by Mihretu
ገነት
ወይም Garden ቦታ ሲሆን መንግሥተ ሰማያት/Kingdom of God/ ማለት ግን
የእግዚአብሔር አገዛዝ ማለት ነው። የሰማያት ወይም የሰማይ መንግሥት ማለት ደግሞ የእግዚአብሔር መንግሥት ማለት ነው፡፡
በአብዛኛው
በማርቆስ ወንጌል "የእግዚአብሔር መንግሥት" የሚለው ቃል ነው በማቴዎስ ወንጌል "መንግሥተ ሰማያት" የተባለው። ትርጉሙም የሰማይ መንግሥት ወይም የእግዚአብሔር መንግሥት ማለት ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች እንደሚናገሩት፤ ማቴዎስ "የእግዚአብሔር መንግሥት" ከማለት ይልቅ "የሰማይ መንግሥት" ወይም በግዕዙ "መንግሥተ ሰማያት" ብሎ የጻፈበት ምክንያት የማቴዎስ ወንጌል የተጻፈው ለአይሁዶች ስለነበርና አይሁዶች ደግሞ "እግዚአብሔር" የሚለውን ስም ደጋግመው መጥራት ያስቀስፋል ብለው ስለሚያምኑ እንደነበር ይናገራሉ (ምክንያቱም በህግ የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ ይላልና)።
ጥቅስ፤
የማርቆስ ወንጌል1፥14-15 ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና። ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ።
የማቴዎስ ወንጌል 4፤17 የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ። ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመር።
የእግዚአብሔር
መንግሥት ደግሞ በደረጃ የምትቀመጥ ቦታ አይደለችም። ነገር ግን የእግዚአብሔር አገዛዝና ፈቃድ የሚፈጸምበት ማለት ነው። ለዚህ ነው በአባታችን ሆይ ጸሎት "መንግስትህ ትምጣ" ካለ በኋላ ወዲያው "ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን" የሚለው።
