ሳለ የዘላለም ሕይወት ይሰጠው ዘንድ ኢየሱስ ወደሰማይ አይማፀንም።
“እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው።”ዮሐ 6፥47 ያለን ጌታ ሕይወት ከሱ ቁጥጥር ውጪ ያለ የሚያስመስለው ቅዳሴ እግዚእ የሰዎች ድርሰት እንጂ የኢየሱስ አይደለም።
እንደዚህ ዓይነቱ አደገኛ ክህደት፤ ሰዎች ለማርያም ባላቸው ፍቅር ውስጥ ተደብቆ ለዘመናት ሕይወትን ከመዳን መንገድ ሲያጠፋ ቆይቷል።
ደግሞም በምሴተ ሐሙስ በጉ የመስዋእቱን ሥርዓት ለሕይወታችን ድኅነት ከሰጠ በኋላ ወደምድር መጥቶ ሁለተኛ ማእድ የሚያዘጋጅበት ምንም መጽሐፍ ቅዳሳዊ አስረጂ የለም። እውነታውን ስናነብ እንዲህ የሚል ቃል ተቀምጦልናል።«ሰዓቱም በደረሰ ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ጋር በማዕድ ተቀመጠ። እርሱም፦ ከመከራዬ በፊት ከእናንተ ጋር ይህን ፋሲካ ልበላ እጅግ እመኝ ነበር፤ እላችኋለሁና፥ በእግዚአብሔር መንግሥት እስኪፈጸም ድረስ፥ ወደ ፊት ከዚህ አልበላም አላቸው። ጽዋንም ተቀበለ አመስግኖም። ይህን እንካችሁ በመካከላችሁም ተካፈሉት» ሉቃ 22፤14-17
"የእግዚብሔር መንግስት እስኪፈጸም ድረስ ከዚህ ማእድ ድጋሜ አልበላም" ያለውን ቃል ያጥፍ ዘንድ ኢየሱስን ዋሾ ማድረግ አደገኛ ክህደት ነው።
በጉ መስዋዕቱን ሕይወት ይሆናቸው ዘንድ ለሰዎች ከሰጠ በኋላ፤ በፍርድ ቀን  የደሙን ምልክት ለተቀበሉት ሁሉ ዋጋቸውን ይሰጣቸዋል እንጂ እሱ የመስዋእቱ ተካፋይ ስላልሆነ፤ ክርስቶስ በቀዳሽነት  ቆርቦ፤ ማቁረብ የሚባል ታሪክ ከወንጌል ቃል የተገኘ ሳይሆን ክፉ ጠላት በጭለማ የዘራው ዘር ነው።

ወደዋናው ሃሳባችን ስንመለስ ለመሆኑ በማርያም ላይ ስንት ቀብር፤ ስንት ትንሣዔና ስንት እርገት ተደረገ? ብለን ብንጠይቅ እንደሚነገረው  ከሆነ ፤

