ካለፈው የቀጠለ.................ክፍል 4
በድንጋይ
መስታወቱን አንዴ ሲያደቁት በበሩ የነበረው ታጣቂ (ቦታው የአስተዳደር አዳራሽ ሰለነበር ነው ) ወደ ሰማይ ለመተኮስ ቢሞክርም አልቻለም። መጨረሻ ላይ
ነፍስ አውጭኝ ብሎ ሸሸ። ከዚያ በኋላ
መራኮት ሆነ። «ዋናው እሱ
ነው፤ እርሱን ያዙት! የሚል ጩኸት
ብሰማም የማላውቃቸው ሰዎች መጥተው ስለሸፋፈኑኝ እኔን ለመግደል ለሞከሩት ሰዎች አልሆነላቸውም ነበር። «ስለ እመ አምላክ
ተዉኝ» ከምትለው ነፍሰ ጡር ጀምሮ «እማዬ የት ነሽ» እያለ እስከሚያለቅሰው
ሕጻን ድረስ ታላቅ ጩኸት በአዳራሹ ውስጥ ሞላ።
መግቢያና
መውጫውን እነርሱ ስለያዙት በየትም መውጫ አልነበረም። የአካባቢው ጸጥታ ኃይሎች እስኪመጡ ድረስ ሰዎቹ ይዘዉት በመጡት መምቻ ሁሉ መቱት።
ማን ምን እንደሆነ ለማወቅ ግን አልቻልንም ነበር። በመጨረሻ የጸጥታ ሰዎች በመጡ ወቅት ግን የተወሰነው እነርሱን ጥግ አድርገን ለማምለጥ ቻልን። ከአካባቢው እየሮጥኩ
ስወጣ ታክሲ ስላገኘሁ የማልረሳውን ቃል ተናገርኩ «ከዚህ ቦታ ወደ ፈለግህበት ውሰደኝ» ምንም እንኳን ለጊዜው ለባለ ታክሲው የተናገርኩት ቢሆንም በዚያ ወቅት ግን ለአምላኬም የተናገርኩት ነበር። «ብቻ ከዚህ
ቦታ ወደ ፈልግህበት ውሰደኝ» ወንድሞቼ በምላቸው
የገዛ ወገኖቼ የአንዲት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስንደበደብ ምን ልበል ? ካሳደገችኝ ቤተ ክርስቲያን ሽሚዜ በደም ጨቅይቶ እንደሌባ በገዛ ሀገሬ ወገኔ ፊት ስሸሽ ምን ልበል
? (ከልለው ባወጡኝ ሰዎች
ደም ጭምር ነበር የዳንኩት! እኔ ብቻ ሳልሆን እነርሱ ለኔ
ደሙልኝ ) የደማሁት ቀላል ቢሆንም በታክሲ የተቻልኝን
ያህል ራቅሁ። የራቅሁት ግን
ሕይወቴን በሙሉ ከሰጠሁበትም ቦታ ነበር።
ከድሬዳዋ
ድብደባ በኋላ ወዲያው ሐረር ነበር የተመለስኩት። በሐረር ሁኔታው ተሰምቶ ስለነበር ሕዝቡ ሁል አንድ ነገር የሆንን መስሎት ነበር። በሰላም መመለሳችን
ደስታ ቢሆንም የእኛን እግር ተከትሎ አንድ አስደንጋጭ ዜና ደረሰ። ከተደበደቡት መካከል
ሦስቱ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና በተለይም አንደኛው በኮማ ውስጥ እንዳለ ተነገረን። ሁላችንም አለቀስን።
