Friday, May 11, 2012

....ተሃድሶ መናፍቃን አይደሉም!

«ቅዱስ ሲኖዶስ አባ ሠረቀ ብርሃንና ዲ/ን በጋሻውንን የኃይማኖት ህጸጽ የለባቸውም ተሃድሶ መናፍቃንም አይደሉም አለ»

       Adiós ማቅ !!!!!       bienvenidos አባ ሠረቀ ወበጋሻው!!

                       የጽሁፉ ምንጭ፦ ዐውደምህረት
በትናንትነው ዕለት የተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የጀመረው ከጥቅምቱ ስብሰባ ወደ ግንቦት የተዘዋወሩ ጉዳዮችንን በመመልከት ሲሆን የመጀመሪያ አጀንዳውም ሊቃውንት ጉባኤውየሐይማኖት ህጸጽአለባቸው ተብለው ስለ ቀረቡ ወገኖች አጣርቶ የደረሰበትን እንዲያቀርብ ማድረግና ውሳኔ መስጠት ነበር። በዚህም መሰረት ማቅ ይወገዙ ይከሰሱልኝ ሲል ካቀረባቸው ሰዎች መካከል የአባ ሠረቀ ብርሃን እና የዲ/ በጋሻው ጉዳይ ታይቶ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል። ይህ ውሳኔ ለማኅበረ ቅዱሳን ትልቅ ውድቀት እንደሆነ ታዛቢዎች እየተናገሩ ይገኛሉ።

Thursday, May 10, 2012

የሰናዖር ማበር



በትልቅ ቸርነት ሌሊቱን አንግቶ
በጽልመቱ ቦታ ፀሐይን አብርቶ
ጨለማን በብርሃን ለለወጠ ጌታ
ምስጋና ሊያቀርቡ፤ ሊያደርሱ ሰላምታ
ወፎች እንኳን አውቀው ሲያሰሙ እልልታ
ክፉ ማኅበር ክፉ  ያነሰ ከእንስሳ
ጠዋት ከመኝታው ከእንቅልፉ ሲነሳ
በስመ አብ ብሎ ማመስገን ሲገባው
መርዝ ሃሳብ ያወጣል ጠማማ ልቡናው
ከደካሞች ጋራ እንዳይኖር ተስማምቶ
ተንኰል የሚዘራ ከመካከል ገብቶ

Tuesday, May 8, 2012

«የሁለቱ ማቆች የታክሲ ውስጥ ወግ »

                                 ምንጭ፦ደጀ ሰላዓም ብሎግ
ሁለቱ የ"ማኅበረ ቅዱሳን" አባላት በትላንትናው ዕለት ሰኞ ከምሽቱ 3፡20 ሰዓት ላይ ከአራት ኪሎ ወደ ቤላ በሚሄደው ታክሲ ጋቢና ውስጥ ጎን ለጎን ተቀምጠው ወጋቸውን ይጠርቃሉ፡፡ በእነርሱ ቤት በታክሲዋ ከተሳፈሩት ሰዎች ውስጥ ከእነርሱ በስተቀር ስለቤተክርስቲያን ሚስጥርና ወቅታዊ ሁኔታ የሚያውቅ ማንም የለም፡፡ ይሁን እንጂ፣ ያላዩት አንድ የቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆነና እነርሱን በደንብ የሚያውቅ ዘጋቢያችን ከጀርባቸው ልጥፍ ብሎ የሚነጋገሩትን በጥንቃቄ ያዳምጥ ነበር፡፡
ሰዎቹ ማንያዘዋልና ዘማሪ ኤፍሬም ነበሩ፡፡ ማንያዘዋል ትውልዱ ከወደ ደብረብርሃን ሲሆን፣ የዘርዓ ያዕቆብ ዘር ነኝ በሚል እየተመፃደቀ ዘወትር ነጭ በነጭ ለብሶ በመንሸራሸር ባህርይው ሰው ሁሉ ሊለየው ይችላል፡፡ ከዚህም በላይ በጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት የልማትና ተራድዖ ክፍል ውስጥ ሲሠራ በፈጸመው የሙስና ተግባር ከሥራው መባረሩ ይታወቃል፡፡ ከዚያ ደግሞ "ማኅበረ ቅዱሳን" በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አካባቢ የቲዎሎጂ ምሩቃን ማኅበር ተጠሪ እንዲሆን አስመድባው እዚያ ላይ ሆኖ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ ኤፍሬም የ"ማኅበረ ቅዱሳን" አባል ከመሆኑ በስተቀር ይህን ያህል የሚታወቅበት የጎላ ገጽታ የለውም፡፡