1/ዮሐንስ ያየውና አፈር ያልነካው እርገት በገነት ዛፍ ስር

2/ አፈር የነካው የሐዋርያቱ ቀብር በነሐሴ 14 ቀን /ከስምንት ወር በኋላ/

3/ ቶማስ ያየው የትንሳዔ እርገት፤ ከቀብር በኋላ በሦስተኛው ቀን ነሐሴ 16

4/ ከአንድ ዓመት በኋላ ሐዋርያት ያዩት የነሐሴ 16 ትንሣዔና እርገት ናቸው።
እንግዲህ በማርያም ሞትና እርገት መካከል አራት ትእይንት መከሰቱን ዛሬም ድረስ ከሚሰጡት የቃል አስተምህሮዎችና የተዘጋጁ ጽሁፎች ውስጥ በግልጽ እናገኛለን። ማርያምን መውደድ አንድ ነገር ነው። ማርያምን ግን እየቀበሩና እያነሱ በቀብርና ትንሣኤ ማሰቃየት ደግሞ ሌላ አሳዛኝ ክስተት ይሆናል። እንዲያውም  ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት መሆን ከቻልኩ ሰባት ጊዜም ቢሆን እሞታለሁ ብላ ለልጇ ተናግራለች የሚሉት ተረትም በተዛማጅ ትምሕርትነት ይሰጣል። የእሷ መሞት የዓለሙ ሁሉ መድኃኒት መሆን ከቻለ የክርስቶስ ከእሷ መወለድ አስፈላጊ አይደለም የሚል ሃሳብን የሚያንጸባርቀው ይህ አባባል ከአሳሳች ትረካዎች ውስጥ የሚደመር ከመሆን አያልፍም።
እኛ  ማርያምን ብንወዳትና ብጽእት ብንላት «እናትህንና አባትህን አክብር»  ያለውን  የአምላክ ቃል መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ለእርሷ  የተነገረ ቃል ስላለም ጭምር ነው። ከዓለመ አንስት መካከል በድንግልና መውለድ የሷ የተለየ ስጦታ ነው። በዚህም መመረጥ መቻሏን እናከብረዋለን። ነገር ግን የዘላለማዊ አምላክ የክርስቶስ ፤ እናቱ ስለሆነች በማዳላት ወይም አምላካዊ ባህርይውን በሰውኛ ጠባይ በመለወጥ ከፍርድ ሚዛኑ በማጉደል  የእሷን ሞትና ትንሣዔ የተለየ ያደርጋል ብሎ ማሰብ ስህተት ነው። የእሷ ሞትም የመድኃኒትነትን ውክልና ለሰው ልጆች የያዘ እንደሆነ ማሰብ ክህደት ነው። ብቸኛው መድኃኒት አንዱ ኢየሱስ ብቻ ነው። ማርያምም ይህንን አሳምራ ስለምታውቅ
«ነፍሴ በአምላኬና በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች» ብላ ተነግራለች። ምክንያቱም ኢየሱስ ከእርሷ የተወለደ ቢሆንም ዓለሙን በማዳን ማንነቱ ውስጥ ለእርሷም አምላኳና መድኃኒቷም ስለሆነ ደስ እንደሚላት መስክራለች። የትንሣዔ በኩር የሆነው ሁላችንም በሞቱ እንድንመስለው እንጂ የተለየ አድሎአዊ ጥቅምን/ favour/ ለተለዩ ሰዎች በመስጠት አይደለም።ወንጌል የሚናገረው ይህንን ነውና። የክርስቶስ ሕይወት ተካፋዮች የምንሆነው በሞቱና በትንሣኤው እርሱን ስንመስል ብቻ ነው።

ሮሜ 6፥5 «ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን»

 ስለዚህ ደጋግሞ መሞት፤ መነሳትና ደጋግሞ ማረግ አለ ከተባለ ያ ነገር ከክርስቶስ ትንሣዔ ጋር ያልተባበረ ስለሆነ አንቀበለውም። እንዲያውን ይህ ኑፋቄና ወንጌልን መካድ ነው።  ሐዋርያው ጳውሎስም የተናገረው ስለክርስቶስ ወንጌል በሞቱም ክርስቶስን እንዲመስል ነበር።

