Friday, September 7, 2012

የግብጽ ኦርቶዶክስና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት መጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር ለምን ተለያየ?

የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለ1600 ዓመትያህል  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የበላይ ሆና ስትመራ መቆየቷ እርግጥ ነው። በዚህ ረጅም ዓመታት ውስጥ ለቤተክርስቲያኒቱ ያበረከቱት እድገትና መንፈሳዊ ልማት እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ይልቁንም በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ለመግባትና በቤተክርስቲያኒቱ የወርቅና የልዩ ልዩ ስጦታዎች ሀብት ማጋበስ እድል ሰጥቷቸዋል። ራሷን በቻለች ጊዜም መሪዋና ኃላፊዋ የመሰረታት ክርስቶስ ነው፤ ከማለት ይልቅ በእኛ አመራርና ኃላፊነት ስር ካልሆናችሁ ፕትርክናውን አንፈቅድላችሁም ሲሉ አስቸግረው እንደነበር የቅርብ ጊዜው ታሪክ ይነግረናል። እንደዚያም ሆኖ በብዙ ነገራችን የመመሳሰላችን ነገር እንዳለ ሁሉ ዋና በሚባለው በመጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር ላይ ግን ትልቅ ልዩነታችንን በ1600 ዓመት ውስጥ ለምን እንደሆነ አልነገሩንም፤ ወይም እኛም አልጠየቅናቸውም። በጅምላ የኦሪየንታል/ምስራቃዊ/ አብያተክርስቲያናት ሁላችንም አንድ ዓይነት እምነትና አስተምህሮ አለን እያልን በረጅም ታሪካችን ውስጥ እስክንድሪያ እናታችን፤ ማርቆስ አባታችን ከማለት ውጪ አንድ ሊያደርገን በሚገባው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እስከዛሬ ባለን ልዩነት የሚነገር ምንም ነገር አለመኖሩ አስገራሚ ነው። እውነቱ ግን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና በኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መካከል የሃይማኖቱ መመሪያ በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሁለቱም ቤተክርስቲያን የቁጥር ልዩነት እንዳላቸው እርግጥ ነው። ለምን? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ የሊቃውንት ጉባዔ ካለ ለመስማት ዝግጁ ነን። እስከዚያው የልዩነትም ደረጃ ለማየት እዚህ ላይ እንዘረዝራቸዋለን።



የግብጽ/ኮፕቲክ/ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍት ዝርዝር፤
የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት

1/ Genesis     ዘፍጥረት                
2/ Exodus    ዘጸአት
3/ Leviticus  ዘሌዋውያን
4/ Numbers ዘኁልቈ
5/ Deuteronomy ዘዳግም
6/ Joshua  ኢያሱ ወልደ ነዌ
7/ Judges  መሣፍንት
8/ Ruth   ሩት
9/ 1 Samuel  1ኛ ሳሙኤል
10/ 2 Samuel  2ኛ ሳሙኤል
11/ 1 Kings   1ኛ ነገ
12/ 2 Kings 2ኛ ነገ
13/ 1 Chronicles  1ኛ ዜና
14/ 2 Chronicles  2ኛ ዜና
15/ Ezra     እዝራ
16/ Nehemiah  ነህምያ

17/ Tobit  ጦቢት
18/ Judith   ዮዲት
19/ Esther   አስቴር
20/ Job    ኢዮብ
21/ Psalms  መዝሙር
22/ Proverbs   ምሳሌ
23/ Ecclesiastes  መክብብ
24/ Song of Solomon  መሐልይ
25/ Wisdom   ጥበብ
26/ Sirach  ሲራክ
27/ Isaiah  ኢሳይያስ
28/ Jeremiah   ኤርምያስ
29/ Lamentations   ሰቆቃ
30/ Baroch    ባሮክ
31/ Ezekiel    ሕዝቅኤል
32/ Daniel   ዳንኤል
33/ Hosea   ሆሴዕ
34/ Joel   ኢዩኤል
35/ Amos   አሞጽ
36/ Obadiah  አብድዩ
37/ Jonah   ዮናስ
38/ Micah  ሚክያስ
39/ Nahum   ናሆም
40/ Habakkuk   እንባቆም
41/ Zephaniah   ሶፎንያስ
42/ Haggai    ሐጌ
43/ Zechariah   ዘካርያስ
44/ Malachi   ሚልክያስ
45/ 1 Machabees   1ኛ መቃቢስ
46/ 2 MachabeesPhilemon  2ኛ መቃቢስ ዘፊልሞና



************************************************

Thursday, September 6, 2012

ሲኖዶሱ ለ15 ቀን የሚቆይ የምህላ አዋጅ አወጀ!

