Showing posts with label ሥነ ግጥም. Show all posts
Showing posts with label ሥነ ግጥም. Show all posts

Saturday, April 7, 2012

አለ በየቦታው ዋሾና ቀጣፊ!

 
                      ዋሾ፤ ቀጣፊ
                                           (ከደጀብርሃን)
እንዲያው ቅጥፍ አርጎ የነገር አበባ
ሳይሸተው የሚያበን የዲስኩር ገለባ
የሰው አረማሞ የሆነ ፍሬ አልባ
መጎንጎን ማፍተልተል፣ተንኮልና ደባ
ሳይጠሩት የሚጮህ ፣ጣልቃ የሚገባ
በከቸቸ ዓይኑ፤ እንደአዞ የሚያነባ
ነጩን የሚያጠቁር ክፋት የሚቀባ
ሰው መሳይ በሸንጎ ፣ለብሶ የእድሜ ካባ
 አለ በሰፈሩ፣ አለ በሀገሩ፣
በዋሾ የተወጋ፣ አለ በመንደሩ፣
                        ያለቀሰም አለ፣ እንባን የፈሰሰ፣ ኑሮን ያመረረ
                        ተወግቶ የደማ ፣ ውስጡ የጠቆረ፣
                        ትዳሩ የፈረሰ፣ ሜዳ ላይ የቀረ
                     ተሰርቶበት ነገር፣ ውድቀት የቆጠረ፣
                     ጓደኛን የጠላ፣ ጸብን ያከረረ፣
                     አለ የተወጋ፣ አለ የተነካ በዋሾ ቀጣፊ
                     በሀሰት ዲስኩሩ፣ በነገር ፈልሳፊ
                   በሃይማኖት ስፍራ፣ አለ መስቀል ይዞ፣
                   እያለቃቀሰ ልክ ፣ እንደአዞ፣
                   ጸብን እየዘራ፣ በሀሰት ደንዝዞ፣
                   አለ በየቢሮው፣ ወንበር ተደግፎ፣
                   አብስሎ ሚያበላ፣ የተንኮልን ገንፎ፣
                   አለ በአስኳላው፣ ደብተር ተሸክሞ፣
                  አጋጭቶ የሚስቅ፤ በክፋት አላትሞ፣
አለ በየቦታው ዋሾና ቀጣፊ
በምታልፈው እድሜ፣ ሳይመስለው አላፊ።
በምታልፈው እድሜ ሳይመስለው አላፊ፣
                        ዛሬም ገና አለ
 ዋሾና ቀጣፊ........

