Thursday, March 22, 2012

አንድ ጥያቄ አለኝ!

 ሰላም ለእናንተ ይሁን
በብሉይ ዘመንና በአዲስ ኪዳን ዘመን ስላሉት ነብያት ልዩነት ላኩልኝ በአዲስ ኪዳን ያሉት ነብያት በበለጠ አገልግሎታቸው እንዴት መሆኑን እንዳለበት ላኩልኝ ተባረኩ! (ስሙን ያልገለጸ ጠያቂ)
ከደጀብርሃን መልስ፣
 በአዲስ ኪዳን ውስጥ ነቢይነት ጨርሶ የሚረሳና የማይሰራ ጸጋ ነው እንዴ?
ስለ ነብይ ምንነት፣ማንነትና አገልግሎት በዚህ በአዲስ ኪዳን ዘመን ብዙ እያከራከረ ይገኛል። አንዳንዶች አብያተ ክርስቲያናት እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ያሉት በአዲስ ኪዳን ስላለ ነብይነት ምንም ሲናገሩ አይሰማም። አዲስ ኪዳን ግን ብዙ ቦታ ላይ ከጸጋ ስጦታዎች አንዱ የነብይነት አገልግሎት እንደሆነ ጽፎ ይገኛል። ስለየትኛውና ስለምን ነብይነት አዲስ ኪዳን እየተናገረ እንደሆነ አንድም ሰው ትንፍሽ ሲል አይሰማም። ለምን?  የተጻፈውን መተንተን ወይም መካድ ወይም መናገር እየተገባ ዝምታ ለምን? ኢየሱስ ነብይ ነው ከሚል ጥቅል ሃሳብ ውጪ ስለጸጋ ስጦታው ምንነት ግን ምንም አለመባሉ ያሳዝናል። ሌሎች ደግሞ እኛ ለነብይነት የተላኩና የተመረጡ ሰዎች ያሉባቸው አብያተክርስቲያናት ነን ይላሉ። እንዴትና ለምን? ብለን እነዚህኞቹንም ብንጠይቅ አጥጋቢ መልስ ከሚሰጡን ይልቅ ለራሳቸው እንደሚመቻቸው አድርገው ይተነትናሉ። ስለአዲስ ኪዳኑ ነብይነት ጨርሶ የረሱና እንደራሳቸው ምርጫ የሚጠቀሙበት ክፍሎች ቢኖሩም ስለብሉይ ኪዳን ዘመን ነብይነት ግን ሁሉም ብዙ አይከራከሩም። አለመከራከራቸውም የሚገለጸው ሁሉንም የብሉይ ኪዳን ነብያት በጋራ ይቀበሏቸዋልና ነው። በሁሉም ዘንድ ማለት በሚቻልበት ደረጃ ሃሳቡና ትርጉሙ የጋራ ተቀባይነት አለው። ከሥነ መለኰት ምሁራንና ሚዛናዊ አስተምህሮ ካላቸው ሊቃውንት ያገኘነውን ትምህርትና መረጃ መሠረት አድርገን ስለነብይነትና የነቢያት እንዴትነት ጥቂት ለማለት እንፈልጋለን።
  ነቢይ ማለት ምን ማለት ነው?
የግሪኩ «ፕሮፌሚ» ቃል ሲሆን ትርጉሙም «አስቀድሞ መናገር» ማለት ነው። ይህም ትንቢቱ ከመፈጸሙ በፊት ትንቢቱ ለተነገረለት ሕዝብ የትንቢቱን ምንነትና የፍጻሜ ሂደት አስቀድሞ ማሳወቅ ወይም ማስተላለፍ ነው።


ብሉይ ኪዳን፣
 

ነብይነት ለምን አስፈለገ?
የነብይነት አገልግሎት የተፈለገው የመጀመሪያው ሰው አዳም ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ግንኙነት ከተቋረጠ በኋላ ነው። እስከ ክርስቶስ መምጣት ድረስ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ግንኙነት የተቋረጠ ስለነበር እግዚአብሔር መልእክቱን «አስቀድሞ መናገር» ፕሮፌማ ሰው ስለፈለገ ለዚህ አገልግሎት ከሰው መካከል በመምረጥ ነው ነብይነት የተፈገለው።
መልእክቱ የሚተላለፍበት መንገድ፣
በራእይ፣ በህልም፤ በድምጽና በምልክት ሊሆን ይችላል።
«እርሱም፦ ቃሌን ስሙ በመካከላችሁ ነቢይ ቢኖር፥ እኔ እግዚአብሔር በራእይ እገለጥለታለሁ፥ ወይም በሕልም እናገረዋለሁ» ዘኁ 12፤6
«እግዚአብሔር ሳሙኤልን ጠራው እርሱም፦ እነሆኝ አለ»1ኛ ሳሙ3፣4
«እርሱም፦ በአንተ ዘንድ ሞገስ ካገኘሁ፥ የምትናገረኝም አንተ እንደ ሆንህ ምልክት አሳየኝ»መሳ 6፣17
ኢሳይያስ ራእይ አይቶ፣ ኤርምያስ ቃል ሰምቶ፣ሕዝቅኤልም ዳንኤልም ራእይ አይተው ነብይነታቸውን ፈጽመዋል። ሌሎቹም እንዲሁ!
እንግዲህ የብሉይ ኪዳን ነብያት ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ሸክም ወደሕዝቡ በማድረስና የሕዝቡንም ጩኸት ወደእግዚአብሔር በማድረስ የነብይነት አገልግሎታቸውን መካከለኛ ሆነው ፈጽመዋል።
አዲስ ኪዳን፣

የተሰደዱ የሐዋሳ ምእመናን የደብረ ዘይትን በዓል...

