የማቅን
ውስጠ ምስጢር ፈልፍላ በማውጣት ከፍተኛ መደናገጥን በመፍጠር ላይ ያለችውን ዓውደ ምሕረት ብሎግ በኢትዮጵያውስጥ እንዳትታይ ከተደረገች
ሳምንታት ተቆጥረዋል። አባ ሰላማ ብሎግ የችግሩን ግዝፈት በመጥቀስ በገጹ ካወጣው በኋላም ቢሆን የዓውደ ምሕረት መዘጋት እስካሁን መፍትሄ አላገኘም። ይህንን ጉዳይ የማቅ ብሎጎች
በሬ ወለደ ለማለት ጊዜ ባይፈጅባቸውም የአዘጋገባቸው ቃና ያስገነዘበን ነገር ቢኖር ለምን ድርግም ብላ አትቀርም የሚል ምኞትን ያረገዙ
ይመስላል። ምክንያቱም በእውነት «ዓውደ ምሕረት» እንዳትታይ ከተደረገ ሳምንታትን ያስቀጠሩ ሆነው ሳለ ነገረ ስላቅን ማቅረብ የጠላት
አሰራር ጥልቅ መሆኑን ያመላክታል። መረዳት የሚገባን ነገር ቢኖር «እውነት አናቷን ሲቀብሯት በጭራዋ ብቅ እንደምትል ማወቅን ለአፍታም
መዘንጋት አይገባንም።
የዓውደ
ምሕረት ዘገባ ከታች ቀርቧል።
ብሎጋችንን
ኢትዮጵያ ውስጥ አንዳትታይ መደረጉ አሁንም ቢሆን እውነት ነው፡፡
የሀገር
ውስጥ አንባቢያን አዲሱን አድራሻ
www.awdemihret.wordpress.com ተጠቀሙ፡፡
(ነሐሴ
5 2004 ዓ.ም. ዐውደ ምሕረት/
www.awdemihret.blogspot.com / www.awdemihret.wordpress.com ) ብሎጋችን አውደ
ምህረት በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳትታይ ከተደረገች ዛሬ ሁለት ሳምንት ሆናት፡፡ አድራሻችንን ማለትም
www.awdemihret.blogspot.com ማንም ኢትዮጵያ
ውስጥ ያለ ሰው ለመክፈት ቢሞክር የሚያገኘው መልስ No data
received Unable to load the webpage because the server sent no data. የሚል ነው፡፡
ይህ ማለት በግልጽ አማርኛ ብሎጉ እንዳይከፈት ተደርጓል ማለት ነው፡፡ ይህንን እውነት አባ ሰላማ በመዘገብዋ “አቤት ውሸት” ሲል አንድ አድርገን ለመተቸት ሞክሯል፡፡ የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ እንደሚባለው ሳልዋሽ ቀኑ እንዳይመሽብኝ እያለች የምትሰጋው አንድ አድርገን የምትዋሽበት ጉዳይ ስታጣ ፍጥጥ ካለው እውነት ጋር መታገል ጀምራለች፡፡ ብሎጋችን ኢትዮጵያ ውስጥ አለመስራትዋን አሁንም ቢሆን ማንም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ሰው ሊያየው የሚችለው ሀቅ ነው፡፡
አንድ
አድርገን “ብሎጉ ሳይዘጋ ተዘግቷል ይላሉ” ስትል ጽፋለች፡፡ ማንም አንባቢ እንደሚያስተውለው ግን ብሎጋችን ተዘግቷል የተባለው ስለተዘጋ ነው፡፡ እኛ እንደእናንተ ልናገኝ የምንችለው ፖለቲካዊ ትርፍ ስለሌለን እንዲህ ያለ ውሸት አንዋሽም ስለማኅበረ ቅዱሳን የምንጽፈው የሆነውን ነው፡፡ እኛን ዋሻችሁ ለማለት ምክንያት ያገኛችሁ መስሎዋችሁ ነበር ነገር ግን እናንተ የራሳችሁን ውሸታምነት ነው የገለጻችሁት፡፡
በሬ
ወለደ የእናንተ ስም እንጂ የእኛ አይደለም፡፡ ብዙ ብዙ ብዙ በሬዎችን አስወልዳችኋል በርካታ ግመሎችን በመርፌ ቀደዳ አሳልፋችሁኋል፡፡ አላማችሁ ሀሳባችሁ መንፈሳዊነታችሁ ሁሉ የተመሰረተው በውሸት ነው፡፡
ማኅበረ
ቅዱሳን ብሎጋችን ላይ የሚወጡት ዜናዎች ራስ ምታት ስለሆኑበት መረጃ የሚሰጠው ማነው እያለ በስብሰባ ራሱን እንደሚያደክም እናውቃለን፡፡ የብሎጉ ባለቤት እገሌ ነው እገሌ ነው የለም እገሌ ነው እያለ ወሬ የሆነ “መረጃ” እንደሚያሰባስብም እናውቃለን፡፡ ብሎጉን ለማዘጋት አይደለም ሌላም እድል ቢኖረው ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም፡፡
ብሎጎችን
ኢንሳም ይዝጋው ማንም ማኅበረ ቅዱሳን እዛ ውስጥ ሰው አያጣም፡፡ እነዛን ሰዎች ተጠቅሞ ብሎጉን ከማዘጋት ወደ ኃላ አይልም፡፡ በዛ ላይ ብሎጉ ለምን ተዘጋ ብሎ ጥያቄ የሚያቀርብ አካል እንደማይኖርም ያውቃል፡፡ ስለዚህ እንዲህ ያለውን ብሎግ ማዘጋት ከባድ አይደለም፡፡