Monday, March 26, 2012

«ማኅበረ ቅዱሳን» ከፍተኛ የፖለቲካ ኪሳራ ደረሰበት

 ይህ ድንቅ ጽሁፍ በደጀብርሃን ሲገለጽ ለበጎች ነጻነት የተቆጣው እንስሳን  ያስታውሰናል ።
(የጽሁፍ ምንጭ፤http://dejeselaam-dejeselaam.blogspot.com)
እውን "ማኅበረ ቅዱሳን" ከመንበረ ፓትርያርክ፣ ከቅዱስ ሲኖዶስና ከጠቅላይ ቤተክህነት በላይ የሃይማኖት ጠባቂ እና ተቆርቋሪ ነውን?
ግርግር ለሌባ ይመቻል፤ "ማኅበረ ቅዱሳን" የዝቋላን እሳት ለማጥፋት ለአንድ ጀሪካን ውኃ 40 ብር ለሁለቱ ደግሞ 80 ብር ያስፈልገኛል ብሏል
በዋልድባ፣ በአሰቦትና በዝቋላ ገዳማት ጉዳይ የ"ማኅበረ ቅዱሳን" ዌብሳይቶችና ብሎጎች ለምን ተንጫጩ? ሌሎቹ ለምን እርጋታ ታየባቸው?
መንግሥት፣ ሃይማኖትና ቀጣዩ ልማታችን
"ማኅበረ ቅዱሳን" በቅርቡ ከገዳማት ሕይወት ጋር ተያይዞ በተነሳው ውዝግብ ከምንጊዜውም በላይ የፖለቲካ ኪሣራ የደረሰበት መሆኑን ልዩ ልዩ ምንጮች አረጋገጡ፡፡ ምንም እንኳን ሃይማኖታዊ ተፈጥሮ ባይኖረውም "ማኅበረ ቅዱሳን" የሃይማኖት ተቋም መስሎ በመንቀሳቀስ ብዙዎችን ቢያሳስትም፣ ዛሬ በፈጠረው የፖለቲካ ግጭት ከመንግሥትና ከሕግ ጋር ተፋጦ በመገኘቱ እውነተኛ ማንነቱ መጋለጡን የወቅቱ ሁኔታው ያስረዳል፡፡
ከአፈጣጠሩ ጀምሮ ከፖለቲካ አካሄድ ተላቆ የማያውቀው "ማቅ" ውስጥ ውስጡን ሲያተራምስ ከርሞ ዛሬ ሙሉ በሙሉ ራሱን በመግለጥ ፀረ ቤተክርስቲያንና ፀረ መንግሥት መሆኑን አሳይቷል፡፡ ይህ የሃይማኖት "ማኅበር" ነኝ ባይ ተቃዋሚ ድርጅት ቤተክርስቲያንን በእርስ በርስ ሁከት ሲያተራምስ ቆይቶ በአሁኑ ወቅት ቀይ መስመሩን አልፎ ከሕዝብና ከመንግሥት ጋር የሚያጋጨውን ድርጊት በመፈጸም ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡
"ማኅበሩ" ከ40 ሺህ እስከ 80 ሺህ የሚሆኑ አባላት አሉኝ የሚል ሲሆን በመንግሥትም ሆነ በቤተክርስቲያን የአባላቱ ዝርዝር አይታወቅም፡፡ ይህ ኅቡዕ አደረጃጀቱም እጅግ አደገኛ፣ ለውንብድናም ለምለም ሁኔታን እንደሚፈጥር ልብ ይሏል፡፡ ስውር ኃይል እንደሚመራውም የማኅበሩ አመራር የሆነው ዳንኤል ክብረት እንዳጋለጠም የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሚደረጉት የገንዘብ ዝውውሮቹ ቁጥጥር አይደረግባቸውም፡፡ ከዚህ የተነሳም አደገኛነቱን ማስተዋል ይቻላል፡፡
ቤተክርስቲያን ላወጣችው መመሪያ አይገዛም፡፡ በዚህም ምክንያት ተከታታይ መመሪያዎች ሲወጡበት ይታያል፡፡ በቤተክርስቲያን ስም የንግድ ፈቃድ ይወስዳል፡፡ ነገር ግን ለቤተክርስቲያንም ሆነ ለመንግሥት ተገቢውን ገቢ አያስገባም፡፡ ገቢዎቹንና ወጪዎቹን ቤተክርስቲያን በምታሳትማቸው ደረሰኞች እንዲመዘግብ ቢነገረውም ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ሀብትና ንብረቱን በነፃና ገለልተኛ ኦዲተር እንዲያስመረምር ቢታዘዝም በእምቢተኝነቱ ጸንቷል፡፡ በአጠቃላይ ሲገመገም፣ የ"ማኅበሩ" አደገኛነት ሊለካ የማይችል እጅግ አስጊ ነው፡፡ ጉዳዩ ፈር እንዲይዝ ከተለያዩ አካላት ለመንግሥትና ለጠቅላይ ቤተክህነት ጥቆማ ቢቀርብም በተለያዩ ምክንያቶች ችግሩ ከመባባስ በስተቀር መፍትሔ አልተበጀለትም፡፡ "ማኅበሩ"ም ባላሰለሰ ጥፋት ውስጥ ቀጠለበት እንጂ የመታረም ዕድል አላገኘበትም፡፡
ምንም እንኳን "ማቅ" መቶ በመቶ ለጥፋቱ ተጠያቂ ነው ባንልም፣ ዛሬ ቤተክርስቲያናችን ለገባችበት ቀውስና አስተዳደራዊ መዋቅሯ ወደ ሁለትና ስምንት ቦታ መከፋፈሏ የ"ማኅበሩ" የሃያ ዓመታት እንቅስቃሴ ውጤት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ መሆኑ አሌ አይባልም፡፡ "ማኅበሩ" ካህናትንና ምዕመናንን በተሃድሶነትና በመናፍቅነት በመክሰስ እና በራሱ ሥልጣን ዱላ ሁሉ በማንሳት ብዙዎችን ከየአጥቢያው በማባረር የግፉአንንና የስደተኞችን ቁጥር አበራክቷል፡፡