ምንጭ፤ ዓውደምህረት ብሎግ 

ሲኖዶሱ 15 ቀን የሚቆይ የምህላ አዋጅ አወጀ  

በትናትናው ዕለት ለጋዜጠኞች በተሰጠ የጽሁፍ መግለጫ ሲኖዶሱ ከጳጉሜ 1 አስከ መስከረም 10 የሚቆይ የምህላ አዋጅ አውጇል፡፡ በብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፊርማ በተለቀቀ የጽኹፍ መግለጫ እንደሚያመለክተው ምህላው ጾምን አያካትትም፡፡ ዋነኛ አላማውም የተሻለ አባት ለቤተክርስቲያን እንዲያስነሳ ነው፡፡ የሰላም አምላክ አግዚዘብሔር ለቤተክርስቲያን የሚበጀውን ያምጣልን፡፡ 

የሱባኤው ዓላማ ተገቢ እና አስፈላጊ ቢሆንም ቀጥታ ፓትርያርክ ምርጫ ጋር ከማተኮር ሁለቱ ሲኖዶሶች የሚዋሀዱበትን ሁኔታዎችን እና እርቁ የሚቀላጠፍበትን ሁኔታ የሚያመቻች ቢሆን ጥሩ ነበር፡፡ ከዚህ በፊት እርቅ እንዳይፈጸም እንቅፋት የሆኑት አቡነ ጳውሎስ ናቸው እየተባልን ኖረናል፡፡ አሁንስ ታድያ ምን እየተደረገ ነው? ምህላ አዲስ ፓትርያርክ ለመምረጥ ከሆነ እርቁ ለምን ያስፈልጋል? ከአሜሪካ መጥተው የሀዘኑ ጊዜ እስኪያልፍ ጠብቁ የተባሉት ሰዎችስ ምን ሊባሉ ነው? እውን አሁን ያሉት አባቶቻችን እርቁን ይፈልጉታል? ይህንን ጉዳይ በተመለከተ አባቶቻችን አንድ ብትሉን መልካም ነው፡፡


 የጸሎተ ምህላውን ደብዳቤ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Wednesday, September 5, 2012