ፊልጵ 3፥10-11  «እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ»
የማርያም ሞትና ትንሣዔ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ካዘጋጀው የትንሣዔው በኩር አንድያ ልጁ የተለየ አያደርገውም። ከመግቢያችን ላይ ጀምሮ ለመግለጽ እንደሞከርነው የኤፌሶኑና የኢየሩሳሌሙ ታሪክ እንዳለ ሆኖ አብያተክርስቲያናት ሁሉ የተለያየ የሞትና የትንሣዔ አስተምህሮ ከመያዛቸው አንጻር  ኤጲፋንዮስ እንዳለው ትክክለኛው የታሪክ ቀን አይታወቅም። ቢታወቅም ስለድነታችን የሚጨምረውም: የሚቀንሰውም ነገር የለውም። አሁን የሚደረገውም ፍልሰታ ለማርያም በዓል ከልምድና ትውፊት ከተረትና ክህደት ጋር በማር የተለወሰ መርዝ ስለሆነ መጠንቀቅ አለብን።
ማርያምን እንወዳለን እያሉ በጥር ሞተች፤ ገነት ዛፍ ስር ስምንት ወር በሬሳ ቆየች፤ በስንት ሱባዔ ስጋዋ መጥቶ ነሐሴ ተቀበረች፤ እስከነ ምድራዊ ልብሷ አረገች፤ በዳመናው ጎዳና  ላይ ከቶማስ ጋር ጨርቅ ተለዋወጠች፤ እድል ላመለጣቸው ሐዋርያት ዳግመኛ በስንት ሱባዔ በሌላ ትንሣኤና እርገት ተረጋገጠች፤ መንበር ሆና ተነጠፈች ወዘተ በማለት እየገደሉና እያነሱ በማርያም ላይ መጫወት ተገቢ ነው ብለን አናምንም። የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤንም ማፋለስና መካድ ይሆናል። የማርያም ትንሣኤና እርገት ለክርስትና ከታሪክ ባለፈ ለሕይወት የሚሰጠው የሕይወት ዋስትና የለውም። ሕይወት ኢየሱስ ብቻ ነው።  ሕይወት እንዲሆንላችሁ ከፈለጋችሁ ከተረት ዓለም ውጡ።
“ነገር ግን ሕይወት እንዲሆንላችሁ ወደ እኔ ልትመጡ አትወዱም።” ዮሐ 5፥40  የተባለው እንዳይፈፀምባችሁ በሕይወት መኖር አይሻላችሁምን?
ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር የሌላ የማንም ሞትና ትንሣኤ  ለሰው ልጆች መዳን የቀረበ መስዋእት የለም።
የማርያምም ሞትና ትንሣኤ ማንንም ሊያድን አይችልም።
የተነገረን በማርያም ትንሣኤ እንድናምን ሳይሆን “በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።”
  ዮሐ 3፥36 ተብሎ እንደተነገረው የቤዛነት ምትክ በሌለው በኢየሱስ ብቸኛ አዳኝነት ልናምን ይገባል!
መጽሐፍ እንዳለው "“መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።”ሐዋ 4፥12
ከላይ የተጻፈው ጽሑፍ ዋና መልእክት ማርያንም ለመቃወም ወይም ንጽሕት: ቅድስት ማርያምን ከመጥላት የተነሳ አይደለም። ማርያም ራሷ የማትቀበለው ከእውነትና ከወንጌል ቃል ተቃራኒ አስተምህሮን በእግዚአብሔር ቃል ለማፈረስና ሰዎች ሁሉ ባልተሸቃቀጠው ወንጌል ብቻ እንዲኖሩ ለማስቻል ነው። በዚህም እውነት ለመገዛት እግዚአብሔር ይርዳን! አሜን!



















Friday, May 14, 2021

ኦርቶዶክስን የማፍረስ ዘመቻ!

 


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስን ተዋሕዶን የማፍረስ ዘመቻ ዛሬ የተጀመረ አይደለም። አብዛኛዎቹ ዘመቻዎች ውጫዊ ነበሩ። የዮዲት ጉዲት ዘመቻ: ከደቡብ ወደሰሜን የተካሄደው የገዳዎች ወረራ: የግራኝ: የማህዲስት: የካቶሊክ ሚሲዮናውያን: የፋሺስት ጣሊያን ዘመቻዎች ሁሉ መሰረታቸው ኢትዮጵያን የመቆጣጠርና ግዛት የማስፋፋት ቢሆንም ቤተ መንግስቱንና ቤተ ክህነቱን ትቆጣጠር የነበረችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የማፍረስ ግብ የሁሉም ወራሪዎች ተመሳሳይ አላማ ነበር። የሕዝቡን እምነትና ለመንግስት አሜን ብሎ የመገዛት ስነልቦናውን ለማፍረስ መጀመሪያ ኦርቶዶክስን ማጥፋት የሁሉም ግብ ነበር። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከውጪ የመጣባትን ጥቃት ሙሉ በመሉ በመቋቋም ከመጥፋት ተርፋ ይሄን ሁሉ ዘመን መዝለቅ የቻለችው ውስጣዊ አንድነት ስለነበራት ብቻ ነው። ነገር ግን ከ1966 ዓ/ም በኋላ የኦርቶዶክስ ሲሶ መንግስትነት ተንኮታኩቶ ፈጣሪ የለሽ መንግስት በቦታው ሲተካ ከውጫዊ ጥቃት ይልቅ ውስጣዊ አንድነቷን የሚፈታተን አደጋ ተጋርጦባታል። ለሁለተኛው ፓትርያርክ በደርግ መገደል መነሻው ምክንያት የውስጠኛው አመራር  የሆነው የሲኖዶሱ መከፋፈል ነበር። ለአራተኛው ፓትርያርክ ሹመት የነመላኩ ተፈራ ደርጋዊ እጅ ቤተ ክህነቱ ውስጥ ዘልቆ መግባቱና ለአምስተኛው ፓትርያርክ ሹመትም ተረኛው የወያኔ እጅ እንደፈለገው ማቡካት መቻሉን ስለምናውቀው እውነቱን መካድ አይቻልም። 