(ደጀብርሃን ብሎግ ለሐዋሳ ምእመናን አድናቆቱንና አክብሮቱን ይገልጻል)
ከወንጌል፣ ከሠላምና ከልማት ውጪ የተለየ አጀንዳ እንደሌላቸው በድጋሚ አረጋገጡ

አቡነ ገብርኤል የተከፈለም ሆነ የተሰደደ ሕዝብ የለም ያሉት የሀዋሳ ምዕመናን የደብረ ዘይትን በዓል አስመልክቶ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ ማዘጋጀታቸውን የደረሰን መረጃ ያረጋግጣል፡፡ ይኸው ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀው ታላቅና ደማቅ መንፈሳዊ ጉባዔ በየዕለቱ በሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ እንደተከታተለው ታውቋል፡፡

እንደወትሮው ሁሉ ገቢው የነጠፈባቸው አሥር የማይሞሉ ኪራይ ሰብሳቢ ነጋዴዎችና የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ስድስቱን አጥቢያ ቤተክርስቲያናት በማሰተባበር ጉባዔውን ለማደናቀፍ እና ሕዝቡን ለመበተን አውደ ምሕረት ላይ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት፣ ሲመቻቸው ደግሞ ዱርዬዎችን በመላክ፣ በሉ ሲላቸው ደግሞ ሕጋዊ በመምሰል በየፍትሕ እና ፀጥታ መሥሪያ ቤቱ በመዞር አስቁሙልን እያሉ ሲውተረተሩ ከርመዋል ተብሏል፡፡ ይሁን እንጂ ግፉአኑ እምነታቸውን በነፃነት የማራመድ ካላቸው ሕገ መንግሥታዊ መብት አንፃር መንግሥት ተረድቶላቸው ጉባዔውን ሊያኪያሂዱ መቻላቸው ታውቋል፡፡
 ከመጋቢት 7 እስከ መጋቢት 9/ 2004 ዓ.ም ለሦስት ቀናት በተካሄደው በዚህ ጉባዔ ተጋባዥ ሰባክያነ ወንጌል እና መዘምራን ተገኝተው ያገለገሉ ሲሆን፣ በጠላት ዲያብሎስ ሤራ ተዳክሞ የነበረው የወንጌል አገልግሎት እንደገና ትንሣኤ ያገኘበት ታላቅ የሐሴት ጉባዔ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

Wednesday, March 21, 2012

አንድ ጥያቄ አለኝ!

 ትክክለኛ እድሜ የትኛው ነው?
[መንገሥ በጀመረ ጊዜ አካዝያስ የሀያ ሁለት ዓመት ጕልማሳ ነበረ በኢየሩሳሌምም አንድ ዓመት ነገሠ። እናቱም ጎቶልያ የተባለች የእስራኤል ንጉሥ የዘንበሪ ልጅ ነበረች] 2ኛ ነገ 8፡26

[አካዝያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ዕድሜው አርባ ሁለት ዓመት ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም አንድ ዓመት ነገሠ እናቱም ጎቶሊያ የተባለች የዘንበሪ ልጅ ነበረች] 2ኛ ዜና 22፣2 (በደጀብርሃን፣ የተጠየቀ)

በደጀብርሃን የተመለሰ፣
ይህ ጥያቄ ብዙ ጊዜ ሲቀርብ አይቻለሁ። ምናልባትም እናንተም አጋጥሟችሁ ይሆን ይሆናል። ከዚህም የተነሳ እዚህ ላይ ፖስት በማድረግ እኔ ከማውቀው የተለየ ምላሽ ካለ ለማየት ጠብቄ ነበር። እስካሁን ምላሽ የሚሰጥ ስላላገኘሁ እኔ ያገኘሁትን መረጃ በምላሽነት ላስቀምጥ ወደድሁ። ወደፊት የተሻለ ምላሽ የሚሰጥ ካለ እጠብቃለሁ።
በእብራይስጥ አኀዝ የሚጻፈው በፊደል (alphabet) ነው። በዚሁ መሠረት የአካዝያስ እድሜ በቀደሙት የሱርስትና የዐረቢያ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሁሉም ቦታ 22 እድሜ እንደነበረው ተጽፎ ይገኛል። የሰባ ሊቃናት ትርጉም በተባሉት መጻሕፍትም ውስጥ 22 ዓመት ስለመሆኑ በዜና መዋእል ውስጥ ሳይቀር ተጽፎ ተገኝቷል። በአንዳንዶች ውስጥ ደግሞ 42 ዓመት እንደሆነ ተቀምጦ ይገኛል። ይህ የሚያሳየው ተርጓሚዎች ከአንዱ ቋንቋ ወደ ሌላ ቋንቋ ሲገለበጡ ያመጡት ክስተት መሆኑን ነው። ከላይ እንደተገለጸው የእብራይስጥ ቁጥር አኀዝ ሳይሆን ፊደል ስለሆነ 20 ለማለት כ የሚጻፍ ሲሆን 40 ለማለት ደግሞ מ ይጻፋል።
እነዚህ ፊደላትን አስማምቶ በቁጥር ካለማስቀመጥ የመጣ ሊሆን እንደሚችልና አካዝያስም ሲነግስ እድሜው ከአባቱ ከኢዮራም ኖሮ ከሞተበት እድሜ በሁለት ዓመት ሊበልጥ ስለማይችል (ኢዮራምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሠላሳ ሁለት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ስምንት ዓመት ነገሠ 2ኛ ነገ 8፣17) በማለቱ የትርጉሙን ስህተት ማየት ይቻላል። የእብራይስጡን ב +כ =22 በማለት እንደማስቀመጥ 42=ב מ+ በማለት ስህተቱን መገንዘብ ይቻላል። ለተጨማሪ መረጃ ፤(ይህንን ይጫኑ)