የዳላስ ደ/ፀሐይ አቡነ አረጋዊ ወተ/ሃይማኖት ቤተክርስቲያን የፊት ገጽታ
በመሠረቱ ቤተክርስቲያንን ለመንፈሳዊ አገልግሎት
ማቋቋም ቀና ሃሳብ መሆኑ አይካድም። ጥፋት የሚሆነው አንዲቱን ቤተክርስቲያን ለማዳከምና ምእመናን በቡድን ለመከፋፈል ሲባል ከሆነ
የመንፈሳዊ ተግባርን እሳቤ በማደብዘዝ ስውር ዓላማን ለመፈጸም መንፈሳዊ ካባን የደረቡ ወረበሎች የሚጠቀሙበት ስልት መሆኑ እየታየ
ነው። እናም ቄስ መሥፍን ማሞ የተባለው የዳላስ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን ሰባኬ ወንጌል የነበረው ግለሰብእ የተሰጠውን የማቅን ተልእኰ
አንግቦ በኅቡእ የቆየ ቢሆንም ሰዓቱ ሲደርስ ከዛሬ ጀምሮ ተገንጥያለሁ ማለቱ ተሰምቷል።
በኢትዮጵያ ሀገር ውስጥ ያለ ዋና ሲኖዶስ ፤ በስደት ያለ ዋና ሲኖዶስ እና አሁን ደግሞ በፓትርያርክ ማኅበረ ቅዱሳን የሚመራ አዲስ ሲኖዶስ በምድረ አሜሪካ
እየተገነጠለና ራሱን እያራባ ወደ ሦስትነት እያደገ ይገኛል።
በዳላስ አቡነ አረጋዊ ወተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን
ሰባኬ ወንጌል የሆነው የማኅበረ ቅዱሳኑ ታማኝ ሎሌ ለመገንጠልና በይፋ አውጆ በ5000 ዶላር ቤት ተከራይቶ የወጣ ሲሆን መነሻ ምክንያት የሆነው ነገር ሲቃኝ እንዲህ መሆኑን ምንጮቻን አረጋግጠዋል።
በታህሳስ ወር ገደማ በአዝማሪ መዘምራን ሴቶች
የታጀበና በገበሬ አስደንግጥ ስብከቱ ስሙዓ ዜና በሆነው ዳንኤል ክብረት
የተመራው ከፍተኛ የማኅበረ ቅዱሳን የልዑካን ቡድን ጥቂት መርዝ ነስንሶ፤ ብዙ ምርት ማፈስ በሚል መርህ በሄዱበት የ3 ቀናት ዘመቻ
ማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎት ወቅት ከዳህጸ ልሳን በዘለለ የተነገረው ዲስኩር ለችግሩ መነሻ ምክንያት ሆኗል። ይኼው ቄስ መሥፍን የተባለው
የማኅበረ ቅዱሳን አባል የደብሩ ስብከተ ወንጌል ኃላፊ እንደመሆኑ መጠን አዝማሪ መዘምራኖቹና ገበሬ አስደንግጥ ሰባኪያኑ ከደብሩ
እንዲገኙ ሁኔታዎቹን በማመቻቸት ግንባር ቀደሙ ሰው ነበር።
ዳንኤል ክብረት በወቅቱ ወዴት እንሂድ? ኢትዮጵያ
ውስጥ ታፍነን ተሰቃየን እኰ? ዝምታው እስከመቼ ነው? ወዘተ የሚሉ ቅስቀሳዎችን ሲያስተላልፍ የደብሩ አስተዳዳሪም የዳንኤልን «ሁሉም ነገር ወደጦር ግንባር» ዓይነት ስብከቱን በመቃወም አሁን ይሄ ስብከት
ነው? በባእድ ሀገር ለሚገኝ ምእመንና ምእመናት ከአንድ ሰባኪ የሚሰጥ የሕይወት ቃል ይሄ ነው?