ደርግ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሀብትና ንብረት ወርሶ ለ17 ዓመት: ህወሀት ለ27 ዓመት የቤተ ክርስቲያኒቱን የውስጥ አመራር ተቆጣጥረውት የቆዩት ለፖለቲካዊ አላማቸው የማታስቸግር ቤተ እምነት እንድትሆን ቀፍድዶ ለመያዝ እንደነበር ይታወቃል። 

ለኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የውስጥ አስተዳደር መበላሸትና ለጥቃት ተጋላጭ ያደረጋት ዋናው ምክንያት ቅዱስ የተባለው ሲኖዶስ በሚጠበቀው ደረጃ አስተዳደሩን በቅድስና መምራት አለመቻሉ እንደሆነ እርግጥ ነው። ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ ከ25ሚሊዮን በላይ አማኞቿ ትተዋት የኮበለሉት በቁጥርም: በዝናም ሲኖዶስ የተባለው ማኅበር በጨመረ ቁጥር ነው። ለምን? ብሎ መጠየቅ የግድ ይላል። ይሄ ሲኖዶስ የሚባለው ማኅበር ትክክለኛው የበጎች እረኛ ሳይሆን የበጎቹን መንጋ ለቀበሮ አሳልፎ የሚሰጥ ለደመወዝ የሚኖር ቅጥረኛ ስለሆነ ብቻ ነው። በነቀዘ የአስተዳደር መዋቅር: በጉቦና በዘረፋ የተሰማራ አመራር: ዘመኑን የሚዋጅ ሃይማኖታዊ አስተምህሮ አለመኖር:  ፍትህ በአፍጢሙ በመደፋቱና በሌሎች ውስጣዊ ገፊ ምክንያቶች የተነሳ ብዙዎች ቤተ ክርስቲያኒቱን ለቀው ሄደዋል።  ያሉትም በሚያዩት ነገር ተስፋ ቆርጠው ቤታቸው ተቀምጠዋል። በአንድ ወቅት አንድ የሙስሊም ስኮላር ያለውን አስታውሳለሁ። እስልምና የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች በሙሉ ሲቆጣጠር የነቢያችንን ዘመዶች የተቀበለችው ኢትዮጵያን መቆጣጠር ያቃተን በኦርቶዶክስ የተነሳ ነበር። እኛ ያቃተንን ጳጳሳቶቿ ራሳቸው እያዳከሙልን ስለሆነ ምስጋና ይገባቸዋል ሲል ተደምጧል።  ነገሩን ቆም ብለን ስንመረምር ቤተክርስቲያኒቷ ጳጳሳት በበዙ ልክ ማደግ ሲገባት ጳጳሳቱ በበዙ መጠን እያሽቆለቆለች መገኘቷ የስጋውያን መሪነት የመንገሱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። 

በአጠቃላይ ከ1966 ዓ/ ም በፊት የነበሩ ውጫዊ አደጋዎቿን በውስጣዊ አንድነቷ መቋቋም የቻለችው ቤተ ክርስቲያን ውስጣዊ አንድነቷን የሚያናጋ ውስጣዊ ችግሮችን እያመረተች በመገኘቷ በምእመናኖቿ ቁጥር የቁልቁለት ጉዞዋን ተያይዛዋለች። በመንፈሳዊ ወሥጋዊ ዘመናዊ አስተዳደር አለመኖርና የፋይናንስ ስርአቱ ብልሹነት የተነሳ ዘረፋ: ጉቦ: ዘረኝነትና ዐመፃ በመንሰራፋቱ ራሷን ከውጪ ጥቃት እንዳትከላከልና ውስጣዊ ተጋላጭነቷ ከፍ እንዲል አድርጓታል።

ይህ ሁሉ ዐመፃና ስርአተ አልበኝነት ነግሶ እያለ አንዳንዶች እግዚአብሔር ስለሚጠብቃት ኦርቶዶክስ አትፈርስም ሲሉ ይደመጣሉ። ይሄ ግን በስመ እግዚአብሔር የሚፈፀም ራስን የማታተል ግብዝነት ነው። በራእየ ዮሐንስ ላይ የተመለከቱት ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ዐመጽና በደልን እንዲተዉና ወደእግዚአብሔር የቀደመ መንገዳቸው እንዲመለሱ ቢነገራቸው መስማትና ንስሐ መግባት ባለመፈለጋቸው የተነሳ አብያተ ክርስቲያናቱ በሙሉ ፈራርሰው ዛሬ በሙዚየምነት የሚጎበኙ የእስላማዊ ቱርክ የገቢ ምንጭ ፍርስራሽ ሆነው ቀርተዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም መጨረሻ በዚህ መልኩ እንዳይደመደም የሚያስችል ሁኔታ እየታየ አይደለም። ሲኖዶስ የተባለው በስመ ቅድስና የተሰየመው የበላይ አካል በቅድስና እየመራት ከሆነ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ዐመጽ: ዘረፋ: ጎጠኝነት: የአመራር ክፍፍልና ልዩነት ለምን መለያዋ ሊሆን ቻለ? 