Sunday, April 1, 2012

የአቡኑ ገዳም



ቡኑ ገዳም
ተራራ ወጥቼ፣ ቡኑ ዘንድ ሄጀ መስቀል ለመሳለም
ክረምቱ በረታ፣ ምንም  ልተቻለ፣ ያሰብኩት ሳይሞላ፣ ሳይሆንልኝ ቀረ
ዳመናው ዝናቡ፣ ጉምና ጭጋጉ፣ ይህ የዛሬ ክረምት መች ያነቃንቃል!
ደጁን ጨቀይቶት፣ ወንዙም ጐርፍ ሞልቶት፣ ጅጉን ስፈሪ፣ በጣም ያስጨንቃል
በታምር በፀሎት፣ ከተራራው ፋፍ፣ ከዳመናው በላይ የገደሙት ገዳም
ደካማው ጉልበቴ፣ ንደምን ይቻለው፣ ጭቃውን ሸርተቴ፣ የኖኁን ዝናም
ዛሬ፣ ነገ ያልኩ ሰማዩና ምድሩን ሳስስ ስመለከት፣ ስቃኝ ድማሱን
ዓይኖቼም ደከሙ፣ ለቀ ጉልበቴ፣ መቃብር ቁፋሮ፣ ሰርክ መማሱን!
ማለዳ-ማለዳ ደረትዋን ገልብጣ፣ ድምጿንም ከፍ ደርጋ የምትጮኸው ወፍ
የቀሰቀሰች  ንቅልፍ ነሳችኝ፣ ሽፍንፍን ብዬ፣ ተኝቼ በሰላም በደህና ንዳላርፍ!
ምድር-ዓለሙ ክዶኝ፣ ሁሉም ጥሎኝ ሄዷል፣ ጠያቂም የለኝም ከቶ ሚያጽናናኝ
ወፊቱስ የት ሄደች? ከጠፋች ቆይታለች፣ ድምጿንም ልሰማሁ፣ ንዳታዝናናኝ
ደጋግሞ የቆየ የሚነፍሰው ነፋስ ለው መጥፎ ጠባይ፣ ኃይለኛ ዙሪት
የጐጆየን ክዳን በትኖ ያነሳ፣ ምን ዓይነት ተንኮል ነው፣ ምን ዓይነት ብሪት!
መቸ ይኸ ብቻ! ሰማዩን ተርትሮ ስደንጋጭ ብልጭታ መብረቅ ሲፈነጥቅ
ከታትሎ ይሏል የሰማይ ነጐድጓድ ቤቱን ንቀጥቅጦ ጆሮ ስኪሰነጥቅ
ተራራ ልወጣህ፣ ታቡን ዘንድ ልደረስኽ፣ መስቀል ልተሳለምክ ብሎ ነው መሰለኝ
ከዚያ ላይ ስወጣ ገደል ከምገባ፣ ወድቄ ከምሞት፣ ወይም ንሸራትቶኝ ከሚሰባብረኝ
ከዚሁ ከቤቴ ካልጋዬ ተኝቼ፣ በንፋስ፣ በመብረቅ ነጉዶ ንጐዳጉዶ እንዳሻው ያድርገኝ!
                              
 ገ/ኢ ጎርፉ

Wednesday, March 28, 2012

ፍጹም ከቅጣቱ!


ማን ይገኝ ነበረ?


(By dejebirhan)     to read in PDF (click here)
በከንቱ አትጥራኝ፤ ስሜን ባንተ ይክበር
ኢታምልክን ጠብቅ፣ ምልክት አታስቀር
ባልንጀራን ውደድ፤በሀሰት አትመስክር
እድሜህ እንዲረዝም፤ ወላጅህን አክብር
ገላህንም ቀድስ፣ክልክል ነው ማመንዘር
አድርግና ጠብቅ፣ የቆመውን አጥር
ያልሰማ ማን አለ? ኦሪት ስትናገር?
በከንቱ የጠራው በደለኛ ይሆናል፤ (ዘጸ ፳፣፯)
ከአምላኩ መጽሐፍ፤ ከርስቱ ይፋቃል፤ (ዘጸ ፴፪፣፴፫)
ቢሰግድና ቢወድቅ ለቀረጸው ምስል
ቢያሸው፤ ቢዳብሰው ሥሩ ቢንከባለል
የአምላኩ መልክ ሆኖ ከፊቱ ቢተከል፣
ኢታምልክን ሽሯል ትለዋለች ኦሪት
ሕጓን ትጠቅስና፣ ታወርዳለች ቅጣት
...................ከቶ ያየኝ የለም፤
አይቶኝም የሚቆም፣ (ዘጸ ፴፫፣፳)
ምስሌ ምንድነው፣ ከማን ጋር ልተያይ? (ኢሳ ፵፮፣፭)
ከቶ ማን አይቶኛል? ከደመናት በላይ፣ (ዘዳ ፴፫፣፳፮)
በምድር የተካኝ ፣እኔነቴን ወካይ፣
ከወዴት ተገኘ፣ሴትና ወንድ መሳይ? (ዘዳ ፬፣፲፮)

Friday, January 6, 2012

እኔ ማነኝ?



(by dejebirhan)

«እኔ ማነኝ? አንተስ ወንድሜ ማነህ?»

