ብዙ ጊዜ ስለማኅበረ ቅዱሳን በሚቀርቡ ጽሁፎች
ላይ አስተያየት የሚሰጡ የማኅበሩ አቀንቃኞች የሚያዩን ስለማኅበሩ
ጭፍን አመለካከት እንዳለንና ሥራውን ሁሉ እንደምናቃወም አድርገውን ነው። ይሁን እንጂ ማኅበሩ እንደማኅበር የሰዎች እንጂ የቅዱሳን
መላእክት ስብስብ ባለመሆኑ በጉዞው ውስጥ መልካምም ይሁን መጥፎ ሰውኛ ድክመቶች የሚገለጽበት መሆኑን ሁሉም አምኖ እንዲቀበልና ጥንካሬው
ለቤተክርስቲያን ጠቃሚ እንደሚሆን ሁሉ ድክመቱም አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚያመጣ በመገንዘብ ራሱን እንዲያይ፤ እኛም ማን መሆኑን በማወቅ
የተሻለ ግንዛቤ ይዘን እንደባህሪው የበኩላችንን ድርሻ እንድንወጣ
ነው። ለስህተት ትምህርቶችን የአዞ እንባ አፍሳሽነት፤ የሁሉን አውቃለሁና ጠበቃ ነኝ ባይነት መጥፎ ዐመል፤ የእኔ ላቡካው፤ እኔው
ልጋግረው ግብዝነት፤ ከቤተክርስቲያኗ ኪስ ወደራስ ጓዳ የመሰብሰብ አባዜ፤ የሰላይ፤ የመቺ፤ የአሳዳጅና የፈራጅ ቡድን የማዋቀር ሲሲሊያዊ
አካሄዱን ነቅሰን በማውጣት ይህን፤ ይህን ስትሰራ ቆይተሃል፤ ይህን ይህንንም እየሰራህ ትገኛለህ፤ መረጃዎቻችንም እነዚህ ናቸውና
ከተነቃብህ እራስህን አርም፤ አስተካክል ወይም ቢያንስ ራስህን እስኪ
ጠይቅና ከሚወራው ውስጥ የትኛው እውነትና የትኛውስ ስም ማጥፋት ነው ብለህ ፈትሽ በማለት ለማሳሰብ ነው። እኔ ቅዱስ እንጂ ስህተት የማይጎበኘኝ ነኝ ማለት ሲያበዛ ደግሞ አንተ ፈሪሳዊ
ሆነህ ሳለ መጸብሐዊው አይጸድቅም የምትል ግብዝ ነህና መንገዳችንን አትዝጋ፤ የናቡከደነጾር የህልም ሀውልት ስለሆንክ ከተራራው የሚወርደው
ዐለት ይፈጭሃልና ግዙፍነትህን አይተህ አትመካ እንለዋለን። ሌላውም እንዲያይ የእስከዛሬ ማንነቱን ገልጠን ለሌሎች እናሳያለን። በዚህም ሥራችን
ብዙዎች ራሳቸውን እንዲጠይቁ፤ የሚባለውን እውነትነት እንዲመረምሩ አድርገናል። በዚህም የመረጃ ስርጭትና ማንነቱን የመግለጽ ሥራችን
ግምገማቸውን ወስደው ራሳቸውን ከማኅበሩ ክፉ ስራ ያገለሉ ብዙዎች ናቸው። ተሸፍኖ የነበረባቸውን የማኅበሩን ማደንዘዢያ መርፌ ነቅለው
ከድንዛዜ ወጥተው፤ እስከዛሬ የት ነበርኩ? ያሉና ራሳቸውን የጠየቁ ብዙዎች ናቸው። ከዚህ በታች ያለውም የማኅበረ ቅዱሳን አቀንቃኝ
ብሎጎች ማጭበርበርና የነፍስ ውጪ፤ ነፍስ ግቢ ውሸት ማሳያ ቀርቧልና
ሄዳችሁ ብሎጎቹን አንብባችሁ ከታች በቀረበው መረጃዎች ላይ ተመርኩዛችሁ ማቅ ማን መሆኑን ተመልከቱ! ሁሌም ውሸት! ውሸት!
ውሸት! አቤት ማቅ?
ምንጫችን፤ ዓውደ ምሕረት ብሎግ፤
- ሊቀ ሥዩማን ኃይለ ጊዮርጊስ መኪና አልተቀማም
- ጉባኤ አርድእት ስብሰባ እንዳይሰበሰብ አልታገደም
- መንግስት ለማኅበረ ቅዱሳን የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ማንም አልሰማም በማለት ወደ ጉባኤ አርድዕት ለማዞር ሞክረዋል
የማኅበረ
ቅዱሳን ብሎጎች በተለመደው ዋሾ ባህሪያቸው ያልሆነውን ሆነ እያሉ መዘገብን ቀጥለውበታል፡፡ ስለጉባኤ አርድዕት በመፈራረቅ በሰሩት ዜናም ገና በመደራጀት ላይ ያለውን ጉባኤ ተፈረካከሰ ተልፈሰፈሰ ሄደ ተመለሰ እያሉ የጅል ምኞታቸውን ይነግሩን ይዘዋል፡፡ ሊቀ ሥዩማን ኃይለጊዮርጊስም በጠቅላይ ቤተክህነቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ፊርማ መኪናው ስለተበላሸ ቅያሪ መኪና እንዲሰጠው የትብብር ደብዳቤ እንደተፃፈለት እያወቁ ደብዳቤውን ከኛ
በቀር ማንም አያገኘውም በማለት ተበላሽቶ ወደ ጋራዥ የገባውን መኪና ተቀማ በማለት ዘግበዋል፡፡
እነዚህ
የማኅበሩ የውሸት ቃል አቀባይ የሆኑ ደጀ ሰላምና አንድ አድርገን የተባሉት ብሎጎች በጉዳዩ ላይ እርስ በእርሳቸው እንኳ መስማማት አቅቷቸዋል። ዋሽቶ ስምምነት የት አለና?። ደጀ ሰላም ኃይለጊዮርጊስ መኪና የተቀማው በአቡነ ጳውሎስ ትዕዛዝ ነው ብላ ጀምራ ወደ ታች ወደ ወረድ ሲባል ደግሞ በምክትል ስራ አስኪያጁ በተስፋዬ ነው በማለት ራስዋን ተጣልታ ዘግባለች። አንድ አድርገን ደግሞ በምክትል ሥራ አስኪያጁ አቶ ተስፋዬ ነው ትላለች።
እውነታው
ግን ሌላ ነው በምክትል ሥራ አስኪያጁ አቶ ተስፋዬ ፊርማ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው የኃይለጊዮርጊስ መኪና በብልሽት መቆምዋን እና እንዲያውም ተለዋጭ መኪና እንዲፈለግለት ልማትና ክርስቲያናዊ መምሪያን የሚጠይቅ ነው።
ደብዳቤውን ለማንበብ ( እዚህ ይጫኑ )