አሁን በቅርቡ በታየው የቤተ ክርስቲያኒቱ መግለጫ በተባለው ጉዳይ ላይ (አባ) ወ/ ኢየሱስ ወይም ህፃን የተባለው ጎረምሳ ቤተ ክርስቲያኒቱን ወክሎ ያደረገው ንግግር የሚያሳየው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሥርዓትና ሕግጋት እየፈረሰ መሆኑን ያመላክታል። ይህ ሰው በመኪና ስርቆት ወንጀል ተፈርዶበት 4 ዓመት ከርቸሌ የከረመ መሆኑ እየታወቀ በቤተ ክርስቲያኒቱ ዓመታዊ በዓላት በልደት: በጥምቀት: በዘመን መለወጫ: በከፍተኛ ስብሰባዎች እየተገኘ በውክልና መግለጫ የሚሰጠው በምን አግባብ ነው?



 አባ ሕጻን (በአማን ዘውእቱ ሕጻን) ከዘመናዊ ትምህርት ይሁን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ትምህርት ሩቅ ነው። ግን መግለጫ በመስጠት ቀዳሚ ነው። እውነት ነው: ሲኖዶሱ በዝምታ ድባብ ሲዋጥ አላዋቂዎች ቢሰለጥኑባት አይገርምም። "ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ" እንዲሉ!

የዓሳ ግማቱ ከጭንቅላቱ ነው እንደተባለው በመላው ሀገሪቱ እየታየው ባለው የቤተ ክርስቲያን መቃጠልና የምእመናን እልቂት ፊት ለፊት መናገር ሲገባቸው እንደቀንድ አውጣ አንገታቸውን ቀብረው የቆዩ ሁሉ ቅዱስ ፓትርያርኩ በትግራይ እየተከሰተ ያለውን እልቂት ማውገዛቸውን ተከትሎ ፓትርያርኩ ላይ አፋቸውን ሲከፍቱ ስናይ ቅጥረኞች ቤተክርስቲያኒቱን እንደወረሯት ማሳያ ነው። በልብስ ሰፊነት ባደለቡት ገንዘብ ያገኙትን ሹመት በመንፈሳዊ ብቃት ያገኙት ያህል እንድንቆጥርላቸው ይፈልጋሉ። የብርሃኑ ጁላ ታናሽ ወንድም 



ሆነው ፓትርያርኩ የተናገሩትን የግላቸው አቋም ነው ብለው የማን ቅጥረኛ እንደሆኑ ሲያሳብቁ እነርሱ በማን ፈቃድ? የማንን አቋም? እንዳንፀባረቁ ድንቁርናቸው ራሱ ያጋልጣቸዋል። ጊዜ ወለድ የሆኑ ጳጳሳት ባሉባት ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገርመው ውድቀቷ ቶሎ አለመፈፀሙ ብቻ ነው። 

የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መስራቹ አቶ በላይ መኮንን ባቋቋመው ቲቪ ላይ ከጀነራል ጳጳሳቱ ጋር ተሰይሞ እንደሕዝብ አማራን: እንደተቋም አሁን ያለው ሲኖዶስ ሲያዋርዱና ሲዘለፉ ተመልክተናል።  


ፓትርያርኩ የትግራይ ህዝብ እየተጨፈጨፈ ነው ብለው መናገራቸው ስህተት ተደርጎ የተቆጠረው የኦሮሚያ ኦርቶዶክስን ለማቋቋም እንደእጅ መንሻ ለመንግስት ለማቅረብ መሆኑ ያልገባው ካለ እሱ ጅል መሆን አለበት። ፓትርያርኩ የአስተዳደር ብቃት ችግር እንዳለባቸው ይታወቃል። ነገር ግን ለቤተክርስቲያን ባለመቆርቆር ወይም በዘረኝነት እሳቸውን ለመክሰስ ብቃት ያለው አንድም ጳጳስ እንደሌለ እርግጠኞች ነን።