ጌታም ወደ እግዚአብሔር ፍቅር ወደ ክርስቶስም ትዕግሥት ልባችንን ያቅናው 2ኛ ተሰ 3፤5


ስለትዕግስትና ታጋሽነት ብዙ ብዙ ሰምተናል። ትዕግስት መራር ናት ፍሬዋ ጣፋጭ ነው፤ በለሷን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል ፤ የመሳሰሉት ጥቅሶች የትዕግስትን አስፈላጊነት የሕይወታችን አንድ ክፍል የማድረግን ነገር የሚያሳስቡን ኃይለ ቃሎች ሆነው አገልግለውናል ወይም ለተገልጋዮች ተናግረናቸዋል። ትዕግስትን ብዙ ምሁራን፤ሊቃውንትና መሪዎችም በገባቸው መጠን በማሳያነት ጠቅሰው ከትበውልናል።
ሚልን የተባለው ምሁር ትዕግስትን በወንዝ ጉዞ ስዕላዊ መንገድ ሲነግረን  «ወንዞች እንዴት እንደሚፈሱ ስለሚያውቁ ቁልቁል ይፈሳሉ፤ ብዙውን ጠመዝማዛ መንገድ በረጅም ትዕግስት አቋርጠው ከመጨረሻቸው ይደርሳሉ» ይለናል። ሚልን ስለትእግስት በምሳሌ የነገረን ነገር በእርግጥም ትልቅ እውነት ነው። ዓባይን የሚያክል ወንዝ በእርጋታ ከጣና ተነስቶ በረሃውንና ቁልቁለቱን አቋርጦ፤ ሀገራትን አካልሎ ከሜዲተራንያን ገብቶ እረፍት ለማድረግ ብዙ ትዕግስት ማድረጉ በእርግጥም አስገራሚ ነገር  ነው።
«The book thief» የተባለውን መጽሐፍ የደረሰው ማርከስ ዙሳክ ደግሞ ስለትዕግስት እንዲህ ብሏል። «ትዕግስት የሌለው ሰው የራሱን ምስል በጥቁር ቀለም የሳለ የእአእምሮ ንክና  ዓለምን ማሸነፍ ያልቻለ ሰው ነው» ሲል ገልጾታል።
«ፓውሎ ኮልሆ» ደግሞ ስለትዕግስት አስፈላጊነት እንዲህ ሲል ይመከረናል። «ትዕግስት ለምን እንደሚያስፈልግ ታውቃላችሁ?» በማለት ይጠይቅና ለጥያቄው ምላሽ ራሱ እንዲህ ሲል ይሰጣል።  «ምክንያቱም የትዕግስት ማጣት ለነገሮች ተገቢውን ትኩረት እንዳናደርግ ይከለክለናል» ሲል አስቀምጦታል።
ጃሮክ ክኒትዝ ደግሞ  የትዕግስትን አስፈላጊነት ሲገልጸው« ወንድሜ! ውሃው ሳይፈላ፤ እንፋሎት አይወጣምና ታገስ» ሲል እጥር ምጥን ባለ ቃል ገልጾታል።
እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ የዘመኑ ምሁራንና ፈላስፎች ስለትዕግስት አስፈላጊነት በየመድረኩ ሳይናገሩ የቀሩበት ጊዜ የለም።  ጥቅሶቻቸውን ከማነብነብ ውጪ ምን ያህላችን የትዕግስትን አስፈላጊነት ገላጭ ምክሮቻቸውን በሕይወታችን ውስጥ ተግባራዊ እንዳደረግን ቤቱ ይቁጠረው። ይሁን እንጂ ትዕግስት አስፈላጊ ስለመሆኗ ሁላችንም በአንድ ቃል እንስማማለን። አባቶቻችንም የትዕግስትን አስፈላጊነት ሲገልጹ «ለዚሁ ነው በሬዬን ያረድኩት» ያለውን ሰው ምሳሌ የሚያቀርቡት የመታገስ አቅምን ከማጣት ጋር አስተሳስረው ሲነግሩን ኖረዋል። በትዕግስት ማጣት ብዙ ችግር ሊመጣ እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነው። ግን የትዕግስት መጠኑ እስከየት ድረስ ነው? ይሄም ብዙ ያነጋግራል። ስለዚህም ብዙ የተባለ እንደሆነ ይታወቃል።  የርእሳችንን መነሻ ያሰፋዋልና ትተነዋል።
የዚህ ጽሁፍ ዓላማ በምሁራን የትዕግስትን ገላጭ ቃላትና የትዕግስትን የገደብ ጣሪያ እስከየትነት ለመተንተን ሳይሆን በሕይወት ዘመናችን ውስጥ ዓለማውያን ሊቃውንቶች ምክርና ተግሳጽን በመስጠት ትዕግስትን ገንዘብ እንድናደርግ የለገሱንን በማንሳት፤ ዓለም የዚህን ያህል ተራምዳ ስለትዕግስት አስፈላጊነት ከተናገረች መንፈሳዊ ሕይወትስ እንዴትና እስከየት እንደተናገረችን ለመዳሰስ በመሻት መንደርደሪያ ይሆን ዘንድ አስቀምጠነዋል።
ወደ ርእሳችን ስንመለስ እንዲህ ይላል።