እኔ አበባ ነኝ ፣ የማለዳ ጤዛ ያረፈብኝ፣

ፍካት፣ ድምቀት የከበበኝ፣

ያይን ስስት፣መዐዛ ሽታ፣ የሞላብኝ፣

የንብ ቀሰም፣ ጣፋጭ ማር ነኝ፣

የከበርኩኝ፣ ውበትን የታጠርኩኝ፣

አበባ ነኝ፣ አበባ ነኝ፣

«እኔ ማነኝ፣ እንዴት አልኩኝ?

«አንተስ ማነህ፣ ለምን አልኩኝ?።

                                  ጠያቂ አዋቂ፣ ያ'በው ወግ፣

                                 ጸገየ እጽ ፣ የፍጥረት ሕግ፣

                              ለካስ ነበር-ወደማታው፣ መጠውለግ፣

                                      የመፍረስ ጫፍ ፣ ሌላ ጥግ፣

ታዲያስ እኔ ማነኝ?

ፍካት ድምቀት፣ የማይዘልቀኝ፣

ውበት ጤዛ፣ የሚያረግፈኝ፣

ከሰሎሞን የተሻልኩኝ፣ውበት የደረብኩኝ፣

ሆኜ ሳለሁ፣ ባዶ ገላ ያሸነፈኝ፣ እኔ ማነኝ?

                                   መልስ አገኘሁ፣ የራሱ ካደረገኝ፣

                                    ሳልፈልገው ከፈለገኝ።

                                   እኔ የኔ አይደለሁም፣

                               ውበቴን ሽንፈት አይጥለውም፣

                               መርገፍ ልብሴ፣ ወልቆ አይቀርም፣

አበባዬ ክርስቶስ ነው፣

እርቃኔን የሸፈነው፣

የኔን ከለሜዳ የለበሰው፣

ክብሩን ለኔ ያወረሰው፣

ሞት ሸማዬን የገሰሰው፣

እኔ ማነኝ? ብዬ ስለው፣

አበባህ ረግፎ የማትቀረው፣

አንተ የኔ ነህ፣ ሲለኝ ሰማሁ፣

እኔም ያንተ፣ ቃሌን ሰጠሁ፣

ዛሬም አለሁ፣ ነገም አለሁ፣

አበባዬ አይረግፍም፣ ዛሬም አብባለሁ፣

ነገም በሰማይ አብቤ፣ አብሬው እኖራለሁ።

                                አንተስ ወንድሜ ማነህ? ያለኸው የትነው?፣

                                  የወደቅኸው፣ ከወዴት ነው?፣

                                  ስታበዛ ሩጫ፣ ልብስ ስትሻ፣

                                 የትም የለ፣ ማካካሻ፣

                                     የዚህ ዓለም ማረሳሻ፣

                                ይልቅ ና አበባ ሰው፣

                                መርገፍ ገላ፣ ከሚፈርሰው፣

                               አዲስ አርጎ፣ የሚያድሰው፣

                                 ክርስቶስን ልበሰው!!!!
«ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ» ኤፌ 4፣24



Monday, December 5, 2011

ይከራከሩኛል!


                 ይከራከሩኛል
ይከራከሩኛል፣ እየተጋገዙ
በከንቱ ላይረቱኝ፣ አምላክን ሳይዙ።
እንዳገሩ ልማድ- ለተማረ ዳኛ፣
ቅጣት ይገዋል-ይህ ደፋር አፈኛ፣
ብሎ ፈረደብኝ- የወንጌል ምቀኛ።
ክርስቲያን የሆነ-ሲኖር በዓለም፣
መመርመር ነው እንጂ- ክፉና መልካም።
እውነት እስኪገለጽ አጥብቆ መድከም፣
እንዲሁ ቢያከፉት- የወንድምን ስም፣
እጅጉን ነውር ነው-ጌታ አይወደውም።
ማርያምን ጻድቃንን-አይወድም ያሉት፣
በምቀኝነት ነው- ስሜን ለማክፋት።
በክስ ቢጠይቁኝ- ስለሃይማኖት፣