የአቶ አሻግሬ መንግሥት ተለያይቶ የነበረውን ሲኖዶስ ያሰባሰበው በተለያየ ጎራ በፖለቲካ ውጊያ እንዳያስቸግሩትና ሰብሰብ ባለ ጠላት ላይ ኃይሉን በሙሉ ለማሳረፍ እንዲያስችለው እንጂ መንፈሳዊ መልእክት ከሰማይ ወርዶለት አይደለም። በአጠቃላይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የማፈራረስ እቅድ በመንገድ ላይ ይገኛል። ውስጣዊ አንድነቷ የለም። ሲኖዶሱ እንደእከ " እኔን ነው?" ከማለት  የእንቅልፍ አዚም መውጣት አልቻለም።

ምእመኑ የተመሪነት ፍላጎቱ ቢኖረውም መሪ እንደሌለው የበግ መንጋ በሃዘንና በስቃይ እየተቅበዘበዘ ነው። የጊዜ ጉዳይ እንጂ ኦሮሙማ ቤተ መንግሥቱንና ቤተ ክህነቱን ከመዋጥ ከመሰልቀጥ አይመለስም። መጨረሻውስ ምን ይሆን?

እድሜ ይስጠን ገና ብዙ እናያለን: እንሰማለን!

Saturday, February 22, 2020

ጉባዔ ከለባት እና የዘመኑ ሆድ አደር ሲኖዶስ!

ፓትርያርኩ እድል ይሁን የችሎታ ማነስ ቤተ ክርስቲያን በዘመናቸው እየፈረሰች ነው።
ጳጳሳቱስ ችግር ፈቺ ናቸው ወይስ ችግር ፈጣሪ? ሁሉም ቤተ ክርስቲያንን በማፈራረስ የየድርሻቸውን እየተወጡ ናቸው።
አቡነ ጃዋር: አቡነ ጃዊሮስ ቀውስ በላይንና ሌሎች ሃይማኖት የለሽ ኦነጋውያንን ማስቆም ያልቻለ ሲኖዶስ ጥጉን ይዞ ይስቃል።


Friday, December 20, 2019

የዛሬ 7 ዓመት ይህን ተናግረን ነበር!

አዲሱ ፓትርያርክ ብዙ ሥራ ይጠብቃቸዋል!


በዚህም ተባለ፤ በዚያ አቡነ ማትያስ ፮ኛው ፓትርያርክ ሆነው ተሹመዋል። ባለፈው ግድፈትና እውነት ላይ  እያነሳንና እየጣልን ጊዜ አናጠፋም። ይልቅስ ብዙዎች የታገሉለት የምርጫው ስኬት እንዳሰቡት ጥሩ የሥራ ጊዜ ይዞ ይመጣላቸው  እንደሆነ የምናይበት፤  ገሚሶቻችንም የምናያቸው የቤተ ክህነት ተግዳሮቶች የሚቀረፉበት፤ ሰናይ የአስተዳደርና መንፈሳዊ ዘመን ናፍቆታችንን ተስፋ በማድረግ እንደዚህ በፊቱ አስቀድመን አንዳንድ ነገሮችን ለማመልከት ወደድን።
የአዲሱ ፓትርያርክ አዲስ የሥራ ዘመን ቀላል እንደማይሆን ይገመታል። የተጠራቀሙ የቤተ ክህነቱ ችግሮችና ብዙ እንከኖች  ከፊታቸው ይጠብቋቸዋል። የችግሮቹ ዓይነቶች፤ ደረጃና ጥልቀት የተለያዩ እንደመሆናቸው መጠን የተለያየ ውሳኔና እርምጃንም የሚጠይቁ ናቸው። ለዚህ የተዘጋጀ የአእምሮ ዝግጁነት፤ የእውቀት በሊህነት፤ ድፍረትና ማስተዋል እንደሚጠይቁም አይጠረጠርም።  ያንን ዓይነት ሰው ከየት እናገኛለን ብለን አናሳብም። ምክንያቱም ምርጫው /ከተባለ/ ትልቅ አባት ሰጥቶናልና። ስለዚህ ወደችግሮቹ እንንደርደር።