«ጌታም ወደ እግዚአብሔር ፍቅር ወደ ክርስቶስም ትዕግሥት ልባችንን ያቅናው» 2ኛ ተሰ 3፤5
ወደ ክርስቶስም ትዕግስት እግዚአብሔር እንዲያቀናው የሚፈለገው ትዕግስት ምን ዓይነት ይሆን?
በመንፈሳዊው ዓለም ከክርስቶስ የሆነ ትዕግስት የሌለው ሰው ክርስቲያን ሊሆን አይችልም።  በመባልና በመሆን መካከል ትልቅ ልዩነት እንዳለ ልናስተውል ይገባል። ብዙ ሰዎች ክርስቲያኖች ሊባሉ ይችላሉ። ክርስቲያኖች የተባሉ ሁሉ ግን ክርስቲያን ሆነዋል ማለት አይደለም። የሚወዷቸውን የሚወዱ ክርስቲያኖች ሞልተዋል፤ ነገር ግን የሚጠሏቸውን የሚወዱ ክርስቲያኖች ማግኘት አዳጋች ነው።  እነዚህ ክርስቲያኖች ይባላሉ ግን ክርስቲያን መሆን ያልቻሉ ቀራጮች ናቸው። ወንጌል እንዲህ ካለ እነዚህ ሰዎች ቀራጭ ክርስቲያኖች የማይባሉበት ምክንያት የለም።
የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ማቴ 5፤46
ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ክርስቶስም ትዕግስት ልባችንን ያቅናው ያለበት ምክንያት መውደዳችን በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኘንበትን ምስጢር ከቀራጭነት ሚዛን እንድናወጣው መሆኑ ግልጽ ነው። ክርስቶስ እኛን የወደደበት ትዕግስት ሚዛን የለውምና ነው።
የክርስቶስ የፍቅሩ ትዕግስት እኛን ለማዳን መፈለጉ ብቻ አልነበረም። እኛን ለማዳን ከመጣና ከኃጢአት ብቻ በቀር  በሥጋ  ከተዛመደን በኋላ ማዳኑን በደስታ ለመቀበል ከእኛ የተገባ ማንነት የሚጠበቅ ሆኖ ሳለ ሊያድነን የመጣበት ትዕግስት ሳያንስ እንዲያድነን መግደላችንን መታገስ መቻሉ እጅግ አስገራሚ ያደርገዋል።
ማንም ሰው መልካም ስጦታ ይዞለት የመጣውን ሰው በድሎት ሲያበቃ ከተበዳዩ ሰው ፍቅርን መጠበቅ አስቸጋሪ እንደሚሆንበት መገመት አይከብድም። ክርስቶስ ኢየሱስ ሌላ መድኃኒት በስጦታ አላመጣም፤ ይልቁንም ራሱን ሞት ለሚገባው ሰው፤ ምትክ ሆኖ ለመሞት ፍቅሩ ፍጹም በሆነ ትዕግስት የመጣ መድኃኒት ነበር። ለዚህ የሞት ምትክ መድኃኒት የቀረበለት መስዋእት የደስታ ምስጋና ሳይሆን እስከሞት የሚያደርስ መከራ ነበር። የሚገርመው ነገር ይህ ሁሉ ሆኖ ትዕግስቱ ምን ጊዜም ሞት በሚገባቸው ሰዎች ላይ የጸና መሆኑ ነው።
«ኢየሱስም፦ አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ» ሉቃ 23፤34 እንደዚህ ዓይነት ትዕግስት ከወዴት ይገኛል?
ዛሬ አንዱን ክርስቲያን በቅጽበታዊ ንዴት ሌላውን ክርስቲያን፤ ጉንጩን በጥፊ ቢመታው  ከመ ቅጽበት አጸፋዊ ምላሹን ከመንጋጋው ወይም ዓይነ ስቡን በተጠናከረ ምት የማይሰጥ ለማግኘት  ከተአምር ቢቆጠር አይገርምም። እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ ወይም ወንድምህ ሆኜ ሳለሁ እንደዚህ የመታኸኝ ምን በደልኩህ? የሚል ቢኖር በእውነት ክርስቲያን ማለት እሱ ነው።
በየሚዲያው፤ በየጉባዔውና በየመድረኩ  የምንወራወራቸው የቃላት ናዳዎች ያልፈነከቱት ወይም ያላሳመሙት ለማግኘት ከባድ ነው። እንደዚያም ሆኖ በማስተዋል ላይ ሆነን ነገሮችን ከክርስቶስ ትዕግስት አንጻር ባለመመልከት ናዳዎቹ ከየአእምሮአችን ጓዳ እየተፈነቀሉ ቀጥለዋል። ከሁሉም የሚከፋው እኔ ያልኩትና የተናገርኩት ብቻ ትክክል ነው የሚለው ናዳዎች እየተፈነቀሉ መወርወራቸውን አለማቋረጣቸው ነው።  እንደዚያም ሆኖ ክርስቲያኖች እንባላለን። ግን እስከመቼ?