ዓላማን ለይቶ ወደ ፖለቲካው መግባት አለበለዚያም ምእመናንን የሚያጽናና ትምህርት መስጠት ሲገባ ይህን ሁሉ ሀገር አቋርጣችሁ ከመጣችሁ
በኋላ ህዝብን መቀስቀስ ተገቢ አይደለም ሲሉ ሀዘኔታቸውን ገልጸዋል። ቤተክርስቲያን የሚመጣ ደጋፊም፤ ተቃዋሚም እንደመሆኑ መጠን ቤተክርስቲያን ማስተማር
የሚገባት ሁሉንም የሚያንጽ እንጂ የአንድ አቅጣጫን ዓላማ ማስተጋቢያ መሆን የለበትም የተባለ ሲሆን የገበሬ አስደንግጡ ስብከት ውድቅ
ተደርጓል። ማቅና ገበሬ አስደንግጥ ሰባኪያኑ ዳግመኛ እንዳይመጡ በመነገሩ ይህ ለማቅ ትልቅ ኪሳራ ሆኖ ነበር።
የማቅ ታማኝ አገልጋያቸው የደብሩ ስብከተ ወንጌል
ቄስ መስፍን ገበሬ አስደንግጦችን በማሰባሰብና በማስጮህ ብዙ የለፋበት የማቅ አገልግሎት ዋጋ በማጣቱና ተቀባይነት ባለማግኘቱ ውስጥ
ውስጡን ሲቆስል ቆይቶ ከነፍስ አባቱ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ከመከረ በኋላ የደብሩን አስተዳዳሪ፤ ካህናትንና ማኅበረ ምእመናንን ቆይ
ሳንሰራላችሁ ብንቀር በሚል ብቀላ አዲስ ቤት በአምስት ሺህ ዶላር ገደማ ተከራይተው እዚያው በቅርብ ርቀት የተተከለ ሲሆን ይህም
በፓትርያርክ ማኅበረ ቅዱሳን የሚመራው ሦስተኛው ሲኖዶስ መሆኑ ነው።
ከሁሉም የሚያሳዝነው ደግሞ ሀገረ ስብከቱ በአቡነ
ፋኑኤል የሚመራ መሆኑ እየታወቀ የሀገር ቤቱን ሲኖዶስ ከድተው ማኅበረ ቅዱሳን ቤት ተከራይቶ ሲያትል በሚያኖራቸው የሶስተኛው ሲኖዶስ
ቋሚ አባል በሆኑት በአቡነ ኤዎስጣቴዎስ በኩል የቄስ መሥፍን ቤት ተመርቆ መከፈቱ ነገሩን አስገራሚ ያደርገዋል። በእርግጥ ሦስተኛውን
ሲኖዶስ በምድረ አሜሪካ ቤቶችን በመክፈት ላይ የተጠመደው ማቅ ምንም ሀገረ ስብከት የሌላቸውን አቡነ ኤዎስጣቴዎስን ቤት ተከራይቶ
ማስቀመጡ ምናልባት የአሜሪካ ፓትርያርክ አደርግዎታለሁ የሚል ተስፋ ሰጥቷቸው ይሆናል። በዚያ ላይም ለማቅ አልገዛም፤ አልታዘዝም ያሉትን አቡነ ፋኑኤልን ለማናደድ ጭምር የተጠቀመበት
የግንጠላ ስልት ሲሆን ካከራየበት ቤት ጎትቶ በማምጣት ጳጳሱ ታዛዥነታቸውን
ማሳየታቸው ነገሩን አስገራሚ ያደርገዋል። አቡነ ኤዎስጣቴዎስም የጵጵስና
ማእረግ ወንድማቸውን ለማቅ ደስታ ሲሉ መጥላታቸውና ሕገ ቤተክርስቲያንን ማፍረሳቸውን ስንመለከት እንዲህ ብለንለመጠየቅ እንገደዳለን። እሳቸው ከጣሱት የትኛውን ህገ ቤተክርስቲያን ተግባራዊ ለማድረግ ነው የጰጰሱት እንላቸዋለን?
አንዳንድ የማቅ ደጋፊዎች አቡነ ፋኑኤልም በአቡነ አብርሃም ላይ እንደዚሁ ሰርተዋል በማለት ሊሞግቱ ይፈልጉ ይሆናል።
ያለፈ ጥፋት ካለ፣ ላሁኑ ጥፋት እንደትክክለኛ መከራከሪያ ሆኖ ሊቀርብ አይችልም።
ጎረምሳው ቡድን የራሱ ዓላማ ያለው ሲሆን ጳጳሱ ደግሞ የራሳቸውን የሲኖዶስ ዓላማ ጥለው ለማቅ ዓላማ ስኬት መዞራቸው ያሳዝናል።
ዘወትር የአቡነ ፋኑኤልን ስም በየድረ ገጾቹ እያነሳ የሚያጨልማቸው
አልበቃ ብሎት፤ አቡነ ኤዎስጣቴዎስን ወስዶ በአቡነ ፋኑኤል ሀገረ ስብከት ላይ ቤት እንዲመርቁ ያደረገው እርር ድብን ላድርጋቸው
ብሎ እንጂ ሕገ ቤተክርስቲያን ያንን እንዲያደርግ የሚፈቅድ ሆኖ አልበረም።
ነገሩ ባልበላውም ልድፋው ነው!