1/ የቤተ ክህነቱ ላዕላይና ታህታይ መዋቅር ማሻሻል

የቤተ ክህነቱ ቀዳሚው ችግር ሥራና ሠራተኛ የተገናኘበት ተቋም አለመሆኑ ነው። ሥራና ሠራተኛ ካልተገናኘ ደግሞ  በየትኛውም መልኩ የቤተ ክህነቱ የሥራ አፈጻጸም «ከርሞ ጥጃ» መሆኑ አይቀርም። ሥራና ሠራተኛ ማለት ለተገቢው ሥራ ተገቢ ባለሙያ ወይም ተቀራራቢ ችሎታ ያለው ሰው ማለት ነው። እንደዚህ ባለው ሰው ላይ የተቋሙን ዓላማና ግብ በደንብ ካስጨበጡት ከችግሮቹ ብዛት አንጻር ባንድ ጊዜ ፈጽሞ ባይወገድም፤ ከየትኛውም ጊዜ የተሻለ ለውጥ ሊመጣ ይችላል። በዘመድ አዝማድ የተለጣጠፉና የተደረቱ ክፍሎችን ይዞ መቀጠል ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ይሆናልና አሁን ያለን የሥራና ሠራተኛ አቋም የችግሩ ዋና ምንጭ ነው ባይባልም የችግሩ አካል ነውና ከጥገናዊ ለውጥ ወይም ከማስመሰል /pseudo/ የራቀ ለውጥ ያስፈልገዋል። ከአቅም በታች ለመሥራት የእድሜ ጣሪያ የገደባቸውም  በየመልኩ ቦታቸውን መያዝ  ካልቻሉ ቤተ ክህነት የዘመዳ ዘመዶች የጡረታ ተቋም ሆኖ ይቀጥላል እንጂ የሥራ ብቃት መለኪያ ስፍራ ሊሆን አይችልም። 

Wednesday, December 18, 2019

ብጹዕ አቡነ ገዳ!

ብጹዕ አቡነ ገዳ
ልጆቼ: በምሥራቅ ሸዋ ለመኖር ብዬ የክርስቶስን መስቀል በማስቀመጥ የዋቄፈታን ባህላዊ እምነት የሆነውን የወንድ ብልት ዱላ: የቃልቻ መግረፊያ አለንጋና የገዳን የሰንደቅ አርማ ለመያዝ ተገድጃለሁ።



Wednesday, April 4, 2018

«አሮጌውን እርሾ አስወግዱ፤ ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና»



ዕብራውያን פֶּסַח «ፔሳኽ» ይሉታል። ፋሲካ ማለት ነው። በወርኀ ኒሳን በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን ይከበራል። ሥርዓቱ የሚጀመረው በዐሥራ አራተኛው ቀን ዋዜማ ሲሆን በፋሲካው ሳምንት እርሾ የገባበት ምንም ዓይነት ምግብ መመገብ ክልክል ነው።ዕለቱን ተቦክቶ ወዲያው የሚጋገር እንጂ የኮመጠጠ ወይም የቦካና የዋለ፤ያደረ መመገብ በሕጉ እንደተቀመጠው ከእስራኤል አንድነት ያስወግዳል። ከማንኛውም እርድ ላይ ጥሬ መብላት ወይም ከበሉትም አስተርፎ ማሳደር አይፈቀድም። ለመስዋዕት የሚቀርበው የበግ ወይም የፍየል መስዋዕትም እድሜው ከአንድ ዓመት ያልበለጠ ጤናማና የተመረጠ መሆን ይገባዋል። በዐሥራ ዐራተኛው ቀን ምሽት መስዋዕቱ ይታረዳል።ሥጋውን ደግሞ ሌሊት ከመራራ ቅጠል ጋር ቀላልቅለው ይበሉታል። ደሙን ደግሞ የበሩን ሁለት ረድፍ «መቃንና ጉበኑን» ይቀቡታል። ሁለቱን ቋሚ መቃንና የላይኛውን ጉበን ሲቀቡት ይህንን ቅርጽ ይይዛል።


Sunday, January 28, 2018

ኢየሱስ አስተማማኝ መድኅን ስለሆነ እኔ: እኔ ይላል!



ኢየሱስን ብቻ መተማመንና የሌላ የማንንም ተስፋ አለመጠበቅ ለምን የግድ ሆነብን? ወደኢየሱስ ለመቅረብና ከኢየሱስ ለመታረቅ ሌላ መንገድ እንደሌለ ማወቅ የሚገባን ምርጫ የለሽ መሆኑን መረዳት የሚገባንስ ለምን ይሆን?