እግዚአብሔር ለምን ሰው ኾኖ መገለጥ አስፈለገው?


ለአዳም ካሣ በመክፈልና የእግዚአብሔርን ትክክለኛ ፍትሕ በመጠበቅ ሞትን ለመሻር የተደረገ መገለጥ

       * * *
የተወለደ ከአዳም፣
መሬት ያልገዛ የለም፡፡
ግብሩን መገበር አቅቷቸው፣
ገና ብዙ ዕዳ አለባቸው፡፡[1]
 * * *
ለክርስቶስ በስብዕና መገለፅ ዋና ምክንያት ተደርጎ የሚወሰደው በአዳም መሳሳት የተነሳ በሰው ልጆች ላይ ያረፈውን የሞት ፍርድ በመሻር ለማስቀረት ሲኾን በሞት መሻርም የእግዚአበውሔር ትክክልኛ ፍርድ ሳይዛባ እንዲፈፀም ለማድረግ ነው፡፡ ምክንያቱም አዳምና ሔዋን በገነት በነበሩ ጊዜ እግዚአብሔር እንዳይበሉ ያስጠነቀቃቸውን ዕፀ በለስ በመብላት ትዕዛዙን በመሻራቸው ሞት የሚባል ዕዳ በሰው ልጆች ኹሉ እንደመጣባቸው በመጽሐፍ ቅዱስ የኦሪት ዘፍጥረት ታሪክ ተገልፆ ይገኛል፡፡ ምናልባት እዚህ ላይ ‹የተሳሳቱት አዳምና ሔዋን ለምን ልጆቻቸው የሞት ቅጣት ተቋዳሽ ይሆናሉ?› የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ገለፃ ከኾነ ግን አዳምና ሔዋን የተሳሳቱ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ናቸው፤ኹሉም በዓለም ላይ በመዋለድ የተራባው የሰው ዘር ደግሞ ከእነሱ የመጣ ነው፡፡ ይህም የኾነው ስህተት ፈፅመው የሞት ፍርድ ከተላለፈባቸው በኋላ ስለኾነ ማንም ከእነሱ የተወለደ ዘር ኹሉ የእነሱን ሀብትና ማንነት ይወርሳል፡፡ ከእነሱ የተገኘው ሀብትም በስህተት ላይ የተመሠረተ የስብዕና ማንነት ሲኾን የእሱም መቋጫም ሞት ነው፡፡ ስለዚህ ልጆቻቸው ወይም ዘሮቻቸው በሙሉ በስህተት የመጣ የሞት ፍርድ ተካፋይ ናቸው፡፡ ያለበለዚያ በእነሱ ላይ የተፈረደውን የሞት ፍርድ ልጆቻቸው መውረስ የለባቸውም ከተባለ  የእነሱን የስብዕና ማንነትም ልጆቻቸው መውረስ የለባቸውም፡፡ እንዲሁም በአዳምና ሔዋን የተወከለው የሰው ዘር በሙሉ ነው እንጂ የሁለት ሰዎች የመሳሳት ጉዳይ አይደለም፡፡ ምክንያቱም አዳምና ሔዋን ልጆቻቸውን በአብራካቸው ውስጥ በመያዝ ወክለው ትዕዛዙንና ፍረዱን ተቀብለዋል፤ ፍርዱም የተላለፈው ለሰው ልጅ ኹሉ ነው፡፡ ልጆቻቸው የእነሱ ዝርዝር ማንነቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ የሞት ፍርድ የተላለፈው በአዳምና በሔዋን ከእነ ልጅ ልጆቻቸው ነው፡፡

Sunday, March 25, 2012

አቡነ ሳሙኤል በቅ/ሥላሴ መንፈሳዊ ኰሌጅ ...

አቡነ ሳሙኤል ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ውስጥ ሽምቅ ውጊያ መጀመራቸው ተሰማ


በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ለጳጳሳት ማረፊያ በተሰራው ህንጻ ውስጥ ሳይሆን፣ ተምረው ባላለፉበት በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ የሚኖሩት የልማት ኮሚሽን የበላይ ጠባቂ አቡነ ሳሙኤል ከማህበረ ቅዱሳን የተሀድሶ መናፍቃንን ዘመቻ ለመከላከል በሚል ከሰበሰበው ገንዘብ ላይ እንደተለቀቀላቸው በሚታመነው ገንዘብ አንዳንድ የኮሌጁን ተማሪዎች በማባበልና ከብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው የሚባሉ ተማሪዎችን በመዋጋት በውስጣቸው ተዳፍኖ አልወጣላቸው ያለውን መፈንቅለ ፓትርያርክ እንደገና ለመሞከር ሽምቅ ውጊያ መጀመራቸው ተሰማ፡፡
አቡነ ሳሙኤል ከማህበሩ ጋር በመቀናጀት ለጀመሩት ሽምቅ ውጊያ አንዱ የቤት ስራቸው በኮሌጁ ውስጥ ከዚህ ቀደም በደጀሰላም ድረገጽ ላይ ወጥቶ የነበረውና ማህበረ ቅዱሳን ‹‹ተሀድሶ ናቸው ይባረሩልኝ›› ብሎ ያለባለቤትና አድራሻ የላከውንና በኮሌጁ አስተዳደር ውድቅ የተደረገውን ክስ እንደአዲስ ማንቀሳቀስና የተባሉትን ደቀመዛሙርት ከኮሌጁ ማስወጣት ነው፡፡ ከሰሞኑም ያው ስም አጥፊ ደብዳቤ እንደ ተለመደው ያለባለቤትና አድራሻ ተልኮ ለኮሌጁ አስተዳደር ከደረሰ በኋላ ፍሬከርስኪ ሆኖ በመገኘቱ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ምክንያቱም ባለቤት የለውም አድራሻም የለውም፡፡