የጽሁፍ ምንጭ፤ ዓውደ
ምሕረት
ማኅበረ ቅዱሳን ደጀ ሰላም በተባለው አሸባሪ ብሎጉ ጉባኤ አርድእት የተባለ ማኅበር ተቋቋመብኝ ይህ ማኅበር ደግሞ አያያዙ በሞኖፖል ይዠው የነበረውን የቤተክህነት ሥልጣን ሊነጥቀኝ ነው። የተሰበሰቡት ሰዎችም ከኔ ጨዋና ጥራዝ ነጠቅ አመራሮች የተሻሉ ስለሆነ ግርማ ሞገሳቸው አስፈርቶኛል የሚል አንድምታ ያለው ባለ 9 ገጽ ጽሁፍ ከለቀቀ በኃላ ይህ ገና ከመቋቋሙ ማኅበሩን በጥላው ያሸበረው ጉባኤ አለማው ምንድን ነው? በማለት በቤተክህነት አካባቢ ያለውን ነገር እያጣራን ሳለ gubae ardiet የሚል የፌስ ቡክ ገጽ ላይ አላማውን የሚያስረዳ ጽኁፍ ስላገኘን አላማውን ታውቁት ዘንድ ልናቀርብላችሁ ወድደናል።
ማኅበረ ቅዱሳን በአንድ እግሩ ፖለቲካ በሌላኛው እግሩ ሃይማኖት እየረገጠና በሁለት ሀሳብ እያነከሰ ያለ እኔ ቤተክርሰቲያን ዋጋ የላትም እያለ ቤተክርስቲያንን ለዘመናት ሲጠብቅ የነበረውን መንፈስ ቅዱስን ስፍራ ልቀቅ በማለት ያለአቅሙ እየተውተረተረ በየአቅጣጫው አቧራ በመበተን ቤተክርሰቲያንን እየረበሸ በመገኘቱ ያሳዛናቸው የቤተክህነት ሠራተኞች የመምሪያ ኃላፊዎችና የደብር አለቆች የተሰባሰቡበት ጉባኤ አርድእት አላማው በጽሁፉ እንደሚነበበው ቤተክርስቲያንን ከምንደኞችና ከእበላ ባዮች ለመታደግ እና አባቶችን በሚያስፈልገው ሁሉ ለመርዳት ነው።
እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ሁላችንም የምናውቅ ኦርቶዶክሳዊ ጋብቻ የሚባሉ የቤተከርስቲያኒቱ አባለት እርስ በርስ በተገቢው የቤተክርስቲያን ሥርዓት ሲጋቡ ነው። ማኅበረ ቅዱሳን እራሱን ከማኅበርነት ወደ ቤተክርሰቲያንነት ስለቀየረ ማህበረ ቅዱሳን ያልሆነ ሰው እንዳታገቡ የሚል ቀጭን ትእዛዝ ለአባላቱ አስተላልፎል። እንዲህ ያለው በቤተክርስቲያን ላይ የተቋቋመው የአንጃነት ስሜት በሙስሊሙ እንደተቋቋመውና አውነተኛ ሙስሊም ሰለፊ ነው እንደሚለው የሰለፊያ አስተሳሰብ
ሁሉ ኦርቶዶክሳዊነት ማለት ማኅበረ ቅዱሳንነት ነው ወደሚል አባዜ መቀየሩ አስጊነቱን የተረዳው መንግስት ከሁለት ሳምንት በፊት መንገድ ትራንስፖርት በማህበሩ ዋና ሰው በሆነው አቶ ካሳሁን ቢሮ የባለስልጣን መስሪያ ቤት ሠራተኞችን ሰብስቦ
“ማኅበረ ቅዱሳን ከሚባል ሃይማኖት ተጠበቁ” ማለቱ የሚታወስ ነው።
አሁንም ህዝቡ ማኅበረ ቅዱሳን ከሚባል ሃይማኖት እራሱን እንዲጠብቅ እና በቤተክርስቲያን ጥላ ውስጥ ብቻ እንዲሰባሰብ ኃላፊነት ያለባቸው በትምህርትም በአገልግሎትም የተመሰከረላቸው እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆች የሆኑ የመምሪያ ኃላፊዎች ሌሎች በቤተክርስቲያኒቱ በኃላፊነት ቦታ ላይ ያሉ አገልጋዮች ያቋቋሙት ይህ ጉባኤ በጥላው ማኅበሩን እንዲህ ያስበረገገ ሥራ ሲጀምርማ ምን ውጤት እንደሚያመጣ በጉጉት የሚጠበቅ ሆኗል። አለማውን በተመለከተ የተዘጋጀውን ጽኁፍ እንድታነቡት አቅርበናል። መልካም ንባብ ይሁንላችሁ።)
ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት
ሐዋርያት በሰበሰቡአት፣ ከሁሉ በላይ በሆነች በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡
"ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ"
"የአርድእት መንፈሳዊ ኅብረትን ለመመሥረት የቀረበ መነሻ ጽሑፍ"
"ወንድሞች በኅብረት ቢኖሩ እነሆ መልካም ነው፤ እነሆም ያማረ ነው" (መዝ 132(133) ፡ 1)