በኢየሱስ ብቻ መታመንና ወደእሱም ለመቅረብ ሌላ አድራሽ መንገድ ወይም አቋራጭ ጎዳና ላለመኖሩ አሳማኙ ምክንያት እኛ ሳንፈልገው ፈልጎን የመጣ መተኪያ የሌለው መድኃኒት እርሱ ብቻ ስለሆነ ነው።
 ነቢዩ ኢሳይያስ በመጽሐፈ ትንቢቱ ላይ እንደከተበው: በኋለኛው ዘመን ይህንን የእግዚአብሔርን ቃል መገለጥ እንዲህ ጽፎልናል።

"ላልጠየቁኝ ተገለጥሁ፥ ላልፈለጉኝም ተገኘሁ፤ በስሜም ያልተጠራውን ሕዝብ። እነሆኝ፥ እነሆኝ አልሁት። " (ኢሳ 65: 1)

ይህ የኢየሱስ መገለጥ ለእኛ ያተረፈልን ነገር በስሙ ላልተጠራነው ለእኛ የእግዚአብሔር ልጆች መባልን አስገኝቶልናል። በሞት ጥላ ሥር ወድቀን ለነበርን የሕይወት መትረፍረፍ በዝቶልናል። በጨለማ ግዞት ተውጠን ለነበርን ዘላለማዊ ነጻነትን የሚያጎናፅፍ የምሥራቹ አዋጅ ተሰብኮልናል። ስለሆነም ወደአብ ለመቅረብ ሌላ መንገድና በር በላይ በሰማይ ይሁን በታች በምድር ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ የለም።
      የኢየሱስ ክርስቶስ እኔነት ለእኛ የሕይወት እኔነት ብቁ ዋስትና የሆነው ኢየሱስ መተኪያ የሌለው ሕይወትን የመስጠት እኔነት ስላለው ነው። ይህንንም በቁና አስተማማኝ እኔነት በመዋዕለ ሥጋዌው ኢየሱስ ራሱ ብዙ ጊዜ ነግሮናል። እስኪ ጥቂቱን እንመልከት።

"እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል"(ማቴ 10: 40)

"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ"(ማቴ 11:28)

"እርሱም÷ እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው" (ማቴ16: 15)

" ኢየሱስ ግን አንድ ሰው ዳስሶኛል፥ ኃይል ከእኔ እንደ ወጣ እኔ አውቃለሁና አለ"
(ሉቃ 8:46)

Tuesday, January 2, 2018

ኢየሱስ አዳነን እንጂ ከአብ ጋር እንታረቅ ዘንድ አላማለደንም ማለት ኑፋቄ ነው!!


****************
አንድ ሰው በፌስቡክ ገጹ ላይ "ኢየሱስ አዳነን እንጂ አላማለደንም" የሚል የስሕተት ትምህርት ፅፎ ስላየኹ ይቺን አጭር ፅሑፍ ለመጻፍ ተነሳሳሁ። ማስረጃችንም ቅዱስ መጽሐፍ ነው።

መልሴን በጥያቄ ልጀምር። " አዳነን እንጂ አላማለደንም" ማለት ምን ማለት ነው? ይህ አባባል "ኢየሱስ ይፈርዳል እንጂ አያማልድም" የሚሉ ሰዎች ለሞገት የሚያቀርቡት ክርክር እንደሆነ እረዳለሁ። ይህ የስነ ሞገት ክርክር ጥያቄ ማስከተሉ የግድ ነው። እርግጥ ነው: ኢየሱስ ፈራጅ አምላክ ነው። ታዲያ ፈራጅ አምላክ ሆኖ ሳለ እኛን የአዳም ልጆች ከዘላለማዊ ቁጣ ለማዳን ለምን ሰው መሆን ይጠበቅበታል? በሰማያዊ አምላካዊ ሥልጣኑ " ድናችኋል" የሚል ቃል ቢሰጥ የሚቃወመው ማነው? መከራና ሞት ወደሚያስከትል ደካማ ሥጋ በመምጣት ሰው መሆን ምን ያደርግለታል?
  ያዳነን በፈራጅነቱ እንጂ በምልጃ አይደለም የሚሉ ሰዎች አምላክ ሰው መሆን ሳያስፈልገው በለይኩን ቃሉ ለምን እንዳላደን ወይም ከፈራጅነቱ ምን ጎድሎበት ሰው ወደመሆን እንደወረደ ሊገልፁልን ይገባል።
ከአብ ጋር ለማማለድ ካልሆነ በስተቀር የማዳን ሥልጣን አንሶት ነው ሰው የሆነው? ብለን እንጠይቃለን። ያለምልጃውም አልዳንም: መዳንም የለም እንላለን።